Category Archives: Socity / ማህበራዊ

«የእሥር ውሳኔውን ያስተላለፉት የተወሰኑ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት እንደሆኑ አውቃለሁ» ወ/ሮ ነፃነት አበራ

” .. የምናወራው ጉዳይ የጤንነቱ ጉዳይ ነው። ጤናው በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ ነው የሚገኘው። የልብ በሽተኛ ነው። የመተንፈሻ መሣሪያ ካልተገጠመለት ተኝቶ ማደር አይችልም። ሌላኛው ጉዳይ ያው የቤተሰብ ጉዳይ ነው። ስለልጆቻችን እንመካከራለን ማለት ነው…”

! … አቶ ገዱ የነበራቸው አቋም፤ ከአሠራር ክፍተት አኳያ ሁላችንም እንፈተሽ ከተባልን፤ ጥረት ላይ ከተፈጠረው በአሥር እጥፍ የሚበለጥ ግድፈት ሊገኝብን ይችል ይሆናል። ልዩነቱ ጥረት ላይ ሰው አሰማርተን መረጃ የማጥራት ሥራ መሥራታችን ነው። በዚህ ደረጃ ብንሄድ የሚቀር ሰው የለም የሚል አቋም እንደነበራቸው አውቃለሁ…”

BBC Amharic

በትግል ስማቸው ‘ጥንቅሹ’ ተብለው የሚታወቁት እና የጥረት ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት አቶ ታደሰ ካሳ ከአዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ የታገዱት ከወራት በፊት ነበር። ይህ ተሰምቶ ብዙም ሳይቆይ አቶ ታደሰ እና አቶ በረከት ስምዖን መታሠራቸው ተዘገበ። አሁን አቶ ታደሰ እና አቶ በረከት ከባህርዳር ከተማ ወጣ ብሎ የሚገኝ ማረሚያ ቤት ውስጥ ይገኛሉ።

ጥር 15፣ 2011 ዓ. ም. የተፈጠረውን የሚያስታውሱት የአቶ ታደሰ ካሳ ባለቤት ወ/ሮ ነፃነት አበራ፤ «የቀድሞው የአማራ ክልል ፕሬዝደንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸውም ሆነ አቶ ደመቀ እነ ታደሰ እንዲታሰሩ ፍላጎት አልነበራቸውም» ይላሉ። ሙሉ ቃለ ምልልሱ እነሆ።

ቢቢሲ፦ አቶ ታደሰ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የዋሉ ጊዜ የነበረውን ሁኔታ ያስውሱታል?

ወ/ሮ ነፃነት፦ ንጋት 1፡45 ገደማ ነበር። ፖሊሶች መጥሪያ ይዘው መጡ። በወቅቱ የት ነው የምሄደው? ብሎ ጠይቋቸው ነበረ። ያው ታደሰ በሥራ ብዛት ምክን አቶ ገዱ የነበራቸው አቋም፤ ከአሠራር ክፍተት አኳያ ሁላችንም እንፈተሽ ከተባልን፤ ጥረት ላይ ከተፈጠረው በአሥር እጥፍ የሚበለጥ ግድፈት ሊገኝብን ይችል ይሆናል። ልዩነቱ ጥረት ላይ ሰው አሰማርተን መረጃ የማጥራት ሥራ መሥራታችን ነው። በዚህ ደረጃ ብንሄድ የሚቀር ሰው የለም የሚል አቋም እንደነበራቸው አውቃለሁ።ያት የተለያዩ በሽታዎች አሉበት። የልብ ሕመም አለበት። ለማንኛውም ለዝግጅት እንዲሆን የት ነው የምሄደው? አማራ ክልል ነው ወይስ ፌዴራል ነው? የሚል ጥያቄ አቅርቦ ነበር። እዚሁ ፌዴራል ነው ጉዳያችሁ የሚታየው ነው ያሉን። ልብስ መያዝም አልፈቀዱለትም። ምናልባት ለዛሬ የሚሆን መድኃኒት መያዝ ትችላለህ ነው ያሉት። ስናረጋግጥ ግን ቻርተር አውሮፕላን አዘጋጅተው ነበር። በቀጥታ ወደቦሌ ነው የወሰዱት።

ቢቢሲ፦ ባህርዳር ከገቡ በኋላ የነበረውን ሁኔታ አቶ ታደሰ ነግሮዎታል?

ወ/ሮ ነፃነት፦ በግዜው እኔ አልሄድኩም። የአቶ በረከት ባለቤት እና ልጄ ነበር የሄዱት። ወደ ባህርዳር ዘጠነኛ ፖሊስ ጣብያ ነበር የሄዱት። እዚያ ሰብዓዊ መብታቸውን የሚጥስ ሁኔታ ነው የተፈፀመባቸው። መያዛቸውን ያወቁ ሰዎች በስድብ እና ዛቻ ነው የተቀበሏቸው። ሌቦች፣ ፀረ-አማራዎች እና የመሳሰሉ ስድቦች ሲሰደቡ ነበረ። ፖሊስ ወጣቶቹ ገለል እንዲሉ ጥረት አድርጓል፤ ግን ብዙ ሊርቁ አልቻሉም። በዚህም ምክንያት በ48 ሰዓታት ውስጥ ሊቀርቡ አልቻሉም። በእኔ እምነት ዘጠነኛ ፖሊስ የነበረውን ወከባ ለመቀነስ የፖሊስ ኃይል በመጨመር መካላከል ይቻል ነበር። ከእነሱ ቁጥጥር ውጪ የሆነ ነገር አለ የሚል እምነት የለኝም። እንዲሰደቡም ጭምር የአሣሪው አካል ፍላጎት አለ የሚል እምነት ነው ያለኝ።

ቢቢሲ፦ አቶ ታደሰ በሕግ ጥላ ሥር ከመዋላቸው በፊት ይህ ቀን ሊመጣ ይችላል ብለው አስበው ያውቃሉ? አውርታችሁ ታውቃላችሁ ስለዚህ ጉዳይ?

ወ/ሮ ነፃነት፦ የብአዴን 12ኛ ድርጅታዊ ጉባዔ አባል ነበርኩ። የፓርቲው የሁለት ዓመት ተኩል አፈፃፀም ላይ ያተኮረ ነበር ብዬ አልወስድም፤ በወቅቱ ስለነበርኩ ማለት ነው። በረከት እና ታደሰ ላይ ያተኮረ ስድብና ዛቻ ነው የነበረው። ጉባዔተኛው፤ «እነዚህ ፀረ-አማራ ናቸው፤ ታደሰ ትግሬ ነው፤ በረከት ደግሞ ኤርትራዊ ነው፤ ሰርገው የገቡ ናቸው፤ ጥረት ለብክነት የዳረጉ ናቸው፤ የሕወሓት ተለጣፊ ናቸው» እና የመሳሰሉ ነገሮች ሲነሱ ነበር። ማጠቃለያ ላይ የተነገረው ነገር ተገቢ አይደለም። የተናገረ፣ ሥነ ስርአት ያስያዘ ከፍተኛ አመራር ግን አልነበረም። ስለዚህ በጉባዔ ደረጃ የመጨረሻ መደምደሚያ የሆነው በሕግ እንጠይቃቸዋለን ነበር። ሁለቱም [አቶ ታደሰ እና አቶ በረከት] ይህንን ያውቁታል። ቢሆንም ታደሰ እታሠራለሁ የሚል እምነት አልነበረውም። ምክንያቱም በጥረት ጉዳይ የአሠራር ግድፈት ሊኖር ይችል ይሆናል፤ ይህ ደግሞ አስተዳደራዊ በሆነ መልኩ ሊታይ የሚችል እንጂ የሙስና ወንጀል ሆኖ እስከ አሥራት ሊያደርስ የሚችል አይደለም የሚል ፅኑ እምነት ነው የነበረው። እኔ ግን የስም ማጥፋት ዘመቻ እየተካሄ ነው፤ በሕዝቡ ዘንድ ስማችሁ ጠፍቷል እና ይህን ማስታገስ የሚችሉት እናንተን በማሠር ነው የሚል እምነት ነበረኝ። እሱ ግን ምንም ዓይነት ጥርጣሬ አልነበረውም። ጥር 15፤ በግምት 1፡45 አካባቢ ሲይዙትም ሳይገርመው አልቀረም።

ቢቢሲ፦ አቶ ታደሰ ላይ የጥላቻ ዘመቻ ተከፍቷል እያሉኝ ነው። ይህን የጥላቻ ዘመቻ ማነው የከፈተባቸው ብለው ያስባሉ?

ወ/ሮ ነፃነት፦ በስም እከሌ ብዬ መጥራት አልፈልግም። መሆንም የለበትም። እንደ ኮሚቴ የተሠራ ሥራ ነው ብዬ አስባለሁ። ሁሉም የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት በታደሰም ሆነ በአቶ በረከት መታሠር ፈቃደኛ ነበሩ ብዬ አላስብም። እንደሰማሁት እንግዲህ፤ መረጃው ያው ምስጢር አይደለም፤ ማዕከላዊ ኮሚቴ ላይ መታገድ አለባቸው እና የለባቸውም በሚል ክርክር ተደረገ። ውሳኔው ደሞ አቶ በረከትን ያካተተ አልነበረም። ታደሰ እና አቶ ምትኩ በየነ [የአምባሰል ንግድ ሥራዎች ኃላፊ] ላይ ነው የነበረው። በድምፅ ብልጫ ከማዕከላዊ ኮሚቴ እንዲታገዱ ተወሰነ። እዚህ ውሳኔ ላይ አቶ ገዱ የነበራቸው አቋም፤ ከአሠራር ክፍተት አኳያ ሁላችንም እንፈተሽ ከተባልን፤ ጥረት ላይ ከተፈጠረው በአሥር እጥፍ የሚበለጥ ግድፈት ሊገኝብን ይችል ይሆናል። ልዩነቱ ጥረት ላይ ሰው አሰማርተን መረጃ የማጥራት ሥራ መሥራታችን ነው። በዚህ ደረጃ ብንሄድ የሚቀር ሰው የለም የሚል አቋም እንደነበራቸው አውቃለሁ። አቶ ደመቀም ተመሳሳይ አቋም እንደነበራቸው አውቃለሁ።

ቢቢሲ፦ በሕግ ጥላ ሥር እንዲውሉ በመወሰኑ ላይስ?

ወ/ሮ ነፃነት፦ እንዲታሠሩ በመወሰኑ ላይ የእያንዳንዱ ሰው ሚና ምንድነው? የሚለውን በዝርዘር ባላውቅም፤ 25 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ተሰብስበው ነበር። በነገራችን ላይ 25 የብአዴን [አዴፓ] ሕጋዊ የማዕከላዊ ቁጥርም አይደለም፤ የአባላቱ ቁጥር 65 ነው። ከዚያ 13 ሰዎች ይታሠሩ፤ 12 ሰዎች ደግሞ አይታሠሩ የሚል ድምፅ ሰጡ። ስለዚህ በውሳኔ ነው የታሠሩት። ከከፍተኛ አመራሩ ማን ምን ብሎ ድምፅ እንደሰጠ ግን በውል አላውቅም።

ቢቢሲ፦ የኮሚቴው አባላት 65 ከሆኑ ለምን 25 ሰዎች ብቻ ተሰበስበው ይህን ውሳኔ ሊያስልፉ እንደቻሉ የምታውቁት ነገር አለ?

