Tag Archives: featured

የቲቪ ቢዝነስ እየሞተ ነው!! ህትመት ወደ ኦንላይን ገበያ!!

ዛሬ በኢትዮጵያ የግል ቴሌቪዥኖች ህልውና አደጋ ላይ ነው። ችግሩን መቋቋም አቅቷቸው የተዘጉም አሉ። በአብዛኛው የጠላና አልኮል ማስታወቂያ ተሸክሟቸው የነበሩ የቴሌቪዥን ተቋማት ማስታወቂያውን የሚያቅብና ህግ ከወጣ በሁዋላ መንኮታኮታቸውን በአዲስ አበባ በሙያው የተሰማሩ እየገለጹ ነው።

ስም መዘረዘሩ አስፈላጊ ባይሆንም ሰራተኛ የበተኑ፣ የቀነሱ፣ ከነ አካቴውም ያቆሙ አሉ። በተመሳሳይ በዘርፉ ለመሰማራት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ አዳዲስ ነጋዴዎችም ለጊዜው ራሳቸውን ተመልካች ማድረግ መርጠዋ።

ወደ ሳተላይት ለመውጣት ቃል ገብተውና ማስታወቂያ አስለፍፈው የነበሩ አንድም ማስታወቂያ ባማስነገር፣ አለያም ሃሳባቸውን ለጊዜው በመግታት የዩቲዩብ ምሽግ ውስጥ ሆነው በተልመካች ብዛት የሚገኘውን ገቢ እየተቋደሱ ናቸው። እስከመቼም በዚሁ መንገድ እንደሚዘልቁና የራሳቸውን ወጥ ስራ ለተመልካች የማቅረብ አቅማቸውን እንደሚያሳድጉ ፍንጭ አይታይም። የዲሲ ነዋሪ ለዛጎል እንዳለው የዩቲዩብ ገቢ ባለሙያ አሰማርቶ ሙያው የሚጠይቀውን ሁሉ ለማድረግ ስለማይቻል የመንግስት ሚዲያዎችና ማህበራዊ ገጾችን ምንጭ በማድረግ፣ በመቅዳትና በማሰራጨት አሁን እንደሚታየው ከማዝገም ውጪ አማራጭ የለም።

ይኸው አስተያየት ሰጪ እንደሚለው አሁን የሚስተዋለው አካሄድ ሙሉ ለሙሉም ባይባለም ባብዛኛው ” ገበያ ተኮር ወይም ክሊክ ተኮር” በመሆኑ አርእስት በማስጮህ፣ ባብዛኛው ለአሉባልታ ማናፈሻ ፣ የርስ በርስ መላተሚያና የፖለቲካ አጀንዳ ማስፈጸሚያ ሲያልፍም ለገቢ ሲባል ድርጅቶችንና ግለሰቦችን መደብደቢያ ሆኗል። በዚህ ባህሪው መቀጠል ስለማይችል የዩቲዩብ ገበያውም በሂደት ተመሳሳይ ችግር እንደሚገጥመው ይገምታል።

በተመሳሳይ የጋዜጣ ወይም የህትመት ሚዲያዎችም ወደ ኦንላይን ገበያ ማምራታቸው አይቀርም። በአዲስ አበባ የዘርፉ ባለሙያ በማህበራዊ ገጹ ላይ እንዳለው የሕትመት ውጤቶች ቀደም ሲል ጀመሮ በህትመት ዋጋ ንረት ደብዛቸው ጠፍቷል። ያሉትም ቢሆኑ በማስታወቂያ እየተደጎሙ እንጂ የጋዜጣ ሽያጭ የሚያካሂዱት በኪሳራ ነው። አሁን ደግሞ ማስታወቂያውም በወረርሽኙ ምክንያት እየቀነሰ በኪሳራ ማሳተሙ አዳጋች የሆነበት ወቅት ነው። በዚህ መልኩ መቀጠልም አይቻልም።

