Category Archives: Socity / ማህበራዊ

ከጣልያን ሐኪሞች አዲስ መረጃ ወጣ – “የእስካሁኑ የኮቪድ 19 ትርክት ሃሰት ነው”

ክብርና: ምስጋና: ለጣሊያን:የጤና: ባለሙያዎች::ከዚህ: በታች: የሠፈረው: እጅግ: አበረታችና: ፋና: ወጊ: የሆነ:ትንታኔ:ከጣሊያንኛ: ወደእንግሊዝኛ: በጣሊያኖች: በራሳቸው: የተተረጎመ: ሲሆን: ከእንግሊዝኛ: ወደአማርኛ: የተረጎምሁት: እኔ: ዶ/ር: ነጋሽ: አምሳሉ:ነኝ::እስካሁን: ድረስ: የዓለምን: የተለያዩ: የጤና: ባለሙያዎችና: ተመራማሪዎች: ሲአፋጅና: ሲአዎዛግብ: የቆየው: የኮሮና: ቫይረስ(ኮቪድ 19) በሽታ:ጉዳይ: በስተመጨረሻው: በጣሊያን: የፓቶሎጂ: ባለሙያዎች: ትክክለኛው: ማብራሪያና: ትርጉም: የተሰጠው: ይመስላል::እነሆ: የማብራሪያው: ትርጉም:እንዲህ: ይነበባል::ይህ: ወረርሽኝ: በዓለም: ዙሪያ:በሚደረገው: ርብርብ:በጣም: እየተሸነፈና: እየተጠቃ: በመሄድ: ላይ: ያለ: ይመስላል::

ሕይዎታቸው: በወረርሽኙ: በአለፉ: ሰዎች: ላይ: በተደረገው: መጠነ: ሰፊ: ከአስከሬን:ናሙና: ምርመራ: በተገኘው: መሠረት: እስካሁን: ድረስ:”ኒ ሞ ኒ ያ”( የሳንባ: ኢንፌክሽን):እየተባለ: ሲነገር: የነበበረው: ትርክት: ውሸት: መሆኑና: ችግሩ: ኒሞኒያ: ሳይሆን: በደም: ሥሮቻችን: ውስጥ: የሚፈጠር:የደም: መርጋት: ወይም: የደም: መጏጎል( Disseminated Intravascular Coagulation( thrombosis) ነው:: ይህም: በአጭሩ: DIC ይባላል::ስለሆነም: ይህን: በሽታ: ለመዋጋት: መጠቀም: ያለብን(የነበረብን) የሚከተሉትን: መድኃኒቶች:ይሆናል::

እነዚህም: ፀረ-ኅዋሶች( antibiotics, antivirals): ፀረ-ኢንፍላሜሽን( anti-inflammatories እንዲሁም: ደም: እንዳይረጋ ( እንዳይጏጉል) የሚአደርጉ(anticoagulants) ይሆናል: ማለት: ነው::ከአሁኗ: ስዓት: ጀምሮ: የህክምና: አሰጣጥ: ፕሮቶኮል:ይቀየራል: ማለት: ነው::ከጣሊያን: ፓቶሎጂስቶች: በተገኘው: ጠቃሚ: መረጃ: መሰረት: በሰፊው: ሲዎራለት: የነበረው: የቬንትሌተርና: የፅኑ: ህሙማን: ማቆያ(ICU) በጭራሽ: አስፈላጊ: አልነበሩም::

ለሁሉም: የበሽታ: ዓይነቶችና: በሁሉም: ቦታ: የሚሰራ: ከሆነ: ይህ: ወረርሽኝ: ከታሰበው: ጊዜ: ቀድሞ: መፍትሄ: ሊገኝለት: ይችላል::ስለኮሮና: ቫይረስ:አዲስና: ጠቃሚ:መረጃ:: የበሽታው: ምንነት: በትክክል: ባለመታወቁ:በመላው:ዓለም: ለኮቪድ19:የተሳሳቱ: ምልከታዎችና: ህክምናዎች: ስንከተል: ቆይተናል:: ይህም: diagnostic error ይባላል::

በአሜሪካ: የሚኖሩ: የሜክሲኮ: ቤተሰብ:በቤታቸው: ውስጥ: ባደረጉት: እራስን: የማከም: ሙከራ: መፈወሳቸው: በጣም: አስደናቂና: አስደማሚ:ሁኔታ: ነው::የተፈወሱትም: ሦስት: ባለ 500 mg አስፒሪን: በሎሚ: ጭማቂ: በጥብጠው: ከማር: ጋር: ቀላቅለው: ካፈሉ: በኇላ: ትኩሱን: በመጠጣት: በነጋታው: ሙሉ: ፈውስ: አግኝተው: ከእንቅልፋቸው: ተነስተዋል::ከዚህ: በታች: የሚከተለው: የሳይንስ: መረጃ: የፈውሱን: ቅቡልነት: ያረጋግጣል::በነገራችን: ላይ: ይህ: መረጃ: የተለቀቀው: በአንድ: የጣሊያን: ተመራማሪ: ነው::ከሃምሳ: በላይ:በኮቪድ 19: የሞቱ:የሬሳ(አስከሬን): ምርመራ(autopsy) ላደረጉት: የጣሊያን: ፓቶሎጂስቶች: ምስጋና: ይግባቸውና: የምርመራ: ግኝቱ: የሚአሳየው: ኒሞኒያ: ሳይሆን:በጥቃቅን: የደም: ሥሮች: ውስጥ: የሚከናዎን: የደም: መርጋት: ነው:: በዚህ: ዐይነት: የደም: መርጋት: በሽታ: ሳንባችን: በጣም: የታውቀ: የሰውነት: ክፍል: መሆኑ: ይታወቃል: ስለሆነም: በእነዚህ: ህዋሶች(viruses) አማካኝነት: በሚፈጠረው: inflammation ደም: ሰለሚጏጉል: የልብና: የአንጎል( heart attack and stroke) ህመም:ይከተላል:: ይህ: የረጋ: ደም: አያሌ: የአካል:ክፍሎችን: በማዎክ: ለህይዎተ: ኅልፈት:ይዳርጋል: ይህም: multi-organ failure ይሰኛል::