ወ/ሮ ነፃነት፦ እኔ ይህን አላውቅም። ሕጋዊ ነው የሚልም እምነት የለኝም። የኮሚቴው አባላት ቁጥር 65 ነው። ምናልባት በአንዳንድ ምክንያቶች የተወሰኑ ሰዎች ቢቀሩ 60 ወይ 50 ሊሆን ይችላል እንጂ በዚህ ደረጃ ዝቅ ያለ የማዕከላዊ ኮሚቴ ቁጥር አላውቅም።

ቢቢሲ፦ አቶ ታደሰን እየሄዱ የሚጠይቋቸው መች መች ነው? ሲያገኟቸውስ ምን ጉዳዮች አንስታችሁ ታወራላችሁ?

ወ/ሮ ነፃነት፦ እኔ በየሁለት ሳምንቱ እሄዳለሁ። ልጄ ግን ሁሌም ችሎት ባለ ቁጥር ትሄዳለች። ስንገናኝ ብዙ ጊዜ የምናወራው ስለ ፍርድ ሂደቱ ነው። እንደሚታወቀው ጠበቃ የላቸውም። ማግኘት አልቻሉም። ሁለት ጠበቆች አግኝተን ነበር። ነገር ግን ማስፈራሪያ ከደረሳቸው በኋላ ጉዳዩን መከታተል እንደማይችሉ ነገሩን። በሕግ ነው የተያዙት፤ ስለዚህ ጉዳዩ በሕግ ማለቅ አለበት። አስፈፃሚው አካል፤ ሕግ አውጭውም ጭምር የአማራ ማስ ሚድያን ተጠቅመው ጠበቃ እንዳይቆም እየተደረገ ያለው ነገር ትክክል እንዳልሆነ በይፋ መግለጫ መስጠት አለባቸው ብዬ አስባለሁ። ስለዚህ እዚህ አዲስ አበባ ላይ ያማከርናቸውን ጠበቆች ሐሳብ ነግረዋለሁ። ችሎት ላይ የተባለውን ነገር መነሻ በማድረግ እዚህ ካሉ ጠበቆች ጋር እንመክራለን። ሌላው የምናወራው ጉዳይ የጤንነቱ ጉዳይ ነው። ጤናው በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ ነው የሚገኘው። የልብ በሽተኛ ነው። የመተንፈሻ መሣሪያ ካልተገጠመለት ተኝቶ ማደር አይችልም። ሌላኛው ጉዳይ ያው የቤተሰብ ጉዳይ ነው። ስለልጆቻችን እንመካከራለን ማለት ነው።

ቢቢሲ፦ የሚያስፈልጋቸውን ሕክምናና የምግብ አገልግሎት እያገኙ ነው?

ወ/ሮ ነፃነት፦ ያው እሥር ቤት ውስጥ እንደማንኛውም ሰው የምግብ አቅርቦት ነው ያለው። ባለው ርቀት ምክንያት የሚያስፈልገውን ነገር ልናደርግ አልቻልንም። እዚያው ማረሚያ ቤት ውስጥ አንድ ካፌ አለ እዛ ነው የሚጠቀመው። የጤና ጉዳይ እዚያ ባለው ክሊኒክ ወይም ሆስፒታል መፍትሄ ማግኘት የሚችል አይደለም። ነገር ግን አስፈላጊው መድኃኒት እንዲቀርብላቸው እናደርጋለን።

ቢቢሲ፦ አቶ ታደሰ ያለፈውን ነገር ዞር ብለው ሲያዩት ምን እንደሚሰማቸው ጠይቀዋቸው ያውቃሉ?

ወ/ሮ ነፃነት፦ በአንድ በኩል መታሠሩ ግፍ እንደሆነ ያየዋል። ታደሰ የጥረት ኮርፖሬት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆኖ ሲገባ 4 ድርጅቶችን ነው የተረከበው። በስምንት ዓመታት ውስጥ በሱ አመራር ሥር ድርጅቶቹ ከ4 ወደ 21 አድገዋል። ይሄ በግልፅ የሚታወቅ ነገር ነው። አማራ ውስጥ ስለ ኢንዱስትሪ ጉዳይ ሲነሳ ጥረት በታደሰ እየተመራ የሠራቸው ሥራዎች ናቸው የሚነሱት። ይሄን ለሠራ ጀግና፤ ይሄን ለሠራ የልማት አርበኛ ሽልማት ሲገባው በአሠራር ጉድለት፤ በተለይ ደግሞ የፖለቲካ ልዩነትን መነሻ በማድረግ እሥር ቤት መግባቱ፤ ይህን ደግሞ ያደረጉት አብረውት የታገሉ፤ የሚያምናቸው ሰዎች መሆናቸው በጣም ያሳዝነዋል። በአንድ በኩል ይሄ ነው። በሌላ በኩል ግን ጀግንነት ይሰማዋል። እኔ ታደሰ ካሳ በሕይወት ታሪኬ በሙስና የምታወቅ አይደለሁም። እንደውም አይበላ አያስበላ ነው የምባለው። ስለዚህ እውነተኛ ፍትህ ካለ የጠፋውን ስሜን አጠራለሁ። ነገ ከነገ ወዲያ የአማራ ሕዝብ እውነታውን ይረዳል ብሎ ያስባል።

ቢቢሲ፦ የሚቆጫቸው ነገርስ ይኖር ይሆን? ባደርገው ወይም ባላደርገው ኖሮ የሚሉት?

ወ/ሮ ነፃነት፦ ብዙም የሚቆጨው ነገር የለም። የሚያስቆጭ ሥራ አልሠራም። የሚቆጨው ይሆናል ብዬ የማስበው ከሐምሌ ጀምሮ የተደረገ የስም ማጥፋት ዘመቻ አለ። ምናልባት ራሱን ግልፅ ለማድረግ የሚያስችል መድረክ አለማግኘቱ ነው። ብዙ ጊዜ የስም ማጥፋት ዘመዛ ሲደረግ በዝምታ አልፏል። በዝምታ ከማለፍ ማን ምን እንደሆነ መናገር ነበረብኝ ይላል። ይሄ ይቆጨዋል ብዬ አስባለሁ።

ቢቢሲ፦ ከሃገር የመውጣት ሃሳብስ አልነበራቸው ይሆን?

ወ/ሮ ነፃነት፦ ታደሰ ከሃገር የመውጣት ፍላጎት የለውም። ሃሳቡ ጡረታ ከወጣ በኋላ አዲስ አበባ ሳይሆን ቢሆን ሰቆጣ ወይ ደግሞ ወልዲያ እሄዳለሁ የሚል ነበር። እውነት ለመናገር ከሃገር መውጣት ቢፈልግ መውጣት የሚያስችሉ ብዙ አማራጮች ነበሩት። የሁለት ዓመት የአሜሪካ ቪዛ አለው። የእንግሊዝም አለው። ነገር ግን በተገኘው አጋጣሚ ሕዝቡን የማገልገል ሃሳብ ነበር የነበረው።

ቢቢሲ፦ አቶ ታደሰ የተመሠረተባቸው ክስ ውድቅ ሆኖ በቅርቡ እለቀቃለሁ ብለው ያስባሉ?

ወ/ሮ ነፃነት፦አ. . . አዎም አይደለም ነው የዚህ ምላሽ። እውነተኛ ፍትህ ኖሮ፤ ዳኞች እና አቃቤ ሕጎች የአስፈፃሚው አካል ተፅዕኖ ከሌለባቸው፤ ወደ ክስ መከራከሪያ ሳንገባ በክስ መቃወሚያችን ብቻ ይሄ አያስከስስም ተብሎ፤ ውድቅ ተደርጎ ልንወጣ እንችላለን [አቶ ታደሰና አቶ በረከትም] የሚል ሃሳብ አለ። ምክንያቱም በሙስና ወንጀል የተከሰሱ ሁሉም ከአሠራር ግድፈት ጋር የተያያዘ ስለሆነና የአሠራር ግድፈት ደግሞ የሙስና አንቀፅን መጥቀስ ስለማይችል ዳኞች ያቀረብነውን መቃወሚያ አይተው ውድቅ ሊሉት ይችላሉ። ይህ ግን ፍትህ ካለ ነው። የአስፈፃሚው አካል ተፅዕኖ ከሌለበት ይህ ሊሆን ይችላል የሚል እምነት አለው። ነገር ግን እየተደረገ እንዳለው ጠበቃ ሊቆምላቸው ካልቻለ፤ የስም ማጥፋት ዘመቻ በሚድያ ከተደረገባቸው፤ ይህ ደግሞ በዳኞች እና በፍትህ ሥርዓቱ ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድር ከሆነ በነፃ መውጣት የሚቻልበት ሁኔታ የማይታሰብ ነው የሚል እምነት አለው።

ቢቢሲ፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ የአቶ በረከትን ቤተሰቦችን እንዳናገሩ ሰምተናል። በፍርድ ሂደቱ ጣልቃ መግባት እንደማይችሉ፤ ነገር ግን ፍትህ እንዳይጓደል እንደሚያሳስቡ ሰምተናል። የአቶ ታደሰን ቤተሰብስ አግኝተው ነበር?

ወ/ሮ ነፃነት፦ አዎ! ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በጋራ ነው ያገኙን። የአቶ በረከት ባለቤትንም፤ እኔንም ጠርተው ነው ያናገሩን። ስላሉበት ሁኔታ፤ ስለደረሰባቸው የሰብዓዊ መብት ጥሰት፤ እሥሩ ፖለቲካዊ እንደሆነ፤ በተለይ ደግሞ ጠበቃ የማጣታቸው እና የጤንነታቸው ጉዳይ እንደሚያሳስበንና በፍትህ እንዲዳኙ እንደምንሻ ነግረናቸዋል። ከምንም በላይ ፍትህ ብቻ እንዲዳኛቸው እኔም አናግሬያቸዋለሁ።

ኢትዮጵያ የኒውክሌር ቴክኖሎጂን መጠቀም ትሻለች

ኢትዮጵያ የኒውክሌር ቴክኖሎጂን በህክምና፣ በግብርናና በኢንደስትሪ ዘርፍ ጥቅም ላይ ለማዋል እንቅስቃሴ መጀመሯን ዐስታወቀች። የህክምና ዘርፉን በኢትዮጵያም ለማዘመን የቀዶ ጥገና ህክምናውን ጥራት ለማሻሻል እንዲሁም የኢነርጂ እና የግብርና ክፍለ ኢኮኖሚ ዘርፍ ለማሳደግ የኒውክሌር ቴክኖሎጂ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረውም ሚኒስትሩ አስረድተዋል።

የኒውክሌር ቴክኖሎጂ በኢትዮጵያ ለመጀመር እንውስቃሴ መጀመሩ ተገልጧል

ኢትዮጵያ የኒውክሌር ቴክኖሎጂን በህክምና፣ በግብርናና በኢንደስትሪ ዘርፍ ጥቅም ላይ ለማዋል እንቅስቃሴ መጀመሯን ዐስታወቀች። የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ጀማል በከር በተለይ ለዶቼ ቨለ (DW) እንደገለጹት በቅርቡ በ11 ኛው ዓለም አቀፉ የአቶም ኤክስፖ ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ ከሩሲያ ጋር የተፈራረመችው የሁለትዮሽ የኒውክሌር ቴክኖሎጂ የፍኖተ ካርታ ትግበራ ስምምነት ዓለም አቀፍ ሰላማዊ ስምምነቶችን እና ድንጋጌዎችን መሠረት ያደረገ ነው ብለዋል። በአሁኑ ወቅት በዓለም ላይ እያደገ የመጣውን የህክምና ዘርፍ በኢትዮጵያም ለማዘመን የውጭ ምንዛሪ ወጭን ለማዳን እንዲሁም የቀዶ ጥገና ህክምናውን ጥራት ለማሻሻል እንዲሁም የኢነርጂ እና የግብርና ክፍለ ኢኮኖሚ ዘርፍ ለማሳደግ የኒውክሌር ቴክኖሎጂ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረውም ሚኒስትሩ አስረድተዋል።