ሰብለ ዮሃንስ በአገር ውስጥ የሚታተሙ የህትመት ስራዎች ወደ ኦንላይን ገበያ ካመሩ አሁን ባላቸው ይዘት ተፎካካሪ አይሆኑም። ሰብስክራይበርም በሚፈልጉት መጠን አያገኙም ባይ ናት። ስታስረዳ ዛሬ ማህበራዊ ሚዲያዎች ሁሉንም ጉዳይ በየደቂቃው ይዘግባሉ። ተቋማትና ባለስልጣናት መረጃ በማህበራዊ ገጻቸው ያስተላልፋሉ። ዛሬ ምንጭ ተብለው የሚጠቀሱት የባለስልጣናትና የተለያዩ ተቋማት የማህበራዊ ገጾችና የመንግስት ሚዲያዎች ናቸው። በዚህ መነሻ እነዚህን መረጃዎች ደግሞ በማተም ሰብስክራይብ የሚያደርግ አካል ይኖራል ብሎ በጉጉት መጠበቁ አግባብ አይሆንም።

የንግድና ስትራቴጂ ባለሙያ መሆኗን የምትናገረው ሰብለ፣ ሚዲያዎች ወደ ኦንላይን ቢዝነስ ከገቡ ሊነበቡ የሚችሉ፣ ወይም ሊሰሙ የሚችሉ የራሳቸው የሆነ ወጥና ጥልቅ ስራ በየዘርፉ ማዘጋጀት አለባቸው። ይህ ደግሞ ብቃትንና እውቀትን ይጠይቃል።

በውጭ አገር በገንዘብ የሚሸጡ ታሪኮች፣ የምርመራ ሪፖርቶች፣ መረጃዎችና የባለሙያዎች ትንታኔ ለለመደው ህዝብ ከመንግስት ሚዲያና የባለስልጣናት የመረጃ መረብ ወይም ማህበራዊ ገጾች ላይ እየገለበጡ ቀን በመጠበቅ ማተም አዋጪ እንደማይሆን ሰብለ ታሳስባለች። አታሚዎች ይህንን አስቀድመው ሊያስቡበት እንደሚገባም ትመክራለች።

በውጪው ዓለም ማን አንባቢ፣ አምን የዩቲዩብ ወሬ ተከታትይና የማህበራዊ ሚዲያ ምርት አፋሽ እንደሆነ ለማወቅ አሉባልታ የሚናፈስባቸውን ገጾች፣ የገጹን ባለቤቶችና፣ የሚተላለፈውን ወሬ በማየት ስንት ተከታይ እንዳላቸው ማስላት በቂ ነው። ሰብለ እንደምትለው ዲጂታል ሚዲያው ምን ያህል ስራና ጥረት፣ እንዲሁም መረጃን በቅጽበት ውስጥ የማዳረስ የጊዜ ሩጫው ቀላል አይሆንም።

በአገር ውስጥ ደግሞ የኢንተርኔት ጥራትና ፍጥነትም እንዲሁ በትልቁ ግምት ውስጥ የሚገባ ነው!!የኢትዮጵያውያን ተጋሩ ማሕበር በትግራይ ክልል አፈና እና እስራት እየተፈጸመ ነው አለ

ሕወሃት ምርጫው የግድ በቀነ ገደቡ መሰረት መካሄደ አለበት የሚል አቋም ቢያራምድም በተለይም በትግራይ ክልል የፖለቲካ ምህዳሩ ጠቧል፤ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ አመራሮችና ደጋፊዎች ላይ አፈና፣ እስርና ግፍ እየተፈጸመ ነው ፤ በአጠቃላይ ነፃ፣ ገለለልተኛና ፍትሃዊ ምርጫ ለማካሄድ አንዳችም ምቹ ሁኔታ የለም ብለዋል:

በኢትዮጵያ የኮረና ወረርሽኝን ለመከላከል በተጣለው የአስቸኳይ ጊዜ ድንጋጌ ምክንያት ተፎካካሪ ፓርቲዎች ከቦታ ቦታ ተዘዋውረው ሕዝቡን ለምርጫ ለመቀስቀስና መርሃግብራቸውን ለማስተዋወቅ የሚያስችላቸው  ዕድል ባለመኖሩ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ምርጫውን ማራዘሙ ተገቢ እንደነበር በጀርመን የኢትዮጵያውያን ተጋሩ ማሕበር አስታወቀ::