አዲሱ: የህክምና: ፕሮቶኮል: የፀረ: ቫይረሱን: መድኃኒት: ገሸሽ: በማድረግ: የፀረ:የደም: መርጋትንና: የኢንፍላሜሽን: መከላከልን: ትልቅ: ግምት: ይሰጣል:: ስለሆነም: እነዚህ: ሁለት: መድኃኒቶች: በፍጥነት: ለታማሚዎች: መሰጠት: አለባቸው:: ፈዋሽነታቸው: የተረጋገጠ: ነውና::ቻይናውያን:ይህን:በወቅቱ: ባለመገንዘባቸው: ጊዚያቸውን: በቤት: ሳይሆን: በፅኑ: በሽተኞች: ማቆያ(ICU): በከንቱ: አባክነዋል::በመላ: ሰውነት: ደም: መርጋት(thrombosis(DIC)ይህን: ሁኔታ: ለመዋጋት: ፀረ-ህዋስ(antibiotics &antivirals): ፀረ-ኢንፍላሜሽንና: ፀረ: ደም: መርጋት( anti-inflammatories & anticoagulants) መጠቀም: የግድ: ይሆናል::

የዚህን: አዲስ: ግኝት: ተአማኒ: የሚአደርገው: የጣሊአን: ፖቶሎጂስቶች: በቤርጋሞና: በሚላኖ: ከተሞች: ከሰባ: በላይ: በዓለም: ከፍተኛውን:የአስከሬን: ምርመራ: ያደረጉ: ሲሆን: ቻይናዎች: ግን:ሦስት: ብቻ: የሬሳ: ምርመራ: ያደረጉ: በመሆኑ: ነው::ይህ: ቫይረስ: በደም:ስር: ከፍተኛ: የደም: መጏጎል:በመፍጠር: የደም: መርጋት: በሽታ: እንጂ: ኒሞኒያ: ተብሎ: የተሰራጨው: ትንታኔ: ግዙፍ:diagnostic error ነበር::በፅኑ: ህመምተኛች: ክፍል(ICU) ሲደረግ: የነበረው: ከፍተኛ: ወጭ: ያስከተለው: ህክምና: እጅግ: አላስፈላጊ: ነበር::

ወደኋላ: በመመለስ: ከወር: በፊት: ታማሚዎች: የተነሱትን: የራጅ: ምርመራ( X-Ray): የኮኔክቲቭ: ቲሹ: ኒሞኒያ( interstitial pneumonia) በማለት: ሲጠራ: የነበረው: አሁን: ላይ: ሆነን: ስናየው: በደም: መርጋት( DIC) የሚታይ: መሆኑ: ምንም: የማያሻማ: የኒሞኒያ: ዲያግኖሲስ: ነው::

የረጋውን: ደም: ሳናክም: በፅኑ: ህክምና: ማቆያ: ውስጥ: ስናደርገው: የነበረው: ሩጫ: ድካምና: ወጭ: ከንቱና: ፋይዳቢስ: ነበር: ማለት: ይቻላል::የረጋውን: ደም: ሳናሶግድ:ቬንትሌተር: በመጠቀም: ሳንባን: በአየር: ማከም: እንደዚሁ: ከንቱ: ድካም: ነበር:: ምንም: ጥቅም:አልነበረውም: ማለት: ነው:: ቬንትሌሽን(ventilators) ከተጠቀሙት: ታማሚዎች: ውስጥ: ከአስር: ታማሚዎች: ዘጠኙ: እንደሚሞቱም: ተረጋግጧል::

ችግሩ: የሳንባ: በሽታ: ሳይሆን: የልብና: የደም: ሥሮች(cardiovascular) በሽታ: ነውና::የሞትም: ዐብይ: ምክንያቱ:በደም: መልስ(veins) የሚከናወነው: የደም: መርጋት: እንጅ: ኒሞኒያ: አይደለም::ለመሆኑ: ደም: ለምን: ይረጋል ?ይህ: የሚካሄደው: ኢንፍላሜሽን(inflammation): በሚአስከትለው: የፓቶፊዚዖሎጂካል: ውስብስብ: ዘዴዎች: ነው:: በጣም: የሚአስቆጨው: እውነታ: የሳይንሱ: ህብረተ:ሰብ: በተለይ: ቻይናዎች: እስክ: መጋቢት( Mid March) ድረስ: anti-inflammatory መጠቀም: አያስፈልግም: የሚል: የተሳሳተ: አቋም: በመያዛቸው: ነበር::