እንደ ጎርጎሪዮሱ አቆጣጠር ከግንቦት ወር 1954 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ የተለያዩ ክፍሎች የዩራንየም ክምችት መገኘቱን ኒዎርክ ታይምስ እና ሌሎችም የመገናኛ አውታሮች በዘገባቸው ዐስታውቀው ነበር። ሆኖም ይህን ለተለያዩ የምርት ግብአቶች እና ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች እጅግ ጠቃሚ እና ተፈላጊ የሆነ የተፈጥሮ ሃብት አገሪቱ ጥቅም ላይ ሳታውለው ለበርካታ ዓመታት ቆይታለች። በቅርቡ ግን በሩስያ በተካሄደው 11ኛው ዓለማቀፍ የአቶም-ኤክስፖ ጉባኤ ላይ የኢትዮጵያ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር  ዶ/ር ጌታሁን መኩሪያ እና የሩስያ መንግሥት አቶሚክ ኢነርጂ ኮርፖሬሽን ዳይሬክተር ጀነራል አሌክሲ ሌካቼቭ የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያስችል የሁለትዮሽ የትግበራ ፍኖተ-ካርታ ስምምነት ተፈራርመዋል። ይኸው ስምምነት የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ለኃይል ማመንጫ፤ ለግብርና፤ ለኢንዱስትሪው ዘርፍ ግብዓት የሚውሉ ዘመናዊ ቁሶችን ለማምረትና፤ የህክምናውን ዘርፍ ለማዘመን ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያስችል መሆኑንም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ጀማል በከር በተለይ ለዶቼቨለ (DW) ገልጸዋል።

Äthiopien | Innovation & Technology Minister Jemal Beker Audio to listenAudio to listenAudio to listenAudio to listen

 

የኒውክለር ቴክኖሎጂን በኢትዮጵያ ማስፋፋት በተለይ በዓለም እያደገ የመጣውን የህክምና ዘርፍ በኢትዮጵያ በማዘመን የጨረር ህክምና አገልግሎቶችን ለህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ ለማዳረስ እንዲሁም በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ በሌሎች አገራት እንደ ካንሰር ያሉ በሽታዎችን ለመታከም ህሙማን ያወጡት የነበረውን  ወጪ ለማስቀረትና ለመንግስት ፈተና የሆነውን የውጭ ምንዛሬ እጥረትም ለመቅረፍ ይረዳል ነው የሚሉት ሚኒስትሩ።  ከዚህም ባሻገር የቀዶ ጥገና ህክምናን የተቀላጠፈ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል ሲሉ ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ጀማል አስረድተዋል። ቴክኖሎጂው ትላልቅ ኢንደስትሪዎችን በኢትዮጵያ ለመገንባት ብሎም በዝናብ ላይ ጥገኛ ከሆነው የኃይል ማመንጫ ኢትዮጵያን በማላቀቅ ወደ ድብልቅ የኢነርጂ አማራጮችም ለማሸጋገር ጠቀሜታ አለው ነው ያሉት።

ኢትዮጵያ እንደ ኦፓል የከበረ ማዕድን እንዲሁም ለሞባይል ስልኮች እና ልዩ ልዩ የኤሌክትሮኒክስ ምርቶች ግብአት እጅግ ተፈላጊ የሆነውን  ታንታለምን ጨምሮ ለኒውክለር ቴክኖሎጂ ምርት የሚያገለግለው ዩራኒየም ከፍተኛ ክምችት እንዳላት ቢታወቅም በምርቶቹ ሽያጭ እና ገቢ ላይ መንግሥትን ግልጽነት ይጎለዋል የሚሉ ነቀፌታ እና ትችቶች በተለያዩ ወገኖች ሲሰነዝሩ ቆይተዋል። በተለይ በሚንስቴር መስሪያቤቱ አሁን ለመጀመር የታቀደው የኒውክለር ቴክኖሎጂ ዓለማቀፍ ሰላማዊ የኒውክሌር ቴክኖሎጂ ስምምነቶችን በማክበር ለተፈለገው አገልግሎት ብቻ ጥቅም ላይ የመዋሉን ሂደት በተመለከተ የትግበራ ፍኖተ ካርታ ስምምነቱ ምን ምን ያህል ግልጽነት የተሞላው ነው ስንል  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታውን አቶ ጀማል በከር ጠይቀናቸው ነበር።  ” በ 11 ኛው ዓለማቀፉ የአቶም ኤክስፖ ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ ከሩሲያ ጋር የተፈራረመችው የሁለትዮሽ የኒውክሌር ቴክኖሎጂ የፍኖተ ካርታ ትግበራ ስምምነት ዓለማቀፍ ሰላማዊ ስምምነቶችን እና ድንጋጌዎችን መሰረት ያደረገ ነው ” ሲሊ ነው ሚኒስትር ዴኤታው የሃገራቱ ስምምነት የተመሰረተበትን ዋና ማዕቀፍ ያብራሩት።

Audio to listen

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የኒውክለር ቴክኖሎጂን በኢትዮጵያ ለማስፋፋት ከጀመረው እንቅስቃሴ ጎን ለጎን የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲም የኒውክሌር ግንባታ፤ የባዮ ቴክኖሎጂዎች፤ ዘላቂ የኃይል አቅርቦትና የሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪ ተማሪዎች የምርምር ስራዎቻቸውን የሚያከናውኑባቸው፤ሌሎች የልህቀት ማዕከላትን አቋቁሞ አገሪቱን ዓለም ከደረሰችበት ዘመናዊ የዕድገት ደረጃ ለማድረስ ጥረት እያደረገ ሲሆን ለምርምርና ቴክኖሎጂ ስርፀት Audio to listenተግባራት የሚያገለግል ግዙፍ የቤተ-ሙከራ ማዕከላትን ያካተተ ተጨማሪ ህንፃም ለመገንባት እየተዘጋጀ መሆኑን በቅርቡ አስታውቋል።

እንዳልካቸው ፈቃደ -ማንተጋፍቶት ስለሺ – ሸዋዬ ለገሰ

ከማህጸን ስለሚወጣ ፈሳሽ ምን ያህል ያውቃሉ?

እድሜያቸው ወደ 60 ዓመት የሚጠጋ ወይዘሮ ናቸው። ወደ ሃኪም ዘንድ የሄዱት ደም የቀላቀለ ፈሳሽ ከማህጸናቸው መውጣት ከጀመረ ከዓመት በኋላ ነበር።

ወይዘሮዋ ቀደም ብሎ ከፍ ያለ ህክምና እንዲያገኙ በሃኪም ቢታዘዙም ባለቤታቸው ፈቃደኛ ስላልሆኑ ቤታቸው ቆይተዋል።

ችግሩ ሲከፋ ወደ ሃኪም ዘንድ ቀርበው ለዶ/ር ቤርሳቤህ መናሻ “ከዚህ በፊት አንድ ጊዜ ታምሜ ሪፈራል ተፅፎልኝ ባለቤቴ ስላልፈቀደ ችላ በማለት ሳልታከም ቀረሁ” ብለው ሲነግሯት በጣም እንዳዘነች ታስታውሳለች።

“ማህበረሰባችን የበሽታውን ክብደት ብዙም ስለማይገነዘበው በርካታ ሴቶች ህመማቸውን ይዘው ከፍተኛ ደረጃ ላይ እስኪደርስ ድረስ ይቆያሉ” ትላለች ዶ/ር ቤርሳቤህ።

ለወይዘሮዋ አስፈላጊውን ምርመራና ህክምና አድርጋ በድጋሚ ለተጨማሪ ህክምና ከፍ ወዳለ ሆስፒታል ስትልካቸው ባለቤትየው “እህል የምናበረይበት ወቅት ስለሆነ ሰው ያስፈልገኛል” ብለው ሞገቱኝ ትላለች።

ይህ አጋጣሚ የእኚህ እናት ብቻ አይደለም። ብዙ ሴቶች ይህን አሳዛኝ ታሪክ እንደሚጋሩ ዶ/ር ዳግም ታደለም “ብዙዎቹ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ሲደርሱ ነው እኛ ጋር የሚመጡት” በማለት ያረጋግጣል።

ከማህጸን የሚወጣ ፈሳሽ የካንሰር፣ የአባላዘር በሽታዎችና የሌሎች ኢንፌክሽኖች አንዱ ምልክት ሆኖ ሳለ ብዙዎች ስለጉዳዩ ዕውቀት አለማግኘታቸውና ለመነጋገር አለመቻላቸው ችግሩን አባብሶታል።

እርሶስ ስለጉዳዩ ምን ያህል ያውቃሉ?

ከማህጸን ስለሚወጣ ፈሳሽ በማህበረሰቡ ውስጥ በቂ እውቀት እንዲኖር የሚያስችል አጋጣሚ የለም የሚሉት ባለሙያዎቹ የራሳቸውን ተሞክሮ ያስታውሳሉ።

ዶ/ር ቤርሳቤህ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷ ውስጥ በግልፅ ከማህፀን ስለሚወጣ ፈሳሽ ባለመማሯ “የህክምና ሙያ ባላጠና ኖሮ ስለዚህ ጉዳይ አለላውቅም ነበር” ትላለች።

የጥቁር አንበሳ የህክምና ትምህርት ቤት ተማሪ የሆነው ሃብቶም አለሙም ዩኒቨርሲቲ ከመግባቱ በፊት ስለዚህ ጉዳይ ለምን በትምህርት ቤት ሳለ እንዲያውቅ እንዳልተደረገ ጥያቄ እንደፈጠረበት ይናገራል።

ከማህፀን የሚወጣ ፈሳሽ ምንድን ነው?

በእንግሊዘኛው ‘ቫጃይናል ዲስቻርጅ’ የሚባለው ከማህፀን የሚወጣ ፈሳሽ የአንድ ሴት የወር አበባ ኡደትን ተከትሎ በተለያየ መጠንና ዓይነት ከማህጸን የሚወጣ ፈሳሽ ነው።

ማህፀንና ፅንስን የሚያጠኑት ዶ/ር ዳግም ከማህፀን የሚወጣ ፈሳሽ ጤናማ የሆነ ተፈጥሯዊ ነገር ሲሆን፤ በሽታ ሲይዝ ግን ጤናማ ያልሆነ ሽታ ሊያመጣና ቀለሙም ሊቀየር እንደሚችል ይናገራሉ።

ይህ ከማህፀን የሚወጣ ተፈጥሯዊ ፈሳሽ ከሆርሞን የሚመነጭ እንደሆነ የሚናገሩት ዶ/ር ዳግም “አንዲት ሴት ሁሌም ይህ ፈሳሽ ሊኖራት ይችላል። እንዲያውም በቀን ከ 1 እስከ 4 ሚሊሊትር ሽታ የሌለው ከማህፀን የሚወጣ ነጭ ፈሳሽ ጤናማ ተደርጎ ይወሰዳል” ይላሉ።

ይህ ተፈጥሯዊ የሆነ የፈሳሽ መጠን ግን ሴቷ ጤናማ ሁኔታ ላይ ሆናም በእርግዝናና በአንዳንድ እርግዝና መከላከያዎች ምክንያት መጠኑ ሊቀየር እንደሚችል ዶክተሩ ይናገራሉ።

ከማህፀን የሚወጣው ፈሳሽ የማህፀን ካንሰርና በግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎች ምልክት ሊሆን ይችላል። እነዚህ በሽታዎች በሚያጋጥሙ ጊዜም የፈሳሹ መጠን፣ ጠረንና ቀለም ሊለወጥ ይችላል።