የማህበሩ ዋና ጸሐፊ አቶ ዮናስ መብራቱ  እንዳሉት ሕወሃት ምርጫው የግድ በቀነ ገደቡ መሰረት መካሄደ አለበት የሚል አቋም ቢያራምድም በተለይም በትግራይ ክልል የፖለቲካ ምህዳሩ ጠቧል፤ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ አመራሮችና ደጋፊዎች ላይ አፈና፣ እስርና ግፍ እየተፈጸመ ነው ፤ በአጠቃላይ ነፃ፣ ገለለልተኛና ፍትሃዊ ምርጫ ለማካሄድ አንዳችም ምቹ ሁኔታ የለም ብለዋል:: በፌደራል መንግሥቱና በትግራይ ክልል መካከል ያለው አለመግባባትና ከምርጫው ጋር በተያያዘ የሚነሱ የህጋዊ ቅቡልነጥ ጥያቄዎች በውይይትና በድርድር እንዲፈቱም ጠይቀዋል::

DW

ፖሊስ ራሷን ንግሥተ ነገሥት ብላ በሰየመችው ጠንቋይ ላይ ምርምራውን አጠናክሯል

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ራሷን ንግሥተ ነገሥት ብላ በምትጠራው ግለሰብ ላይ ምርመራ አጠናክሮ መቀጠሉን አስታወቀየአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ራሷን ንግሥተ ነገሥት ብላ በምትጠራው እና የአራት ልጆች እናት በሆነችው እኅተ ማርያም ላይ ምርመራ አጠናክሮ መቀጠሉን አስታወቀ።ከሁለት ዓመት በፊት ባሏ በሞት የተለያት የ43 ዓመቷ እኅተ ማርያም በሚል መጠሪያ የምትታወቀው ሴት ስለ ማንነቷ ለፖሊስ ስትገልጽ፣ ትክክለኛ መጠሪያ ስሟ ትዕግሥት ፍትሕአወቀ አበበ መሆኑንና መኖሪያዋ ኮልፌ መብራት ኃይል አካባቢ እንደሆነ ተናግራለች።

ግለሰቧ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በመጣስ በመኖሪያ ቤቷ በሃይማኖት እና በምገባ ስም እስከ መቶ የሚደርሱ ሰዎችን ሰብስባ በመገኘቷ በቁጥጥር መዋሏ ይታወቃል።በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የልዩ፣ ልዩ ወንጀሎች ምርመራ ዲቪዥን ሓላፊ ምክትል ኢንስፔክተር በድሉ ግርማ፣ ተጠርጣሪዋ በማኅበራዊ ድረ ገጽ ኮሮናቫይረስ የለም ተሳሳሙ፣ ተቃቀፉ፣ ተጨባበጡ በማለት አዋጁን በመፃረር የዜጎችን ሕይወት ለአደጋ አጋልጣለች በሚል መጠርጠሯን ገልጸዋል።

ከሃይማኖት ጋር በተያያዘ የተጠረጠረችበት ወንጀል ጉዳይ እየታየ መሆኑንም ተናግረዋል።ተጠርጣሪዋ በ2008 ዓ.ም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ መሀል ላይ የሚገኘውን ኮከብ ቀድዳ አውጥታ በማቃጠሏ መቀጣቷም ተጠቅሷል።ግለሰቧ ከሰማይ ታዝዤያለሁ በማለት ማረሚያ ቤት ድረስ በማቅናት ታራሚዎችን ልታስወጣ ስትሞክር እጅ ከፍንጅ ተይዛ መቀጣቷንም ኢንስፔክተሩ ገልጸዋል።

ከትላንት በስቲያ ማምሻውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተላልፋ በቁጥጥር ስር ስትውል አብረው ፖሊስ ጣቢያ ድረስ የመጡ 30 የሚጠጉ ተከታዮቿ ግርግር ሊፈጥሩ ቢሞክሩም ፖሊስ መክሮ ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ ማድረጉንም አመልክተዋል።ከእርሷ ጋር በግብረ አበርነት የተጠረጠሩ ሁለት ሴቶች ግን ምርመራ እየተካሔደባቸው መሆኑን ምክትል ኢንስፔክተር በድሉ ተናግረዋል። ግለሰቧ ለፖሊስ በሰጠችው የእምነት ክሕደት ቃል ርትዕት ተዋሕዶ የተሰኘ ሃይማኖት ለማስተዳደር ከሰማይ እንደተላከች እና ራሷም ንግሥተ ነገሥት ዘኢትዮጵያ መሆኗን ተናግራለች።