አሁን: በጣሊያን: አገር: የሚሰጠው: ህክምና: (antibiotics and anti-inflammatories ) በመሆኑ: በሆስፒታል: አስተኝቶ: ማከም: በጣም: እየቀነሰ: ይገኛል::በርካታ: በሽተኞች: በትኩሳት: እየተሰቃዩ: በተገቢው: ሳይታከሙ: ህይዎታቸው: በከንቱ:ሊአልፏል: ችሏል::ቫይረሱ: ያስከተለው: inflammation በውስጥ: አካላችን: ላይ: ያስከተለው: ከፍተኛ: ጉዳት( extensive tissue damage) ለከፍተኛ: የደም: መርጋት: በሽታ: ያጋልጣል:: ዋናው: ችግር: ቫይረሱ: ሳይሆን: ቫይረሱ: የተደበቀበትን: ቲሹ: ነጎድጏዳማ: የ immune hyper-reaction ስለሚአጠቃው: ነው::

በጣም: አስገራሚ: ሁኔታ: እንንገራችሁ: Rheumatoid Arthritis ያለባቸው: በሽተኞች: ኮርቲኮስቴሮይድ: የተባለ: anti-inflammatory ስለሚወስዱ: ከነዚህ: ሰዎች: መካከል: አንዳቸውም: ICU አልገቡም::በጣልያን: ከላይ: በተጠቀሰው: ምክንያት: ሆስፒታል: ማስተኛት: በጣም: ቀንሷል:: በመኖሪያ: ቤት: ማከም: ሆስፒታል: ማስተኛትን: ብቻ: ሳይሆን: ደም: መርጋትንም: በእጅጉ: ይቀንሳል:: ይኸን: እውነት:ልብ: ይሏል:: ይህ: ሁሉ: ምስቅልቅል: ሊመጣ: የቻለው: የደም: መርጋት: ዋና:ዋና: ምልክቶች: ግልፅ: ስላልነበሩና: ስለጠፉም: ነው::

በዚህ: ትልቅ: ግኝት: ላይ:በመመርኮዝ:ወደተለመደው: ጤነኛ: ህይዎት: መመለስ: ይቻላል: በማቆያ: የታጎሩትን: ቀስ: በቀስ:መክፉት: ይቻላል::ይህ: ግኝት: በታዋቂ: ጆርናሎች: መውጣት: አለበት: :በየአገሩ: የሚገኙ:የጤና: ሙያ:ባለስልጣናት: ሊዎያዩበትና: ሊተነትኑት: ይገባል: እንላለን:: ብሎም: ሞትን: ሊከላከሉ: ይገባል:: ያሳዝናል!!የክትባቱ:ጉዳይ: ቀስ: ብሎ: ይደርሳል:: መጠበቅ: ይቻላል::በጣሊያን: አገር: ፕሮቶኮሉ: እየተቀየረ:ነው::በጣሊያን: ፓቶሎጂስቶች: ጠቃሚ: ግኝትና: መረጃ: መሠረት: ventilators and ICU are unnecessary.በመጨረሻም: መዋዕለ: ንዋያችንን: በሚገባ: ተጠቅመን: ይህን: ቸነፈር: እናጥፋ::

ተርጏሚ:ዶ/ር: ነጋሽ:አምሳሉ ከአሜሪካ

በጎ አድራጊዋ በ12 ሚሊየን ብር ምስራቅ ጎጃም ትምህርት ቤት ሊገነቡ ነው

 ግለሰቧ በምስራቅ ጎጃም ዞን ማቻከል ወረዳ ትምህርት ቤት ሊገነቡ እንደሆነ ሰምተናል፡፡ ትናንት በኢንጅነር ጸደቀ ይሁኔ ደሴ ላይ አዳሪ ትምህርት ቤት ተገንብቶ ሥራ በመጀመሩ ባለብሩህ አዕምሮ የአማራ ክልል ልጆች እየተማሩበት ይገኛል፡፡

ቀጥሎም የዳስ ትምህርት ቤት መኖሩን የሰማው ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረ ስላሴ ‹‹ እንዴት!? ይህማ አይደረግም! ቦታውን ሄጄ ማየት አለብኝ!›› ብሎ ወሰነ እና ጉዞውን ወደ ዋጎች ምድር አደረገ፡፡ ዜናው እውነት ሆኖ አገኘው፡፡ ከዚያው እንዳለም ወሰነ፤ በሦስት ወራት ውስጥ ደረጃውን የጠበቀ አድርጎ ለማስገንባትና ለ2012 የትምህርት ዘመን ዝግጁ ለማድረግ፡፡
ኃይሌ ቃሉን ተገበረና ብዙዎቹን አስደመመ፤ ወደ ስፍራው ተመልሶ ሄዶም አስመርቆ አስረከበ፡፡ ደብረ ብርሃን ላይም አንድ በጎ አድራጊ ኢትዮጵያዊት አዳሪ ትምህርት ቤት እያስገነቡ እንደሆነ ሰምተናል፤ ከስፍራው ሄደንም አረጋግጠናል፡፡

ዛሬ ደግሞ ሌላ ዜና! ሌላ የአዕምሮ ልማት፣ ሌላ የትውልድ ቀረጻ ጉዞ! ወሬው የተሰማው ከወደ ምስራቅ ጎጃም ዞን ማቻከል ወረዳ ነው፡፡ ወይዘሮ አያልነሽ ባይሌ የተባሉት በጎ አድራጊ ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ማስተማሪያ ትምህርት ቤት ነው የሚያስገነቡት፤ ለግንባታው ደግሞ 12 ሚሊዮን ብር ወጪ እንደሚያስፈልግ ታውቋል፡፡

በጎ አድራጊዋ በምስራቅ ጎጃም ዞን ማቻከል ወረዳ ዘመናዊ የመጀመሪያ ደረጃ ሙሉ ሳይክል ትምህርት ቤት ለማስገንባት ቦታ ተረክበዋል፡፡ ‹‹የሕዝብን አዕምሮ መቀየር ለሁሉም ነገር ቁልፍ ነው›› በማለት በበጎ ተግባሩ ላይ ለመሰማራት እንደፈለጉ የማቻከል ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መላኩ ሙሉሀብት ለአብመድ ዛሬ ነሐሴ 22/2011 ዓ.ም በስልክ አስታውቀዋል፡፡

