Category Archives: Socity / ማህበራዊ

የቆሼ አደጋ ተጎጂዎች “መንግሥት ለቃሉ ሙሉ በሙሉ ታማኝ አልሆነም “

ከ130 ሰዎች በላይ ሕይወትን የቀጠፈው የቆሼ አደጋ ሁለት ወራት ቢያልፉትም፣ እስካሁን ድረስ ቃል የተገባው ዕርዳታ እንዳልደረሳቸው በአደጋው ተጎጂ የሆኑ ግለሰቦች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡

አደጋው በተከሰተ ማግሥት ማለትም መጋቢት 2 ቀን 2009 ዓ.ም. በነበሩ ሁለትና ሦስት ሳምንታት፣ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችን ጨምሮ የተለያዩ ግለሰቦች ዕርዳታ እንደሚሰጡ ቃል መግባታቸው ይታወሳል፡፡ ከመንግሥትና ከተለያዩ ግብረ ሰናይ ተቋማት፣ እንዲሁም ከባለሀብቶች ወደ 75 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ብር ማሰባሰብ ተችሎ ነበር፡፡

ከዚህም በተጨማሪ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤተሰቦቻቸውን በሕይወት ላጡ ተጎጂዎች አሥር ሺሕ ብር ለቀብር ማስፈጸሚያ፣ እንደሁም ቤታቸውን ላጡ ሕጋዊ ተከራዮችና ባለንብረቶች ለሆኑ ቤተሰቦች የካ አባዶ ኮንዶሚኒየም ሳይት የስቱዲዮ ቤት ማስረከቡን አስታውቆ ነበር፡፡

ሪፖርተር ያነጋገራቸው ቤተሰቦች እንደሚሉት ግን ለ54 ቤተሰቦች ቃል የተገቡት ቤቶች እስካሁን አልተሰጡም፡፡

ሪፖርተር ሥፍራው ድረስ ሄዶ እንዳረጋገጠው እነዚህ ተጎጂ ቤተሰቦች አሁንም ድረስ በኮልፌ ክፍለ ከተማ በሚገኘው መጠለያ ማዕከል፣ ወይም በተለምዶ የወጣቶች ማዕከል ውስጥ ተጠልለው ይገኛሉ፡፡

የሪፖርተር ጋዜጠኞች ባደረጉት ጉብኝት እነዚህ ቤተሰቦች በመጠለያ ጣቢያው ፖሊስ ተመድቦላቸው ሲወጡና ሲገቡ ስማቸውን አስመዝግበው ብቻ መንቀሳቀስ እንደሚችሉ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በእዚህ መጠለያ ብቻ 98 ያህል ተጎጂ ቤተሰቦች ይኖራሉ፡፡

ሪፖርተር ካነጋገራቸው ተጎጂ ቤተሰቦች መካከል ስሟ እንዲጠቀስ ያልፈለገች በ20ዎቹ የዕድሜ ክልል የምትገኝ የሰባት ወር ሕፃን እናት ትገኝበታለች፡፡ እሷ እንደምትለው እስካሁን ምንም ዓይነት የገንዘብ ዕርዳታ አልተሰጣቸውም፡፡ ሌሎች ተያያዥ ዕርዳታዎችም እየቀነሱ ነው ብላለች፡፡

አደጋው በደረሰ ማግሥት ምግብ በቀን ሦስት ጊዜ ይሰጥ የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ግን ምሳና እራት ብቻ በየቀኑ ከ9፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት አንድ ላይ እንደሚመጣላቸው፣ ቁርስ ግን ከጊዜ በኋላ እንደቀረ ትናገራለች፡፡

ይህንንም ሪፖርተር በቦታው ተገኝቶ አረጋግጧል፡፡ ግለሰቧ በምትኖርበት የመጠለያ ጣቢያ አንደኛው ክፍል ብቻ ወደ 22 የሚጠጉ ቤተሰቦች እናቶች፣ አባቶችና እንዲሁም ሕፃናት ይኖራሉ፡፡ ከእነዚህም ውስጥ 12 ያህሉ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች ነው፡፡ ከአሁን በፊት አራስ ለሆኑ እናቶች ለሕፃናት ንፅህና መጠበቂያ የሚያስፈልጉ አቅርቦቶች ይመጡ እንደነበር፣ አሁን ግን መቆማቸውን ሪፖርተር ያነጋገራቸው ተጎጂዎች ገልጸዋል፡፡

‹‹ሌላው ቢቀር ነፃ ሕክምና ስናገኝ የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ግን ሄደን ተጎጂዎች መሆናችንን ገልጸን አገልግሎት ስንጠይቅ እንኳን አያምኑንም፡፡ በአሁኑ ወቅት ቤት ተሰጥቶን ጥሩ ሕይወት እንደጀመርን ነው ሰዎች የሚያስቡት፤›› ሲሉ አንድ ተጎጂ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

ሪፖርተር ሥፍራው ድረስ ሄዶ እንዳረጋገጠው የካ አባዶ ኮንዶሚኒየም ሳይት በከንቲባ ድሪባ ኩማ የተላለፉት ቤቶች ገና ተሠርተው አልተጠናቀቁም፡፡ ማንም ገና እንዳልገባባቸውም ለማወቅ ተችሏል፡፡

ሌላው አደጋው ከተከሰተ ከሳምንታት በኋላ ቤተሰቦቻቸው በሕይወት ያሉ ነገር ግን በአደጋው እንደገና ሊጠቁ ይችላሉ የተባሉ ግለሰቦች ከቦታው ተነስተው ነበር፡፡ ከእዚህ ጋር በተያያዘ ግማሽ የሚሆኑት ቆሼ አቅራቢያ የተሠሩ የመንግሥት ቤቶችን እንዲወስዱ የተደረጉ ሲሆን፣ የተቀሩት ደግሞ አስኮ የሚገኝ ቤት እንደሠፈሩ ማወቅ ተችሏል፡፡ ከእዚህ ውስጥ ቆሼ አቅራቢያ በንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ የሠፈሩት እስካሁን ለቤቶቹ ሕጋዊ ውል እንደሌላቸውና መብራትም ገና እንዳልገባላቸው ማወቅ ተችሏል፡፡

ሌላው ገንዘብ ይሰጣል ተብሎ ቃል የተገባው ነው፡፡ ተጎጂዎቹ የባንክ አካውንት እንዲከፍቱ ቢደረግም፣ እስካሁን የገባላቸው ገንዘብ እንደሌለ ይናገራሉ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ሕጋዊ ይዞታ ለነበራቸው 14 አባወራዎች፣ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ውስጥ 175 ካሬ ሜትር ቦታ እንደሚሰጥ መገለጹ ይታወሳል፡፡

ሪፖርተር ያነጋገራቸው አቶ ተመስገን መኮንን የተባሉ ግለሰብ በቆሼ ስምንት ዓመታት እንደኖሩ ይናገራሉ፡፡ በአደጋው ስድስት ቤተሰቦቻቸውን በሕይወት እንዳጡ የሚናገሩት አቶ ተመስገን፣ እስካሁን ያገኙት ምንም ዓይነት ምትክ ቦታ እንደሌለ አስረድተዋል፡፡

‹‹በጣም ተቸግረናል፡፡ ገንዘብም አልተሰጠንም፡፡ ምግብ የምበላው ጓደኞቼ እየጋበዙኝ ነው፤›› ሲሉ አቶ ተመስገን ተናግረዋል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ አደጋው ከደረሰበት ቆሼ አቅራቢያ ያሉ ለአደጋ ተጋላጭ ቤተሰቦች እንዲነሱ መደረጉ ቢታወቅም፣ አሁንም ድረስ ቦታው ላይ የሚኖሩ ሰዎች እንዳሉ ሪፖርተር በቦታው ተገኝቶ መመልከት ችሏል፡፡

አደጋው ከደረሰበት ቦታ ያልተነሱ አሥር ያህል አባወራዎች እንዳሉ ሪፖርተር ያነጋገራቸው ግለሰቦች ይገልጻሉ፡፡ ‹‹እኛ ተጎጂ ስላልሆንን ምንም የተደረገልን ዕርዳታ የለም፤›› ሲሉ በአካባቢው ነዋሪ ከሆኑት መካከል ወ/ሮ ራድያ መሐመድ ይናገራሉ፡፡

ከአሁን አሁን አዲስ ነገር ይመጣል በማለት በደንብ ተንቀሳቅሰው መሥራት እንዳልቻሉ ተጎጂዎች ይናገራሉ፡፡

ጉዳዩ ባለው ውስብስብነት ምክንያት የማጣራቱ ሥራ ጊዜ እንደፈጀና አሁን ግን ሥራው እየተጠናቀቀ መሆኑን፣ ሪፖርተር ጥያቄ ያቀረበላቸው የአዲስ አበባ ከተማ የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ አንድ የሥራ ኃላፊ ይናገራሉ፡፡ ‹‹ትክክለኛውን ከአጭበርባሪው መለየት አለብን፤›› ሲሉ ኃላፊው ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ነስረዲን ሙሐመድ በበኩላቸው፣ ‹‹ባለን መረጃ መሠረት ሕጋዊ ለሆኑት ገንዘብ ተሰጥቷል፤››

ሪፖርተር አማርኛ

“ጫት አቆምኩ…አቃተኝ! ልጆቼን ከትምህርት ቤት ማምጣት ተሳነኝ” በጫት ተሸነፍን ይሆን?

በጫት ተሸነፍን ይሆን?

170x170-ct‹‹ጫት ፈጣሪ የሚወደው ዛፍ ነው፡፡ በፈጣሪ ተባርኮ ለእኛ የተሰጠን ውድ ስጦታ፡፡ ይህ የተባረከ ዛፍ ላይ ሰው ምንም ስልጣን የለውም። የተለያዩ ሰዎች ጫትን ለማጥፋትና ለመቆጣጠር ዋጋውን በማናር ጭምር ሞክረዋል፤ ማንም ግን አልተሳካለትም። ጫት እኮ ተራ አትክልት አይደለም፤ ጫት የአላህ ቅጠል (leaf of Allah) ነው፡፡››
ይህን የሚሉን  አደም አልዩ ጄላን የተባሉ የአወዳይ ከተማ ነዋሪ የሆኑ ሽማግሌ ሲሆኑ፤ ዶ/ር ሕዝቅኤል ገቢሳ ከአስራ ሶስት ዓመታት በፊት “Leaf of Allah Khat & Agricultural Transformation in Harerge, Ethiopia, 1875–1991”

ሰሎሞን የኔነህ (ስሙ ለዚህ ጽሑፍ ሲባል የተቀየረ) ኑሮውን መቐለ ከተማ ያደረገ፣ ወደ አዲስ አበባ በሚመጣባቸው የስራ  አጋጣሚዎች የመገናኘት ዕድሉ ያለን የረጅም ዓመታት ወዳጄ ነው።  በቅርቡ እንደ ወትሮው ሁሉ ከሰሎሞን ጋር ተገናኝተን ስለ ሥራ፣ ኑሮና ልጆች ከተጠያየቅን በኋላ፤ በድንገት:
“ጫት አቆምኩ” አለኝ በድል አድራጊነት ስሜት።
እኔም፤ ‹‹በእውነት?›› አልኩት፤
ፈጠን ብሎ፤ ‹‹አዎ! አቃተኝ! ልጆቼን ከትምህርት ቤት ማምጣት ተሳነኝ፣ እንዴት ልነሳ ጫቱን ትቼ” አለኝ እጆቹን እያወራጨ።
ጫት ሁለመናውን ሽባ አድርጎት እንደነበር ለማወቅ ፊቱን ማየት ብቻ በቂ ነበር፡፡ ሰሎሞን ጫት በዘመናችን ያመጣው ጣጣ አይነተኛ ማሳያ (microcosm) ነው፡፡ ከሰሎሞን ተነስተን ስንቶቹ ከስራ ገበታቸው እንደተፈናቀሉ፣ ትዳራቸውን እንደበተኑና ከኑሯቸው እንደተጣሉ መናገር የአደባባዩን እውነታ መድገም ነው የሚሆንብን።
“The poison leaf”
ብሪታኒያ ወደ አገሯ በዓመት ከሚገባው 2560 ቶን ጫት 2.5 ሚሊዮን ፓውንድ አመታዊ የታክስ ገቢ እንደምታስገባ ሪፖርቶች ያሳያሉ። ነገር ግን ይህ ትርፍ ጫትን ወደ አገሯ እንዳይገባ ከማድረግ አላገዳትም። ከአንዳንድ የፓርላማ አባላት የቱንም ያህል ተቃውሞ ቢገጥመውም፣ በመጨረሻም ጫት በአደንዛዥ እፅነት ተመድቦ፣ ከተከለከሉ እፆች ተርታ ለመካተት በቅቷል።  ለክልከላው መሰረት የሆነውም የዓለም የጤና ድርጅት ጥናቶች ናቸው፡፡
ጫትን አስመልክቶ ሁለገብ ርዕሶችን በማካተት ከስምንት ዓመታት በፊት “The Khat Controversy: Stimulating the Debate on Drugs” በሚል ርዕስ በአራት ፀሃፍት የተዘጋጀው ጥናት፤ የጫትንና የአዕምሮ ጤናን ግንኙነት አስመልክቶ 41 የተለያዩ ጥናቶችን ጨምቆ ያቀረበ ሲሆን በውጤቱም ጫት የአዕምሮ ጤና ችግርን አባባሽ ብቻ ሳይሆን ዋነኛ መነሻም እንደሆነ ያስረዳል::
በጫት የጤና ጠንቅነት ላይ እጅግ ብዙ ጥናቶች በተለያዩ ደረጃዎች የተሰሩ ሲሆን፣ ከላይ ካነሳነው በተጨማሪ በሳኡዲ አረቢያው ጃዘል ዩኒቨርሲቲ ጥናት ያቀረቡት ዶ/ር ሁሴን አጊሌ፤ በየመን ውስጥ በ1118 አዲስ የተወለዱ ህፃናት ላይ የተደረገ ጥናትን ጠቅሰው እንዳመላከቱት፤ በሕፃናቱ ላይ የክብደት መቀነስ እንደሚታይና ይህም የሆነው በእርግዝና ወቅት እናቶች ጫት ተጠቃሚ ስለነበሩ እንደሆነ ይገልፃሉ። ከዚህም ሌላ የሆድ ድርቀት፣ እንቅልፍ ማጣት፣ የአዕምሮ እረፍት ማጣት፣ የጥርስ/ድድ (dental cavities) ጉዳት መድረስና የደም ግፊትን የመሳሰሉ የጤና መዛባቶችን እንደሚያስከትል ዶክተሩ “Health and Socio-economic Hazards Associated with Khat Consumption” በተሰኘ ጽሁፋቸው ላይ አበክረው ገልፀዋል።  ከተለያዩ ጥናቶችና የቤተ ሙከራ ግኝቶች በመነሳት የዓለም የጤና ድርጅት (WHO) ጫት፤ “Cathine” እና “Cathinone” የተባሉ አደገኛና መራዥ ንጥረ ነገሮችን መያዙን በጎርጎሮሳዊያኑ አቆጣጠር በ2006 ባደረገው አሰሳም ይፋ አድርጓል።
“Leaf of Allah”
‹‹ጫት ፈጣሪ የሚወደው ዛፍ ነው፡፡ በፈጣሪ ተባርኮ ለእኛ የተሰጠን ውድ ስጦታ፡፡ ይህ የተባረከ ዛፍ ላይ ሰው ምንም ስልጣን የለውም። የተለያዩ ሰዎች ጫትን ለማጥፋትና ለመቆጣጠር ዋጋውን በማናር ጭምር ሞክረዋል፤ ማንም ግን አልተሳካለትም። ጫት እኮ ተራ አትክልት አይደለም፤ ጫት የአላህ ቅጠል (leaf of Allah) ነው፡፡››
ይህን የሚሉን  አደም አልዩ ጄላን የተባሉ የአወዳይ ከተማ ነዋሪ የሆኑ ሽማግሌ ሲሆኑ፤ ዶ/ር ሕዝቅኤል ገቢሳ ከአስራ ሶስት ዓመታት በፊት “Leaf of Allah Khat & Agricultural Transformation in Harerge, Ethiopia, 1875–1991” በሚል ርዕስ ባሳተሙት የጫትን የመቶ ዓመታት የምስራቅ ኢትዮጵያ ታሪክ በሚያወሳው መጽሐፋቸው ካናገሯቸው ግለሰቦች አንዱ ናቸው፡፡ ለሽማግሌው ዓደም ጫት ኢኮኖሚያዊ፣ ማሕበራዊና መንፈሳዊ መሰረት የሆነ በፈጣሪ ትዕዛዝ ለሰው ልጆች የተበረከተ ስጦታ ነው። ይህ ስሜት ግን የዓደም ብቻ አይደለም፡፡
ካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ በፈረንጆቹ መስከረም 2016 የደቡብ ክልልን እንደመነሻ ወስዶ ባስጠናው ጥናት፤ በርካታ ቤቶች የጓሮ አትክልት ልማትን ወደ ጫት ማሳነት መቀየራቸውን ተከትሎ፣ ለምን ወደዚህ ዘርፍ እንደገቡ ጠቅለል ያለ ፅሁፍ አቅርቦ ነበረ። በጥናታዊ ጽሑፉ እንደተመለከተውም፤ በ1980 ከ40 አባወራዎች አንዱ ብቻ የጫት ማሳ እንደነበረው የተጠቀሰ ሲሆን፣ ከ1990 ወዲህ ግን ከ40 አባወራዎች 38ቱ ማሳቸውን ወደጫት ማሳነት እንደቀየሩት ያመላክታል፡፡ ይሄም አዲስ እውነታ ለእንሰትና ለተለያዩ ዛፎች ተይዞ የነበረው ቦታ እንዲቀንስ ማድረጉን ጥናቱ ጠቁሟል። አያይዞም ይህ እውነታ የአካባቢው አርሶ አደሮች ወደ ሌሎች ከተሞች አስቤዛ ሽመታ እንዲወጡ ማድረጉን ጥናቱ ላይ የተሳተፉ ግለሰቦችን ጠቅሶ፣ ይገልጻል። በአስገራሚ ሁኔታም አንድ በጥናቱ ላይ የተሳተፉ ግለሰብን ጠቅሶ ለ20 ዓመታት በጫት ልማት ላይ እንደነበሩና አሁን ግን ፊታቸውን ወደ ቀድሞ እርሻቸው መልሰው እንዳዞሩ በማተት ለዚህም እንደ ገፊ ምክንያት የሆነው በቤተሰባቸው ውስጥ ለምግብነት የሚውል የአትክልት እጥረት እንደሆነ ይገልፃል፡፡