የስድስተኛው አገር አቀፍ ምርጫ ጉዳይ ለመጨረሻ ውስኔ ለቋሚ ኮሚቴ ተመራ

150 ሺህ የሚሆኑ የምርጫ አስፈጻሚዎችን ለማሰልጠንም እንዲሁ ወረርሽኙ አዳጋች በመሆኑ ቦርዱ የዳሰሳ ጥናት አካሂዶ ውሳኔ ላይ ደርሷል

(ኢዜአ) በኮቪድ-19 ምክንያት ለጊዜው እንደማይካሄድ የውሳኔ ሀሳብ የቀረበበት ስድስተኛው ብሔራዊ ምርጫ ለሕዝብ ተወካዮች ቀርቦ ለመጨረሻ ውስኔ እንዲረዳ በዝርዝር እንዲታይ ለቋሚ ኮሚቴ ተመራ።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ከተወያየባቸው ጉዳዮች ውስጥ አንዱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ስድስተኛው ብሔራዊ ምርጫን በተመለከተ ያቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ ማጽደቅና ቀጣይ የመፍትሄ ሀሳብ እንዲቀርብ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መምራት ነው።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ የጠቅላላ ምርጫን በተመለከተ ለምክር ቤቱ ዝርዝር ማብራሪያ አቅርበዋል።

ዘንድሮ ይካሄድል ተብሎ ለነበረው ምርጫ በቦርዱ የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ መሰረት የመራጮች ምዝገባ የሚጀምረው ከሚያዚያ 14 ቀን 2012 ዓ.ም ነበር።

በዚሁ መሰረት ከዚህ ቀን ጀምሮ የምርጫ አስፈጸሚው ምልመላ፣ ስልጠናና ስምሪት፣ የመራጮች ትምህርትና መመዝገቢያ ቁሳቁስ ስርጭቶችን ለማካሄድ ታስቦ ነበር ብለዋል።

ይሁን እንጂ ኮቪድ-19 በወረርሽኝ መልክ መከሰቱ ቁሳቁስ ለማሸግና የህትመት ውጤቶችን ለመዘጋጀት እንዳልተቻለ ተናግረዋል።

“በተጨማሪም 150 ሺህ የሚሆኑ የምርጫ አስፈጻሚዎችን ለማሰልጠንም እንዲሁ ወረርሽኙ አዳጋች በመሆኑ ቦርዱ የዳሰሳ ጥናት አካሂዶ ውሳኔ ላይ ደርሷል” ብለዋል።

የቦርዱ ውስኔም በጊዜ ሰሌዳው መሰረት መከናወን ያለባቸው ሥራዎች ለጊዜው እንዲቆሙ ተወስኗል፣ በቀጣይ ነገሮች ሲለወጡ ቦርዱ አዲስ የምርጫ ኦፕሬሽን ዕቅድና ሰሌዳ በማውጣት እንቅስቃሴ እንደሚጀምርም ተወስኗል።

ሌላው ቦርዱ መሰራት የሚችሉትን ስራዎች እየሰራ ለመቆየት ውስኔ መወሰኑን ጠቅሶ ምክር ቤቱ በዚህ ሁኔታ ምርጫውን ማካሄድ እንደማይቻል ተገንዝቦ ውስኔ እንዲያሳልፍ ጠይቀዋል።

ከአንድ የምክር ቤት አባል በስተቀር በአመዛኙ የምክር ቤቱ አባላት ውሳኔው ወቅታዊ፣ ትክክለኛና የሕዝቡን ደህንነት ያስቀደመ በመሆኑ ቦርዱ ሊመሰገን ይገባል ብለዋል።

እንድ አባል “እንደዚህ አይነት ውሳኔዎችን ረጋ ብሎ፣ አስተውሎ፣ የሚከተለውን ጦስ አመዛዝኖ ውሳኔ ላይ መድረስ አስፈላጊ ነው” ብለዋል።

አባሉ በምርጫ ቦርድ በኩል የቀረበው ውሳኔ ውስንነቶች ያሉበት መሆኑን ገልጸው በተለይ ደግሞ ቫይረሱ አሁን በኢትዮጵያ ወረርሽኝ ደረጃ ላይ ስለመድረሱ ጥርጣሬ እንዳላቸውም ገልጸዋል።