Image copyright AFP Contributor

በግልጽ የማይነገር ጉዳይ

በርካታ ሴቶች ከማህጸን ስለሚወጣ ፈሳሽ በግልጽ በአስፈላጊው ጊዜ ለመናገር አይደፍሩም። ለሃኪሞችም ቢሆን የሚገልጹት ከብዙ ጉትጎታ በኋላ ነው።

“ታካሚዎች ከማህፀን የሚወጣ ፈሳሽ ለውጥ እንዳለ የሚናገሩት ሌሎች ምልክቶችን ጠቅሰው ሲጨርሱ መጨረሻ ላይ ነው” የምትለው ዶ/ር ቤርሳቤህ ለማውራት ነፃነት እንዲያገኙም ባሎችን ወይም ሌሎች ሰዎችን አስወጥተን ነው የምናነጋርራቸው ትላለች።

አንድ ታካሚዋ ከማህጸኗ የሚወጣው ፈሳሽ ደም ከመቀላቀል አልፎ ህመም ሲበረታባት እንደመጣች የምታስታውሰው ዶ/ር ቤርሳቤህ “በርካታ ሴቶች የማህፀን ፈሳሻቸው ከተለመደው የተለየ ሲሆን ህክምና ፈልገው አይመጡም፤ ሁሌም ከእሱ ጋር የተያያዘ ሌላ ህመም ሲኖራቸው ብቻ ነው የሚመጡት” ትላለች።

በተለይ ከከተማ ውጪ የሚኖሩ ሴቶች ከማህፀን የሚወጣ ፈሳሽ ሲቀየር ህክምና ባለማድረጋቸው ምክንያት ችግሩ ከማህጸን ጫፍ ወደ ውስጥ በመግባት ኢንፌክሽን ፈጥሮ ሌላ ከባድ ችግር ሲያጋጥማቸው ወደህክምና እንደሚሄዱ ዶ/ር ዳግምም ይናገራሉ።

ዶ/ር ቤርሳቤህ እንደምትለው ከማህጸን የሚወጣው ፈሳሽ የካንሰር፣ የአባላዘር በሽታዎችና የሌሎች ኢንፌክሽኖች ምልክት ሆኖ ሳለ በጉዳዩ ላይ በግልጽ መነጋገር ስለማይደፈር፤ ያለው የህክምና አገልግሎት እርዳታ እንዳያደርግ መሰናክል እንደሆነበት ትናገራለች።

ከማህጸን በሚወጣ ፈሳሽ ላይ የሚታዩ ለውጦችን በመከታተል በጊዜ ወደ ህክምና መሄድ ከቻሉ ለካንሰርም ሆነ ለአባላዘር በሽታዎች የተሻለ ህክምና በማግኘት ጤናቸውን የማሻሻል ዕድል እንዳለ ባለሙያዎቹ ይመክራሉ።

የህክምና ድጋፍ ለማግኘትም የሚከተሉትን ምልክቶች ትኩረት ሰጥቶ ማስተዋል ያስፈልጋል። ከማህጸን የሚወጣ ፈሳሽ ሽታ ወይም ቀለም መቀየር፣ ደም መቀላቀል፣ የመራቢያ አካላት መቅላትና በግብረ ሥጋ ግንኙነት ወቅት የህመም ስሜት ካለ ባለሙያ ጋር በመሄድ ማማከር ያስፈልጋል።

ትምህርት ቤቶችና የሥነ ተዋልዶ

የትምህርት ተቋማት ለተማሪዎቻቸው ከማህጸን ስለሚወጣ ፈሳሽና ስለሌሎች የሥነ ተዋልዶ ጉዳዮች በግልጽና በአግባቡ ማስተማር ከቻሉ በህብረተሰቡ ውስጥ ያለው ሀፍረትና የህክምና ድጋፍ ለማግኘት ያለመድፈር ጉዳይ ሊቀረፍ እንደሚችል ባለሙያዎቹ ይናገራሉ።

በአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሳለች “ስለ ሥነ ተዋልዶና የተያያዠ ጉዳዮች ስንማር በአስተማሪው ተነሳሽነት ላይ ይወሰን ነበር” የምትለው ዶ/ር ቤርሳቤህ፤ ብዙም ጠለቅ ያለና ስለጉዳዩ በቂ ግንዛቤን የሚያስጨብጥ ትምህርት እንዳልሆነ ታስታውሳለች።

አክላም በመጀመሪያና በሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷ ወቅት ስለ ሥነ ተዋልዶና ስለየወር አበባ ብትማርም ሴቶች ስለሚያጋጥማቸው ከማህፀን የሚወጣ ፈሳሽ ምንም ነገር ስላልተማረች በወቅቱ ምንም የምታውቀው ነገር እንዳልነበረ ትገልጻለች።

አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው የቦሌ መሰናዶ ትምህርት ቤት መምህር የሆኑት አቶ ተሾመ መሳፍንት የባዮሎጂ መምህር ሲሆኑ፤ የሥነ ተዋልዶ ትምህርት 7 እና 8ተኛ ክፍል እንደሚሰጥ ነገር ግን በ11ኛ እና 12ኛ ክፍል የባዮሎጂ ትምህርት ውስጥ እንደሌለ ይናገራሉ።

ዶ/ር ቤርሳቤህ “ወንዶች ህክምና ካላጠኑ በስተቀር ከማህፀን ስለሚወጣ ፈሳሽ የማወቅ እድል የላቸውም” ስትል ከዚህ ተመሳሳይ በሆነ መልኩ ዶ/ር ዳግምም “ህክምና ስማር አንብቤ ነው ያወኩት” ብሏል።

ከታች ባሉት የትምህርት ክፍሎች ውስጥ ከሥነ ተዋልዶ ትምህርት ጋር ተጣምሮ ከማህጸን ስለሚወጣ ፈሳሽ ትምህርት ቢሰጥ መልካም እንደሆነ የሚገልጹት ሁለቱ የህክምና ባለሙያዎች እነሱም ስለፈሳሹ ያወቁት ህክምና በማጥናታቸው እንደሆነ ይመሰክራሉ።

BBC Amharic

በጀነራል ዋቆ ጉቱ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ባልታወቀ ምክንያት ራሳቸውን ስተው ወደ ሆስፒታል የገቡ ተማሪዎች በመልካም ሁኔታ እንደሚገኙ ተገለጸ

በጀነራል ዋቆ ጉቱ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ራሳቸውን ስተው ወደ ሆስፒታል የገቡ ተማሪዎች በጥሩ ጤንነት ላይ የሚገኙ መሆኑን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

ዛሬ ከሰዓት በትምህርት ቤቱ ለጊዜው ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ 37 ተማሪዎች ራሳቸውን ስተው መውደቃቸውን እና አስፈለጊው የህክምና ድጋፍ ተደርጎላቸው አብዛኞቹ ተማሪዎች ወደ ቤታቸው መመለሳቸው ተገልጿል።

የቢሮው ምክትል ሃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ እንደገለጹት ራሳቸውን ስተው የወደቁ ተማሪዎችን ወደ ቤቴል ሆስፒታ እንዲወሰዱ በማድረግ ህክምና ማግኘታቸውን ተናግረዋል።

ህክምና ከተደረገላቸው በኋላም 34 የሚሆኑ ተማሪዎች ተሽሏቸው በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙና ሶስቱ ተማሪዎች ተጨማሪ ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በቤተል ሆስፒታል በተደረገው ምርመራ ይሄነው የሚባል ውጤት ባለመገኘቱ የታካሚዎቹ የደም ናሙና ለተጨማሪ ምርመራ ወደ ጳውሎስ ሆስፒታል መላኩን ከአዲስ ቲቪ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

FBC

ሸዋ ዳቦ ከመንግስት ጋር የነበረውን ትስስር በመተው የዋጋ ጭማሪ አድርጓል

ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች በርካታ ማከፋፈያዎች ያሉት ሸዋ ዳቦ ከመንግስት ጋር የነበረውን ትስስር በመተው የዋጋ ጭማሪ አድርጓል።

ሸዋ ዳቦ በረጅም ዘመን አገልግሎቱ እና በምርቱ ጥራት ሲወደስ ቢቆይም ከሚያዚያ 1 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ የዋጋ ጭማሪ ማድረጉ ቅሬታን አስነስቷል።

ድርጅቱ ባለ መቶ ግራሙን ዳቦ ከ1 ብር ከ30 ወደ 2 ብር ከ50 ሳንቲም እንዲሁም ባለ 200 ግራሙን ደግሞ ወደ 5 ብር ዋጋቸውን ከፍ አድርጎታል።

ለዚህም በመንግስት በድጎማ የሚቀርበው ስንዴ መቆራረጥን ተከትሎ በግሉ ከገበያ በገዛው ስንዴና ዱቄት አምርቶ ለገበያ ለማቅረብ መወሰኑን የድርጅቱ የአስተዳደር፣ ምርትና ቴክኒክ ሀላፊ አቶ ግርማ ታደሰ ተናግረዋል።

በስንዴ አቅርቦት ችግር ምክንያት 40 ሚሊየን ብር የወጣበት ዳቦ መጋገሪያ ማሽን ስራ ማቆሙንም አስታውሰዋል።

በኢትዮጵያ አሁን ባለው ገበያ ስንዴ በኩንታል እስከ 1 ሺህ 700 ብር ሲሸጥ በውጭ ሀገራት ግን ከትራንስፖርት እና ሌሎች ወጪዎች ውጭ 550 ብር በሚደርስ ዋጋ ይገኛል።

እናም ሀገሪቱ በየአመቱ በገፍ ስንዴን ከውጭ እያስገባች ለህብረተሰቡ ዳቦ እና ዱቄት መንግስት በሚቆርጠው ዋጋ ለሚያቀርቡ አምራቾች እና አከፋፋዮች በድጎማ ታቀርባለች።

በዚህም ህብረተሰቡም ሆነ አምራቾች ተጠቃሚ መሆናቸውን ነው የንግድ ሚኒስቴር የሚገልፀው።

ሸዋ ዳቦ ግን የሚቀርብለት የድጎማ ስንዴ በቂ አለመሆኑንና በፍጥነት እንደማይደርስለት በመጥቀስ በድጎማ ስንዴው ምርት እያመረቱ በመንግስት በተቆረጠ ዋጋ ማቅረብ አዋጭ አይደለም በሚል ከንግድ ሚኒስቴር ጋር ውሉን ቀዷል።

የንግድ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተሩ አቶ ወንድሙ ፍላቴ፥ ሚኒስቴሩ የድርጅቱን ውሳኔ እንደሚያከብር ጠቅሰው ስራው ትርፋማ መሆኑን ራሱ ድርጅቱ ባጠናው ጥናት አረጋግጧል ይላሉ።

ከዋጋ ጭማሪው ጋር በተያያዘም በነፃ ገበያ መርህ ሸዋ ዳቦ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ እንደሚችልና አቅሙ ያለው መግዛት እንደሚችል ጠቁመው፥ ሚኒስቴሩም ጭማሪው በሰፊው ማህበረሰብ ውስጥ ከፍተኛ ችግር እንዳይፈጥር እየሰራ ነው ብለዋል።

ሚኒስቴሩ በተለይም በአዲስ አበባ የመንግስትን የዋጋ ድጎማ በመጠቀም በተተመነው ዋጋ ዳቦ እና ዱቄት የሚያመርቱ ተቋማት ጋር ተወያይቶ መግባባት ላይ መድረሱንም ገልጸዋል።