Awaday+Khat+Market+_04_5354
ይህ ጥናት  የሲዳማ ዞን ገበሬዎች የጓሮ አትክልታቸውን ወደ ጫት ማሳነት የቀየሩበትን ምክንያት ሲዘረዝር፤ የተሻለ ገንዘብ ማስገኘቱ፣ የዘር አቅርቦትና ማዳበሪያ እጥረት መኖሩ መሆናቸውን የጥናቱን ተሳታፊዎች አጣቅሶ ይገልፃል። እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ አቆጣጠር ከ1990 እስከ 2000 ባሉት አስር ዓመታት ውስጥ የጫት ዋጋ ከ9 ብር ወደ 45 ብር ከፍ ማለቱንና ያም በየ300 ኪ.ሜ ራዲየስ ውስጥ 20 የተለያዩ የጫት ገበያዎች እንዲከፈቱ ምክንያት መሆኑን ያትታል።
ይሄንና መሰል ጥናቶች የሚያመላክቱት ነገር ቢኖር ጫት የኢትዮጵያን ግብርና ምን ያህል ሊቀይረው እንደሚችልና ራሷን መመገብ ያልቻለች አገር ላይ እንዲህ ያለ ተጨማሪ ፈተና ሲደረብ ደግሞ ‹‹በምግብ ራስን መቻል›› የሚባለውን ጉዳይ ወደ ተረትነት ሊቀይረው እንደሚችል ነው።
“The Dollar Leaf”
በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ጫት ከቡናና ከጥራጥሬ ምርቶች ጎን ለጎን የውጭ ምንዛሬ በማስገኘት ተወዳዳሪ ያልተገኘለት ቅጠል ሆኗል። ‘The Dollar Leaf’ የሚለው ቅጥያውም ዘልቆ እየተሰማ ይገኛል፡፡ ለአገሪቱ አዲሱ የኢኮኖሚዋ ዋልታ ጫት በመቶ ሚሊዮን ዶላሮችን በየዓመቱ የሚያሳፍስ ቅጠል እንደሆነ የቅርብ ጊዜ መንግስታዊ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
የጫት ምርትን ከአገራችን ወደ ውጭ መላክ የተጀመረው በደርግ ዘመን ቢሆንም ኢሕአዴግ ስልጣን ከያዘበት 1983 ወዲህ በዘርፉ የሚገኘው የውጭ ምንዛሬ እያደገ ይገኛል፡፡ በ1983 ዓ.ም  በዘርፉ የወጪ ንግድ ከ56 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የገንዘብና ኢኮኖሚ ቢሮ መረጃዎች ያመላክታሉ፤ በ2007 ዓ•ም ከጫት ንግድ 332 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ መገኘቱን የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን መረጃዎች ይጠቁማሉ። ከ2008 እስከ 2012 ዓ.ም  275 ሺ ቶን ጫት ወደ ውጭ በመላክ፣ ከ 1.5 ቢሊዮን ዶላር በላይ ለማግኘት ታቅዶ እየተሰራ እንደሆነ መንግስታዊው ዕቅድ ይጠቁማል።
በዓለማቀፍ ተቋማት እንደ መርዘኛ አደንዛዥ እፅ በሚቆጠር የሰብል አይነት ላይ ይሄን ያህል መደገፍ ለጊዜው ለአገሪቱ ዶላር ቢያመጣላትም ቋሚና ዓለማቀፋዊ ተቀባይነት ያላቸውን ምርቶች ወደ ገፍቶ የማታ ማታ አገሪቱን ታላቅ ኪሳራ ላይ እንዳይጥላት የሚያሰጋ ነው፡፡
ጫት በዓለማቀፍ ተቋማት በመርዘኝነት የታወቀ ቅጠል ቢሆንም በኢኮኖሚያዊና ማሕበራዊ ምክንያቶች የተነሳ ስርጭቱ እጅግ እየሰፋ መሔዱ የማይካድ እውነት ቢሆንም በዚህ ድምዳሜ ላይ ጥርጣሬ እንዳላቸው የሚገልፁ ግለሰቦችም አልጠፉም፡፡ ዶ/ር ኤፍሬም ተሰማ ከእነዚህ ተጠራጣሪዎች መካከል አንዱ ናቸው፡፡ ዶ/ር ኤፍሬም ለዶክትሬት ማሟያቸው በሰሩት ጥናት ላይ የጫትን አዎንታዊ ጎን ለማጥናት ሙከራ አድርገዋል። አያይዘውም በ1960ዎቹና 70ዎች በነበረው የትግል ንቅናቄ ወቅት ጫት የነበረውን አስተዋፅኦ ይገልጻሉ። በትግሉ ላይ ለነበሩ ወጣቶች ጫት የጀርባ አጥንት እንደነበረ አስረግጠውም ይናገራሉ፣ “ወጣቶቹ ፓምፍሌቶችን በማባዛት፣ ማርክሲስት ሌኒናዊ ርዕዮተ ዓለምን ሌሊቱን ሙሉ እያጠኑ ለመቆየት ጫት አስተዋፅኦ ነበረው” ይላሉ ዶክተር ኤፍሬም። በወቅቱ የነበረው እድገት በህብረት ዘመቻም ወጣቶቹን ከጫት ጋር ለማስተዋወቅ  የራሱ የሆነ አስተዋፅኦ እንደነበረው ያትታሉ። በተጨማሪም እስከ 13ኛው ክፍለ ዘመን የሚመዘዝ ታሪካዊ ዳራ ያለውና በአብያተ ክርስቲያናትና በገዳማት እንዲሁም በሙስሊሙ ማሕበረሰብ ውስጥ የተለያዩ አስተዋፅኦ ያበረከተ ቅጠል እንደሆነ አበክረው ይናገራሉ፡፡ አስከትለውም ጫት ላይ ሕግና ፖሊሲ ከመርቀቁም በፊት ሰፊ ጥናት እንደሚያስፈልግና በዘርፉ ላይ ለመስራት የሚሳተፉ ቡድኖች ጥልቅ ምርምርን አድርገው ‹‹ጫት ይከልከል›› አልያም ‹‹አይከልከል›› የሚለው ነገር ቢወሰን የተሻለ ይሆናል ይላሉ።
ዶክተር ኤፍሬም ለዚህ ሐሳባቸው ሰሚ ያጡም አይመስልም። ባሳለፍነው ዓመት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የምሁራን ስብሰባ ላይ የተገኙ ከጎንደር የመጡ መምህር፣ የወጣቱን የጫት ሱሰኝነት ተከትሎ መንግስት ምን እንዳሰበ ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጥያቄ አቅርበው የነበረ ሲሆን፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩም የዶክተር ኤፍሬምን ጥርጣሬ በሚያንጸባርቅ መልኩ “ጫትን የመቃወም የመደገፍ አቋም የለኝም፣ ጫት ይጠቅማል፣ አይጠቅምም የሚሉ ወገኖች ምርምር አድርገው ተከራክረው ያሳምኑን። ያኔ በማስረጃ ጎጂ ነው ከተባለ እናስቆማለን፣ እስከዛው ድረስ ግን የሚያስገኘውን ዶላር እየበላን እንቆያለን” የሚል አስገራሚ መልስ ሰጥተው፣ መንግስት ጫትን ለመቆጣጠር ፖሊሲ የማርቀቅም ሆነ ሕግ የማውጣት ፍላጎት እንደሌለው ጠቆም አድርገው ነበር።
ይህ በምዕራቡ ዓለም ከሚታየው የዓለም ሙቀት መጨመር ጋር ተያይዞ ከሚነሳው ክርክር ጋር እጅግ ተመሳሳይነት ያለው ሆኖ ነው ያገኘሁት። ምንም እንኳን ለመቶ ዓመታት እጅግ ብዙ የዓለም ሙቀት መጨመርን አስመልክቶ የተሰሩ ጥናቶች ቢኖሩም አንዳንድ የአየር ንብረት መለወጥን የሚክዱ (Climate change deniers) ሊቃውንት ግን ‹‹የለም፤ የዓለም ሙቀት መጨመር ብሎ ነገር የለም›› ብለው በመካድ ለአንዳንድ ፖለቲከኞች የተሳሳታ የፖሊሲ ግብዓት ሲያቀርቡ ይታያል። ጫትና ተያያዥ ጉዳዮችን አስመልክቶም እጅግ ብዙ ጥናቶች የቅጠሉን ጎጂነት በመግለፅ በአገሪቱ ላለው የአዕምሮ ጤና መዛባት የራሱን አስተዋፅኦ እያበረከተ እንደሚገኝና፣ ኢኮኖሚያዊና ማሕበራዊ ኪሳራው እጅግ ብዙ እንደሆነ፤ እንዲሁም የንግድና የእርሻ ትስስር ላይ እጅግ አሉታዊ ተጽእኖዎች እንደሚያሳድሩ ቢጠቁሙም ‹‹የጫትን ጎጂነት የሚያመላክት ማስረጃ እስኪቀርብልን ድረስ  የሚያስገኘውን ዶላር እየበላን እንቆያለን›› የሚለው የመንግስት ምላሽ፣ በመግቢያዬ የጠቀስኩት ሰሎሞንና እሱን መሰሎቹ ቤት ሲበተንና የአዕምሮ ጤና መዛባት ከመቼውም ጊዜ በላይ በዜጎች ላይ ከተከሰተ በኋላ እርምጃ ቢወሰድ “ቀድሞውን ነበር እንጂ መጥኖ መደቆስ አሁን ምን ያደርጋል ድስት ጥዶ ማልቀስ” እንዳይሆንብን ያሰጋል።

addisadmass news paper

‹‹ያማረ ሕንጻ ግንባታ ማስታወቂያ ሥር፣ግንባታው ምንም የማይፈይድላቸው የጎዳና ልጆች በቡድን ተኝተዋል››

‹‹ያማረ ሕንጻ ግንባታ ማስታወቂያ ሥር ምንም የማይፈይድላቸው የጎዳና ልጆች በቡድን ተኝተዋል›› DW AFRICA

የዶቼ ቨሌ የእንግሊዝኛ ክፍል የዐማራ ሕዝብን በተመለከተ አንድ ዘገባ ትናንት ሜይ 10፣ 2017 ይዞ ወጥቷል፡፡ የመገናኛ አውታሩ በእርሱ ላይ ‹‹የድሮ ሥርዓት ናፋቂው የዐማራ ሕዝብ›› ይላል፡፡ የተለያዩ የጎንደርና የባሕር ዳር አካባቢ ነዋሪዎችን አነጋግሮ የሰራው የዶቼ ቨሌ ዘጋቢ ህወሃት የዐማራው ሕዝብን እንዴት እየበደለው እንዳለ በማስረጃ አትቷል፡፡ ዘጋቢው የጎንደር ከተማን ሲጎበኝ ‹‹በየቦታው የኢትዮጵያን አንድነት መሀንዲስ አጼ ቴዎድሮስ ምስልና ሐውልት በጎንደር ከተማ በየቦታው ይገኛል›› ብሏል፡፡

ቅዱስ የተባለ የጎንደር ነዋሪ ‹‹ዐማራነት ይከበር እያልን ነው የምንታገለው›› ብሎታል ጋዜጠኛውን፡፡ እንደ ሄኖክና ዳዊት ያሉ ወጣቶች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁንና መራዘሙን፣ የአባቶቻችን ሰንደቅ መከልከል ብሎም የጭቆና መብዛትን አምርረው ተቃውመው የዐማራ ገበሬዎችን ተጋድሎ እንደሚያስደስታቸው በኩራት ተናግረዋል፤ ‹‹አነጣጥረው ተኳሾች›› በማለት አሞካሽዋቸዋል- ገበሬዎቹን፡፡

የድሮ ዘመን ናፋቂ ያላቸው የጀርመን ሬዲዮ ጋዜጠኛው በቀደመው ዘመን አበባ የነበረችው የነገሥታት አገር ጎንደር አሁን መንገዶቿ በምንዱባን የተሞሉ ናቸው ሲል ከቀደመው ዘመን እንዴት ኑሮ እንደከፋ በንጽጽር አስቀምጧል -እስጢፋኖስ የተባለ የሆቴል ሥራ አስኪያጅን ዋቢ አድርጎ፡፡

ህወሃት የዐማራን ወጣቶች ኑሮ እንዴት ሲኦል እንዳደረገባቸው የራሳቸውን ሕይወት መሠረት አድርገው ይናገራሉ፤ ዳዊት የተባለ በነርሲንግ ዲፕሎማ ያለው የ25 ዓመት ወጣት ‹‹መኪና አጥባለሁ፤ ሌላ ሥራ መሥራት አልቻልኩም፤ መንግሥትም ስራ ሊሰጠኝ አልቻለም፤ ከአንድ መቶ ጊዜ በላይ ለሥራ አመልክቼ መቀጠር ግን አልቻልኩም›› ሲል ተናግሯል፡፡ ዳዊት የእርሱን እኩያዎች ሕይወት በተመለከተ ሲናገር ‹‹ወንዶች ጫማ ይቀባሉ ወይም ጋራዥ ቤት ይበይዳሉ፤ ሴቶች ደግሞ ማታ ማታ ገላቸውን ይቸረችራሉ›› ሲል ሕይወት ምን ያህል የከፋ እንደሆነ ተናግሯል፡፡

ጋዜጠኛው በባሕር ዳርም የተለያዩ ሰዎችን አናግሯል፡፡ ሳምራዊት የ28 ዓመት ወጣት ናት፤ እንዲህ ትላለች ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አመጹን ለመደፍጠጥ ጥሩ ሊሆን ይችላል፤ የዜጎችን መብት ግን በእጅጉ ይጎዳል››፡፡ ኃይሌ የተባለ ወጣትም አሁን አሁን በትግሬና በዐማራ የዩንቨርሲቲ ተማሪዎች መካከል ስላለው ግጭት ተናግሯል፡፡

ዓባይ ድልድይ አካባቢ የተገኙት ቄስ ደግሞ የአጋዚ ወታደሮች በነሐሴ 2008 ዓም 52 ንጹሐን ዜጎችን ያለርህራሔ እንዴት እንደገደሏቸው በማዘን አስታውሰውታል፡፡ ያማረ ሕንጻ ግንባታ ማስታወቂያ ሥር ምንም የማይፈይድላቸው የጎዳና ልጆች በቡድን ተኝተዋል ይለናል ይኼው ጋዜጠኛ፡፡ የግጭትና እርቅ ምሁሩ አሜሪካዊ ፕሮፌሰር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁም ሆነ መንግሥት ለዜጎች ያመጣው የተሸለ አግልግሎት የለም ሲል መስክሯል፡፡

የዶቼ ቨሌው ጋዜጠኛ እንዳሻሽ የተባለችን እናት አስተያየት ነው መዝጊያ ያደረገው፤ ‹‹የደረግ ዘመን በጣም የተሻለ ነበር፤ ደርግ ቢያንስ ከሀብታም ወስዶ ለሕዝብ ያከፋፍላል›› ሥትል የሥርዓቱን ቀማኛነት ትናገራለች፡፡

ብራና ለንባብ እንዲመች አድርጎ እንዳሰፈረው

ሙሉ ዘገባውን ቀጥሎ ባለው ድረ ገጽ ያንብቡ

Fierce pride

amhara

A statue of 19th century Ethiopian Emperor Tewodros, a hero to many Ethiopians, dominates the center of Gondar. The Amhara still remember how they ruled Ethiopia until the present-day Tigrayan-led government took over in 1991. “We have no sovereignty,” says Gondar resident Kidus, “Hence our cry of protest: Amharaneut Akbiru! Respect Amhara-ness!”

Rebels with a cause

amhara 2

Young men like Henok and Dawit talk scathingly of the Ethiopian government’s state of emergency which was declared in October 2016 and recently extended. They also complain about the current ban on the older, pan-Ethiopian national flag. But they are full of praise for a professed Amhara resistance movement of armed farmers. “They’re like snipers with their guns,” Henok says.

Glory days of old

amhara 3

Gonder was once the seat of power in Ethiopia: a city of grand castles, banquets, pomp and ceremony. Nowadays, as soon as one leaves the city’s main roads, one is struck by the poverty. “Inflation is getting worse, and the government only increases the salaries of a few sectors,” says hotel manager Stephanos. Locals complain the government is not investing enough in the city.

The daily grind

amhara 4

“I wash cars, there’s no chance to get any other type of job,” says 25-year-old Dawit. “I have a nursing diploma, but the government doesn’t want to give me a job, I’ve tried 100 times.” Others make money however they can: boys and teenagers clean shoes, men solder metal work, women sell their bodies at night before heading to church the next day.

A world away from conflict

amhara 7

South of Gondar, in the Amhara regional capital of Bahir Dar, men prepare boats beside Lake Tana at dawn to ferry tourists to the island monasteries. Here tempers appear less frayed and more conciliatory. “People are tired of the trouble and want to get on with their lives,” says Tesfaye, a tour operator.

Looking for a job

amhara 8

Beneath palm trees and sparkling sunshine, crowds gaze forlornly at job noticeboards. High levels of unemployment and poverty helped fuel last year’s protests. “The state of emergency has been 50/50,” says Samrawit, 28, a local accountant. “It’s been good at calming the situation, but it’s not been good for people’s freedom.”