ነገሩ በአግባቡ ካልተጤነ ሊያስከትል የሚችለው የፖለቲካ አደጋ ቀላል አለመሆኑን መገንዘብና ለፖለቲካ ጤንነቱም መጨነቅ ተገቢ መሆኑን አሳስበዋል።

ሌሎች የምክር ቤት አባላት ግን ኮሮናቫይረስ የዓለም ዓቀፍ ስጋት እንደመሆኑ ቅድሚያ ለሰብዓዊነትና ለሰው ልጅ መስጡቱ ተገቢ ውስኔ ነው ብለውታል።

የቀረበው ውስኔ እውነታን መሰረት ያደረገ፣ ሕዝብ ከምርጫ በላይ መሆኑ የተገለጸበትና ትክክለኛ ውሳኔ ነው በማላትም ገልጸዋል።

ሂደቱ የኢትዮጵያን ፖለቲካና ፖለቲከኞች ሁኔታ የሚፈትን እንደመሆኑ መጠን አሁንም በዚህ ጉዳይ ሁሉንም አማራጮች መቃኘት ተገቢ መሆኑም ተመልክቷል።

አባላቱ የተወሰኑ አካላት በሽታውን ተገን አድረገው የስልጣን ጥማቸውን ለማርካት እየተንቀሳቀሱ መሆኑንም ጠቁመው ለዚህም በር መክፈት እንደማያስፈልግም ጠቁመዋል።

የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ በበኩላቸው ምክር ቤቱ ቦርዱን በቅርበት ክትትል ሲያደርግና ሲደግፍ መቆየቱን ያስታውሳሉ።

ውሳኔው ለሕዝቡ ጤንነት ቅድሚያ የሚሰጥና የፖለቲካ ጤናማነት ማስጠበቅ የሚያስችል እንዲሁም ሕግ መንግስቱን አክብሮ ለማስከበር የሚረዳ ነው ብለውታል።

በመጨረሻም ምክር ቤቱ ውሳኔውን በአብላጫ ድምጽ መርምሮ ካጸደቀ በኋላ ቀጣይ ለመጨረሻ ውሳኔ ይረዳ ዘንድ የመፍትሄ ሃሳብ እንዲቀርብ ለሕግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርቷል።

በተመሳሳይ ምክር ቤቱ በዛሬ መርሃግብሩ ለቆላማ አካባቢ የኑሮ ማሻሸያ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የሚውል ከዓለም አቀፍ ግብርና ልማት ፈንድ የተገኘ የ90 ሚሊዮን ዶላር ብድርም አጽድቋል።

“ብድሩ በአራት ክልሎች ለሚገኙ 100 ወረዳዎች የሚውል ሲሆን በዚህም 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሰዎችን ተጠቃሚ ያደረጋል” ተብሏል።

ከዚህ ባለፈ ኢትዮጵያ ለሁለተኛው አገር አቀፍ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት፣ ሳኒቴሽንና ሃይጂን ፕሮግራም ማስፈጸሚያ እንዲሁም ለደብረማርቆስ – ሞጣ መንገድ ማሳደጊያና ማሻሻያ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ ከሳዑዲ ለማት ፈንድ ጋር የተደረሰውን የብድር ስምምነት ረቂቅ አዋጅ አጽድቋል።

ሌላው ምክር ቤቱ በዛሬው ዕለት ያጸደቀው ረቂቅ አዋጅ የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የልህቀት ማዕከል መመስረቻ ማስፈጸሚያ እንዲውል ከኮሪያ ኤግዚም ባንክ ጋር የተደረገ የብድር ስምምነት ነው።

ምክር ቤቱ የኤሌክትሮኒክ ትራንዛክሽንን ለመደንገግ የወጣውን ረቂቅ አዋጅም ለሰው ኃብት ልማትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች መርቷል።