የንግድ ሚኒስቴር በየወሩ ከ600 ሺህ ኩንታል በላይ ስንዴ በመላ ሀገሪቱ በድጎማ የሚያሰራጭ ሲሆን፥ ከዚህ ውስጥ ከ160 ሺህ በላዩ በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ የዳቦ እና ዱቄት ፋብሪካዎች የሚሰራጭ ነው።

አሁን ላይም ይህ አቅርቦት እንዳይቋረጥ እየተሰራ ነው ያሉት ዳይሬክተሩ ከግዥ ስርዓት መጓተት ጋር በተያያዘ አቅርቦቱ በቂ አለመሆኑንም ይገልጻሉ።

በዚህ በጀት አመትም 4 ሚሊየን ኩንታል ስንዴ ገዝቶ ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት ጥረት እየተደረገ ነው ያለው ንግድ ሚኒስቴር፥ ከመንግስት ጋር ትስስር ለፈጠሩ የዳቦ እና ዱቄት ፋብሪካዎች በድጎማ የሚቀርበው ስንዴ አይቋረጥምም ብሏል።

በቅርብ አመታት ውስጥ ግን የሀገሪቱ የግብርና ምርታማነት በማሳደግ ከውጭ በመንግስት ድጎማ የሚገባውን ስንዴ ለማስቆም አቅጣጫ መቀመጡንም አስታውቋል

ኤፍ ቢ ሲ)

በፋሲካው ታደሰ

‹‹እንዴት አቅሙ ባላቸው ሀገራት ዕርዳታ የሚጠይቅ አምባሳደር አጣን?›› በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን

በተለያዩ የዓለም አካባቢዎች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ቃጠሎ እንዳሳሰባቸውና ዓለማቀፉ ማኅበረሰብ ዕውቅና ኖሮት ዕርዳታ አለመጠየቁ እንዳሳዘናቸው እየተናገሩ ነው፡፡

ነዋሪነታቸውን በኖርዌይ ኦስሎ ያደረጉት አቶ ልዑል መኮንን ከደቂቃዎች በፊት ለአብመድ ስልክ ደውለው በሰጡት አስተያዬት የስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የእሳት ቃጠሎ እጅግ እንዳሳሰባቸውና በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ አምባሳደሮች ዕርዳታ አለመጠየቃቸው እንዳሳዘናቸው ተናግረዋል፡፡

መሠል የተፈጥሮ አደጋዎች ሲያጋጥሙ በውጭ የሚኖሩ ዲፕሎማቶች ሚና ከፍተኛ መሆን እንዳለበት ያስገነዘቡት አቶ ልዑል ኢትዮጵያ የእሳት አደጋን መቆጣጠር የሚያስችል ቴክኖሎጂ አለመያዟ ባይደንቅም የዲፕሎማቶች ዝምታ እንዳስገረማቸው ተናግረዋል፡፡ ‹‹እንዴት አቅሙ ባላቸው ሀገራት ዕርዳታ የሚጠይቅ አምባሳደር አጣን? ለዓለማቀፉ ማኅበረሰብ የሚያሳውቅና ፈጣን ምላሽ እንዲሰጥ የሚወተውት ዲፕሎማት ለምን ጠፋ?›› ሲሉም ጠይቀዋል፡፡

‹‹ጠንካራና ለሀገር ተቆርቋሪ ዲፕሎማቶች ቢኖሩን ኖሮ በዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን ቢሮዎች እያንኳኩ ጭምር በቀናት ውስጥ ከፍተኛ ዕርዳታ ያስገኙ ነበር›› ያሉት አቶ ልዑል ስለአደጋው አሳሳቢነት በዓለማቀፍ መገናኛ ብዙኃን ዘንድ አለመሰማቱ እንዳሳሰባቸውም ተናግረዋል፡፡

እጅግ ሩቅ ለሆኑና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸው ደካማ ለሆኑ ሀገራት ጭምር መሠል የእሳት አደጋ ሲያጋጥም ፈጥነው ምላሽ ለሚሰጡት እንደ እስራኤል ያሉ የኢትዮጵያ ወዳጅ ሀገራት አሳውቆ ዕርዳታ አለመጠየቅ ትልቅ ስህተት መሆኑንም ነው አቶ ልዑል የተናገሩት፡፡

‹‹እስራኤል ኢትዮጵያውያን በችግሯ ጊዜ ቀድመን ልንደርስላትና ሕይወታችን ልንሰጣት የማንሳሳላት ሀገር ናት፤ እኛ የገጠመንን ችግርም የእስራኤል መንግሥት ሰምቶ ዝም እንደማይል አምናለሁ›› ያሉት አቶ ልዑል አምባሳደሮች በፍጥነት ለዓለም ኅብረተሰብ በማሳወቅ ዕርዳታ እንዲጠይቁ አሳስበዋል፡፡

ከለንደን እንደደወሉ የነገሩን አቶ መላኩ አለልኝ ደግሞ ‹‹የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን የዘገባ ትኩረት ባለመስጠትና በዓለማቀፍ ቋንቋ ባለመዘገብ ከዩኔስኮና ሌሎችም ዓለማቀፍ ተቋማት ዕርዳታ እንዳይገኝ እያደረጉ ነው›› ብለዋል፡፡

ፖርቱጋልና ስፔን በየጊዜው ከፍተኛ የደን ቃጠሎ እንደሚያጋጥማቸው የገለጹት አቶ መላኩ በዲፕሎማቶቻቸውና በሚዲያዎቻቸው ተጽዕኖ ፈጣን ዓለማቀፍ ድጋፍ እያገኙ እሳቱን እንደሚቆጣጠሩ ተናግረዋል፡፡ አቶ መላኩ እንዳሉትም እስራኤልና ሳዑዲ ዐረቢያ በከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ቢጠየቁ ከአካባቢያዊ ቅርበትም አንጻር ፈጣን ምላሽ ሊሰጡ ይችላሉ፡፡ ‹‹አምባሳደሮቻችን ጎበዝና ተጽዕኖ ፈጣሪ መሆናቸው የሚለካው እንዲህ ባለው የአደጋ ጊዜ ጭምር ነው፤ ስለዚህ አምባሳደሮቻችንም በትጋት ድጋፍ መጠየቅ አለባቸው›› ነው ያሉት፡፡

ዘጋቢ፡- አብርሃም በዕውቀት

ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 05/2011ዓ.ም (አብመድ)

ፖሊስ በሌላት አዲስ አበባ….ተዘረፍኩኝ!

……ከትላንት በስቲያ ሰኞ ቀኔ ጎዶሎ ነበር። ወደፊት ለሚጀመር አንድ የሬዲዮ ፕሮግራም አንዳንድ ቀረፃዎችን ሳከናውን አምሽቼ ሰአቱ ገፋ ብሎ ነበር። ከአንድ ጓደኛዬ ጋር በላዳ ታክሲ መጣንና የእሱ ቤት ሩቅ ስለነበር ታክሲው መርካቶ አካባቢ ሲደርስ ለእሱ አዝኜ እንዲመለሱ በመንገር በአመዴ ገበያ በኩል ወደላይ በእግሬ ማዝገም ጀመርኩ። አንዳንዴ በደንብ የምታውቁት አካባቢ የሚሰማችሁ የደህንነት ስሜት አለ አይደል? ከታች ከምዕራብ ጀምሮ ያሉ የሱቅ እና የድርጅት ጥበቃዎችን፤ የመንገድ ላይ ሻይ ነጋዴዎችን፤ መኪና የሚጠብቁ ወጣቶችን፤ ሽቀጦችን የሚሸጡ ጀብሎዎች፤ ጎዳና ተዳዳሪዎችን እና አልፎ አልፎም መንገድ ላይ ገበያ የሚጠብቁ ምስኪን ሴተኛ-አዳሪዎችን ሳይቀር ስለምግባባ በሆነ አጋጣሚ ሳመሽ ያን ያህል የፍርሃት ስሜት አይሰማኝም….. የሚሸኙኝም ህፃናት ብዙ ናቸው ። ግን ከላይ የቀን ጎዶሎ ያልኳችሁ በሕይወታችን የሚገጥሙን ነገሮችን በራሳችን ኃይል የመወሰን ብቃቱ የለንም። ትላንት ያላጋጠመን ነገር ዛሬ አያጋጥመንም ማለት አይደለም።
፨…..እናም ሀገር አማን ነው ብዬ ወደ ሰፈሬ የሚወስደኝ የአውቶብስ ተራን ዋና መንገድ ልቀላቀል 20 ሜትር ያህል ሲቀረኝ ከየት እንደመጡ ህልም የመሰሉኝ ወደ አስር ጎረምሶች እየተጯጯሁ በቅፅበት ከበቡኝ። ምንም አይነት ነገር ማሰብ እስከማልችልበት በግራ መጋባት ተዋጥኩኝ። እጄን ወደላይ አንስቼ <የምትፈልጉትን ውሰዱ ብቻ አትጉዱኝ! ስላቸው አንደኛው ቀድሞ በጨበጣ ድንጋይ ጭንቅላቴን ፈነከተኝ።

ትኩስ ደም በአንገቴ ሲወርድ ይሰማኛል፤ ከዚያ ደረቴን: ጀርባዬን፤ ሆዴን…. ያገኙት ቦታ እየቀጠቀጡ ተረባረቡብኝ። የፈለጉትን እንዲወስዱ ፈቅጄላቸው ለምን ይሄን እንደሚያደርጉ አልገባኝም። አንገቴን ጨምቆ ይዞ አንደኛው መሬት ላይ ሲጥለኝ ሌሎቹ መጀመሪያ ኪሴ ስር ገብተው ሁለት ሞባይል፤ በርካታ ኢንተርቪዎች የያዘ ድምፅ መቅረጫ፤ ፍላሾችን፤ ቻርጀር፤ የተወሰነ ገንዘብ እና ኪሴ ስር የነበሩ የወረቀት ዝርያዎችን አንድም ሳያስቀሩ ወስደው ሳያበቁ….ከትከሻዬ ላይ ያንጠለጥልኩት እና ብዙ ፋይሎች እና ጠቃሚ ሰነዶች የያዘውን ተንጠልጣይ ቦርሳዬን ለመውሰድ ሲታገሉ እሱን ለማዳን ተፍጨረጨርኩ። ግን ከወደኩበት በእግራቸው እየጨፈለቁና ከአስባልት ላይ እያጋጩ ጭንቅላቴን አደነዘዙት። ከዚህ በኋላ አልቻልኩም….ቦርሳውን ለቅቄ ተዘረርኩ፤ ልጆቹ ምንም የፈሩት ነገር የለም። ተነስቼ ምንም ነገር ብሞክርና ብከተላቸው አንገቴን እንደሚቀነጥሱት በያዙት ረጅም ሳንጃ አስጠነቀቁኝ።

ጉዳዩ የደፈጣ ዝርፊያ ሳይሆን ገሃድ የሆነ የቡድን ዝርፊያ ነበር። መንገድ ላይ ያገኙትን ሁሉ እየጠራረጉና እየዘረፉ ነበር የመጡት። እንደሌላው መደበኛ ዘራፊ ሳይሆን የተፈቀደ ህጋዊ ስራ የሚሰሩ ይመስሉ ነበር። ከእኔ በኋላም ሌላ መንገደኛ ፍለጋ በፉከራ እያሰሱ በኩራት ወደ መርካቶ ወረዱ። ተነስቼ ደሜን እየጠረኩኝ እና ራሴን አረጋግቼ ቁጭ ባልኩበት ከደቂቃዎች በኋላ የተወሰኑ ፖሊሶች ከሌሎች የተዘረፉ ሰዎች ጋር እየሮጡ መጡ። አንደኛው ቴሌግራም የያዘው ፖሊስ ኃይል እንዲጨመር ንግግር ይዟል። ልጆቹ በተወሰነ ርቀት ላይ ሆነውም ፖሊሶቹን አልፈሯቸውም። ጭራሽ ድንጋይ ይዘው <ልብ ካለህ ተከተለን> እያሉ ለውርወራ ተዘጋጁ። ከፖሊሶቹ አንዱ እየተንቀጠቀጠ ወደ ላይ አይሉት ወደ ታች አንድ ጥይት ተኮሰ። አሁን ልጆቹ ሩጫ ጀመሩ…..