Animosity among the young

amhara 9

For people like Haile, who has a job with Ethio Telecom and can afford to splash out on a pair of jeans, it’s not just economic issues that are proving worrisome. “Three years ago I went to university and no one cared where you were from,” Haile says. “Now Amhara and Tigray students are fighting with each other.”

Protests in Bahir Dar

amhara 10

In 2016, demonstrators crossed this bridge over the Blue Nile on the outskirts of Bahir Dar, carrying palm tree leaves as a sign of peace. A few kilometers further on, the march ended when 52 unarmed protesters were shot by security forces. “Security forces suddenly emerged from buildings and shot into the march for no reason,” says a local priest. “They were waiting for an excuse to shoot.”

Missing out on the economic boom

amhara 11

A group of homeless men on the streets of Bahir Dar wake up beside a billboard advertising a new construction project that is unlikely to benefit them. “Grievances haven’t been addressed by the state of emergency or by the government’s commitment to tackle corruption and boost service delivery,” says Terrence Lyons, a U.S. professor specializing in conflict analysis and resolution.

Informed society

amhara 7

More Ethiopians than ever have access to TV and the Internet. Hence Ethiopian society is inexorably becoming more freethinking and informed. “The time of the Derg was better, they took from the rich and gave to the people,” says 65-year-old grandmother Indeshash, housebound in Gonder due to ongoing leg problems. “If my legs worked I would have protested.”

 

ከሳዑዲ ወደ ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም የታየው የስደተኞች ቀውስ እንደገና እንዳይከሰት ተሠግቷል

– ወደ አገራቸው ለመመለስ የተመዘገቡ 20 ሺሕ ብቻ ናቸው    – የምሕረት ቀነ ገደቡ ሊጠናቀቅ 45 ቀናት ብቻ ቀርተውታል

ሳዑዲ ዓረቢያ በሕጋዊ መንገድ ያልገቡ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የአገሪቱን መንግሥት የምሕረት አዋጅ በተገቢው ሁኔታ ባለመጠቀማቸው ምክንያት፣ ከዚህ ቀደም የታየው ዓይነት ቀውስ እንዳይፈጠር ሥጋት ተፈጥሯል፡፡ ችግሩ መንግሥትን እጅግ እንዳሳሰበ ቢገለጽም፣ መንግሥት ለስደት ተመላሾች የሚገባውን ቃል አያከብርም ተብሎ ተተችቷል፡፡

በቅርቡ የሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥት ሰነድ አልባ ስደተኞች ያለ ምንም ቅጣት ከአገሪቱ እንዲወጡ ያስቀመጠው የሦስት ወራት ቀነ ገደብ ሊጠናቀቅ 45 ቀናት ብቻ  የቀሩት ቢሆንም፣ እስካሁን  የኢትዮጵያውያኑ ተመላሽ ተመዝጋቢዎች ቁጥር ከ20 ሺሕ እንደማይበልጥ ተጠቁሟል፡፡

ዓርብ ግንቦት 4 ቀን 2009 ዓ.ም. በውጭ  ጉዳይ ሚኒስቴር ሥር የተቋቋመው የተመላሾች አስተባባሪ ግብረ ኃይል ሰብሳቢ ሚኒስትር ዴኤታው አክሊሉ ኃይለ ሚካኤል (ዶ/ር)፣ ከሚኒስትሩ ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም ጋር በጋራ በመሆን ከሚዲያ ባለሙያዎች ጋር  ውይይት አድርገዋል፡፡

‹‹ከሳዑዲ ዓረቢያ አለመውጣት አማራጭ አይደለም፤›› ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፣ መንግሥት ለጉዳዩ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ የማንቀሳቅስና የማስተባበር ሥራ እያከናወነ ቢሆንም፣ እስከ ዛሬ በአጥጋቢ ቁጥር የምሕረት አዋጁን እየተጠቀሙ በአለመሆናቸው የሚያሳሰብ ነው ብለዋል፡፡

ስደተኞቹ በፍጥነት ያልመጡትና የምሕረት አዋጁን ያልተጠቀሙባቸው በርካታ ምክንያቶችን ጠቅሰዋል፡፡ ብዙዎቹ አዋጁ ተግባራዊ ሊሆን ስለማይችል ሌሎች ከወጡ በኋላ የተሻለ ገንዘብ ይገኛል እንደሚሉ፣ የቤተሰብ ጫናና መዘናጋት ተጠቃሽ እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡ በተለይ ደግሞ በአካባቢው የሚገኙ ሕገወጥ ደላሎች እንደዚህ ዓይነት ወሬዎችን በማስወራት፣ ዜጎች በሰላም ወደ አገራቸው እንዳይመጡ እያደረጉ ነው ብለዋል፡፡

የምሕረት ቀነ ገደቡ ሊጠናቀቁ የቀሩት 45 ቀናት ብቻ ቢሆኑም፣ በአካባቢው የኢትዮጵያ መንግሥት ባቋቋማቸው ሰባት የምዝገባ ጣቢያዎች እስካሁን የተመዘገቡት 20 ሺሕ ተመላሾች ብቻ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ እሳቸው እንደሚሉት፣ ከዚህ በፊት በ2005 ዓ.ም. በተመሳሳይ ከሳዑዲ ዓረቢያ ያጋጠመው ዓይነት ከፍተኛ የሆነ የሞት፣ የአካል መጉደልና እሱ ያስከተለው ሰብዓዊ ቀውስ እንደገና የመከሰት ዕድሉ ከፍተኛ ነው፡፡

እስካሁን የሚዲያ ሚና ከፍተኛ መሆኑን የተናገሩት ቃል አቀባዩ አቶ መለስ  በበኩላቸው፣ ጉዳዩ ከሳዑዲ ዓረቢያና ከኢትዮጵያ የሁለትዮሽ ግንኙነት ጋር እንደማይገናኝ ገልጸዋል፡፡ እያንዳንዱ የኅብረተሰብ ክፍልና ቤተ ዘመድ፣ እንዲሁም የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ቅስቀሳ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ‹‹ቆሼ ላይ የደረሰው አደጋ ድንገተኛ ነው፡፡ ይኼኛው ግን እያየነው እየመጣ ያለ ጎርፍ ነው፤›› ብለዋል፡፡

ከሚዲያ ባለሙያዎች አንዳንድ አስተያየቶች የተሰነዘሩ ሲሆን፣ በተለይ ቀደም ሲል የሳዑዲ ተመላሾችን ለማስተባበር የተቋቋመው ብሔራዊ ኮሚቴ ምን እንደሠራ ጥያቄ ቀርቧል፡፡ ሥራው አይታወቅም፣ የተገባላቸውን ቃል ተስፋ አድርገው የመጡ ተመላሾች ተበትነው ቀርተዋል፣ ይህም ተመላሾቹ ወጣቶች ወደ አገር ቤት እንዳይመለሱና ተስፋ እንዲቆርጡ አድርጓል የሚሉ አስተያየቶች ተሰጥተዋል፡፡

አስተያየት ሰጪዎቹ ክልሎች ቃል እንደሚገቡት በተግባር እንደማይሠሩ፣ ከዚህ በፊት በስንት ችግር ከመጡ ስደተኞች መካከል ብዙዎቹ ተመልሰው መሄዳቸውንና መንግሥት ዘላቂ መፍትሔ እንዳላበጀ በመጠቆም ተችተዋል፡፡

በተለይ ‹‹እዚህም ሞት  እዚያም ሞት›› የሚል ከፍተኛ ተስፋ የመቁረጥ ስሜት በስደተኞቹ ዘንድ እንዳለ አስተያየት የቀረበ ሲሆን፣ መንግሥት ቢመለሱ ለማስተናገድ ምንም የተለየ ፓኬጅ ባለማዘጋጀቱ ትችት ቀርቦበታል፡፡

ከሁሉም በላይ ግን ቀደም ሲል የተጀመረውና በርካታ ዓመታት ያስቆጠረው  ዜጎች መብታቸው ተከብሮላቸው ወደ አካባቢው በሕጋዊ መንገድ ተጉዘው እንዲሠሩ ያስችላል የተባለ አዋጅ እስካሁን ሥራ ላይ ባለመዋሉ ትችት የቀረበ ሲሆን፣ ለአዋጁ አፈጻጸም አጥጋቢ ምላሽ ሲሰጥ አይስተዋልም ተብሏል፡፡

በተለይ የሳዑዲ ዓረቢያ ተመላሾች የምሕረት አዋጁን ተጠቅመው  አገር ቤት ቢመጡ አሻራ ሳይሰጡ ስለሆነና ተመልሰው በሕጋዊ መንገድ እንዲሄዱ የሚፈቅድ በመሆኑ፣ አዋጁ ተግባራዊ ቢደረግ ስደተኞቹን ወደ አገር ቤት በቶሎ ለማምጣት ተስፋ ይሆን ነበር ተብሏል፡፡

በሳዑዲ ዓረቢያ በመቶ ሺሕ የሚገመቱ ኢትዮጵያውያን በሕገወጥ ስደት ላይ ይገኛሉ፡፡ ብዙዎቹ አሰቃቂ የሆነውን የባህርና የበረሃ ጉዞ ሲያደርጉ ከሞት የተረፉ ናቸው፡፡

ሪፖርተር አማርኛ

” You will forever be in our hearts our beloved brother!” Obang Metho

The passing of Fekade Shewakana

As citizen, as teacher, and as community leader, Fekade exemplified everything good about the true leader and public service. It was never about him, but always about helping all Ethiopian people. He was an independent voice who never hesitated to speak his mind.

by Obang Metho 

I am deeply saddened to hear the passing of brother Fekade Shewakana. I am proud to have known him and grateful for what he did for our country.

I have known him for more than 10 years and was one of the most assuredly the most patriotic man I ever met. I respected him greatly and had a deep affection for him.

He was a great man, a good leader, and professor. He was also a brave, gentle, kind, full of love for his fellow Ethiopians and patriotic Ethiopian who loves his people, country and his every action. He was a uniquely talented leader who served our society and country.

He was a true nationalist who cares about the wellbeing of all Ethiopian people regardless of race, ethnicity, or religion, men and women and he stood up for the unity of Ethiopia.

I never look at him as an ethnic or a tribal leader but, as a great national leader who defended one Ethiopia and one people’s and the peoples of Ethiopia.

He was a unifier who thought outside the box, never gave up and worked hard for the ideas he believed in up until the very end of his life

With his passing, our beloved country of Ethiopia has lost an icon. His death will leave a void and he will be will be missed by everyone who knew him.

As citizen, as teacher, and as community leader, Fekade exemplified everything good about the true leader and public service.

It was never about him, but always about helping all Ethiopian people. He was an independent voice who never hesitated to speak his mind.

Many students at Addis Ababa University and Ethiopia benefited from his extraordinary service, but he had a special place in his heart for his beloved country of Ethiopia. We will miss his courage and inspiration, he showed us all.

He always told me he appreciated my work and he was desire to be part of it. He once said: “Mr. Obang I strongly believe that your way of national reconciliation, healing and forgiveness is the only way that will bring our people closer to lasting peace to Ethiopia. Please keep pushing forward with it”

I will miss brother Fekade Shewakana, a great friend and a true mentor, and our nation will mourn the loss of a dedicated public servant without equal.

It is with a heavy heart that I say goodbye to my brother, friend and colleague. My thoughts and prayers are with his family at this difficult time.

May you Rest in Perfect Peace not the disturbed and unsettled peace of this world of oppression, injustice, hatred greed, guns and destruction.

You will forever be in our hearts our beloved brother!

We the living will continue to carry on from where you left off in defending the rights of all our people and country.

We will continue to defend our people and uphold our values of humanity not ethnicity. It is now our task to carry on the struggle and pass it on to the next generations.

አፍላቶክሲን አደገኛው የጤና ጠንቅ

የተለያየ የጥራት ደረጃ የሚወጣላቸው ዛላ የበርበሬ ዓይነቶች በየማዳበሪያው ተሞልተው ተደርድረዋል፡፡ አንደኛ የሚባለውና በኪሎ 60 ብር የሚሸጠው፣ ዛለው ረጃጅምና ደማቅ ቀለም ያለው ነው፡፡ ሁለተኛው በኪሎ 50 ብር የሚሸጠው ሲሆን፣ ከአንደኛው መለስ ያለ ደረጃ የሚሰጠው ነው፡፡ ሌሎቹ የበርበሬ ዘሮች የተሰባበሩ፣ ነጫጭ የሚበዛባቸው ከበርበሬነት ይልቅ በቀለማቸው ወደሌላ የምርት ዓይነት የሚያደሉት በኪሎ እስከ 30 ብር የሚሸጡ ናቸው፡፡

በሾላ ገበያ በርበሬና የተለያዩ ቅመማ ቅመሞችን የሚሸጡት ወይዘሮ ዘመናይ ይርጋ (ስማቸው የተቀየረ ነጋዴ) ፀዳሌ፣ ማረቆና ሃላባ የተባሉት የበርበሬ ዓይነቶች ተመራጭ እንደሆኑ ይናገራሉ፡፡ በአጠቃላይ ግን ቆዳው ወፍራምና ዛላው ትልልቅ ሆኖ ደማቅ ቀለም ያለው አንደኛ ተብሎ በውድ ዋጋ ይሸጣል፡፡ ልቃሚ የሚበዛውና አመድማ ዛላ ያለው በርበሬ በርካሽ ዋጋ እንደሚሸጥ ይገልጻሉ፡፡

‹‹አንደኛው ቀለሙ በጣም ቀይ ነው፡፡ ወጥ ሲሠራበትም ያጣፍጣል፡፡ የመጨረሻው ግን አፈር የመሰለ ነው ቀለሙም አያምርም፤›› በማለት በሁለቱ የበርበሬ ዓይነቶች መካከል ያለው ልዩነት ከቀለም ያለፈ እንዳልሆነ ያብራራሉ፡፡ ልዩነታቸውም ከአለቃቀምና ከምርት አያያዝ የመነጨ እንደሆነም በልበ ሙሉነት ይናገራሉ፡፡ በሁለቱ በርበሬዎች መካከል ያለው ልዩነት በሻጋታ የተፈጠረ እንደሆነ ግን የገባቸው አይመስሉም፡፡

በቅናሽ ዋጋ የሚሸጠው በርበሬ በአብዛኛው ሻጋታ ይታይበታል፡፡ ሻጋታ የሚፈጠረውም ምርት እርጥበቱ ሳይጠፋ በሚከማችበት ጊዜ እንደሆነ የሥነ ምግብ ባለሙያዎች ሲናገሩ ይደመጣሉ፡፡ ‹‹ኪሎ እንዲያነሳ በማለት ገበሬውም ነጋዴውም በርበሬ ላይ ውኃ ያርከፈክፋሉ፡፡ በርበሬ ዕርጥብ ሲሆን ከአንድ ኩንታል እስከ አሥር ኪሎ ትርፍ ይገኛል፡፡ ይህ በርበሬ ቶሎ ካልተሸጠ ግን ስለሚሻግት በቅናሽ ዋጋ እንሸጠዋለን፤›› በማለት ኪሎ እንዲያሳ ሲባል ውኃ የሚርከፈከፍበት በርበሬ ሻጋታ እንዲፈጥር መንገዱን እየጠረጉ ስለመሆኑ ነጋዴዋ ይናገራሉ፡፡ በርበሬ ሲሻግት በጤና ላይ የሚፈጥረው ችግር እንደሚኖር ግን አንድም ጊዜ አልጠረጠሩም፡፡ በሻጋታ ውስጥ ካንሰር አማጭ የሆነው አፍላቶክሲን የተባለው ኬሚካል እንደሚፈጠር የሚያውቁት ነገር የለም፡፡

በተለያዩ ጊዜያት የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት በርበሬ፣ በቆሎ፣ ለውዝ እንዲሁም ቦሎቄ ከፍተኛ የአፍላቶክሲን ክምችት ሊገኝባው የሚችሉ የቅባት፣ የቅመማቅመምና የእህል ዝርያዎች ናቸው፡፡ በቅርቡ ወደ እንግሊዝ የተላከ ሁለት ኮንቴነር በርበሬ በአፍላቶክሲን ተጠርጥሮ እንዲጣል መደረጉን ሚዲያዎች መዘገባቸው ይታወሳል፡፡

ሞቃታማና እርጥበት አዘል በሆኑ የዓለም አካባቢዎች በተለይም ከሰሐራ በታች በሚገኙ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች ውስጥ በሚመረቱ የእህል ዓይቶች ውስጥ አፍላቶክሲን በብዛት ይከሰታል፡፡ አፍላቶክሲን በሕፃናት ዕድገት እንዲሁም በማስተዋል ችሎታ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ከማሳደሩ ባለፈ ብዙዎችን ለካንሠርና ለተለያዩ ከባድ በሽታዎች እየዳረገ ይገኛል፡፡

አፍሪካ ባላት የአየር ጠባይ ሳቢያ 80 በመቶ የሚሆኑ ሕዝቦቿ ለአፍላቶክሲን ጉዳቶች የተጋለጡ ናቸው፡፡ በአኅጉሪቱ በተለያዩ ጊዜያት በመከሰት ብዙዎችን ከሚያረግፉት የወባና የሳንባ ወረርሽኞች የበለጠ አፍላቶክሲን በርካቶችን ለሞት እየዳረገ እንደሚገኝ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

25 በመቶ በዓለም የሚመረተው ሰብል በአፍላቶክሲን የተበከለ መሆኑም ይነገራል፡፡ በአፍሪካም አንድ ሦስተኛው ለምግብነት የሚውለው ሰብል ከሚገባው በላይ በአፍላቶክሲን የተበከለ ነው፡፡