“… ከእንቅልፌ ስነቃ እዛው ነኝ ለካ… “

የትላንት ስብሰባ ላይ የተከበሩ ዶክተር አዲስ ዓለም ባሌማ ህወሃትን ወክለው ሲናገሩ በቀጥታ ቴዲ አፍሮ የዘፈናት ዘፈን ነበረች ያቃጨለችብኝ። ” … ከእንቅልፌ ስነቃ እዛው ነኝ ለካ ” ቴዲ ይደጋግማታል!!የተናጋሪውን ሃሳብ፣ እምነትና፣ የተሰጣቸው ተልዕኮ ልክ ሌሎችም በተመሳሳይ እንደሚያደርጉት ነውና አልገረመኝም። ከ”ባንዳነት” በቀር በፖለቲካው ዓለም መለዋወጥ/ መገለባበጥ የተለመደ በመሆኑ። ይህም የተለመደ የፖለቲካና የፖለቲከኞች አክሮባት ጊዜን፣ አካባቢያዊ ሁኔታን፣ ዓለም ላይ የሚከሰቱ ለውጦችን ወዘተ ተከትሎ ይሆናል። ሆኗል። ወደፊትም ይሆናል!! እድሜ የሰጠው ብዙ ያያል።እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ ህወሃትን የወከሉት ዶር አዲስዓለም ስለ ግልጽነት፣ መተማመን፣ ፍትሃዊ ምርጫ … እጅግ አስፈላጊነት ሲናገሩ ስሰማ ” እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ? እኔ ያለፉት 28 ዓመታት ጡት እጠባ ነበር? በአፍዝ አደንግዝ መስማትና ማየቴ ተውስዶ ነበር? ጤነኛ አልንበሩክም? …” እያልኩ እጠይቅ ነበር። እዛው፣ እድሮው ሰፈር መሆናቸው አስዘነኝ። ከማዘንም ባለፈ አስደነገጠኝ!!ሁለት የምርጫ ዘመን ከሃያ ወረዳዎች በላይ ምርጫ ሲዘረፍ አይቻለሁ፤ መዘረፍ ብቻ ሳይሆን በብሄር እየተለዩ ሰዎች ካርዳቸውን እንዳሻቸው እንዳይጠቀሙ ሲደረግ የነበረውን ሰምቻለሁ። በሚስጢር የተነገረኝም ጉድ አለ። የቻልኩትን ሪፖርት አድርጊአያለሁ። አዲስ አበባ የተወለድኩብት ቀበሌ ኮሮጆ ሲሰረቅ ህዝብ በነቂስ ወጥቶ በላንባዲና እያሰሰ ሲያስመልስ አይቻለሁ። እኚህ ሰው በአመራር ያሉበት ትህነግ መቶ በመቶ ምርጫ አሸነፍኩ ብሎ በአደባባይ የቃፊር ተስካር ደግሶ ራሱን ሲሞሽር አይቻለሁ። ይህንን ሁላችንም አይተናል። እናም ስለየትኛው የምርጫ ግልጽነት፣ ተአማኝነት፣ መተማመን ለማን እንደሚናገሩ ሳስብ ነው ወዲያው ዘፈኑ ያነቃኝ!! ” … ከእንቅልፌ ስነቃ እዛው ነኝ ለካ ” ከሁሉም በላይ ግን እኚህ ሰው ሰለ ግልጽነትና ስለመተማመን እየሰበኩን ባለበት ሰዓት የትህነግ ይፋዊ የፌስ ቡክ ገጽ ዲፋክቶ ስቴት ለማቋቋም እየሰራ መሆኑንን ይፋ አድርጎ ነበር። ከሁሉም በላይ ደግሞ ስለ አካታች፣ አሳታፊነትና መተማመንን የሚያሰርጽ ምርጫ አስፈላጊነት ሲናገሩ በአቋማቸው ሳቢያ አሸባሪ ተብለው ከኢትዮጵያ ፖለቲካ እድል ፈንታቸውን የተነፈጉ ፊት ለፊት ነበር። ይህ ብቻ አይደለም እሳቸው ያሉት ካልሆነ አገሪቱ ወደ እልቂት ታመራለችም ብለውናል። ይህን ስሰማ አንድ አፍቃሪያቸው “የስልክ እንጨት ዘመን” ብሎ ያስረዳኝ ታወሰኝ!!