በበጎ አድራጊዋ ወይዘሮ አያልነሽ ባይሌ የተቋቋመው አያልነሽ የበጎ አድራጎት ድርጅት በወረዳው ኳሽባ በተባለ ቀበሌ ላይ ነው ትምህርት ቤቱን የሚገነባው፡፡ ትምህርት ቤቱ ሲገነባ ሩቅ ቦታ ተጉዘው መማር ላልቻሉ የአካባቢዉ ህጻናት እፎይታ የሚሰጥ እንደሆነ የገለጸው የማቻከል ወረዳ አስተዳደር ግለሰቧ ለምትገነባው ትምህርት ቤት 1 ነጥብ 8 ሄክታር መሬት ማስረከቡንም ነው ያስታወቀው፡፡

የትምህርት ቤቱ ግንባታ በቀጣዩ ዓመት እንደሚጀመር ታውቋል፡፡ ግንባታው ደረጃውን በጠበቀ መልኩ የመማሪያ ክፍል፣ ቤተ መጽሀፍት እና ቤተ ሙከራ ተሟልቶለት በ 5 ዓመታት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ማስታወቃቸውንም ዋና አስተዳዳሪው አቶ መላኩ ተናግረዋል፡፡ እስከዚያው ድረስ ደግሞ በአካባቢው ለሚገኝ ሌላ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የተማሪዎች ወንበር ድጋፍ እንዳደረጉ ዋና አስተዳዳሪው ነግረውናል፡፡ የግለሰቧን አርዓያነት ሌሎች እንዲከተሉም ዋና አስተዳዳሪው ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በጎ አድራጊ ግለሰቧን ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፤ እንዳገኘናቸው የእርሳቸውን ሀሳብ አካትተን እናቀርባለን፡፡ በየአካባቢው የምትገኙ ባለሀብቶችስ ትምህርት ቤቶችን በመገንባት የትውልድን አዕምሮ ለማልማት ምን እየሰራችሁ ነው?

በምስጋናው ብርሃኔ (አብመድ)

ፎቶ፡- ከማቻከል ወረዳ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት

ስለቺኩንጉኛ-ቺክ (Chikungunya -CHIK)

በድሬዳዋ ከተማ ብቻ 7258 ሰዎች በ ቺኩንጉኛ ቫይረስ ወረርሽኝ ተጠቅተዋል:: ሌሎችም እየተጠቁ ስለሆነ ቁጥሩ በቀናት ልዩነት ከፍ ሊል ይችላል::ስለበሽታው ምንነት አንዳንድ መረጃዎችን ከዚህ በታች የሚከተለው ላቀርብ እሞክራለሁ::

ቺኩንጉኛ (ቺክ) በእንግልዘኛው Chikungunya (CHIK) የሚመጠው በቺኩንጉኛ ቫይረስ Chikungunya virus (CHIKV) ሲሆን ከህመምተኛው ሰው ወደ ጤነኛው ሰው የሚተላለፈው አዴስ አልቦቺክታስ (Aedes albopictus) እና አዴስ አጂፒቲ (Aedes aegypti) ተብለው በሚጠሩና በቫይረሱ በተጠቁ የትንኝ አይነቶች ንክሻ አማካኝነት ነው::

አዴስ አልቦቺክታስ የሚባለው የትንኝ አይነት በብዛት የሚገኘው በደቡብ ምዕራባዊው ኤስያ ሲሆን ከድንበር ተሻጋሪ እንቅስቃሴዎች የተነሰ ባርካታ የአለማችን ክፍሎች መታየት ጀምሯል:: ይህ የትንኝ አይነት በሆዱና በእግሩ ላይ ከሚታየው ዝንጉርጉርነት የተነሰ የኤስያው ነብር የሚል ቅጥል ስም አለው (ፎቶ: 5 ይመልከቱ ):: አዴስ አልቦቺክታስ ከቺኩንጉኛ በተጨማሪ Yellow fever Virus (በተለምዶ ቢጫ ወባ ተብሎ የሚታወቅ): Dengue virus (ደንጉ ቫይረስ) ና ዲሮፍላሪያ ኢሚቲስ (Dirofilaria immitis) የሚባሉ በሽታ አምጭ ተዋህሳን ተሸካሚ መሆኑ ይታወቃል:: ከዚህ በተጨማሪ ዚካ ቫይረስንም (Zika virus) ተሸካሚና አስተላላፊ መሆኑ ይታመናል::