አቶ ዘሪሁን አበበ፣ በኢትዮጵያ ተስማሚነትና ምዘና ድርጅት የኬሚካል ቴስቲንግ ላቦራቶሪ ቡድን መሪ ናቸው፡፡ እሳቸው እንደሚሉት፣ ቅርፊት ያላቸው እንደ በቆሎና ለውዝ ያሉ የእህል ዘሮች በእርጥበታማ ቦታዎች በሚከማቹበት ጊዜ በቅርፊታቸው እርጥበት የመያዝ ባህሪ ስላላቸው የመሻገት ዕድላቸው ሰፊ ነው፡፡ ቅርፊት ያላቸውን ያህል ባይሆንም ሌሎችም የሰብል ዓይነቶች በእርጥበታማ ቦታ ከተቀመጡ መሻገታቸው አይቀሬ ነው፡፡

ሁሉም ሻጋታ የአፍላቶክሲን መንስዔ ባይሆንም፣ በፍጥነት ማስተካከል ካልተቻለ ግን ወደ አፍላቶክሲን መቀየሩ አይቀሬ ነው፡፡ አፍላቶክሲን ‹‹ኤስፐርጊለስ ፍሌቨስ›› እና ‹‹ኤስፐርጊለስ ፓራሲተከስ›› በተባሉ የፈንገስ ዝርያዎች የሚከሰት አደገኛ ኬሚካል ነው፡፡ b1፣ b2፣ G1፣ G2 የሚባሉ ዝርያዎችም አሉት፡፡ እነዚህ በሰብሎች ላይ የሚከሰቱ ናቸው፡፡ m1፣ m2 የተባሉ በእንስሳት ተዋፅኦዎች ውስጥ የሚገኙ ዝርያዎችም አሉ፡፡

እንስሳት በአፍላቶክሲን የተበከሉ መኖዎች በሚመገቡበት ጊዜ ኬሚካሉ ወደ ተዋጽኦዋቸው ይተላለፋል፡፡ ነገር ግን ኬሚካሉን ወደሌላ ዓይነት ይዘት እንዲቀየር (ሜታቦላይዝ) ስለሚያደርጉት በቀጥታ እንስሳቱን አይጎዳም፡፡ እነዚህ የአፍላቶክሲን ዝርያዎች የሚያደርሱት የጉዳት መጠን የተለያየ ነው፡፡ b1 የሚባለው የአፍላቶክሲን ዝርያ ከሌሎቹ በተለየ አደገኛ ነው፡፡ የጨጓራ ካንሰር የሚከሰተው በዚሁ b1 በተባለው የአፍላቶክሲን ኬሚካል አማካይት ነው፡፡ M1 የተባለው በእንስሳት ተዋጽኦ ውስጥ የሚገኘው ኬሚካል እንደ b1 ሁሉ አደገኛ የሚባል ነው፡፡

በአንድ ኪሎ ግራም ምግብ ውስጥ መገኘት የሚገባው ከፍተኛው የአፍላቶክሲን ክምችት እንደየ ዝርያው ዓይነት ይወሰናል፡፡ በኢትዮጵያ ስታንዳርድ መሠረት b1 የሚባለው አደገኛው የአፍላቶክሲን ዝርያ፣ በአንድ ኪሎ ምግብ ውስጥ የሚኖረው ክምችት ከአምስት ማይክሮ ግራም መብለጥ የለበትም፡፡ በሕፃናት ምግብ ውስጥ የሚገኘው መጠንም በአንድ ኪሎ ግራም ውስጥ ከሁለት ማይክሮ ግራም በላይ ከሆነ አደገኛ ነው፡፡ በአዋቂ ምግቦች ውስጥ እስከ 20 ማይክሮ ግራም ከተገኘ አደገኛ የሚያስብለው ደረጃ ላይ የሚመደብ ነው፡፡

ሰብሎች በማሳ ሳሉ ሊሻግቱና በአፍላቶክሲን ሊጠቁ ይችላሉ፡፡ በአፍላቶክሲን የተጠቃ ምርት በማሳ ላይ በሚራግፍበት ወቅትም ኬሚካሉ ወደ አፈር ውስጥ በመግባት ማሳውን ሙሉ ለሙሉ ሊያበላሸው ይችላል፡፡ ‹‹በምርት ወቅት ማሳ ላይ ከተሠራጨ ችግር ነው፡፡ ኬሚካሉ አፈር ውስጥ ስለሚገባ በማሳው የሚበቅል ምንም ነገር በአፍላቶክሲን የተበከለ እንዲሆን ያደርጋል፡፡ ይሁንና ይህ ከብዙ ጊዜ በጥቂቱ የሚከሰት ነው፡፡ ሰብሎች ማሳ ላይ ሻግተው ችግር ለመፍጠር ረዘም ያለ ጊዜ ይፈጃሉ፤›› ለማለት ችግሩ በብዛት እየተከሰተ ያለው ከማሳ ተሰብስቦ በሚከማችበት ወቅት መሆኑን አቶ ዘሪሁን ይናገራሉ፡፡

እንደ እሳቸው ገለጻ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ምርት ከመታጨዱ ወይም ከመሰብሰቡ በፊት እንዳይረግፍ እየተባለ በተገቢው ደረጃ ሳይደርቅ የሚታጨድበት ሁኔታ የተለመደ ነው፡፡ በወጉ ያልደረቀው ምርት ጎተራ ከመግባቱ በፊት እንዲደርቅ እየተባለ በአንድ ላይ ይከማቻል፡፡ ይህም ሻጋታ እንዲፈጠር የመጀመሪያውን መንገድ ይከፍታል ያሉት አቶ ዘሪሁን፣ ገለባው ከፍሬው ተለይቶና ተወቅቶ ወደ ጎተራ በሚገባበት ጊዜም ተገቢው ጥንቃቄ ስለማይደረግ፣ በወጉ ያልደረቁ ፍሬዎች ተቀላቅለው ይገባሉ፡፡ በመሆኑም በጎተራ ውስጥ ታፍኖ የሚቀመጠው ምርት የመሻገት ዕድሉ ከፍተኛ እንደሆነ ያብራራሉ፡፡

‹‹አንዳንዴ ገበያ ላይ ጤፍ እምክ እምክ አለ ይባላል፡፡ ይህ የሚሆነው ጤፉ እርጥበት እንደያዘ ጎተራ ውስጥ ታፍኖ እንዲቆይ ሲደረግ ነው፡፡ ሁሉም ሻጋታ አፍላቶክሲን አይደለም፡፡ ቶሎ ካልተደረሰበት ግን ወደ አፍላቶክሲንነት ይቀየራል›› ይላሉ፡፡

የአፍላቶክሲን ጉዳይ የዓለምን ትኩረት መሳብ የጀመረው እ.ኤ.አ. በ1960ዎቹ ውስጥ በእንግሊዝ የሚገኝ አንድ የዶሮ እርባታ ውስጥ የነበሩ 100,000 ዶሮዎችን እንደ ጤዛ ካረገፋቸው በኋላ ነው፡፡ ይኸው አፍላቶክሲን በኢትዮጵያ መነጋገሪያ ለመሆን የበቃውም ዓለምአቀፉ የእንስሳት ምርምር ኢንስቲትዩት የተባለው ተቋም ተመራማሪዎች ያወጡትን ጥናት ተከትሎ ነው፡፡ ከዓመት በፊት ይፋ የተደረገው ጥናቱ፣ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚገኙ የወተት ላም አርቢዎችን መነሻ ያደረገና በወተት ውስጥ የሚገኘውን የአፍላቶክሲን ክምችት የሚያሳይ ነበር፡፡

በወቅቱ በርካቶችን ያወዛገበና የእንስሳት ተዋጽኦ ገበያን ሥጋት ውስጥ ጥሎ  እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡ ከዚህ ክስተት ወዲህ ስሙ የገነነው አፍላቶክሲን፣ ከእንስሳት ተዋጽኦ ባሻገር በተለያዩ የምግብ ይዘት ባላቸው ነገሮች ውስጥ ለጤና አስጊ በሆነ የክምችት መጠን እንደሚገኝ የሚያሳዩ ጥናቶች ይፋ እየወጡ መጥተዋል፡፡

 በዚህ መርዛማ ኬሚካል በእጅጉ እየተጠቁ ያሉትም የለውዝና የበርበሬ ምርቶች እንደሆኑ አቶ ዘሪሁን ገልጸዋል፡፡ አገሮች ካስቀመጧቸው መሥፈርቶች የበለጠ የአፍላቶክሲን መጠን የሚታይባቸውና እንዲመለሱ እየተደረጉ ካሉት ምርቶች ግንባር ቀደም ሆነው ተገኝተዋል፡፡

 ከውጭ የሚገቡ ምግብ ነክ ሸቀጦች እየተፈተሹ መሥፈርቱን የሚያሟሉት እንዲገቡ ሲፈቀድላቸው፣ የማያሟሉት ግን ወደየመጡበት እንዲመለሱ ይደረጋሉ፡፡ ወደ ውጭ የሚወጡትም እንደዚሁ እንደየአገራቱ አሠራርና መሥፈርት ተፈትሸው መሥፈርቶቹን ስለማሟላታቸው የማረጋገጫ ሠርተፊኬት እየተሰጣቸው ይላካሉ፡፡

በዚህ መሠረት ለፍተሻ ወደ ተቋሙ ከሚሄዱ የበርበሬና የለውዝ ምርቶች ውስጥ ከፍተኛ የአፍላቶክሲን ክምችት እንደሚያጋጥም አቶ ዘሪሁን የታዘቡትን ጠቅሰዋል፡፡ በኪሎ ግራም ውስጥ እስክ 60 ማይክሮ ግራም የአፍላቶክሲን ክምችት እንደሚያጋጥም አስታውሰዋል፡፡ ሌሎች መረጃዎች እንደሚያሳዩት፣ በአንድ ኪሎ ግራም ለውዝ ውስጥ እስከ 500 ማይክሮ ግራም የአፍላቶክሲን ክምችት የሚገኝበት ክስተትም ይታያል፡፡ በአውሮፓ ስታንዳርድ መሠረት በአንድ ኪሎ ግራም ለውዝ ውስጥ መገኘት የሚገባው የአፍላቶክሲን ክምችት ከአሥር ማይክሮ ግራም መብለጥ የለበትም፡፡

በኢትዮጵያ በለውዝ ምርት የሚታወቁት በምሥራቅ ሐረርጌ የሚገኙት የባቢሌ፣ የፈዲስና የጉርሱም አካባቢዎች ናቸው፡፡ በእነዚህ አካባቢዎች በሚገኝ የለውዝ ምርት ላይ የተደረገ ጥናት እንደመሚያመለክተው፣ ተከማችተው በሚገኙ የለውዝ ምርቶች ውስጥ 85 በመቶ ያህል የአውሮፓ ኅብረት ካስቀመጠው በላይ ከፍተኛ የአፍላቶክሲን ክምችት የሚገኝባቸው ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ የጥራጥሬ፣ የቅባት እህሎችና ቅመማ ቅመም አምራቾችና ላኪዎች ማኅበር ሥራ አስኪያጅ አቶ አሰፋ ዮሐንስ እንደሚሉት፣ ከመጠን ባለፈ የአፍላቶክሲን ክምችት ምክንያት ወደ ውጭ የሚላከው የለውዝ ምርት ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ መጠን እየቀነሰ ይገኛል፡፡ እ.ኤ.አ. በ2011 ወደ ውጭ ተልኮ የነበረው የለውዝ መጠን 14,424 ቶን ነበረ፡፡ ይሁንና እ.ኤ.አ. ከ2012 እስከ 2016 ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ የተላከው የለውዝ መጠን በእጅጉ ማሽቆልቆሉን ከማኅበሩ የተገኘው አሃዛዊ መረጃ ያሳያል፡፡ 12,609 ቶን፣ 592 ቶን፣ 124 ቶን እያለ ወርዶ እ.ኤ.አ በ2016 የተላከው የለውዝ መጠን ወደ 79 ቶን ሊያሽቆለቁል ችሏል፡፡

አስፈላጊውን የፍተሻ ሒደትና መሥፈርት ሳያሟሉ ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶች ከመጠን ያለፈ የአፍላቶክሲን ክምችት በሚገኝባቸው ወቅት እንዲወገዱ ሲደረግ፣ ጤናማ የሆኑት ደግሞ በላቦራቶሪ ተፈትሸው ደኅንነታቸውም ተረጋግጦ ወደ ውጭ ይላካሉ፡፡ ይሁንና ስለ ጉዳዩ ብዙም ግንዛቤ የሌላቸው ሸማቾች፣ በየዕለቱ የሚመገቧቸው ነገሮች ምን ያህል ለጤና የሚገባውን መሥፈርት እንደሚያሟሉ አረጋግጠው ስለመጠቀማቸው በእርግጠኝነት መናገሩ አጠያያቂ ነው፡፡ በዓይን የማይታዩ የኬሚካሎችን ዝርያ ከመመገብ መጠንቀቁ ቀርቶ ሻጋታን የመጠየፍ ባህሉ እስከምን ድረስ እንደሆነ ጥያቄ የሚጭሩ ልማዶች ይታያሉ፡፡

‹‹Assessment of Mothers Knowledge towards Aflatoxin Contamination›› በሚል ርዕሥ እ.ኤ.አ. በ2016 የተደረገ ጥናት፣ ማኅበረሰቡ ስለ አደገኛው ኬሚካል ያለው ግንዛቤ ዝቅተኛ በመሆኑ ምክንያት ችግሩ አሳሳቢ እንደሆነ ለማመላከት ሞክሯል፡፡ በአማራ፣ በትግራይ፣ በኦሮሚያና በደቡብ ብሔር ብሐረሰቦች የሚገኙ እናቶች በጥናቱ ተካተው ነበር፡፡

ምርት ከማሳው ጀምሮ ለምግብነት እስኪሚውልበት ድረስ ያሉትን ሒደቶች በሚያሳየው በዚህ ጥናት መሠረት፣ 64 በመቶ እናቶች ምርት ከማሳው ከተሰበሰበ በኋላ በተለያዩ ዘዴዎች አድርቆ የማስቀመጥ ልምድ እንዳላቸው ታይቷል፡፡ 68 በመቶዎቹ ምግባቸውን መሬት በማንጠፍ በፀሐይ ይደርቃሉ፡፡ 94 በመቶዎቹ ደግሞ ምርት በጎተራ ውስጥ ከማከማቸታቸው በፊት ጎተራቸውን በፀረ ባክቴሪያ ኬሚካሎች እንደሚያፀዱ ጥናቱ ያሳያል፡፡

የተሻለ ጥንቃቄ በማያደርጉት በኩል ያለው ምርት በሻጋታ የሚጠቃበት አጋጣሚ ብዙ ነው፡፡ በሻጋታ የሚከሰት ባክቴሪያንም እሳት ላይ ሞቅ ሞቅ በማድረግ መግደል እንደሚቻል የሚያምኑም አልታጡም፡፡ ከፊሉን ለእንስሳት መኖነት፣ የተቀረውን ደግሞ ለጠላ መጥመቂያነት እንደሚያውሉትም ጥናቱ ያትታል፡፡

የተበላሸ የሻጋታ ጥራጥሬን ለጠላ መጥመቂያነት የማዋሉ ነገር በአገሪቱ ክፍሎች የተለመደ ነወ፡፡ የሻገተ እንጀራን በምጣድ ሞቅ አድርጎ መብላትም አዲስ አይደለም፡፡ እንዲያውም እንጀራ ሻጋታ መያዝ ሲጀምር ድርቆሽ ማድረግና አቆይቶ መብላት ምግብን ከብክነት እንደመጠበቅ ይቆጠራል፡፡ በሻጋታ ምክንያት የተቋጠረ (የጓጐለ) ዱቄትን አሽተው ለመብል ማዘጋጀት፣ የሻገተ የበርበሬ ዛላን በርካሽ ገዝቶ ለምግብነት ማዋል ሊያደርስ ስለሚችለው የጤና ቀውስ የሚጨነቁ በጣም ጥቂቶች ናቸው፡፡

ምርት ከማሳ ላይ ተነስቶ ወደ ጎተራ እስኪገባ ባሉት ሒደቶች የሚፈጠረው አፍላቶክሲን በቀላሉ መከላከል እንደሚቻል አቶ ዘሪሁን ይናገራሉ፡፡ ‹‹ምርት እስኪደርቅ ጠብቆ ማጨድ፣ ወደ ጎተራ ከመግባቱ በፊትም በፀሐይ ማድረቅ ተገቢ ነው፡፡ በእኛ አገር የአየር ፀባይ ምግብ ያለ ብዙ ልፋት ይደርቃል፡፡ በዚህ የታደልን ነን፤›› በማለት ዋናው ነገር ምርት ጎተራ ውስጥ በሚከማችበት ጊዜ እርጥበት እንዳይነካው ጥንቃቄ ማድረጉ ላይ እንደሆነም ይመክራሉ፡፡

በተፈጥሮ መከላከል የማይቻል ከሆነም ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም እርጥበትንና ሻጋታን መከላከል ይቻላል፡፡ አቶ ራሺም ጀማል የሃይቴክ ትሬዲንግ ሥራ አስኪያጅ ናቸው፡፡ ሃይቴክ ኩባንያ የተለያዩ የግብርና የኢንዱስትሪ ማሽገሪዎችና ግብዓቶችን ወደ አገር ውስጥ በማስገባት ሥራ ዘርፍ ይንቀሳቀሳል፡፡ ሻጋታን በባህላዊ መንገድ ማለትም በፀሐይ በማድረቅ መከላከል ካልተቻለ፣ የፈንገስን ዕድገት መግታት የሚችሉ አየር ወደ ውጭና ወደ ውስጥ የማያስገቡ ሄርሜቲክና ሜታል ሳይሎ የተባሉ ቴክኖሎጂዎች የተሻሉ አማራጮች መሆናቸውን አቶ ራሺም ይገልጻሉ፡፡ ሜታል ሳይሎ የሚባለው የዓለም የምግብና የእርሻ ድርጅት በብዛት የሚያከፋፍለው፣ አየር እንዳያስገባና እንዳያስወጣ ተደርጎ የሚዘጋጅ እንደ በርሜል ያለ ዘመናዊ ጎተራ ነው፡፡