የዚህን ጊዜ ፖሊሶቹ የልብ ልብ ተሰምቷቸው የፍርሃት ጩኽት እየተጯጯሁ <ያዘው! ያዘው!> እያሉ መከተል ያዙ። ፖሊስ ያልያዛቸውን ወንጀለኞች ማን እንደሚይዝላቸው እግዜሩ ይወቀው!!…..እንደምንም ተነስቼ በደመ-ነብስ ከፖሊሶቹ ጋር ተከተልኩኝ። ምናልባት ቦርሳውን እንኳን ቢጥሉት የሚል ተስፋ ነበረኝ። በተነገራቸው የቴሌግራም መልህክት ከየአቅጣጫው የት ተደብቀው እንደቆዩ የማይታወቅ ተረኛ ፖሊሶች እየተቀላቀሉ የልጆቹ የመጨረሻ ማምለጪያ መንገድ የሆነው ተክለሃይማኖት በርበሬ ተራ መግቢያ ዋናው አስባልት ስንደርስ ከየማህዘናቱ የመጡት ፖሊሶች ቁጥር ወደ ሃያ አምስት ይደርስ ነበር። አብዛኞቹ ከሲታ እና ልጅነታቸውን ያልጨረሱ፤ በዚያ ላይ ጭልጥ ካለ እንቅልፍ ነቅተው የሚንቀጠቀጡ ነበሩ።

ፈፅሞ የፖሊስ ተክለ-ቁመና የሌላቸው፤ የመንገዱን መግቢያ መውጪያ የማያውቁና አማርኛ መናገር የሰማይ ያህል የራቃቸው ነበሩ። እኔ የተጎዳሁት እያለው ለእነሱ ከልቤ አዘንኩ። ከስምንት ወንጀለኛ አንዱን መያዝ በልቻለ ፖሊስ ለምትጠበቀው አዲስ አበባ እና ለነዋሪው የወደፊት ደህንነት እያሰብኩ ባዶ ስሜት ታቅፌ ተመለስኩ።

ሰውነቴ በደም ረጥቧል፤ ማዘር እንዲህ ሆኜ ብታየኝ ልቧ በድንጋጤ ቀጥ ይላል። ጓደኛዬ ጋር አድሬ ጠዋት ስገባ ስሜቴ ሁሉ ባዶ ቀፎ ሆኖ ነበር….. በስልኮቼ እና በቦርሳዬ የያዝኳቸው የአመታት ድካሞቼን በምን አይነት ሞራል እመልሳቸው ይሆን? ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ። ነገሩን ለፖሊስ ጣቢያ ሳይሆን ለእግዚአብሔር ሰጥቼ በዚህ የቀን ጎዶሎ ያልገጠሙኝን የከፋ አደጋዎች በማሰብ ፈጣሪን አመሰገንኩት። በያዙት ሳንጃ ወግተው አካለ ጎዶሎ አድርገውኝ ወይ ወደ ሞት ሸኝተውኝ ቢሆን ኖሮ የሳምንት ዜና ብሆን እንጂ ሌላ ምን እጨምር ነበር? ይሄው እስትንፋሴ በመኖሩ የእናቴን ትኩስ አጃ እየጠጣሁ በተውሶ ስልክ ይሄን መጥፎ የቀን አጋጣሚ አካፈልኳችሁ።
ዕድሜ ወንጀለኛና ህግን ላናናቀው የመደመር ፍልስፍና ይሁንና ገና ፖሊስ እያለ የሌለባት ከተማ ወደፊት የነዋሪዋ ፈታኝ አውድማ ትሆናለች።

እግዚአብሔር ከቀን ጎዶሎ ይጠብቃችሁ….ባላችሁበት ሻሎም።

Habte Tadesse fb

በሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ እየወደመ ነው፤ ከሳምንት በሁዋላም ሄሊኮፕተር ለማስመጣት ውይይት እየተደረገ ነው

የቃጠሎው መነሻ ምክንያት በውል ያልተነገረለትና አገር ወዳድ ወገኖችን ከንፈር እያስመጠጠ ያለው የሰሜን ፓርክ ብሄራዊ ፓርክ ቃጠሎ አሁንም መፍትሄ አልተበጀለትም። በከፍተኛ ደረጃ እየወደመ ያለው ይህ ፓርክ እሳቱ ከተነሳበት ጊዜ ጀመሮ በአየር ለማጥፋት እንቅስቃሴ አለመጀመሩ አሳዛኝ ሆኗል። ይህ ወደር የማይገኝለት የአገር ሃብት እየወደመ እንቅልፍ የሚወስዳቸው ወገኖች ቢያሳፍሩም፣ በሚችለው ሁሉ እሳትን በመጋፈጥ ላይ ያለው ወገን ግን ክብር የሚሻው ነው።

የእሳት ማጥፊያ አውሮፕላን ወይም ሄሊኮፕተር ባለቤት አለመሆናችን ከሚፈጥረው ቁጭት በላይ ደኑ እየጋየ በውስጡ ያሉ ብርቅ እንስሶች እያለቁ አማራጭ መፍትሄ አለመገኝቱ ነው። አማራጭ መፍትሄ አለመገኘቱ እያነጋገረ ባለበት ወቅት ዛሬ የአማራ መገናኛ ብዙሃን ከኬንያ ሄሊኮፕተር  ለማስመጣት እየተሰራ መሆኑንን ገልጹዋል።

በፓርኩ ላይ የተነሳውን እሳት ማጥፊያ ሄሊኮፕተር ለማስመጣት በሂደት ላይ መሆኑን ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ። በሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ላይ የተነሳውን እሳት ማጥፊያ ሄሊኮፕተር ከኬንያ ለማስመጣት በሂደት ላይ መሆኑን ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታውቋል።

ከኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመሆን ጉዳዩን ለማስፈፀም እየተሰራ መሆኑን በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የውጭና ዓለማቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ አባተ በተለይም ለአብመድ ተናግረዋል።

ኬንያ ፈቃደኛ መሆኗንና የእሳት ማጥፊያ ሄሊኮፕተሩን በቶሎ ለማስመጣትና ቃጠሎውን ለመቆጣጠርም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ ከኬንያ መንግስት ጋር እየተነጋገሩ መሆኑንም አቶ ገዛኸኝ ነግረውናል። ሁሉም ፓርኩን በማዳኑ ስራ እንዲረባረብም ጠይቀዋል።

የኢፌዴሪ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን፣ የቱሪስት አስጎብኝ ድርጅቶች እና ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ፓርኩ ስለተጋረጠበት አደጋ አሁን አዲስ አበባ ላይ እየመከሩ ነው።

ከውይይቱ በኋላም በተቀናጀ መልኩ እሳቱን ለማጥፋት በሚያግዝ ኃላፊነት አደጋው ወደ ተከሰተበት ቦታ እንደሚሄዱ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን አስታውቋል። ሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ አሁንም እየተቃጠለ፤ ብዝሀ ሕይዎቱም ለአደጋ እየተጋለጠ ነው።

ፓርኩ ከ21 ዓመታት ለአደጋ የተጋለጡ የጎብኝ መዳረሻ ስፍራዎች መዝገብ ውሰጥ ቆይታ በኋላ “ከአደጋ ነፃ” ከተባለ ሁለት ዓመታት ሆኖታል። አሁን ደግሞ ተደጋጋሚ ቃጠሎ እየደረሰበት ይገኛል። ከሳምንት በፊት በተከሰተው እሳት ከ342 ሄክታር በላይ የፓርኩ ክፍል ላይ ጉዳት መድረሱ ይታወሳል።

ዘጋቢ፦ አስማማው በቀለ – አማራ መገናና ብዙሃን

ፎቶ፦ በደስታ ካሳ

“ባለቤቴ እንደገዛችው እቆጥረዋለሁ” ከ5 ሚሊዮኑ ዶላር ሎተሪ እድለኛ – ሰሎሞን ክፍሌ ጋር

ድሮ በህብረ ትርኢት የቴሊዝቪዥን ፕሮግራምና በስፖርት ዘገባው፣ አሁን በቪኦኤ ጋዜጠኝነቱ ይታወቃል። ሰሞኑን ደግሞ ሎተሪ ቆርጧል። በዚህ የተነሳ ወሬ አቀባዩ ራሱ ወሬ ሆኗል። ወዳጆቹም ከሱ ጋር ሆነን ወሬውን ተጫውተንበታል።

ሶስታችን አልፎ አልፎ እንደምናደርገው ጋሽ አያልነህና ከቪ.ኦ.ኤው ጋዜጠኛ ሰሎሞን ክፍሌ ጋር ምሳ ለመብላት ተቀጣጠርን። ሁሌ እማይለያቸው የቅርብ ወዳጃቸን ጋሽ ሙሉጌታ ሉሌ ቢኖር ምናልባት አራት እንሆን ነበር። ለማንኛውም ሎተሪው ከወጣለት በኋላ የመጀመሪያው ምሳችን መሆኑን ነው። በተለይ ከኔ ጋር። እነሱ ቀድመውኝ በቦታው ደርሰው ነበር። ሰሎሞንን ገና ስጨብጠው “እርግጠኛ ነኝ ሚሊዮነር ስትጨብጥ የመጀመሪያ ጊዜህ ነው” አለኝ። ወደ ጋሽ አያልነህም ዞሮ – “አንተስ ብትሆን ሚሊዮኔር ጨብጠህ ታውቃለህ- ምን ልትል ነው?” አለው ። ይቺ ገና ለገና እማትቀርለትን ተረብ ለመከላከል መሆኗ ገብታናለች። አልማርነውም።

ከሁቴሉ ገብተን ምሳ ልንበላ ምግባችንን አዘዝንና “እሚጠጣስ?” ሲባል “ለሁላችንም ዋይን!” አለና “በቦትል አድርጊው!” አላት ሰሎሞን። እድልም አልሰጠን። መቸም ሚሊየነሮችና ባለሥልጣናት የሰውን ምርጫ መወሰን ይወዳሉ። አጋጣሚ ሆኖ አስተናጋጃችን ሀበሻ ነበረች። የቀልዴን ጣልቃ ገብቼ “የእኔ እህት እባክሽን በጣም ትልቁንና እጅግ ውድ የሆነውን ዋይን አምጭልን…” ስላት፣ ሁላችንም ተሳሳቅን። መቸም የአምስት ሚሊዮን ሎተሪ ፋቅ ፋቅ ሲያደርጉት ሳቅ ሳቅ ያደርጋል። ሰሎሞን ክፍሌ ስቋል። እኛም አብረን እየሳቅን ትንሽ እንደቆየን ሌላ ሳቅ መጣ። ፈረንጁ የሆቴሉ ማኔጄር ዋይናችንን ይዞ መጣ። በጣም በኩራትና በአክብሮት “በቤቱ ውስጥ ያለን ውድ ዋይን ይኼ ነው” አለን። የገዛ ቀልዴ ዋጋ ልታስከፍለን መሆንዋ ገብቶኝ ከሰውየው ጋር መራር ጭቅጭቅ ልጀምር ስል ሌላ ሳቅ ሆነ።