ሌላኛው የትንኝ አይነት አዴስ አጂፒቲ የተገኘውና በብዛትም የሚገኘው አፍሪካ አህጉሪ ውስጥ ሲሆን ከቺኩንጉኛ በተጨማሪ የቢጫ ትኩሳት ቫይረስ: ዚካ ቫይረስ: ማያሮ (Mayaro) እና ደንጉ ቫይረስን ያስተላልፋል:: በብዛት በአፍሪካ ይገኝ እንጂ በብዙ ሞቃታማው የአለማችንም ክፍል እንደሚገኝ ጥናቶች ያሳያሉ:: ይህን ያህል ስለ ትንኙ ካወረሁ በአድስ መልኩ በአገራችን ወረርሽኝ እያስከተለ ስላለው ስለ ቺኩንጉኛ በሽታ አንዳንድ መሰረታዊ እውነታዎችን ልጠቁም::
ከላይ ለመጥቀስ እንደተሞከረው በሽታው የሚመጠው በቫይረስ ሲሆን ዋና ዋና ምልክቶቹ ከፍተኛ ትኩሳት(40 ድግሪ ሴንቲ ግሬድ): ራስ ምታት: የመገጣጠሚያና የጡንቻ ህመም: የመገጣጠሚያ እብጠትና ሽፍታ ናቸው (ፎቶ: 1: 3 ና 4 ይመልከቱ) :: የበሽታውም ስም ከሲዋህለኛ ወደ አማርኛ ሲተረጎም “ማጠፍ” ( በእንግሊዘኛው that bends up) ማለት ነው:: ይህም ከመገጣጠሚያ ህመም የተነሰ ቀጥ ብሎ መቆምም ሆነ መሄድ አለመቻልን ለማመልከት ነው::

የበሽታው ምልክቶች መታየት የሚጀምሩት በበሽታ አምጪ ቫይረስ የተመረዘች ትንኝ በነደፈች ከሁለት እስከ አስረ ሁለት ቀናት በሉት ጊዜያት ነው:: ብዙውን ጊዜ ምልክቶቹም የሚቆዩት እስከ ሳምንት ባለው ጊዜ ቢሆንም የመገጣጠሚያ ህመም ግን ከወራት እስከ አመታት ሊቆይ ይችላል::

የበሽታው የመግዳል አቅም (risk of death) አንድ ሰው ከአንድ ሺ ሰው ነው:: ይህም ማለት በሽታ ከተጠቁ አንድ ሺ ሰዎች መካከል አንዱ ሊሞት ይችላል ማለት ነው:: ይህ ቁጥር ትንሽ የሚባል አይደለም:: በተለይ ህፃነት: አዛውንትና በተለያዬ በሽታ ቀድመው የተጠቁ ሰዎች ላይ አደገኘነቱ ይበረታል::

በላብራቶሪ የቫይረሱን ዘረ-መል (RNA) ወይም ቫይረሱ መጠቃት ምክንያት ሰውነታችን ለመከላከል ያመነጫቸውን ፀረ ቫይረስ ንጥረነገር (antibody) በማየት ሲሆን ይህ አይነቱ ምርመራ እንደ ELISA ና RT-PCR (የላቦራቶሪ ቴክኒኮች ናቸው) ያሉ መመርመሪያዎችን ይፈልጋል:: በእኛ አገር ሁኔታ ለሁሉም ተደራሽ ባይሆንም መሳሪያዎቹ በአገር ደረጃ እንዳሉ አውቃለሁ ነገር ግን ለዚህ ምርመራ የሚያስፈልጉ ተጨማሪ ግብኣቶችን መግዛት ያስፈልጋልና በዚህ ላይ እውቀቱ የለኝም::

ህክምናውን በተመለከተ በሽታው ከላይ እንደጠቀስኩስ በቫይረስ የሚመጣ ሲሆን ለዚህ ቫይረስ ህክምና የሚሆን ፀረ-ቺኩንጉኛ እስካሁን ባለኝ መረጃ የለም:: ስለሆነም ህክምናው የሚያተኩረው በበሽታው ምክንያት የሚከሰቱ ምልክቶችን ማለትም ትኩሳት: ድካም: በትኩሳት ትነት የሚወጣውን ፈሳሽ መተካት ይሆናል ማለት ነው:: በተጨማሪም ለበሽታው መከላከያ የሚሆን ምንም አይነት ክትባት እስካሁን ገበያ ላይ አልዋለም::

የበሽታው መከላከያ የበሽታ አምጪውን ትንኝ መቆጣጠር ሲሆን ከወባ በሽታ መከላከያ ጋር ተመሳሳይ ነው(ፎቶ: 2 ይመልከቱ):: በተላይም እያንዳንዱ ሰው በዙሪያው የሚገኙት ለትንኝ መራቢያ አመቺ የሆኑ ነገሮችን ማስወገድና የአከባቢውን ንፅህና መጠበቅ ፍቱን መፍትሄ ነው:: 
ከወባ በተለየ ሁኔታ ትንኞቹ በቀን (ቀትር) ላይ ዝውውር ስለሚያደርጉ ቀን ላይ ለሚታኙ ህፃናትና የታመሙ ሰዎች ቴንትና በቆዳ ላይ የሚቀባ ትንኙን የሚያርቅ ቅባት መጠቀም ተገቢ ነው:: ይህ ቅባት ለቺኩንጉኛ ተብሎ የተሰረ ወይም በውስጡ ትንኞቹን ማራቅ የሚችል ጠረን ያለውን ንጥረነገር ወይም ኬሚካል የያዘ መሆን አለበት (ከጤና ተቋም ብቻ መግዛት ተገቢ ይሆናል)::

መከላከል እየቻልን አንድም ሰው እንዳይሞት ትኩረት እናድርግ!