ሄርሜቲክ ቴክኖሎጂ የሚባለው ደግሞ ነቀዝን፣ ተባይን፣ እንዲሁም እርጥበትና ሻጋታን ያለምንም ኬሚካልና ርጭት የተፈጥሮ ዘዴን በመጠቀም ማከማቸት የሚያስችል፣ ድርጅታቸው እንደሚያከፋፍለው ያለ የፕላስቲክ ጎተራ ዓይነት ነው፡፡ ይህ የፕላስቲክ ጎተራ ከ60 እስከ 1,500 ኩንታል የሚደርስ እህል የማከማቸት አቅም አለው፡፡ እንዲህ ቴክኖሎጂዎች ምርትን ከአፍላቶክሲን ከመጠበቅ ባሻገር ከፍተኛ የምርት ብክነትን ማስቀረት እንደሚችሉ ይናገራሉ፡፡ ይሁንና ተደራሽነታቸው ውሱን ነው፡፡

የአፍላቶክሲን ምርመራ የሚካህድበት ቴክኖሎጂ ባለመኖሩ በአንድ ወቅት ከፍተኛ ወጪ እየወጣ ባህር ማዶ እየተላ ምርት ይመረመር ነበር፡፡ የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ከ2007 ዓ.ም. አጋማሽ ጀምሮ የአፍላቶክሲን ፍተሻ ማድረግ መጀመሩን የሚናገሩት በድርጅቱ የማርኬቲንግና ኮሙዩኒኬሽንስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ አቶ ተክኤ ብርሃኑ ናቸው፡፡ ወደ ውጭ የሚወጡና ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ ምግቦችን እንፈትሻለን ያሉት አቶ ተክኤ፣ ድርጅቱ ወደ አገር ውስጥ ከሚገቡ በቀር ወደ ውጭ የሚላኩትን በሙሉ የመፈተሽ ሥልጣኑ ውሱን ነው፡፡ ‹‹ስንጠየቅ ብቻ ነው የምንፈትሸው፡፡ ሁሉም ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶች እኛ ጋር ላይመጡ ይችላሉ፡፡ ወደ ሌሎች ተቋማት በመሔድ ሊያስፈትሹ ይችላሉ፤›› በማለት በድርጅቱ ፍተሻ የሚደረገው ጥያቄ ሲቀርብለት ብቻ መሆኑን ያናገራሉ፡፡

 ድርጅቱ በአገር ውስጥ በስፋት ለምግብነት የሚውሉ እንደ የእንስሳት ተዋጽኦ፣ ሽሮ፣ በርበሬ ያሉትን የመፈተሽ አቅም ቢኖረውም፣ ለአገር ውስጥ የሚውሉ የምግብ ዓይነቶችን ለማስፈተሽ ሥራዬ ብሎ ወደ ተቋሙ የሚያመራ አለመኖሩም ሌላው አሳሳቢ ጉዳይ ነው፡፡ ከመጠን ያለፈ የአፍላቶክሲን ክምችት ተገኝቶባቸው ተመላሽ የሚደረጉ ምግብና ምግብ ነክ ሸቀጦች አገር ውስጥ ከገቡ በኋላ ገበያ ውስጥ ይግቡ ወይስ ምን ይደረጉ የሚለው ጉዳይም አጠያያቂ ነው፡፡

አቶ አብነት ወንድሙ፣ በኢትዮጵያ የምግብ፣ የመድኃኒት እና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን፣ የምግብና ጤና ተቋማት የኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ናቸው፡፡ ተገቢው ፍተሻ ሳይደረግባቸው ወደ ውጭ ከሚላኩ ምርቶች በተለይ በርበሬ በከፍተኛ የአፍላቶክሲን ክምችት ምክንያት በብዛት ተመላሽ እየተደረገ ነው፡፡ ባለሥልጣኑ እንዲመለሱ የሚደረጉ ምርቶች ወደ ሕዝብ ከመድረሳቸው በፊት እንዲወገዱ የሚያደርግበት አሠራር እንዳለው አቶ አብነት ይናገራሉ፡፡

‹‹ትልቁ ሥራ ግብርና ላይ ነው፡፡ ከዚያ ውጭ አገር ውስጥ የሚመረቱ አፍላቶክሲን ሊገኝባቸው ይችላሉ ብለን የምንገምታቸውን ምርቶች በየሦስት ወሩ እንዲፈተሹ እናደርጋለን፤›› በማለት ለጊዜው ባለሥልጣኑ ትኩረቱን በወተትና በለውዝ ምርት ላይ በማድረግ እየሠራ እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡

ምስልና ዜና ሪፖርተር 

“አልቅሳችሁ አትቅበሩኝ” የአሰፋ ጫቦ ሥርዓተ ቀብር ተከናወነ

Asefa chebo(ሚያዚያ 27 2009 ዓ.ም)፡- ሚያዚያ 27 ታሪካዊ ቀን ናት ፤ ከሰባት አስርት ዓመታት በፊት ከፋሺስት ጣሊያን ወረራ በኋላ ሀገር ነጻነቷን ያወጀችበት ሕዝብ እንደ ሕዝብ ደስ የተሰኝበት ቀን ናት ፤ የዛኔ በስደት የነበሩት ንጉሥ ከስደት መልስ ሀገራቸው የገቡበት ቀን ነው ፤ ዛሬ ግን በደርግ ዘመነ መንግሥት በጽሑፋቸው ለአስር ዓመት ከስድስት ወር በማዕከላዊ ካሳለፉ በኋላ በዘመነ ኢሕአዴግ የ16 ዓመት እስር የተፈረደባቸው ፤ ላለፉት 25 ዓመታት በስደት በሀገረ አሜሪካ ሕይወታቸውን የገፉት የሦስት ልጆች እና የዘጠኝ የልጅ ልጆች አባት ፤ ሀገራቸውን ለማቅናት እድሜ ዘመናቸው ሲወጡ ሲወርዱ ፤ ሀገሬን ….. ሀገሬን እያሉ ሞታቸው ከስደት ሀገር ከወደ ዳላስ የተሰማው አንጋፋው ጎምቱ ጸሐፊ ፤ የሕግ ባለሙያ ፤ የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ ፖለቲከኛና ምሁር የአቶ አሰፋ ጫቦ ስርዓተ ቀብር የተከናወነበት ቀን ነበር፡፡

አቶ አሰፋ ኢትዮጵያ ሀገራቸውን ፤ ጨንቻ የትውልድ አካባቢያቸውን ለማየት እንደጓጉ መሞታቸው እጅጉን ያሳዝናል ፤ እኚህን የሀገር አድባር የሆኑ ሰው የመጨረሻ ሽኝታቸውን ለማከናወን በርካታ ሰው በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ተገኝቶ ነበር ፤ ሻለቃ ፍቅረስላሴ ወግደረስ ፤ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ፤ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ፤ በርካታ የሀገር ውስጥ(የመንግሥት ጋዜጠኞች አልተመለከትኩም) እና የውጭ ሀገር ጋዜጠኞች …. በዘመነ ኢሕአዴግ ተወልደው እና አድረገው የእሳቸው ጽሑፍ ያነበቡ ወጣቶች ፤ ከትውልድ አካባቢያቸው ከጋሞ ጎፋ ፤ ወዳጅ ዘመዶቻቸው እና በእሳቸው እድሜ የሚገኙ በርካታ ሰዎች ስነ-ስርዓቱን ለመታደም በቅተዋል ፤ በርካታ የቤት መኪኖች እና ከገሞ ጎፋ በቀጥታ ስርዓተ ቀብራቸው ላይ ለመካፈል የመጡ በብሔረሰቡን አልባሳት የደመቁ ሰዎች በስነስርዓቱ ላይ ተገኝተዋል ፡፡ አቶ አሰፋ ‹‹አልቅሳችሁ እንዳትቀብሩኝ ፤ በገሞ ስርዓት ጨፍራችሁ ፤ እንደ ካህናት አሸብሽባችሁ›› ቅበሩኝ ባሉት ስርዓት በቦታው ላይ ስገኝ የማህበረሰቡ አባላት በደመቀ አልባሳት አጊጠው አንድ ከፍተኛ  የማሕበረሰቡ አባል በሚሸኝበት ስርዓት በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ በራፍ ላይ ተገኝተው  እያቅራሩ እና እየጨፈሩ ነበር ፤ በዚህ ሰዓትም በካቴድራሉ አውደ ምህረት ላይ ዲያቆን ሆነው ያገለገሉባት ቤተክርስቲያን የ‹ተስፋ ገብርኤል›ን ጸሎተ ፍትሀት እና ጸሎት እያከናወነች ነበር፡፡

Image may contain: 1 person, standing and outdoor

አባቶች ጸሎታቸውን ከጨረሱ በኋላ ሕይወት ታሪካቸው ሊነበብ አንባቢው ድምጽ ማጉያውን ከአባቶች ሲቀበል ጉም ያዘለውና ሰማይ ለ15 ደቂቃ ዝናብ አውርዷል ፤ ሰማይም ሀዘኑን የገለጸ ይመስል ነበር ፤  በዝናቡ ምክንያት አባቶች ለቀብር የመጣው ሰው ቤተክርስቲያን ተከፍቶ ጫማቸውን አውልቀው እንዲገቡ ፍቃድ ሰጥተዋል ፤ በመቀጠልም አሰፋን እጅግ በሚገልጽ መልኩ የተጻፈው የሕይወት ታሪክ በአውደ ምህረት ላይ ተነቧል፡፡ በሕይወት ታሪኩ ላይ አሰፋ ለአንድ ጓደኛው ነገረ የተባለው ታሪክ አስደማሚ ነበር…… ‹‹ ዝሆን በቀን ሦስት ኩንታል ያህል ሳር የመብላት አቅም አለው ፤ የዝሆን ጥርስ ይህን ሁሉ ሲፈጭ ጥርሱ በተፈጥሮ ራሱን ይተካል ፤ ዝሆን ወደ እድሜው መጨረሻ ላይ ጥርሱ ራሱን በማይተካበት እድሜ ላይ ሲደርስ ደመ ነፍሱ ወደ ሞት እየሄደ መሆኑን ይነግረዋል ፤ እርሱም ወደተወለደበት ቀዬ በመመለስ ከወገኖቹ ዘንድ የመጨረሻውን ረፍቱን ለማየት በመቀላቀል ያርፋል ፤ ከዚህ ዝሆን ጋር የሚዛመዱ ሁሉም በመምጣት ይህን እረፍቱ የቀረበን ዝሆን እየዞሩ የመጨረሻ ሽኝት ያደርጉለታል ፤ ዝሆኑም በስተመጨረሻ ያርፋል›› በማለት እርሱም የመጨረሻ ስንብቱ ሥሩ ከተመዘዘበት ከገሞ ጎፋ ፤ እሱን የሚያውቁት እሱም የሚያውቃቸው ሰዎች ዘንድ እንዲደረግ በምሳሌ ተናግሮ ነበር ፤ ዛሬም የምንወደው እና የሚወደን አቶ አሰፋን ከአሁን በኋላ ጽሑፉን ጽፎ ላያስነብበን ፤ ሀሳቡን ላያካፍለን ሸኝነው፡፡

የሕይወት ታሪክ ተነቦ ካለቀ በኋላ አስከሬኑ አውደ ምህረት ላይ የመጨረሻውን ስንብት ሦስት ጊዜ ካሳለሙት በኋላ ወደ ተዘጋጀለት ማረፊያ አመራ፤ ሳጥኑ እጅግ እንደሚከብድ የሚታወቀው ቀብር አስፈጻሚዎች ፊታቸው ሲታይ ነው ፤ አሰፋ ሀሳቡ ለአምባገነኖች ከዚህ በላይ እንደሚከብድ ማን በነገራቸው!!! ፤ በዚህ ወቅት እመቤት (ብቸኛ ሴት ልጁ) አሰፋን ለሚያውቀው እጅግ ውስጥን የሚረብሽና እንባን የሚያራጭ ቃላት እተናገረች ታለቅስ ነበር ‹‹ አሴ እረፈው… አሁን እረፈው ፤ ታሳሪው ስደተኛ አባቴ እረፈው ፤ አሁን እረፍ ፤ አሴ በቃ ዝም አልክ … በቃ…..በቃ… ›› አንድ ትልቅ የቀዬው ተወላጅ የኃይለሥላሴን ፤ የመንግሥቱን እና የመለስ ዜናዊን ስም መሀል መሀል በማስገባት ከቋንቋቸው ጋር በመቀየት ሀዘናቸውን ሲገልጹ ነበር( ትርጉሙን ማወቅ አልቻልኩም)… በክብር የአሰፋ ቻቦ አስከሬን ወደተዘጋጀለት ኪስ ሳጥን አመራ ፤ መንገዱ በመኪና በመሙላቱ ማቋረጡ አስቸጋሪ ነበር ፤ በካቴድራሉ በስተቀኝ በኩል ህዳር 14  1967 በግፍ በደርግ የተገደሉ የኃይለስላሴ ባለስልጣናትን በጎን ትቶ ከግቢው በመውጣት ካቴድራሉ ባሰራው አዳራሽ አመራ ፤ በጊዜው በአዳራሹ የሰርግ ስነ ስርዓት ለማከናወን ተጋባዥ እንግዶች ጸአዳ ልብስ ለብሰው ወደ አዳራሽ እየገቡ ነበር ፤ አቶ አሰፋ ደግሞ እጅግ ለደከመላት በአይነ ሕሊናው ተሰውራ ለማታውቀው ፤ በሕልሙ ለምትመላለስበት ፤ ከየትም ሀገር ጋር ለማያወዳድራት ውብ ለሆነችው ፤ እስራቷን ሽልማት አድርጎ ለተቀበላት ፤ እስከ እለተ ሞቱ ለሚወዳት ሀገሩ ‹‹ኢትዮጵያ›› ደክሞ ሊያርፍ ወደ አዳራሹ የታችኛው ክፍል እያመራ ነበር ፤ ሰርገኞቹ አቶ አሰፋን አከበሩት ዝምም አሉ ፤ አሰፋን በገሞ ባሕላዊ ልብስ ፤ በጥቁር ልብስ እና በሰርገኞች ጸአዳ በሆነ ልብስ በለበሱ ተሸኝ ፤ እኛም አሰፋን ይዘን ከዘላለማዊ ማረፊያው ገባን ፤ በርካታ (60×60) የሆኑ አስከሬን ማሰረፊያ ኪሶች ውስጥ በስተቀኝ በኩል ስምንተኛው column አራተኛው ረድፍ ላይ የሳጥን ቁጥ 104 ላይ አሳረፍነው ፡፡ ሳጥኑን ወደ ኪሱ ለማስገባት ቀብር አስፈጻማቹ ቢሞክሩም እንደ ሀገሩ ማረፊያ ቀዳዳዋ እምቢ አለች ፤ በሦስት ሆነው እጅግ ገፍተው ወደ ኪሱ ሳጥኑን አስገቡት ፤ አሰፋ በሕይወት እያለ ሀገሩ ለመግባት እጅግ ይፈልግ ነበር ፤ በስተመጨረሻ ግን ለሰው ዘር የማይቀረው ሞት ገፍቶ ሀገሩ ላይ አሳረፈው ፤ በዚህ ሰዓት እመቤት እጅግ እያለቀሰች ነበር ፤ ሰዎችም ተይ ሊሏት ሲሞክሩ ፤ የቅርብ ሰዎች ደግሞ ‹ተዋት ታልቅስ› ብለው ሰዎችን ገለል አደረጉላት ፤ ሁኔታውን ላይ እጅግ አሳዛኝ ሁኔታዎች ነበሩ ፤ እኛስ ዛሬ ለአሰፋ ካላለቀስን መቼ ልናለቅስ ኖሯል?.. እሱ በሕይወት እያለ ‹አልቅሳችሁ እንዳትቀብሩኝ› ቢልም እኛ ግን ስላደረገው ሥራ ሁሉ ፤ ስለወጣው ፤ ስለወረደው ፤ ስለታሰረው ፤ ስለተሰደደው ፤ በስደት ላይ ሳለ ስለብቸኝነት ሕይወቱ …ሁሌም ሀገሬን ..ሀገሬን …ሀገሬን ማለቱን እያስታወስን አልቅሰን ቀበርነው …

ወንድማቸው ‹፣እኔ ለአሰፋ አላለቅስም ፤ ይህን ሁሉ ልጅ ወልዶ ነው የሞተው ፤ እኔ እናንተን በማየቴ ደስተኛ ነኝ ..አላለቅስም›› ብለዋል ፡፡ በቀብር ስነ ስርዓቱ ላይ የመጡትን ሁላ በደከመ የሀዘን ድምጽ እጃቸውን ወደ ላይ በማድረግ አመስግነዋል ፤ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስም በስተመጨረሻ ላይ ዘመድ አዝማድ ጋር በመጠጋት ‹‹አሰፋን እኛ ነው ያጣነው›› በማለት ተናግረዋል ፤ ሻለቃ ፍቅረ ስላሴ ወግደረስም  ቤተሰቦችን አጽንተዋል ፤ የውጭ ጋዜጠኞች ወደፊት በአሰፋ የሕይወት ታሪክ ላይ ዘጋቢ ነገር ለመስራት በማሰብ የቤተሰቦችን ስልክ ቁጥሮች ሲቀበሉ ፤ የቀድሞ ‹‹ጦቢያ›› ላይ ሲጽፉ የነበሩ ጋዜጠኞችም በወቅቱ ራሳቸውን ለቤተሰብ በማስተዋወቅ ሲያጽናኑ ነበር፡፡

አሰፋ ሀገሪቱ ዲሞክራሲያዊ ፤ ፍትህ የሚከበርባት ፤ ፍትህ ርትዕ የነገሰባት ፤ የብሔር ብሔረሰቦች መብት የተከበረባት ሀገር እንድትሆን የቻለውን ያህል ጡብን ከሲሚንቶ እያገናኝ ሀገር ለመገንባት ጥሯል ፤ ከጸጉር የሚበዙ ጠላቶች እያሉት ‹እኔ ጠላት የለኝም› ብሏል ፤ ጋሞነቱ ከኢትዮጵያዊነቱ ጋር ሳይጋጩ አብሮ እስከ ሕልፈቱ ድረስ አዝልቋቸዋል ፤

ጋሽ አሴ ሦስት መንግሥታትን ከተማሪነታቸው ጊዜ አንስቶ ተመልክቷል ፤ ለሁሉም ውስጡ ያመነበትን ለሀር ለወገን ለሕዝብ የሚጠቅመውን አካሔድ በቃል በጽሑፍ አመላክቷል ፤ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምሕርት በጀመረበት ወቅት ቀን ቀን በትምህርት ማታ ማታ ደግሞ በሲቪል አቪኤሽን ባለስልጣን የበረራ መቆጣጠሪያ ክፍል ውስጥ አገልግሏል ፤ ሀገርን በመወከል አለም አቀፍ ካሉ የትምህርት ተቋማት ጋር በመወዳደር ከንጉሡ ሥጦታ ተበርክቶለታል ፤ የወጡበት ማሕበረሰብን ወግ ልማድና ባሕል ከኢትዮጵያዊነት ጋር አንድ በማድረግ አንዱ ከአንዱን ሳይውጥበት ጋሞነትን በኢትዮጵያዊነት ጥላ ሥር በማድረግ ስለ ሀገሩ ብዙ ጽፏል ፤ ተናግሯል ፤ ሀሳብ አካፍሏል፡፡ እንዲህ ብሎ ኖረ ‹‹..እኔ ጋሞ ነኝ፡፡ እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ፡፡ ሁለቱ ተጣልተው ለማሥታረቅ ተቀምጬ አላውቅም፡፡›› ዛሬ ግን የመጨረሻ ቀን ደርሶ ወደማያልፈው የሰው ልጆች ሁላ መጨረሻ የሆነውን የሞት ጽዋ በመጎንጨት እስከ ሞት ሀገሩን ታምኗት  ላይመለስ ጋሽ አሴ አልፏል፡፡ አንድ ሰው እንዲህ አለ ‹‹ሰውየው ያገር ታቦት፤ የታሪክ ፅላት ነው፡፡››

እንደ ግንበኛ ጡብን ከሲሚንቶ በማገናኝት የአቶ አሰፋ ጫቦን ማረፊያ የconcrete ሳጥን በር የመጨረሻዋን ጡብ በማቀበል በመንበር ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን እንዲህ አድርገን ሸኝተነዋል..፡፡

ዛሬ አዝኛለሁ…

ከአክሊሉ ሀብተወልድ

Photo 1 and 2  Guangul Teshager J  Fb.