ሰሎሞን በቃ ግድ የለም ተወው እንጠጣዋለን አለኝ። “ያለው ማማሩ..” ብለን አንዳችን ከአሳ ኮተሌት፣ አንዳችን ከጾም ፓስታ ሹታችን ጋር ወይን ጠጅቱን አጣጣምናት። የአገራችንን ወቅታዊ ሁኔታ ገረፍ ገረፍ አድርገን ወደ ሎተሪው ተመለስን። በጋዜጠኛ ሆድ ሚሊዮን እንጂ ወሬ አያድርምና አፌንም ጆሮዬንም በላኝ። በል እስኪ አጫውተን። እንዴት ቆረጥከው? ሲደርስህ ምን አልክ? ምንስ አደረግክ? ስንት ተቀበልክ? ምን አደረግክበት? በእጅህ ምን ያህል ቀረህ? ሥራህን በቃ ደህና ሰንብች ትላታለህ? ብቻ ምን ያልተጠየቀው ነገር አለ? የወዳጅነትም የጋዜጠኝነትም ተጠይቋል። የወዳጅነቱን አስቀርቼ የጋዜጠኝነቱን ላካፍላችሁ።

ከሥራው ነው የጀመረው። “በሙያዬ እንኳ ቀልድ የለም! እኔ ሎተሪ የወጣልኝ ጋዜጠኛ ስሆን ነው። ጋዜጤኝነት ሙያዬ ብቻ አይደለም ህይወቴ ነው። ሰው እኮ ሎተሪ ሲደርሰው እሚወደውን ነው ማድረግ እሚፈልገው። ያን እያደረግኩ ነው። ሎተሪው ኑሮዬን እንጂ ሙያዬን አይለውጠውም። ይቺን ከያዝክልኝ ሌላውን ምንም ሳላስቀር ላጫውትህ” – አላቋረጥኩትም።

እንግዲህ የደረሰኝ ወጣ የተባለው ሎተሪ 5 ሚሊዮን ነው። ይህን ለመውሰድ ስትሄድ ምርጫ አለህ። በ20 ዓመት ወስደህ እምትጨርሰው ከሆነ በየወሩ እሚሰጡህን ታገኛለህ። ወይም ካሹን ባንዴ ልትውሰድ ትችላለህ። ካሹን ባንዴ ካልክ 1.5 ሚሊዮን ዶላር ያነሱለታል። እኔ ይሁን ብዬ 3.5 ሚሊዮኑን ተቀበልኩ። ቆይ እንጂ ከሱም ደግሞ እኮ የፌደራልና የስቴት ታክስ ይነሳለታል አሉኝ። ወደ 1.1 ሚሊዮን አካባቢ ሲያነሱለት 2.4 ሚሊዮን አካባቢ ቀረኝ። ለነገሩማ የደረሰኝ እኮ 500ሺ ነበር። ሚሊዮን እሚባል አልነበረም፡፡

“ምን አልከኝ?” አልኩት።

ይኸውልህ ሎተሪውን ፍቄ ያየሁት ማታ ቤት ገብቼ ቴሌቪዥን እያየሁ ነው። 500ሺ ዶላር ነው ያኔ የታየኝ። በጣም በጣም ደስ አለኝ። አናቴ ላይ እሚዘፍን ብዙ እዳ ነበር። እንደምታወቀው ልጄን ልድር ነው። ለሠርጉ ተለቅቼም ይሁን ተበድሬ እስካሁን ከ30 ሺብር በላይ አውጥቼበታለሁ። ገና ሌላ 10 ሺህ ያስጨምረኛል። በዚያ ላይ የቤት እዳ አለ። የኔም የልጄም የትምህርት ቤት (“ስቱደንት ሎን”) እዳ አለ። ስቱደንት ሎኑ ብቻ ከሁለት መቶ ሺህ በላይ ነው። የሞርጌጁም 300ሺብር በላይ ይሆናል። እና ያቺ 500ሺ ብር ስትመጣ ቢያንስ በትልቁ ትገነድስልኛለች። እና ማታ እግዜሐብሔርን አመስግኜ ተኛሁ። ጧት ስራ ገባሁ። ሎተሪዪቱን ከኋላ ኪሴ ነው ያስቀመጥኳት። ሥራ ጋብ ሲል – ወጣ አድርጌ አየኋት። አይኔን ማመን አልቻልኩም። ለካ ማታ የዓይንም የደስታም ነገር ሆኖ በደንብ አላነበብኳትም። 500ሺ ሳይሆን 5 ሚሊዮን ተሸክማ ነበር። ከዚያ በኋላማ በቃ ምን እነግርሃለሁ። ጥቃቅንም ብትሆን ብዙ ጊዜ ስለማሸንፍ የት ሄዶ እንደሚወሰድ አውቃለሁ። ወደዚያ መቀበያው ቢሮ ሄድኩ። ኃላፊዎቹ ከኔ በላይ በጣም በጣም ጮኹ። ግን ከኔ ያዩት ምላሽ መልሶ ግራ አጋባቸው። አምስት ሚሊዮን እኮ ነው የደረሰህ አሉኝ። እሱን አውቄ እኮ ነው ልቀበል የመጣሁት አልኳቸው።

እኔ ያቀዘቀዘኝ ይሄ ፎቶ ተነስ እሚሉት ምናምን ነገር መኖሩ ነው። ፎቶ መነሳት አለብህ አሉኝ። ባልነሳ ምን ይመጣል አልኳቸው። ምንም አይመጣም ግን አንተ ገንዘብህን አታገኝም አሉኝ። በቨርጂኒያ ህግ ፎቶ መነሳት ግዴታ ነው። ፍቶውን ተነስቼ ወደ ባንኬ ሄድኩ። በቃ እንዳልኩህ የቤቱን ፣ የመኪናውን፣ የክሬዲት ካርዱን ያለውን እዳ ሁሉ ዘጋሁ። የስቱደንት ሎኑን እዳ ከፋፈልኩ። ልጄ ከሠርጉ በሁዋላ ወደኔ አካባቢ ልትመጣ ነው። አሁን ኒዮርክ ናት። ለሷ ተለቅ ያለ ቤትና መኪና እገዛለሁ። ያለ እዳ እንድትኖር ነው የምንጊዜም ሃሳቤ። እዚህ አገር ትልቁ እዳ የቤት ሞርጌጅ ነው። የኔ ራሱ ትልቁ ደስታዬ ከቤት ኪራይ መገላገሌ ነው።

ሌላው የማደርገው ነገር – ኢትዮጵያ ውስጥ ላሉ ህጻናት መርጃ እሚውል ድጋፍም ለመስጠት እየሰራሁ ነው። በተፈረው እንግዲህ ለኢንቨስትመንት ጣል ካደረግኳት፣ የቀረችውን ለህይወቴ ጡረታ አደርጋታለሁ። ከሁሉ ከሁሉ ግን ትልቁ ነገር የባለቤቴ ነገር ነው። ሎተሪውን ባለቤቴ እንደገዛችልኝ እቆጥረዋለሁ ብዬሃለሁ። ልብ በል ይህ የሆነው የሙት ዓመቷን በቤተከርስቲያን ጸሎት ባከበርኩበት ሳምንት ውስጥ ነው። ሎተሪውን የገዛሁት ማርች 27 ነው ። ሰባት ሰዓት አካባቢ ከምሽቱ። ባለቤትም ያረፈችው የዛሬ አምስት ዓመት ማርች 29 በዚያ ሰዓት ላይ ነበር። እርሷ ካረፈችበት ሁለት ቀናት በፊት መሆኑ ነው ሎተሪው የደረሰኝና አጋጣሚው ያስገርማል።

ሰሎሞን እንዳለው – እኔም አምስት ዓመትና አምስት ሚሊዮን መገጣጠሙ ገረመኝ። ሳያቋርጥ እቤት ውስጥ ፎተግራፏ ካለበት ጠረጲዛ ጎን በየሳምንቱ አዲስ አበባ እንደሚያስቀምጥ አውቃለሁ።

“ባለቤቴ ለልጇ ሠርግ የድርሻዋን ማዋጣቷ ነው። ገንዘቡን ግን ትንሽ አበዛችው።” አለ በማጉተምተም። ከዚያ በኋላ ወሬው ሁሉ እጅግ ስለሚወዳት ስለ ባለቤቱ ወይዘሮ ገነት ገረመው ቀማው ብቻ ሆነ።

ከዚህ በኋላ ዝም ማለት ነበረብኝ። የሎተሪውን ደስታ ወደ ሀዘን መለወጥ አልፈለግኩም። እግዚአብሔር የራሱ መንገድ አለው።

www.facebook.com/100001221707466/posts/2408796135837753

“በወንድሜ ለአምስት ዓመታት ተደፍሬአለሁ”

መገናኛ አካባቢ የሚገኝ ፀጥ ያለ መንደር ነው። ሰባት ወይም ስምንት የሚሆኑ ልጅ ያቀፉ አፍላ ታዳጊዎች እየተሳሳቁ ከአንድ ትልቅ ግቢ በመውጣት ላይ ነበሩ። ሁሉም ልጅ የያዙና በእድሜም ለእናትነት ገና መምሰላቸው ትኩረት ይስባል። ምን እየተባባሉ እንደሆነ ለመስማትም ያጓጓል።

እነሱን አልፈን ወደ ውስጥ ዘለቅን።

የ23 ዓመት ወጣት ነች። ከገፅታዋ ምንም ነገር ማንበብ አይቻልም። ገፅታዋም ሆነ ሁለንተናዋ ፀጥ ያለ ነው። ከዓመታት በፊት ወደ እዚህ ግቢ ስትመጣ የሥራ ማመልከቻ ለማስገባት ወይም ሥራ ለመጀመር አልነበረም። ይልቁንም በእናቷ ልጅ በወንድሟ ተደፍራ ከደረሰባት ከባድ አካላዊና ሥነ ልቦናዊ ጉዳት ለማገገምና መጠለያ ለመሻት ነበር።

የደረሰባት ነገር ሰው እንድትፈራ አድርጓት ነበርና በሙሉ አይኗ ሰው ማየት ያስፈራት፤ ቃላት አውጥቶ መናገርም ይከብዳት እንደነበር ታስታውሳለች።

ትላለች ጊዜውን በማስታወስ። የጉዳቷ መጣን በህይወት እየኖርኩ ነው የማያስብል ቢሆንም ያን ቀን አልፋ ዛሬ ቀና ብላ መራመድ ችላለች። ዛሬ የምትፈልግበት መድረስና ህልሟን መኖር እንደምትችልም በእርግጠኝነት ትናገራለች።

ዛሬ ያኔ ተደፍራ የተጠለለችበትና ለተደፈሩ ሴቶች ድጋፍ የሚያደርገው ‘የሴቶችና የህፃናት ማረፊያ’ ውስጥ ለመሥራት ችላለች።

ምንም እንኳ ያን ጊዜ ማስታወስ ቢያማትም ያለፈችበት መንገድ ሴቶች ለፆታዊ ጥቃት እንዳይጋለጡ አስተማሪ ይሆናል የሚል ፅኑ እምነት ስላላት የሆነችውን ትናገራለች።

ሊያስተምራት አዲስ አበባ ያመጣት ትልቅ ወንድሟ ፖሊስ ነበር። ያኔ እሷ የ16 ዓመት ታዳጊ ነበረች። የሚኖሩት ወንድሟ በተከራየው ቤት ነበር።

“ልጅ ስለነበርኩ ብዙ ነገር አላውቅም፤ መናገርም አልችልም ነበር። ሰው ሳይ ተመሳሳይ ጥቃት ያደርሱብኛል ብዬ ፍራቻ ነበረብኝ” በማለት የነበረችበትን የሥነ ልቦና ስብራት ታስታውሳለች።