ከድሬዳዋ ወደ ሌላው አከባቢ እንደይሰራጭና በቅርቡም ከአገራችን የቺክንጉኛንና የመሰል ወረርሽኝ አምጪ ተዋህሳንን መጥፋት እንደምንሰማ ተስፋ አደርጋለሁ::

ተስፈኛው ተክሌ

Tekle Airgecho  ከኦስሎ ዩኒቨርስቲ

‘የዓለም ሳምባ’ የሚባለው አማዞን ጫካ በአስፈሪ ሁኔታ እየነደደ ነው

BBC Amharic – የፈረንሳዩ ኢማኑኤል ማክሮን ይህ ዓለማቀፍ መቅሰፍት ነው። በበለጸጉ አገራት ጂ7 ስብሰባም ዋናው መነጋገሪያችን ሊሆን ይገባል ብለዋል። በትዊተር ሰሌዳቸው ማክሮን “ቤታችን እየነደደ ነው” ብለዋል።

የብራዚሉ ርዕሰ ብሔር ቦልሶናሮ በበኩላቸው ማክሮንን ወርፈዋል። ጉዳዩን ፖለቲካዊ ገጽታ ለማላበስ ይሞክራሉ በማለት።

ብራዚል በሌለችበት የጂ7 በበለጸጉ አገራት ስብሰባለ ላይ የአማዞንን ሰደድ እሳት ጉዳይ ለማድረግ መሞከር ምዕራባዊያን አሁንም ከቅኝ ግዛት አስተሳሰብ አለመላቀቃቸውን የሚያሳይ ነው ብለዋል፤ ቦልሶናሮ።

በብሔራዊ የህዋ ምርምር የወጣ አንድ የሳተላይት መረጃ እንዳመለከተው በብራዚል የእሳት ቃጠሎ 85 ከመቶ ጨምሯል። ከዚህ ውስጥ ከፍተኛውን መቶኛ የሚይዘው ደግሞ የአማዞን ሰደድ እሳት ነው።

ወግ አጥባቂ ፓርቲዎች የብራዚሉ አዲስ ርዕሰ ብሔር ሚስተር ቦልሶራኖ ለሰደድ እሳቱ ተጠያቂ ናቸው ይላሉ። ምክንያቱ ደግሞ ገበሬዎችንና ሥራ አጦችን ዛፉን እንዲመነጥሩ አበረታትታዋል።

ቦልሳራኖ በበኩላቸው ግብረሰናይ ድርጅቶች እሳቱን ለኩሰዋል ሲሉ ከሰዋል። ነገር ግን ለዚህ ክሳቸው መረጃ እንደሌላቸው አምነዋል።

Image copyright JODY AMIET

በዓለም እጅግ ሰፊ ሽፋን ደን የሆነው አማዞን የዓለም ሳምባ በሚል ይሞካሻል። የዓለም ሙቀት መጨመርን በትንሹ ያረግባል የሚባልለት አማዞን አሁን ምን ያህሉ የደን ሽፋን በሰደድ እሳቱ እንደተበላ የማያወላዳ መረጃ ገና አልተገኘም። ሆኖም የዘንድሮው ባለፉት 10 ዓመታት በአማዞን ከተሰከቱት ሰደድ እሳቶች ሁሉ የከፋው ነው።

አንዳንድ መረጃዎች የሰደድ እሳቱ ጭስ እስከ አትላንቲክ ጠረፍ እንደደረሰ ይገልጻሉ። በሳዎፖሎ ደግሞ ሰማዩን የሰደድ እሳቱ ጭስ ጋርዶታል። ሳዎ ፖሎ ከሚነደው አማዞን በ2ሺ ማይል ትርቃለች።

“የምድርን 20 እጅ ኦክሲጅን የሚያመነጨውን የአማዞን ጫካ ጉዳይ በስብሰባችን ካላነሳን ምኑን ተሰበሰብን” ብለዋል የፈረንሳዩ ማክሮን።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ ጉቴረስ በበኩላቸው “ነገሩ ክፉኛ አሳስቦኛል” ብለዋል።

የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ከቃጠሎው በኋላ

የኳታር መንግስት በአዲስ አበባ ከተማ የኩላሊት ህክምና ሆስፒታል ይገነባል

በኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመካከለኛው ምስራቅ ጉዳዮች ዳይሬክተር አምባሳደር ተበጀ በርሄ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክ ቡድን ከኳታር ልማት ፈንድ የፕሮጀክት ኃላፊዎች ጋር በሀገራችን የኩላሊት ህክምና ሆስፒታል ለማቋቋም ዝርዝር ውይይት አድርጓል።

በልዑክ ቡድኑ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የሚኒስትሩ ልዩ የፕሮጀክት አማካሪ ዶክተር ሰናይት በየነ እና የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የኩላሊት ሕክምና ክፍል ኃላፊ ዶክተር አዲሱ መልኬ ተካተዋል።

እንዲሁም በኳታር የኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሳሚያ ዘካሪያ እና የኤምባሲው ዲፕሎማቶች ተሳትፈዋል።

በኳታር በኩል የኳታር ልማት ፈንድ የልማት ፕሮጀክቶች ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሚስተር ሚስፈር ሃማድ አል ሻህዋኒ እና ሌሎች የተቋሙ ፕሮጀክት ባለሙያዎች በውይይቱ ላይ ተሳትፈዋል።

በውይይታቸውም ከአሁን ቀደም በሁለቱ ሀገራት መሪዎች ስምምነት መሰረት የኳታር መንግስት በአዲስ አበባ የኩላሊት ሕክምና ሆስፒታል ለመገንባት የገባውን ቃል በአፋጣኝ ወደ ተግባር ለማሸጋገር በሚያስችሉ ዝርዝር ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።

በዚህ መሰረትም ፕሮጀክቱን በፍጥነት ሥራ ለማስጀመር ስምምነት ላይ መደረሱ ነው የተገለጸው።

የሆስፒታል ግንባታ ሂደቱ ሁለት ምዕራፎች የሚኖሩት ሲሆን፥ የመጀመሪያው ምዕራፍ የህንፃ ግንባታውንና የባለሙያዎች ስልጠናን የሚያካትት ይሆናል።