መንግስት ረሃብ የለም- “ሌሎች እንዴት እንደሚታያቸው አላውቅም እንጂ እኛ አካባቢ ድርቁም ከፍተኛ ነው ረሀብም አለ”

በኢትዮጵያ ድርቅ መከሰቱ በይፋ ከተገለፀ አራት ወራት አስቆጥሯል። እስካሁን የሞተ ሰው ሪፖርት ባይደረግም ድርቁ ግን ከፍተኛ በመሆኑ 7.8 ሚሊዮን ሕዝብ ለምግብ እጥረት መጋለጡና እንስሳት መጨረሱ ይፋ ተደርጓል። መንግሥት ድርቁን ለመቋቋምና እርዳታውን በአግባቡ ለማዳረስ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑን በመግለጽ “ረሃብ” የለም ይላል። የነገሌ ቦረና ነዋሪ በበኩላቸው“ሌሎች እንዴት እንደሚታያቸው አላውቅም እንጂ እኛ አካባቢ ድርቁም ከፍተኛ ነው ረሀብም አለ” ይላሉ።

በአፍሪካ በተለይ ደግሞ በአፍሪካ ቀንድ ቆላማ አካባቢዎች ከዚህ ቀደም ካጋጠመው ሁሉ የከፋ ድርቅ በዚህ ዓመት ተከስቷል። እንደ ደቡብ ሱዳን እና ሶማሊያ ባሉ ሀገሮች ጦርነት እና ግጭት ሁኔታውን አባብሶ “ረሀብ” ገብቷል። ከምግብ እጥረቱ በተጨማሪ በውሃ እጥረትና በበሽታ ሰዎች መሞት ጀምረዋል።

በሶማሌ ክልል በዋርዴር ወረዳ በድርቁ የተጎዱ ሰዎች የምግብና የውሃ ርዳታ እየጠበቁ

በሶማሌ ክልል በዋርዴር ወረዳ በድርቁ የተጎዱ ሰዎች የምግብና የውሃ ርዳታ እየጠበቁ

ለዚህም ወደ 1 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ እንደሚያስፈልግ እና ከለጋሾች የተገኘው ምላሽ አጥጋቢ ባለመኾኑ የፌደራል እና የክልል መንግሥታት በጋራ ሆነው በድርቁ ለተጎዱ ሰዎች የዕለት ደራሽ የምግብ ርዳታ እያቀረቡ መሆኑን የብሔራዊ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽንና ከመንግሥቱ ጋር በጋራ የሚሠሩ የሰብዓዊ ረድኤት ድርጅቶች በተለያየ ጊዜ ለአሜሪካ ደምጽ ተናግረዋል።

አቶ ጉዩ ሃለኬ በቦረና ዞን ዱብሉቅ አካባቢ የሚኖሩ አርብቶ አደር ናቸው። የዚህ ዓመት ድርቅ አካባቢያቸውን ማድረቅ ከጀመረ ከጥር ወር ጀምሮ ከብቶቻቸው እንዳለቁባቸው ነግረውን ነበር።አቶ ጉዩ በጥር ወር ስናነጋግራቸው ከ30 ከብት ዐሥር እንደሞተባቸውና ሃያ እንደቀራቸው ገልፀው ሁሉም ያልቁብኛል የሚል ስጋት እንዳላቸው ተናግረው ነበር።

ከአራት ወራት በኋላ ስንጠይቃቸው “ሃያ ስምንት ሞተው ሁለት ቀርተውኛል። ይኸው ዛሬ አንዱ ሞቶብኝ አውጥቼ ጣልኩት።” ብለዋል።አቶ ጉዩን እርሳቸና ቤተሰቦቻቸው የሚመገቡት ስንዴና በቆሎ በእርዳታ ቢያገኙም ከብቶቻቸውን ግን ከሞት የሚታደጉበት ምንም ነገር እናዳላገኙ ይናገራሉ።

ባልደረባችን እስክንድር ፍሬው ወደ ሶማሌ ክልል ኮርኔ ዞን ኩትንብ ወረዳ ተጉዞ ያገኛቸው አቶ አብዱላሂ ካሊፍ ከነበሯቸው 100 ፍየሎችና 250 ግመሎች የበዛውን በድርቅ አጥተው 50 ብቻ እንደቀራቸው ተናግረዋል።

ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ በድርቁ የተከሰተው የእንስሳት ሞት ከፍተኛ እንደሆነ ገልፀው የቀሩትን ለማትረፍ ርብርብ እየተደረገ እንደሆነ ይናገራሉ።በደቡብ ክልል ድርቁ በተከሰተበት አካባቢ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ ነዋሪ እየተሰጣቸው ያለው እርዳታ በቂ እንዳልሆነ ገልፀው የእንስሳት ሞት በብዛት እንዳለ ይናገራሉ።

“ገጠር አካባቢ ያሉ ሰዎች ድንች ከመሬት ውስጥ እየቆፈሩ ይበላሉ። እንስሳት ግን እንዳለ እያለቀ ነው፡” ይላሉ።ድርቁ ከተከሰተባው አንዱ አማራ ክልል ዋግምራ አካባቢ ነው። በዚህ አካባቢ ውርጭ፣ በረዶና ጎርፍ በመከሰቱ አሁን የጨመረው የተጎጂዎች ቁጥር ይህን አካባቢም እንደሚያካልል ተነግሯል። በዚህ አካባቢ ነዋሪ የሆኑና ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ነዋሪ ከሁለት ወር በፊት ስለ መኖሪያ ቀያቸው ጠይቀናቸው “እኛ አካባቢ ትልቁ ችግር የመሬት ጥበት ነው” ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተውን ነበር።

በባሌ ዞን በዳሎመና ነዋሪ የሆኑና ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ነዋሪ በባሌ ዞን ብሔራዊ ፓርክና በአቅራቢያው ያሉ ዞንና ወረዳዎች በድርቅ መጎዳታቸውን ደንና የውሃ ኩሬዎች በአሳዛኝ ሁኔታ መድረቃቸውን ተናግረዋል። የሥራ አጥ ቁጥር መጨመሩንም ገልፀዋል። እንዲህም ሆኖ ከፌደራል መንግሥትና ከለጋሾች የሚመጣው ርዳታ በአግባቡ እንደማይሰጣቸው ይናገራሉ።

ድርቁ ይፋ ከተደረገበት ከታኅሣሥ ወር ጀምሮ የግጦሽ መሬትና የውሃ ኩሬዎችን ጭርሱኑ ማድረቁን፣ የአርብቶ አደሮች የኑሮ መሰረት የሆኑትን እንስሳት መጨረሱ ሲዘገብ ቆይቷል። ሥራ ማጣት፣ መፈናቀል እና ተማሪዎች ከትምሕርት ገበታቸው መፈናቀል ተዘግቧል።

በአንፃሩ ኮሚሽኑ የተፈናቀሉት ሰዎች ውሃ ፍለጋ ከቦታ ቦታ የተዘዋወሩ ናቸው ይህ ደግሞ ተረጂዎቹን በአንድ ቦታ አግኝቶ ለመርዳት ያግዛል ብሏል። ተማሪዎቹም በምገባ ፕሮግራም ወደ ትምህርት ገበታቸው እንደተመለሱ ይገልፃል።

ከእነዚህ መግለጫዎች በኋላ ኮሚሽኑ እና የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ማስተባበሪያ ቢሮ (UNOCHA) ለቪ.ኦ.ኤ እንዳስታወቁት የተጎጂዎች ቁጥር በመጨመሩ የሰብዓዊ እርዳታ መጠየቂያው ሰነድ (HRD) ተከልሷል።

የተረጂዎች ቁጥር በ2.2 ሚሊዮን ጨምሮ 7.8 ሚሊዮን ሆኗል። ይህ የኾነው ደግሞ አስቀድሞ ለ5.6 ሚሊዮን ሕዝብ የተፈለገው 1 ቢሊዮን ዶላር ሳይገኝ ነው።

የብሄራዊ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ እንደተናገሩት፤ “እስካሁን ከዚህ ገንዘብ የተገኘው የአሜሪካ መንግስት በዓለም አቀፍ የምግብ ፕሮግራም (WFP) እና በጃይንት ኢመርጀንሲ ኦፕሬሽን አማካኝነት የሰጡት 114 ሚሊዮን ዶላር ነው።” ብለዋል።

የኮሚሽኑ ኃላፊ መንግሥት ድርቁን ለመቋቋም እየሠራ መሆኑን ርዳታውንም በአግባቡ ለማዳረስ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ነው ይላሉ። “ረሃብ” የለም ሲሉም ይከራከራሉ፡ ስማቸውን መጥቀስ ያልፈለጉ የነገሌ ቦረና ነዋሪ “ሌሎች እንዴት እንደሚታያቸው አላውቅም እንጂ እኛ አካባቢ ድርቁም ከፍተኛ ነው ረሀብም አለ” ይላሉ”

ለጋሽ ድርጅቶች በቀጣይ ተመጣጥኝ ዝናብ ካልዘነበና የተጠቀሰው ገንዘብ መገኘት ካልቻለ አደጋው ከፍተኛ ሊሆን እንደሚችል ሥጋታቸውን ከወዲሁ እየገለጹ ነው።የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ እስካሁን አጥጋቢ እርዳታ ባይገኝም የፌደራል እና የክልል መንግሥታት በጀት መድበው እርዳታ እያደረጉ ነው ብሏል።

ስለ ሰብዓዊ ጉዳዮች የዜና ትንታኔ እና ዘገባ በማቅርብ የሚታወቀው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዜና ወኪል (ኢሪን) በኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ እንደ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ጦርነትና የእርስ በእርስ ግጭት የመሳሰሉ አባባሽ ምክንያት ባይኖሩትም “አደጋው ግን ቀላል አይደለም” ብሏል።

በኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት በተከሰተው ድርቅ 10.2 ሚሊዮን ሕዝብ ለምግብ እጥረት ተጋልጦ እንደነበር ይታወሳል።

VOA Amharic  ጽዮን ግርማ

የሥነ ዜጋና ሥነ ምግባር ትምህርቱ ውድቀት፤ “ተማሪዎች የብሄራዊ አገልግሎት ቢሰጡ (National Service) ” ከመፍትሄው ሃሳቦች አንዱ ሆኗል

የሥነ ዜጋና ሥነ ምግባር ትምህርት ከአምስተኛ ክፍል ጀምሮ እስከ ዩኒቨርሲቲ  ድረስ መሰጠት ከጀመረ ከአሥር ዓመታት ያላነሰ ጊዜ አስቆጥሯል፡፡ በእነዚህ ዓመታት ግን ትምህርቱ በተማሪዎች ላይ ያመጣው ለውጥ እዚህ ግባ የሚባል አልሆነም፡፡ ትምህርቱ ሲታቀድ ብቁ፣ አገር ገንቢና በሥነ ምግባር የታነፀ ዜጋ ለመፍጠር ታልሞ የነበረ ቢሆንም፣ የታለመለትን ግብ ሳይመታ ቀርቷል፡፡ የትምህርቱ ውድቀት ከምን የመነጨ ይሆን?

በዜግነት ግንባታና በሥነ ምግባር ላይ አተኩሮ በትምህርት ሚኒስቴርና በፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል ጥናት የተሠራ ሲሆን፣ የጥናቱ ዓላማም ትምህርቱ መሰጠት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በተማሪዎች ላይ ምን ለውጥ አምጥቷል? የታሰበውን ያህል ነው ወይ? ለውጥ ካልታየ ችግሮቹ ምንድን ናቸው? ለሚሉት ጉዳዮች ምላሽ ለማግኘትና የመፍትሔ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ነበር፡፡

በጥናቱ የአማራ፣ የትግራይ፣ የኦሮሚያ፣ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦችና የሱማሌ ክልሎች እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተካተቱ ሲሆን፣ ያካለላቸው የትምህርት ደረጃዎችም ከአምስተኛ ክፍል እስከ ዩኒቨርሲቲ ድረስ ነው፡፡

የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል ተመራማሪው አቶ ሔኖክ ሥዩም አሰፋ እንደሚሉት፣ ትምህርቱ የሥነ ዜጋና ሥነ ምግባር ተብሎ ይሰጥ እንጂ አብዛኛው ትኩረቱ በዜግነት ጉዳዮች ላይ ነው፡፡ ለሥነ ምግባር የተሰጠው ትኩረት አናሳ ስለመሆኑም ለ11ኛ ክፍል ለሥነ ዜጋና ሥነ ምግባር ትምህርት በዓመቱ የተሰጠው ክፍለ ጊዜ 95 ሆኖ ከእነዚህ ሥነ ምግባር ነክ ጉዳዮችን ለማስተማር የተመደበው ክፍለ ጊዜ ሁለት መሆኑን ማየት ብቻ በቂ ነው፡፡ ይህ ከይዘት አንፃር ለሥነ ምግባር በቂ ትኩረት እንዳልሰጠው ያሳያል፡፡ ሥርዓተ ትምህርቱ ለሥነ ምግባር ትምህርት ትኩረት ካለመሰጠቱም በተጨማሪ ተማሪዎችን በሥነ ምግባር የሚያንፅ ይዘት የለውም፡፡

ከአምስተኛ እስከ 12ኛ ክፍል የሚሰጠው ትምህርት ድግግሞሽ ያለበት መሆኑ ሌላው ክፍተት ሲሆን፣ ይህም ለተማሪዎቹም ሆነ ለመምህራኑ አሰልቺ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ትምህርቱ 11 እሴቶች ሲኖሩት፣ አንዳንዱ እሴት ከክፍል ክፍል ሰፋ ሲል፣ አንዳንዴ ደግሞ ራሱ የሚደገምበት ጊዜ ተስተውሏል፡፡

ትምህርቱ የታለመው አገሩን ገንቢ በሥነ ምግባር የታነፀ ዜጋ ለመፍጠር ቢሆንም፣ በመጽሐፉ ላይ ያለው አቀራረብና መምህራን የሚያስተምሩበት መንገድ ዓላማውን ሊያስጠብቅ በሚችል መንገድ አይደለም፡፡ መምህራኑ እንደማንኛውም ትምህርት ዕውቀት ላይ መሠረት አድርገው ያስተምራሉ እንጂ ይህ ትምህርት የተማሪዎች የዜግነትና የሥነ ምግባር ቀረፃ ነው ብለው ትምህርቱ በሚፈልገው ትኩረት ልክና ክህሎት በሚያበለፅግ መልኩ የማያስተምሩ መሆኑም ታውቋል፡፡ ተማሪዎችም ትምህርቱን የሚማሩት ፈተና ለማለፍ እንጂ እንደ ሕይወት ክህሎት ከመቁጠር አንፃር አይደለም፡፡

የሥርዓተ ትምህርቱ አተገባበር ወጥ አለመሆን ሌላው ችግር ነው፡፡ ይህ በተለይ በዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች ውስጥ ታይቷል፡፡ ትምህርት ሚኒስቴር ሒደቱ በምን መልኩ መተግበር እንዳለበት ደረጃ ያወጣ ቢሆንም፣ ወጥ የሆነ የሥርዓተ ትምህርት ትግበራ የለም፡፡ አንዳንድ የሥነ ዜጋ ትምህርት መምህራን የሚያስመርቁ ኮሌጆችም ሕገ መንግሥት ነክ ጉዳዮችን አያስተምሩም፡፡ ሆኖም በቂ ክህሎት ይዘው ያልወጡ መምህራን፣ ሕገ መንግሥት እንዲያስተምሩ ይጠበቃል፡፡