በዛ ስሜት ውስጥ ሆኜ ምላሹን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ” ዘመኑ ተቀይሯል፤ ብትፈልጉ በሚስጢር፣ ብትፈልጉ በቴሌቪዥን ህዝብ እየሰማ ችግር ካለ እንነጋገር” ብለው ሲጀመሩ፣ ቀሪውን ማዳመጥ አቃተኝ። እስኪ ህዝብ እየሰማ በቀጥታ ውይይት፣ ክርክር፣ ንትርክ ይካሄድ … ተመራቅዘን ከምንቀር፣ ምስኪን ሕዝብ በሴራ እየተዥጎረጎረ ከሚባትት መፍትሄ ቢሆን!! ሃምሳ ዓመት ሴራ ያማል!! ሃምሳ ዓመት መካካድ ያማል።ሰለ ” ባንዳነት” የተንሳው ጉዳይ የአገው ፖለቲከኛ አቤቱታ ጋር ተስታኮ ቢሆንም … መመራቀዙ የት እንደደረሰ ፍንትው አድርጎ የሚያሳይና ጉዳይ ከአገው ብሄራዊ ሸንጎ ትከሻና እሳቤ ውጪ መሆኑንን የሚያመላክት ነው። ዛሬ ዓለም ላይ በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ ቁጥራቸው ከ3.2 ሚሊዮን ዘሏል። 227 ሺህ በላይ ሰዎች ሞተዋል። አፍሪካ ጎዳናዋ ሁሉ አስከሬን ይሆናል እየተባለ ነው። ለወሬ፣ ለነጋሪ፣ ለምሁራን፣ ለሳይንቲስቶች፣ ለባለጠጎቹ ግራ ያጋባ ወረርሺኝ ዓለም እያስደገደገ ባለበት በዚህ ጥቁር ዘመን ውሃ የማይዘልቃቸው ደረቅ አልጌዎችንና የስልጣን ጥመኞችን ማየት ያሳዝናል። ተስፋም ያስቆርጣል። ልዩነትን በባንዳነት መመንዘር ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስላሉት ሳይሆን ቀድሞውንም የተደመጥ የአደባባይ ሚስጢር ነው። አገርን አጀንዳ እየቀያየሩ ማተራመስ ሆን ተብሎ በበጀት የሚሰራ የባንዳነቱ መተግበሪያ ቋት እንደሆነ ህዝብ ያውቃል። ለውጡ በእንጪጩ አጥመልምሎና አልፈስፍሶ ለመጣል ያልተማሰ ጉድጓድ የለም። ከግድያ ሙከራ ጀምሮ እስከ መፈንቅለ መንግስት ተሞክሯል። ሊፈርጥና ከሃድ ሊሆን በቋፍ ያለ የአማራ ክልል መሪዎችና ” ኢትዮጵያ” ሲል የሚያኮራው የጀነራል ሰዓረ ግድያም የዚሁ የባንዳነቱ ሌላው ማሳያ ነው።አማራ ክልልን ማፈራረስ፣ የመከለከያውን መሪ ገሎ ሰራዊቱን መበተን፣ የሶማሌ ክልልን ቀውስ ውስጥ መክተት፣ ዜጎችን ማፈናቀል፣ ማፈንና ዩኒቨርስቲዎችን ማተራመስ ሽፍታ ማምረት በባንዳነት ከሚገኝ ሂሳብ የሚወራረድ እንጂ ሌላ ምን ሊሆን አይችልም። ሌላም ሌላም …ይህ ሁሉ ህዝን አይመለከትም። ይህ ሁሉ የህዝብ ጉዳይ ሆኖ አያውቅም። ሴረኞች ለስልጣን ጥም ሲሉ የሚጭኑበት በሽታ ነው። ኮሮናው ብዙም ያልጨከነብን ለዚህ ይሆናል። ብዙ ተጎድተናልና!! ስንቴ እንጎዳ? በስንቱስ እንጎዳ? ደረቅ አልጌዎች የጅምላ መቃብር ፓርካቸው ነው። እዛው ናቸው። አማራና ኦሮሚያ የተፈጠሩ ውስን ዘረኛ ድርጅቶችም መቃብር አቋፋሪ ናቸው። እጅግ ጥቂት ዘረኞች የሚጋልቧቸው ፈረሶች ናቸው። አደጋና ስጋት አይታያቸውም። ድርጎ ልቡናቸውን ስለቦታል። ድርጎ ” ሙክት ያኮላሸውን” እንዲሉ አድርጓቸዋል። ለሁሉም ግን የምስኪኖ ሕዝብ አምላክ አለ!! እነሱ ግን እዛው ናቸው ” … ከእንቅልፌ ስነቃ እዛው ነኝ ለካ ፣ እዛው ነኝ ለካ፣እዛው ነኝ ለካ . እዛው ነኝ ለካ ..…