እነዚህን ሥራዎች ተፈጻሚ ለማድረግም የኳታር ልማት ፈንድ 18 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የመደበ መሆኑ ተገልጿል።

በሌላ በኩል የልዑክ ቡድኑ ከኳታር ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እና ከተለያዩ የጤና ተቋማት ኃላፊዎች ጋር በዘርፉ ትብብር ለማድረግ እንዲቻል የጎንዮሽ ውይይቶችን ማካሄዱን በኳታር የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።

ከዚህ በተጨማሪም በእድሳት ላይ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ትምህርት ቤት የጎበኘ ሲሆን፥ በኤምባሲ በሚገኘው የኮሚዩኒቲ መጠለያ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችንም አነጋግሯል።

ኤፍቢሲ

ኤጀንሲው ለ1ነጥብ 5 ሚሊዮን ዜጎች የስራ እድል መፈጠሩን ገለጸ

የፌዴራል ከተሞች ሥራ ዕድል ፈጠራና ምግብ ዋስትና ኤጀንሲ ለ1ነጥብ 5 ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎች በመደበኛና በመንግሥት ግዙፍ ፕሮጀክቶች ላይ የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉን አስታወቀ።

የኤጀንሲው የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቡድን መሪ ወይዘሮ አቦዘነች ነጋሽ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለፁት፤ በበጀት ዓመቱ 1ሚሊዮን 813ሺ93 ለሚሆኑ ዜጎች በመደበኛና በመንግሥት ግዙፍ ፕሮጀክቶች ላይ የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ 1ነጥብ 5 ሚሊዮን ለሚሆኑ ዜጎች 87በመቶ ሥራ ማስያዝ ተችሏል ።

የሥራ ፈጠራው ሁለት ዓይነት መሆኑን የሚጠቁሙት ወይዘሮ አቦዘነች፣ በመደበኛ አምስት የሥራ ዘርፎች ጥቃቅንና ማኑፋክቸሪንግ፣ ኮንስትራክሽን፣ ከተማ ግብርና አገልግሎትና ንግድ ላይ 882ሺ98 ፤ በመንግሥት ግዙፍ ፕሮጀክቶች ደግሞ ወደ 712ሺ389 የሥራ ዕድል መፈጠሩን አብራርተዋል። ከተቀጣሪዎቹ ውስጥ 47ሺ387 የሚሆኑ የዩኒቨርሲቲ ምሩቃን ወደ 3ሺ407 አካል ጉዳተኞችና 82 ከስደት ተመላሾች መሆናቸውን የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቡድን መሪዋ አስረድተዋል ።

መንግሥት በበጀት ዓመቱ ለ3ሚሊየን ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ላቀደው ሥራ የኤጀንሲው ድርሻ ከፍተኛ እንደሚሆን የተናገሩት ወይዘሮ አቦዘነች፣ የከተሞች ድርሻ 1ነጥብ 5 ሚሊየን እንደሆነ አስታውቀዋል ።

‹‹በመምራት፣ በማስተባበር በመደገፍ ሥልጠና በመስጠት ዐቅም በማጎልበትና በማብቃት ኃላፊነት አለብን›› ያሉት ወይዘሮ አቦዘነች ፣በዚህ ላይም ኤጀንሲውም ሆነ በክልል የሚገኙ የፌዴራል የሥራ ዕድል ፈጠራ ተቋማት በጣም ከፍተኛ ርብርብ እንደሚያደርጉም ገልጸዋል።

እንደ ወይዘሮ አቦዘነች ማብራሪያ፤ኤጀንሲው ዜጎች በየምዝገባ ጣቢያዎች ወይም ቤት ለቤት እንዲመዘገቡ በማድረግ ሥልጠና እንዲያገኙ በማስተባበር ብድር እንዲያገኙና የመሥሪያ የመሸጫ ቦታዎች እንዲሚመቻች የማስተባበር ሥራውን የመምራት የመከታተል አፈፃፀሙን የመገምገም ነገሮች በዋነኛነት ከሌሎች ተቋማት ከወጣቶች ከሴቶች ጋር በመተባበር ይሰራል፡፡

‹‹በኤጀንሲው ዜጎች የሥራ ዕድል እንዲፈጠርላቸው ይመጣሉ ፤ይመዘገባሉ፤ የማስተባበር ሥራ እንሠራለን ፤የቴክኒክና ሙያ ተቋማት በየክልሉ ያሉ ኤጀንሲዎች የቴክኒክና ሙያ ኤጀንሲዎች የቴክኒክም የኢንተርፕረነርሺፕም ስልጠና ይሰጣሉ›› ሲሉ አብራርተዋል።

አዲስ ዘመን ነሀሴ 14/2011

ኃይለማርያም ወንድሙ

ተግባር !! የቀዳማዊት እመቤት ፅህፈት ቤት ያስገነባቸው አራት ትምህርት ቤቶች በመስከረም ስራ ይጀምራሉ

አዲስ አበባ፡- የአይነስውራን ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤትን ጨምሮ በቀዳማዊት እመቤት ፅህፈት ቤት ከሚገነቡት 21 ትምህርት ቤቶች ውስጥ አራቱ በነሀሴ ወር መጨረሻ ላይ ግንባታቸው ተጠናቆ ለመጪው ዓመት ተማሪዎችን የሚቀበሉ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የጽህፈት ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን ፈንታ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ በኦሮሚያና አማራ ክልሎች የተገነቡትና ሊበን ጭቋላ፣ ጉጂ፣ ጃኮና ሎዛ ማርያምየተባሉት አራት ትምህርት ቤቶች ግንባታ ከ80 እስከ 87 ከመቶ የደረሰ ሲሆን በዚህ ክረምትም ግንባታቸው ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ወደ ስራ ይገባሉ፡፡