የሥነ ዜጋንና ሥነ ምግባር ትምህርትን የሚያስተምሩ መምህራን የታሪክ፣ የጂኦግራፊ ወይም የቋንቋ ተማሪዎች ናቸው፣ ይህም ችግር ፈጥሯል በሚል ከጥናቱ ቀድሞ በነበረ መድረክ የተወሳ ሲሆን፣ ጥናቱም በዘርፉ ከተመረቁ መምህራን እጥረት ጋር አያይዞ እንደ ክፍተት አስቀምጦታል፡፡ በዘርፉ የተመረቁ መምህራን ቢኖሩም ትምህርቱን ከሕይወት ክህሎት ጋር አያይዘውና ለዜጎችና አገር ግንባታ ሒደት ዋና ምሰሶ አድርገው የማየት ችግርም ተስተውሏል፡፡

ከተለያየ ትምህርት መጥተው ሥነ ዜጋና ሥነ ምግባር እንዲያስተምሩ የሚመደቡ መምህራን ምን ያህል ፍላጎት አላቸው? ብቃትስ? የሚለው ሳይታይም እንዲያስተምሩ ይገደዳሉ፡፡ እንደምሳሌ የተነሳውም፣ አንድ የጂኦግራፊ መምህር በሳምንት መያዝ የሚገባው የትምህርት ክፍለ ጊዜ ካልሞላ ክፍለ ጊዜውን ለመሙላት ሥነ ዜጋና ሥነ ምግባር እንዲያስተምር ይደረጋል፡፡ ይህም ተገቢ ትኩረት እንዳልተሰጠው የሚያሳይ ነው፡፡

በአመራሩ፣ በመምህሩ፣ ሌሎች ትምህርቶችን በሚያስተምሩ መምህራን፣ በተማሪዎችና በኅብረተሰቡ ዘንድ ለትምህርቱ ያለው አመለካከትም ችግር አለበት፡፡ በጥናቱ እንደታየው፣ አንዳንድ መምህራን ትምህርቱን የፖለቲካ ማስፈጸሚያ መሣሪያ አድርገው ይወስዱታል፡፡ አንዳንዶቹ የገዢው ፓርቲ ጭልጥ ያሉ ደጋፊዎች ይሆኑና የፓርቲውን አመለካከት ማስተማሪያ አድርገው ያንን ይሰብካሉ፡፡ አንዳንዶች ደግሞ በተቃራኒ ጎራ ሆነው የገዢውን ፓርቲ የሚያጥላሉና የሌላ አስተሳሰብና የግል ፖለቲካ አጀንዳን የሚያራምዱ አሉ፡፡ በአመራሩ አካባቢ መምህራንን የሌላ ፓርቲ ሐሳብ አራማጆችና ተማሪዎችን የሚያነሳሱ አድርጎ የማየት ችግሮችም አሉ፡፡ ኅብረተሰቡ ደግሞ መምህራኑን የገዢው ፓርቲ የፖለቲካ አመለካከት አራማጆች አድርጎ ያያቸዋል፡፡ በዚህም የዘርፉ መምህራን ከሁሉም ያጡ መሆናቸው ታይቷል፡፡

ለምን ይህ ተከሰተ፣ ስንል የጠየቅናቸው አቶ ሔኖክ፣ የትምህርቱን ይዘት ባዩበት ወቅት ለአገራዊ ጉዳዮች ብዙ ትኩረት ያልሰጠ፣ ንድፈ ሐሳብ ላይ ብቻ ያተኮረ፣ በአገራችን ታሪካዊ ጉዳዮችና ነባራዊ ሁኔታዎች ላይ ብዙም ያላተኮረና ጠቅለል ያለ ነገር ይዞ የአገርን ጉዳይ የዘነጋ፣ ድግግሞሽ የበዛበትና ምሳሌዎቹም የሌሎች አገሮች ተሞክሮዎች መሆናቸው እንደ ምክንያት እንደሚጠቀስ ገልጸዋል፡፡

የሥነ ዜጋና ሥነ ምግባር ትምህርት ከትምህርት ጥራት ማስጠበቂያዎች አንዱ ፓኬጅ ቢሆንም፣ ይህን የሚመጥን አወቃቀርና ሥርዓት አልተዘረጋለትም፡፡ ለዚህም በትምህርት ሚኒስቴር የሥነ ዜጋና ሥነ ምግባር ትምህርትን የሚከታተል አደረጃጀት አለመኖሩ፣ የሚመራው በሥርዓተ ትምህርት ዳይሬክቶሬት ሥር በአንድ ኤክስፐርት መሆኑ፣ በክልሎችም አንድ፣ አንድ ሰው ብቻ መመደቡና በዞንና በወረዳ ደረጃዎች ምንም ተወካይ አለመኖሩ ማሳያዎች ናቸው፡፡

የዜገችን ሥነ ምግባር የመገንባት ሒደት ብዙ አካላትን የሚያሳትፍ ቢሆንም፣ የሚመለከታቸው አካላት ተሳትፎ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡ ተማሪዎችን በአሉታዊ መንገድ ሊቀርፁ በሚችሉ በርካታ ምክንያቶች የተከበቡ ትምህርት ቤቶችና ተቋማት ባሉበት ሁኔታ አዎንታዊ ተፅዕኖ ፈጥሮ ትምህርት ቤቶችን ከውጫዊም ሆነ ከውስጣዊ አሉታዊ ተፅዕኖ ነፃ ያወጣ የለም፡፡ ከዓመታት በፊት ጀምሮ በተለያዩ መድረኮች የተማሪዎች ሥነ ምግባር እየጠፋ ነው በሚል በተደጋጋሚ ቢነገርም፣ ጆሮ ዳባ ልበስ ተብሏል፡፡ በምርምር ተቋሙ የተሠራው ጥናትም ተማሪዎችን በሥነ ምግባር በማነፅ ሥራው የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ እዚህ ግባ የማይባል እንደነበር ጠቁሟል፡፡

በትምህርት ቤት የተማሪዎች ዜግነትና ሥነ ምግባር ጉዳይ ትምህርቱን ለሚያስተምረው መምህር የተተወ ነው፡፡ በተማሪዎች ዘንድ ጉድለት ሲታይ ጣት የሚቀሰረውም በመምህሩ ላይ ነው፡፡ በትምህርት ቤት የወላጅ፣ መምህርና ተማሪዎች ኮሚቴ ቢኖርም፣ ከአስተዳደራዊና ትምህርት ነክ ጉዳዮች ውጭ የሥነ ምግባር ጉዳይ አጀንዳቸው አይደለም፡፡  ወላጆችም ስለልጆቻቸው የትምህርት ቤት ውሎ የማወቅ ፍላጎታቸው አናሳ ነው፡፡

መገናኛ ብዙኃን ያላቸው ተፅዕኖ ከባድ ቢሆንም፣ በሥነ ምግባር ላይ የሚጫወቱት ሚና ከሚጠበቀው ያነሰ ሆኖ በጥናቱ ተገኝቷል፡፡ በሥነ ዜጋና ሥነ ምግባር ላይ ያተኮሩ ፕሮግራሞችን ማሠራጨት ማኅበራዊ ኃላፊነት ቢሆንም፣ ክፍተት ታይቷል፡፡ በጽሑፍም ሆነ በድምጽና ምስል የሚተላለፉ ጉዳዮች ከሥነ ምግባር አንፃር የሚያሳድሩት ተፅዕኖም በሚፈለገው መጠን ሲፈተሽ አይታይም፡፡ ይልቁንም የወጣቶችን ሥነ ምግባር የሚፈታተኑ አንዳንድ ፕሮግራሞች ይተላለፋሉ፡፡

ከሥነ ምግባር አንፃር ኩረጃ አንገብጋቢ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በተለይ ስምንተኛ፣ አሥረኛና 12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናዎች ላይ የአካባቢ መስተዳድሮች፣ የትምህርት ቤቶች ርዕሰ መምህራን፣ መምህራን፣ ወላጆችና ፈታኞች ተደራጅተው የሚሠሩትና ሥር እየሰደደ የመጣ ችግር ሆኗል፡፡ ጥቂት ቢሆንም መምህራን ለተማሪዎች መልካም አርዓያ ሆነው አለመገኘት፣ ጠጥተው መምጣትና ከትምህርት ቤት ውጪ በተማሪዎቻቸው ፊትና አብረውም ጫት የሚቅሙ፣ ሴት ተማሪዎችን የሚተነኩሱ፣ ውጤት ላይ በሃይማኖትና በአካባቢ ተሳስረው አድልኦ የሚፈጽሙ ተስተውለዋል፡፡

ትምህርት ቤቶች ለመማር ማስተማሩ ሒደት ምቹ ናቸው ወይ? ለተማሪዎች ብቁ የትምህርት መረጃ ያቀርባሉ ወይ? ተማሪዎች በትምህርት ቤቱ ውስጥ ደስ ብሏቸው ራሳቸውን በሚገነቡበት ሁኔታ እንዲያሳልፉ ምቹ ናቸው ወይ? ሲባልም፣ አብዛኞቹ ትምህርት ቤቶች እነዚህን አሟልተው አልተገኙም፡፡ ከሁሉ የከፋው ደግሞ በትምህርት ቤቶች ዙሪያ ያለው ሁኔታ ነው፡፡

 የተማሪዎችን ጊዜ የሚሻሙ፣ ወደ ሱስ የሚስቡ ሁኔታዎች በየትምህርት ቤቱ ደጃፎች መታየት፣ ተማሪዎችም የዚህ ሰለባ መሆን ፀሐይ የሞቀው እውነት ነው፡፡ ጥናቱም ትምህር ቤቶች በቁማርና በሺሻ ቤቶች እንዲሁም በጫት መቃሚያዎች የተከበቡ ቢሆንም፣ እነዚህን ለማዘጋት በደረገ ጥረት የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ በሚፈለገው ልክ አለመሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ከዚህ ቀደም ሴት ተማሪዎችን እየደለሉና በችግሮቻቸው እየገቡ ለወሲብ መጠቀሚያ ማድረግ እንደችግር ተነስቶ ነበር፡፡ ዛሬ ላይ ችግሩ አይሎ ለሴት ተማሪዎች ምግብና መጠጥ በነፃ በማቅረብ ሀብታም ወንዶችን በሴት ተማሪዎቹ መሳብ ተጀምሯል፡፡ አቶ ሐኖክ እንደሚሉትም፣ የጥናታቸው ግኝት ይህንን አመላክቷል፡፡ አንዳንድ ቦታ ላይ ሴት ተማሪዎች በሳምንት ሁለት ቀን ተመርጦ በነፃ የሚጋበዙበት፣ በነፃ መጠጥና ምግብ የሚቀርብበት ሆቴል ድርጅት በጥናቱ ታውቋል፡፡ የድርጅቱ ዓላማም ሀብታም ወንዶችን በሴቶቹ አማካይነት መሳብ ነው፡፡

ጥናቱ እንደ አጠቃላይ ያስቀመጠውም፣ ከአሥር ዓመት በላይ ያስቆጠረውና ከአምስተኛ ክፍል እስከ ዩኒቨርሲቲ ድረስ የሚሰጠው የሥነ ዜጋና ሥነ ምግባር ትምህርት ውጤት አለማሳየቱን ነው፡፡

ይህ ምን ያመላክታል?

የሥነ ዜጋ ትምህርቱ ተማሪዎች ስለዜግነት ያላቸውን ግንዛቤ በንድፈ ሐሳብ ደረጃ ከፍ አድርጓል፡፡ ተሟጋች ዜጋ ለመፍጠርም አስችሏል፡፡ ነገር ግን መብት የመጠየቅን ያህል፣ ግዴታ መኖሩን መገንዘብ ላይ ክፍተት አለ፡፡ መብቱን ያወቀ ግዴታውን የዘነጋ ግማሽ ጐፈሬ ዓይነት ተማሪ ተፈጥሯል፡፡ ኃላፊነትን ለመውሰድ ዳተኛ የሆነና በኃላፊነት መንፈስ ብዙም የማይንቀሳቀስ ተማሪ ከመፍጠሩም አንፃር ትምህርቱ ውጤት አላመጣም ማለት ይቻላል፡፡

ትምህርቱ ጥሩ ሥነ ምግባር ያላቸውን ተማሪዎች ለማፍራት የታቀደ ቢሆንም፣ የጥናቱ ውጤት ያሳየው ያልተዘራውን እንደማጨድ ነው፡፡ ጥሩ ሥነ ምግባር ያለው ዜጋ ማፍራት ተብሎ የተቀመጠውና አብዛኞቹ ዓላማዎችም አልተሳኩም፡፡ ተማሪዎች በሥነ ዜጋና ሥነ ምግባር ትምህርት ብሔራዊ ፈተና ላይ ትልቅ ውጤት የሚያስመዘግቡ ቢሆንም፣ መሬት ወርዶ በተግባር አይታይም፡፡

ምን መደረግ አለበት?

የሥነ ዜጋና ሥነ ምግባር ትምህርት ዓላማውን ማሳካት በሚችልበት መልኩ ሊከለስ ይገባዋል የሚለው የጥናቱ የመፍትሔ ሐሳብ ነው፡፡ ትምህርት የሚሰጥበት መንገድ ከንድፈ ሐሳብ በዘለለ ክህሎት የሚዳብርበት፣ መምህራን ሥልጠና ማግኘት የሚችሉበት እንዲሆንም ጥናቱ ጠቁሟል፡፡

ትምህርቱን የሚመራ በቂ መዋቅር ማዘጋጀት ጥናቱ መደረግ አለባቸው ብሎ ካስቀመጣቸው ውስጥ ሲሆን፣ ከዚህ በተለየ መልኩ ደግሞ ተማሪዎች ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት እንደጨረሱ በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ ብሔራዊ አገልግሎት (National Service) መስጠት የሚችሉበት ሥርዓት ቢዘረጋ የሚለው ይገኝበታል፡፡ ብሔራዊ አገልግሎ ለዜግነትና ለሥነ ምግባር ግንባታው ጉልህ ሚና ይኖረዋል ተብሎም ይታመናል፡፡

ምሕረት ሞገስ’s blog  ሪፖርተር

“ቁስሌ ዝም ብሎ የሚጠፋ አይደለም። የደረሰብኝ ጉዳት ስጋ ሲጠግብ የሚረሳ አይደለም ”

“ማከናውነው ሥራዬን ነው፤ሙገሳና ጭብጨባ ብዙም አልሻም”ኦባንግ

 “… እህታችን ታሪኳን ስትነግረኝ፣ ለፍትህ እንደምትመጥን አመንኩ” ኦባንግ

“… የተረሳሁ ነበርኩ፡፡ የደረሰብኝ ግፍ ጠባሳ የሚያልፍ መስሎ አይታየኝም ነበር። ግን ብርሃን ሆነልኝ። በየትኛውም ወቅት ልረሳው የማልችለው ኦባንግ ሜቶ ችግሬን ዝቅ ብሎ አደመጠኝ። ና ባልኩት ቦታ ሁሉ ፈጥኖ እየደረሰ ፍትህ ደጅ እንድቆም ረዳኝ። ስለ እሱ ለመናገር ቃላቶች የሉኝም። ከሁለት ዓመት በፊት ያለመድሃኒት አልተኛም ነበር። ዛሬ መድሃኒት ከመቃም ተገላግያለሁ። በሴትነቴ የደረሰብኝ በደል ቁስሉ ከህሊናዬ ባይጠፋም ታሪኬ ተቀይሯል። … በየቦታው ፍትህ የተዛባባችሁ ወገኖቼ ዝም አትበሉ። ፍትህ በደጃችሁ ነው። ግን ተናገሩ። ሆን ብላችሁ ያላጠፋችሁት ጥፋት አያሳፍራችሁምና ራሳችሁን ከዝምታ ድባብ አላቅቁ…” ይህ ስሟ እንዳይነገር ከጠቀችው እህት አንደበት ነው።

“… እኔ የሰራሁት ሥራዬን ነው። ነገም የማከናውነው ሥራዬን ነው። ሙገሳና ጭብጨባ ብዙም አልሻም። ካለብን ችግር ብዛት የሰራነው ሥራ እዚህ ግባ የሚባል አይደለምና ይህንን ሰራሁ የማለት ልዩ ኩራት አይሰማኝም። ይልቁኑም ብዙ ጉድለቶች አሉብን። ፍትህ እንዲዛባብን ራሳችን በራሳችን የምንፈቅድበት አጋጣሚ እጅግ የበዛ መሆኑ ሁሌም ያሳዝነኛል። ለፍትህና ራስን ስለማክበር ያለን ጎዶሎ ነገር ራሱን የቻለ ትግል የሚጠይቅ ነው። ራሳቸውን ገልጠው የሚመጡ ወገኖችን መርዳት እርካታ እንዳለው እረዳለሁ…” አቶ ኦባንግ ሜቶ በበኩላቸው ይህን ይላሉ።

ይህች እህታችን የራሷንና የቤተሰቦችዋን ኑሮ ለማሻሻል የመን በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ሠራተኛ ቤት ውስጥ ለመስራት ተስማምታ ወደዛው ታቀናለች። ምስሏ በፎቶው የሚታየው አሜሪካዊት ዲፕሎማት ባለቤቷ
woman የአውስትራሊያ ዜግነት ያለው ሲሆን እርሱ የኤምባሲው ተቀጣሪ አልነበረም፡፡ ነገርግን በዚሁ ቤት ተቀጥራ ደመወዝና የሳምንት ፈቃድ እንዲሁም ሌሎች የሠራተኛ ጥቅማጥሞች እንደሚከበሩላት ቃል ተገብቶላት የመጣችውን እህት ፈጽሞ ያላሰበችውንና ያልጠበቀችውን ጸያፍ ጥያቄ ያቀርብላት ጀመር። ከዚህ በፊት በነበሩ ላይ ተመሳሳይ ጥያቄ እያቀረበ ፍላጎቱን እንደሚፈጽሙና እርሷም ይህንን የማድረግ ግዴታ እንዳለባት ያሳስብ ጀመረ፡፡ ባለቤቱና ቀጣሪዋ ዲፕሎማትም የባሏን ፍላጎት እንድትፈጽም ከመለመን እስከማስገደድ እና እስከመተባበር ገፍታበታለች፡፡ የጥቃቱ ሰለባ የሆነችው እህት ሁኔታው በባህላችን የተወገዘና ክብረነክ ፍጹም ጸያፍ ጉዳይ መሆኑንን በመግለጽ ደጋግማ ድርጊቱን ብትቃወምም አማራጭ አልነበረም።