ሰው አይቷት ሚስጥሯን የሚያውቅ ይመስላት ስለነበር ትምህርት ቤት መሄድና መመለስ፤ ክፍል ውስጥ መቀመጥም እጅግ ስለከበዳት ትምህርት ቤት መሄድ አቆመች።

ወንድሟ ለአምስት ዓመታት አብረው ሲኖሩ ደፍሯታል። በዚህ ጊዜ ውስጥ ሦስት ጊዜም ፅንስ እንድታቋርጥም እንዳደረጋት ትገልፃለች።

ልጅነትና የሥነ ልቦና ቀውስ እንዲሁም የወንደሟ ማስፈራራት ለማንም ምንም ትንፍስ ሳትል እንድትቆይ አድርጓት ነበር። ይኖሩ ከነበሩበት ቤት ለቅቀው ሌላ የኪራይ ቤት የገቡበት አጋጣሚ ግን ጉዳቷን አውጥቶ ለመናገር እድል ሰጣት።

በአጭር ጊዜ ውስጥ ሁኔታዋን ያስተዋሉት አዲሷ የቤት አከራያቸው አንድ ቀን “ለምንድነው ሰው የማትቀርቢው? ዘመዱ ነሽ ወይ?” ሲሉ ድንገት ጠየቋት።

ሁለቱም ጥያቄዎች ለእሷ እጅግ ከባድ ነበሩ። ከምትኖርበት ስቃይ መውጣት ትሻ ነበርና አለባብሶ እንደነገሩ መልስ መስጠት አልፈለገችም። በሌላ በኩል እውነቱን መናገርም መከራ ሆነባት።

እንደምንም ከራሷ ጋር ታግላ የሆነችውን ለአከራይዋ ተናገረች። በነገሩ በጣም የደነገጡት አከራይ ይዘዋት በአቅራቢያ ወደሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ለመሄድ ምንም አላመነቱም።

ከፖሊስ ጣቢያ በኋላ ነበር የተደፈሩ ሴቶችን ወደሚያስጠልለውና የሕግ አገልግሎት ድጋፍ ወደሚያደርገው የሴቶች ማረፊያ ልማት ማኅበር የተወሰደችው።

ከሰልጣኝ ሴቶች መካከል አንዷImage copyrightZELALEM ABERA (AWSAD) አጭር የምስል መግለጫከሰልጣኝ ሴቶች መካከል አንዷ

“ቤተሰብ በኔ ፈረደ”

ነገሩ ወደ ሕግ ከሄደ በኋላ ጉዳዩን የሰሙ ቤተሰቦቿ ‘እሱ እንዲህ አያደርግም፤ ልጅ ስለሆነች ነው እንዲህ ያለ ነገር የምታወራው’ በማለት በፍፁም ሊያምኗት አልቻሉም። በተለይም ትልቅ እህቷ ካለማመን አልፋ የወንድማቸውን ስም ለማጥፋት ‘ያልሆነውን ሆነ እያለሽ ነው’ በሚል ብዙ ሞግታታለች ዝታባታለችም።

“ከእናቴ ውጪ ቤተሰብ ሁሉ እንደ ቆሻሻ ተፀየፈኝ” በማለት ተበዳይ ሆና እንዴት የበዳይ እዳ ተሸካሚ እንደተደረገች ትናገራለች።

በሌላ በኩል ፖሊስ ጣቢያ በሄደችበት ወቅት ያየችው አቀባበል እንደሷ ያሉ የተደፈሩ ሴቶች ይብስ ፈርተው እንዳይናገሩ የሚያደርግ እንደነበር ታስታውሳለች።

ሃዘኔታ በሌለው አንደበት ‘ነይ እዚህ ጋር’ ‘እዛጋ’ ‘እስከዛሬ ምን ትሰሪ ነበር?’ ተብላለች።

ይህ የእሷ ብቻ ሳይሆን የብዙ ሴቶች አስከፊ እጣ ነው። በማህበረሰቡ እንዲህ ስላደረግሽ ነው፣ እንደዛ ባታደርጊ ኖሮ በሚሉ የምክንያት ድርደራዎች ለመደፈራቸው ራሳቸው ጥፋተኛ ተደርገው አንገታቸውን እንዲደፉ የተደረጉ ሴቶችን ቤት ይቁጠራቸው።

በቀድሞ መጠለያዋ በዛሬው የሥራ ቦታዋ በወንድም፣ በአባት፣ በአያቶቻቸውም ጭምር የተደፈሩና የወለዱ ሴቶችም ጭምር አጋጥመዋታል። ሁሉም በቤተሰባቸውና በማኅበረሰባቸው ለመደፈራቸው ጥፋተኛ የተደረጉና የተወገዙ መሆናቸውን ትናገራለች።

“እኔ ስለ ሕግ ብዙ አላውቅም፤ ግን ካለፍኩበትና ካየሁት በሕግ በኩል ያለው ነገርም ደስ አይልም።”

በተለያዩ ምክንያቶች ደፋሪዎች ነፃ ሆነው የመሄድ እድል ያገኛሉ። በተመሳሳይ በእሷ ጉዳይም ክስ ተመስርቶ የነበረ ቢሆንም ክሱ የትም ሳይደርስ፤ ወንድሟም ሳይጠየቅ መቅረቱን ትናገራለች።

“ህመሜን ተቋቁሜ ችሎት ላይ ብቆምም መጨረሻው አላማረም። እዚህ ላይ ብዙ ማለት አልፈልግም” ትላለች።

“ለመረዳት ፍቃደኛ መሆን አለብን”

ባደረገችው ተደጋጋሚ የፅንስ ማቋረጥ የማህፀን ጉዳት ደርሶባት ለረዥም ጊዜ ህክምና ስትከታተል ቆይታለች። በዚሁ ምክንያት ዛሬም ከባድ የወገብ ህመም ስላለባት ለቃለ መጠይቅ ባገኘናት ወቅትም በሃኪም የታዘዘ የወገብ መደገፊያ ቀበቶ አድርጋ ነበር።

ይህ ሁሉ ቢሆንም ግን “በጣም የተጎዳሁት በሥነ ልቦና ነው። በተለይም የቤተሰቦቼ ነገር በእጅጉ ጎድቶኛል ዛሬም አልወጣልኝም” ትላለች።

ወደ ማረፊያው ከገባች በኋላም ምግብ መብላት፣ ሰው እንዲቀርባትና እንዲያናግራትም አትፈልግም ነበር። ፍላጎቷ አንድና አንድ ነበር። ይቺን ዓለም ለመተው ራሷን ለማጥፋትም ሞክራ ነበር።

በመጨረሻ ከዚህ ያወጣት የተደረገላት የሥነ ልቦና ድጋፍ እንደሆነ ትናገራለች።

ደህና ሆና ወደ ራሷ ከተመለሰች በኋላ ደግሞ የተለያዩ የሙያ ስልጠናዎችን ወስዳለች። የሴቶች ማረፊያ ልማት ማኅበር ከሙያ ስልጠና በተጨማሪ ለተደፈሩ ሴቶች ራሳቸውን ከጥቃት መከላከል ይችሉ ዘንድ የቴኳንዶ ስልጠና የሚሰጥ ሲሆን እሷም ይህን ስልጠና ወስዳለች።

ሰዎች በጣም ሲጎዱ ብዙ ነገር አይፈልጉም። ምንም ነገር መስማትም መረዳትም ላይፈልጉ ይችላሉ። “ቢሆንም ግን ሰውን መርዳት የሚፈልጉ ብዙ ሰዎች ስላሉ መጀመሪያ እኛ ለመረዳትና ወደፊት ለመራመድ ፍቃደኛ መሆን አለብን” ትላለች።

ካጋጠማት አካላዊና ሥነ ልቦናዊ ጥቃትና ሰቆቃ ለመውጣትና ከባዱን ቀን ለማለፍ ብርታት ያገኘችው ከእራሷ ነበር። “ራሴን ማመኔ፣ የተበላሸ ህይወቴን ማስተካክል እንደምችል ማመኔ ረድቶኛል” ትላለች።

ባይናገሩም ከእሷ የበለጠ ከባድ ነገር ያሳለፉ ሴቶች ይኖራሉ ብላ ታስባለች። ማህበረሰቡ የእንደዚህ ያሉ ሴቶችን ታሪክ ሰምቶ መጠቋቆሚያ እያደረገ እንደገና ቁስላቸውን ባያደማ በታሪካቸው ብዙዎች እንዲማሩና የተሰበሩትም ቀና እንዲሉ ማድረግ ይቻል ነበር የሚል እምነት አላት።

“ሻርፕ ጠምጥመው ስብር ብለው የሚሄዱ ሴቶች ሳይ ሁሌም የእኔ ታሪክ ይመስለኛል” የምትለው ወጣቷ በእንደዚህ ያለ አጋጣሚ ለምታገኛቸው ሴቶች ምንም ባታደርግላቸው እንኳ ገፍታ እንደምታናግራቸውና እንደምትሰማቸው ትናገራለች።

ማኅበረሰቡ የሴቶች ጉዳይ ግድ እንደሚለው ከተማረና ካመነ በብዙ መልኩ እንደ እሷ የተደፈሩ ሴቶችን ሊያግዝ የሚችልበት መንገድ እንዳለ ታምናለች። ከሁሉም በላይ ደግሞ በዚህ ጥቃትን መከላከልም እንደሚቻል ይሰማታል።

ህፃናትም ይሁኑ ታዳጊዎች ያሉት ቤተሰብ በሉ፣ ጠጡ፣ ለበሱ እና ትምህርት ቤት ሄደው መጡ፤ ከሚለው ባሻገር ቤት ውስጥም ሆነ ውጪ ልጆቹ ላይ ጥቃት ሊፈፀም እንደሚችል ማወቅ አለበት። ይህም ልጆችን ለመጠበቅ ያስችላል ትላለች።

“ማን ይፈልገኛል?”

የቀድሞው ፆታዊ ጥቃት ተከላካይ ማኅበር የአሁኑ የሴቶች ማረፊያ ልማት ማህበር በደረሰባቸው ጥቃት የተጎዱ፣ የተሰበሩና ‘ማን ይፈልገኛል?’ ብለው ራሳቸውን ማጥፋት የፈለጉ በርካታ ሴቶችን ለመደገፍ ጥረት ያደርጋል። ለተደፈሩ ሴቶች የሕግ ድጋፍና የሙያ ስልጠና በመስጠት ከ15 ዓመታት በላይ አስቆጥሯል።

የድርጅቱ መስራች ወ/ሮ ማርያ ሙኒር ማን ይፈልገናል? በሚል ራሳቸውን ለማጥፋት ሞክረው የነበሩ ሴቶች ከፍተኛ ትምህርታቸውን ተከታትለው ህይወታቸው ተቀይሮ ማየት ለሳቸው ትልቅ ነገር እንደሆነ በየጊዜው ምሳሌ የሚሆኑ ሴቶችን ታሪክ ለሚያወጣው ‘ተምሳሌት ገፅ’ ተናግረዋል።

ማኅበሩ በአዲስ አበባ፣ በደሴና በሌሎች ቅርንጫፎቹ እያገለገሉ የሚገኙ ኢንጅነሪንግ፣ ማኔጅመንትና ሌላ ሌላም ያጠኑ ወጣት ሴቶችን አቅፏል። ታሪኳን የነገረችን ወጣትም አዲስ አበባ ውስጥ በሙያ አሰልጣኝነትና በሃላፊነት እያገለገለች ነው።

Read the Original story on BBC Amharic