አራቱ ትምህርት ቤቶች በመጪው የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን ተቀብለው ለማስተማር ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ሙሉቀን ለተማሪዎቻቸውም የደንብ ልብስና ቦርሳ የሚበረክትላቸው እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

ከዚህም ባሻገር ጅግጅጋ ቁጥር አንድና ሁለት፣ አፋር፣ አሶሳ፣ መተከል፣ አዌ ጉዴና፣ ጋምቤላ፣ ዋግህምራና ሽሬ ትምህርት ቤቶችን በመጪው ዓመት ለማጠናቀቅ ግንባታቸው እየተካሄደ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

በመጪው ዓመት ግንባታቸው ከሚጀመሩት ትምህርት ቤቶችም የደባርቅ፣ ሸካ፣ደቡብ ኦሞና ጌዲዮ ትምህርት ቤቶች የግንባታ ጨረታ የተጠናቀቀ መሆኑንና የደባርቅ ትምህርት ቤትም በመጪው ዓመት ተጠናቆ ወደ ስራ የሚገባ መሆኑን ተናግረዋል።

ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶቹ የሚገነቡት በሁሉም ክልሎች ሲሆን፤ በተለይም የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ተከታትለው ወደ ሁለተኛ ደረጃ እንዳይሄዱ የቦታ ርቀት እንቅፋት በሆነባቸው አካባቢዎች እንደሆነ አቶ ሙሉቀን ተናግረዋል።

ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው በመላው አገሪቱ በ304 ሚሊዮን 832 ሺህ 244 ብር ወጪ 20 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን እና በ400 ሚሊየን ብር ደግሞ አንድ የአይነስውራን አዳሪ ትምህርት ቤት ለማስገንባት ከወራት በፊት የመሰረት ድንጋይ ማስቀመጣቸው የሚታወስ ነው።

አዲስ ዘመን ነሃሴ 13/2011

ጌትነት ምህረቴ

አዲሱ የሰራተኞች የስራ መደብ ምዘና ደረጃዎች ምደባ ሰራተኛው የዜጎችን ፍላጎት በሚያሟላ ስነ ልቦና መንቀሳቀስ የሚስችል መሆኑ ተገለጸ

 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አዲሱ የሰራተኞች የስራ መደብ ምዘና ደረጃዎች ምደባ ሰራተኛው የዜጎችን ፍላጎት በሚያሟላ ስነ ልቦናመንቀሳቀስ የሚስችል መሆኑን የኢፌዴሪ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽንአስተወቀ፡፡

የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ በዛብህ ገብረየስ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባካሄደው የአስቸኳይ ስብሰባ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ባቀረባቸው የሰራተኞች የስራ መደብ ምዘና ደረጃዎች ምደባ እና ተያያዝ ጉዳዮች ዙሪያ ባሳለፈው ውሳኔ ዙሪያ ከፋና ብሮድካስቲን ኮርፖሬት ጋር የስልክ ቆይታ አድረገዋል፡፡

ኮሚሽነሩ በዚሁ ቆይታቸው ውሳኔው የመንግስ ሰራተኞች በልማዳዊ መንገድ ለረጅም ዘመናት በተደጋጋሚ ሲሰሯቸው የነበሩትን ስራዎች በአግባቡ በመመዘን በዘመናዊ አግባብ ስራ እና ሰራተኛን የሚያገናኝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ቀደም ሲል የመንግስት ቢሮክራሲ የሲቪል ሰርቪሽ ማሻሻያ በሚል በተቀረጹ በርካታ ማሻሻያና ማስተካከያዎች ስራዎች ሲመራ መቆየቱን ያስታወሱት ኮሚሽነሩ ውሳኔው በሀገሪቱ እየታየ ካለው ዙሪያ መለስ ለውጦች ጋር አስተሳስሮ ስራ እና ሰራተኛን በአግባቡ በማገናኘት ለእኩል ስራ እኩል ክፍያ የመስጠትን ሂደት ያሳልጣል ብለዋል፡፡

አፈፃፀሙ የደሞዝ ስኬል ሽግግርን አድርጎ የተጠናቀቀው ይህ ፕሮጀክት የደሞዝ ጭማሪ ለማድረግ ወይንም ማስተካካያ የመስራት አለማ እንደሌለውም ነው ያስገነዘቡት፡፡

ሰረተኛው የደሞዝ ልዩነትን ባልተመዘኑ ስራዎችን ለመፈለግ ከመስሪያ ቤት መስሪያ ቤት ወይንም ከዘርፍ ዘርፍ የሚያደረገውን ፍሰት የሚያስቀር መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

በዚህም ሰራተኛው የተመደበበት ቦታ እና የስራ ባህሉ በአደገበት ቦታ ላይ የበለጠ እየዘመነ የዜጎችን ፍላጎት በሚያሟላ ስነ ልቦና መንቀሳቀስ የሚያስችል መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባካሄደው የእቸኳይ ጊዜ ስብሰባ የሲቪል ሰርቪስ ባቀረባቸው የሰራተኞች የስራ መደብ ምዘና ደረጃዎች ምደባ እና ተያያዝ ጉዳዮች ላይ አንዳንድ ማሻሻያዎችን በማድረግ ከሃምሌ 1 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረጉ ውሳኔ ማስተላለፉ ይታወሳል፡፡

በእንቻለው ታደሰ