በዚህ ሁኔታ በትግል፣ በሰቆቃ፣ የሚደርስላት በማጣት በተዘጋ ግድግዳ ለመኖር የተገደደችው እህት ሁለት ዓመት ያህል ከተሰቃየች በኋላ አለቃዋ ወደ ጃፓን ስትቀየር ሳትወድ በግድ አብራት ተጓዘች። ጃፓንም ባልና ሚስትም ይህቺን እህት በሳምንት 80ሰዓትና ከዚያ በላይ ማሠራት ሳያንሳቸው መረን የለቀቀውን ሴሰኝነታቸውን ገፉበት። ከዚህም ሌላ ተግባራቸው አደባባይ እንዳይወጣ በዚህች እህት ላይ ከፍተኛ የሆነ ቁጥጥር ማድረግ ጀመሩ፡፡ የምታደርገውን ነገሮች፤ የምትደውለውን ስልክ፤ … መከታተልና መቆጣጠራቸውን ከጸያፍ ተግባራቸው እኩል ቀጠሉበት፡፡ ከዚህም ሳያንስ ወደ ውጭ የምትወጣና ጉዳዩን ለአደባባይ የምታበቃ ከሆነ በቀጥታ ወደ አገሯ እንደሚመልሷት ዛቻቸውንና ማስፈራሪያቸውን ያቆሙበት ቀን አልነበረም፡፡

የፍትህ ደጅ መድረስ የተሳናት ይህቺ እህት አንድ ቀን ወደ ከተማ የመውጣት እድል አግኝታ በመንገድ ካገኘችው ወገኗ ጋር ስልክ የመቀያየርና መጠነኛ መረጃ የማግኘት አጋጣሚ እንደተከፈተላት ታስታውሳለች። እለት እለት የሚደርስባት ግፍ ሲበዛ አንድ ቀን የፍርሃትን በር ሰብራ አመለጠች። ከዚያ በፊት ግን የሚደርስባት በደል መቆም እንዳለበት አምርራ ስትናገር በሁኔታው አለማማር የገባት አሠሪዋ የአንድ መንገድ የአውሮጵላን ቲኬት ገዝታ ወደ ኢትዮጵያ ልትመልሳት ዝግጅቷን ባጠናቀቀችበት ወቅት ይህች ምስኪን አስቀድማ የወሰደችው ርምጃ የህይወቷን አዲስ ምዕራፍ አመላከተ።

አምልጣ እንደወጣች ጎዳና ላይ ላገኘችው ሰው ደውላ “ድረሱልኝ” አለች። አምልጣ መውጣቷን የተረዱት ወንጀለኞች በሁኔታው በመደናገጥ አሠሳ ጀመሩ፡፡ ባል የተባለው ኢትዮጵያ ድረስ በመሄድ ፍለጋ ያዘ፤ ወንጀል ሰርታ ያመለጠች መሆኗን የሃሰት ክስ በመመሥረት ፖሊስ እንዲፈልግለት የሚቻለውን ሁሉ ጣረ፡፡

ለወገን ደራሽ ወገን ነውና ከጨካኞቹ አሠሪዎቿ ከተገላገለች በኋላ ጃፓን በሚገኙት ወገኖቿ ጉያ ተሸሸገች፡፡ እነርሱም በእቅፋቸው ይዘው ሰብአዊ መብት ላይ ከሚሰሩ ድርጅቶች ጋር አስተዋወቋት። ወቅቱ አቶ ኦባንግ በጃፓን የሚገኙ ስደተኛ ወገኖችን ጉዳይ ለመስማትና ለሚመለከታቸው አካላት አቤት ለማለት ሄደው የተመለሱበት ነበር፡፡ የጉዳዩ ባለቤት የሆነቸው እህት ስለሁኔታው ስታስታውስ “ጃፓን ያሉ ወገኖችን እስከወዲያኛው አልረሳቸውም” በማለት ነው።

us embassy japanከለላ የሆኑላት ወገኖች ጉዳይዋን ጃፓን አገር ላለው አለቃዋ ለምትሰራበት የአሜሪካ ኤምባሲ እንዲደርስ አደረጉላት። አምባሳደሩ በጉዳዩ ላይ ምርመራ እንዲካሄድ አዘዙ፤ ዲፕሎማቷና ባሏ ተመሳሳይ ጥቃት በሌሎች ሁለት ሴቶች ላይ ማድረሳቸው ተረጋገጠ፡፡ ከዚህችኛዋ እህት በተጨማሪ ሌላኛዋ የጥቃት ሰለባን ጉዳይ ጥቁሩ ሰው ኦባንግ ሜቶና ድርጅታቸው ከጠበቆች ጋር እየሠሩበት ያለ ጉዳይ ነው፡፡ ለዚህችኛዋ እህት ግን ኤምባሲው የውል ማፍረሻ ገንዘብ ይሰጥሻል፤ ፈቃድ ተሰጥቶሽ ወደ አሜሪካ ትሄጃለሽ ተባለች። እሷ ግን ሞቼ እገኛለሁ በሚል ፍትህ እንደምትፈልግ አስታወቀች። የጉዳዩን መክረር ያስተዋለው ኤምባሲ ዋሽንግተን ዲሲ ለሚገኘው ዋና መ/ቤት አስታወቀ፤ የደኅንነት ሰዎች ጉዳዩን ጃፓን ድረስ በመምጣት መረመሩ፤ ጉዳዩንም አረጋገጡ፤ ወንጀለኛዋን አሠሪዋ ከሥራ እንድትባረር አደረጉ፡፡ በቀጣይም ወደ አሜሪካ የመምጣቷ ጉዳይ ተመቻቸ፡፡

አሜሪካ ከመጣች በኋላ ሁኔታው እንደ ሽልማት የተሰጣት መሆኑን አቶ ኦባንግ በተረዱ ጊዜ ምን እንደምትፈልግ በቀጥታ ጠየቋት፤ እርሷም ፍትሕን የተራበች መሆኗን ገለጸችላቸው፡፡ ኦባንግም ጠበቆች ፈለጉላት፤ ጠበቆቹም ጉዳዩን በጥሞና ከገመገሙና ከእርሷጋር ለረጅም ሰዓታት የወሰደ ቃለምልልስ ካደረጉ በኋላ ጉዳዩ በፍርድቤት መታየት የሚገባው መሆኑን ለአቶ ኦባንግ በማስረዳት የክስ ፋይል ይከፈታል፡፡

“ታሪኳን ስሰማ አዝንኩ። ወንጀሉን የፈጸሙት ሰዎች በትክክልም የፈጀውን ጊዜ ፈጅቶ ፍትህ አደባባይ እንድሚወጡ አመንኩ። እህታችንም ፍትህ እንዲበየንላት የምትመጥን እንደነበር ተረዳሁ” ሲሉ ስለ ጉዳዩ ያስረዱት አቶ ኦባንግ “ለዚህች እህት ጀርባችንን የምንሰጥበት አቅም አልነበረንም” በማለት እርሳቸው የሚመሩት ድርጅት የቆመበትን ዓለት የሆነ ዓላማ አነሱ። የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ /አኢጋን/ የአንድ ኢትዮጵያዊ ህይወት ህይወቱ፣ የአንድ ኢትዮጵያዊ ኑሮ ኑሮው በመሆኑ በማመላከት የተፈጸመው ተግባር ከድርጅታቸው ባህሪና መርህ፣ አብረዋቸው ከሚሰሩ አጋሮቻቸው እምነት አንጻር ሊመዘንና ፍትህ ሊያገኝ  እንደሚገባው ጠቆሙ። ከዚህ አንጻር እርሳቸው በግምባር ቀደምትነት የሚጠቀሱ ቢሆኑም ሥራው ግን የተሠራው በእርሳቸው ብቻ እንዳልሆነና እጅግ በርካታ ስማቸው እንዲጠቀስ የማይፈልጉ ኢትዮጵያውያን ብዙ የለፉበትና መስዋዕትነት የከፈሉበት እንደሆነ ያወሳሉ፡፡ ድርጅታቸው አገራቸውንና ሕዝባቸውን የሚወዱ  በርካታ ያልተዘመረላቸው ጀግኖችን ያቀፈ መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ሳያወሱ አላለፉም፡፡

ከጠበቆች ቡድን ጋር ይህንን ጉዳይ ከዳር ለማድረስ አቶ ኦባንግ በራሳቸው የግል ወጪ ከሚኖሩበት ካናዳ ወደ አሜሪካ በመመላለስ የጠበቃ ቡድኑ ጉዳዩን አምኖበት እንዲቀበለው በዙ ደክመዋል። ከትርጉም ጀምሮ የድርጅታቸው አባላት ድጋፍ አድርገዋል። ብዙ ጊዜ ውሸት ስለሚያጋጥም የማሳመኑ ሂደትም ቀላል አልነበረም። ትግሉ ጉልበት ካላቸው ጋር ስለነበር እህታችንን ማበረታታቱም ሌላ ስራ ነበር። ብቻ ሁሉም ሆኖ በጥቅሉ ለአራት ዓመታት ያህል የፈጀው ክርክር የፍትህን ብርሃን ፈንጥቆ በማብራት ተጠናቀቀ። በፍርድቤቱ ብያኔ 3.3 ሚሊዮን ዶላር ካሳ ተፈረደላት፤ አሸነፈች። የህግ ልዕናው ስጋዋን አጠገገው። ወንጀለኞቹ ወደ አውስትራሊያ ሸሽተው ስለነበር እነርሱን የተከታተሉና የሕግና የመረጃ ድጋፍ የሰጡ አካላት ከካሣው ድርሻቸውን ወስደዋል፡፡ አውስትራሊያዊው የዲፕሎማቷ ባለቤት እዚያው እያለ ህይወቱ አልፋለች፤ እርሷም ፍትህን ለመሸሽ እዚያው ተሸሸጋለች፡፡

“ቁስሌ ዝም ብሎ የሚጠፋ አይደለም። የደረሰብኝ ጉዳት ስጋ ሲጠግብ የሚረሳ አይደለም። በርካታ ስፍራዎችን የነካካ ነው። ሁሉንም ክፍሎች አድኖ ነጻ መሆን ቀላል አይደለም። በደሌ ፍጹም አይርሳም። ሆኖም ዝምታዬን ሰብሬ በመነሳቴ ገሃድ ባይወጡም ዛሬ ለብዙዎች ምስክርና ምሳሌ ለመሆን በቅቻለሁ” በማለት የጥቃቱ ሰለባ የሆነችው እህት ታስረዳለች።

ወደ ኋላ መለስ ብላም ስለባለቤቷ ስትናገር ጃፓን ሆና የሆነችውንና ያጋጠማትን ካስረዳችው በኋላ “ከእኔ ጋር ኑሮ መቀጠል ትፈልጋለህ ?” ስትል ጠየቀቸው። በሶስተኛው ቀን ደውሎ አለቀሰ። ሃዘኑንን ገለጸ። እናም አንድ ትልቅ ማጽናኛ ዜና አሰማት። “ሆን ብለሽ አላደረግሽውም። እንዴት በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሆነሽ እተውሻለሁ?” ነበር ያላት። ወደ አሜሪካ ተዛውራ ፍትህ ከተበየነላትም በኋላ አብረው ናቸው፤ የልጅ በረከትን አይተዋል። “ሳያንቋሽሸኝ ስለተቀበለኝና እንከንየለሽ የኑሮ አጋሬ ስለሆነ አመሰግነዋለሁ!!” ስትል የደረሰባትን ጉዳት ተረድቶ ስላደረገላት ሁሉ ያላትን ክብር ትገልጥለታለች። አዲስ አበባ ባለው የአሜሪካ ኤምባሲ አማካይነት ተጠቅመው ባለቤቷ ላይ ያደረሱትን በደልም በክፉ ትዝታነቱ ታነሳዋለች።

“ዛሬ ባለቤቴ ከኔ ጋር ነው። ከልጃችን ጋር በደስታ ቤተሰባችንን እየመራን ነው። ለባለቤቴ ልዩ ክብር አለኝ። የሆነውን ሁሉ አውቆ ፊቱን አላጠቆረብኝም። ፍቅሩን አብዝቶ ይሰጠኛል። የተፈጸመብኝን ክፉ ድርጊት ከሰማበት ቀን ጀምሮ ለኔ ያዝናል። ‘አውቀሽ ያደረግሽው ነገር ስላልሆነ ያንቺ ችግር አይደለም’ ሲል ሁሌም ስሜቴን ይጠግነዋል። አሁን እንደሚገባኝ ከሁሉም በላይ የሚጠግነኝ መልካምነት ነው። ወገኖቼ፣ ኦባንግ፣ ቤተሰቦቼ፣ ባለቤቴ … ፈውሴን አፍጥነውታል” በማለት ስሜት የተቀላቀለበት ልባዊ ምስጋናን ታቀርባለች።

ይህቺ እህት ጥሪ አላት፤ በዝምታ የተሸበቡ እህቶች እንዲናገሩ። “ገሃድ ውጡ!” ትላለች። አያይዛም “በደል ተሸክመው የተቀመጡ በነፍስም በስጋም የታመሙ አሉ። መጋረጃውን ገልጸው ወደ አደባባይ ካልወጡ ፍትህ መጋረጃ ከፍታ እነሱ ዘንድ አትደርስም” ስትል ሰዎች አውቀው ባልሰሩት ጥፋት ስለማይወቀሱ ፍትህ በሚሻው ጉዳይ ሁሉ መሸሸግ ሞኝነት እንደሆነ አድምቃ ታሰምርበታለች። ማንኛውም ጉዳይ ቢሆን ሊሸሸግ እንደማይገባ አጥብቃ ትናገራለች። መናገር ማርፍ እንደሆነ፣ በመናገር ውስጥ እረፍት እንዳለ ትመክራለች።

በጃፓን ላሉ ወገኖች ለዩ ምስጋና እንዳላት ደጋግማ የምትናገረዋ እህት፣ “ዝቅ ብሎ ለተላላከኝ ኦባንግ ያለኝ ክብር ትልቅ ነው” ስትል ምስጋና አቅርባለች። በመቀጠልም ተመሳሳይ ጥቃት ለሚፈጸምባቸው ወገኖች ድጋፍ ለመስጠት ዝግጁ መሆኗን አስረግጣለች። እንደ እርሷ ለተጎዱ ሁሉ የበኩሏን ሁሉ ለማድረግ ቃል ገብታለች።

አቶ ኦባንግ በበኩላቸው “ይህ ደሞዛችን ነው። ይህ ርካታችን ነው። ከዚህ በላይ ርካታ የለንም” ሲሉ ስሜታቸውን ይገልጻሉ። ማንም ከህግ በላይ እንዳይደለ ከማረጋገጥ በላይ ታላቅ ተግባር እንደሌለ ማሳየት ታላቅ ቁም ነገር እንደሆነና ዜጎች የትም ሆነ የት መብታቸውን ማስከበር እንዳለባቸው፣ ለመብታቸው መታገል እንዳለባቸው ያሳስባሉ። “ይህችን እህት ሳገኛት ዘሯን፤ ብሔሯን ወይም ሃይማኖቷን አልጠየኩዋትም። በደልዋን ሰማሁ። ለፍትህ ትመጥናለች አልኩ። ከሥራ አጋሮቼ ጋር ሆነን ለህግ የበላይነት ተነሳን። ፍትህ ድል ነሳች። ይህና ይህ ነው የእኛ እርካታ!!” ሲሉም ለታፈኑ ሁሉ የ“ተነሱ” ጥሪ ያቀረባሉ። አያይዘውም “ሰዎች ሁሉ እኩል ነን። ጉዳታችን በገንዘብ አይለካም” ሲሉ የህሊና ቁስል ከባድ መሆኑን ይጠቁማሉ።

ደቡብ ኮሪያ

ባለፈው ሳምንት የጥቁሩ ሰው ውሎ ደቡብ ኮሪያ ነበር። ኢትዮጵያዊያን ጀግኖች የዛሬ 56 ዓመት ደም፣ አካልና ህይወት የገበሩላት ህዝብና መንግስታቸው የረሷቸውን ኢትዮጵያዊያኖች እንባ ለማበስ!! በጉዟቸው የአገሪቱን የሰደተኞችና ኢሚግሬሽን ቢሮ ባለስልጣናትን፣ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ሹማምንትንና የማህበራዊ ተቋማትን ኃላፊዎችን አነጋግረው ተመልሰዋል።

የኑሮ መስመሩ የጠፋባቸውን ወገኖች አሰባስበው ባንድ አዳራሽ ውስጥ የጀመሩት ንግግር የዛሬ 56 ዓመት ለደቡብ ኮሪያ ነጻነት ለተሰው ኢትዮጵያዊያኖች መታሰቢያ በቆመው የመታሰቢያ ሃውልት ዙሪያ ተጠናቋል። ሁሉም የመኖሪያ ወረቀት የሌላቸው ወገኖች በቅርቡ ምላሽ የሚያገኙበትን ሁኔታ አመቻችተው ተመልሰዋል። “ላልተዘመረላቸው የወገን አለኝታ ክብር እንሰጣቸው” በሚል በተለያዩ የማህበራዊ ገጾች ስማቸው እየተነሳ ያሉትን አቶ ኦባንግ ሜቶን በደቡብ ኮሪያ ምን አድርገው ተመለሱ? በሚለው ጉዳይ ላይ አነጋግረናቸዋል ዘገባውን እናስከተላለን።

May 2, 2016  goolgule