Category Archives: Head News/መሪ ዜና

የቲቪ ቢዝነስ እየሞተ ነው!! ህትመት ወደ ኦንላይን ገበያ!!

ዛሬ በኢትዮጵያ የግል ቴሌቪዥኖች ህልውና አደጋ ላይ ነው። ችግሩን መቋቋም አቅቷቸው የተዘጉም አሉ። በአብዛኛው የጠላና አልኮል ማስታወቂያ ተሸክሟቸው የነበሩ የቴሌቪዥን ተቋማት ማስታወቂያውን የሚያቅብና ህግ ከወጣ በሁዋላ መንኮታኮታቸውን በአዲስ አበባ በሙያው የተሰማሩ እየገለጹ ነው።

ስም መዘረዘሩ አስፈላጊ ባይሆንም ሰራተኛ የበተኑ፣ የቀነሱ፣ ከነ አካቴውም ያቆሙ አሉ። በተመሳሳይ በዘርፉ ለመሰማራት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ አዳዲስ ነጋዴዎችም ለጊዜው ራሳቸውን ተመልካች ማድረግ መርጠዋ።

ወደ ሳተላይት ለመውጣት ቃል ገብተውና ማስታወቂያ አስለፍፈው የነበሩ አንድም ማስታወቂያ ባማስነገር፣ አለያም ሃሳባቸውን ለጊዜው በመግታት የዩቲዩብ ምሽግ ውስጥ ሆነው በተልመካች ብዛት የሚገኘውን ገቢ እየተቋደሱ ናቸው። እስከመቼም በዚሁ መንገድ እንደሚዘልቁና የራሳቸውን ወጥ ስራ ለተመልካች የማቅረብ አቅማቸውን እንደሚያሳድጉ ፍንጭ አይታይም። የዲሲ ነዋሪ ለዛጎል እንዳለው የዩቲዩብ ገቢ ባለሙያ አሰማርቶ ሙያው የሚጠይቀውን ሁሉ ለማድረግ ስለማይቻል የመንግስት ሚዲያዎችና ማህበራዊ ገጾችን ምንጭ በማድረግ፣ በመቅዳትና በማሰራጨት አሁን እንደሚታየው ከማዝገም ውጪ አማራጭ የለም።

ይኸው አስተያየት ሰጪ እንደሚለው አሁን የሚስተዋለው አካሄድ ሙሉ ለሙሉም ባይባለም ባብዛኛው ” ገበያ ተኮር ወይም ክሊክ ተኮር” በመሆኑ አርእስት በማስጮህ፣ ባብዛኛው ለአሉባልታ ማናፈሻ ፣ የርስ በርስ መላተሚያና የፖለቲካ አጀንዳ ማስፈጸሚያ ሲያልፍም ለገቢ ሲባል ድርጅቶችንና ግለሰቦችን መደብደቢያ ሆኗል። በዚህ ባህሪው መቀጠል ስለማይችል የዩቲዩብ ገበያውም በሂደት ተመሳሳይ ችግር እንደሚገጥመው ይገምታል።

በተመሳሳይ የጋዜጣ ወይም የህትመት ሚዲያዎችም ወደ ኦንላይን ገበያ ማምራታቸው አይቀርም። በአዲስ አበባ የዘርፉ ባለሙያ በማህበራዊ ገጹ ላይ እንዳለው የሕትመት ውጤቶች ቀደም ሲል ጀመሮ በህትመት ዋጋ ንረት ደብዛቸው ጠፍቷል። ያሉትም ቢሆኑ በማስታወቂያ እየተደጎሙ እንጂ የጋዜጣ ሽያጭ የሚያካሂዱት በኪሳራ ነው። አሁን ደግሞ ማስታወቂያውም በወረርሽኙ ምክንያት እየቀነሰ በኪሳራ ማሳተሙ አዳጋች የሆነበት ወቅት ነው። በዚህ መልኩ መቀጠልም አይቻልም።

ሰብለ ዮሃንስ በአገር ውስጥ የሚታተሙ የህትመት ስራዎች ወደ ኦንላይን ገበያ ካመሩ አሁን ባላቸው ይዘት ተፎካካሪ አይሆኑም። ሰብስክራይበርም በሚፈልጉት መጠን አያገኙም ባይ ናት። ስታስረዳ ዛሬ ማህበራዊ ሚዲያዎች ሁሉንም ጉዳይ በየደቂቃው ይዘግባሉ። ተቋማትና ባለስልጣናት መረጃ በማህበራዊ ገጻቸው ያስተላልፋሉ። ዛሬ ምንጭ ተብለው የሚጠቀሱት የባለስልጣናትና የተለያዩ ተቋማት የማህበራዊ ገጾችና የመንግስት ሚዲያዎች ናቸው። በዚህ መነሻ እነዚህን መረጃዎች ደግሞ በማተም ሰብስክራይብ የሚያደርግ አካል ይኖራል ብሎ በጉጉት መጠበቁ አግባብ አይሆንም።

የንግድና ስትራቴጂ ባለሙያ መሆኗን የምትናገረው ሰብለ፣ ሚዲያዎች ወደ ኦንላይን ቢዝነስ ከገቡ ሊነበቡ የሚችሉ፣ ወይም ሊሰሙ የሚችሉ የራሳቸው የሆነ ወጥና ጥልቅ ስራ በየዘርፉ ማዘጋጀት አለባቸው። ይህ ደግሞ ብቃትንና እውቀትን ይጠይቃል።

በውጭ አገር በገንዘብ የሚሸጡ ታሪኮች፣ የምርመራ ሪፖርቶች፣ መረጃዎችና የባለሙያዎች ትንታኔ ለለመደው ህዝብ ከመንግስት ሚዲያና የባለስልጣናት የመረጃ መረብ ወይም ማህበራዊ ገጾች ላይ እየገለበጡ ቀን በመጠበቅ ማተም አዋጪ እንደማይሆን ሰብለ ታሳስባለች። አታሚዎች ይህንን አስቀድመው ሊያስቡበት እንደሚገባም ትመክራለች።

በውጪው ዓለም ማን አንባቢ፣ አምን የዩቲዩብ ወሬ ተከታትይና የማህበራዊ ሚዲያ ምርት አፋሽ እንደሆነ ለማወቅ አሉባልታ የሚናፈስባቸውን ገጾች፣ የገጹን ባለቤቶችና፣ የሚተላለፈውን ወሬ በማየት ስንት ተከታይ እንዳላቸው ማስላት በቂ ነው። ሰብለ እንደምትለው ዲጂታል ሚዲያው ምን ያህል ስራና ጥረት፣ እንዲሁም መረጃን በቅጽበት ውስጥ የማዳረስ የጊዜ ሩጫው ቀላል አይሆንም።

በአገር ውስጥ ደግሞ የኢንተርኔት ጥራትና ፍጥነትም እንዲሁ በትልቁ ግምት ውስጥ የሚገባ ነው!!የኢሳያስ ድንገተኛ ጉብኝት የሞት ዜናውን ወደ ስጋት ቀየረው!! ድንገተኛ ጉብኝት የሞት ዜናውን ወደ ስጋት ቀየረው!!

ኢሳያስ ” በሽታ የለብኝም… የለመድኩት ወሬ ነው “

ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ እንዳያቸው የገለጸ እንደተናገረው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ ላይ ለውጥ አላየባቸውም። መንግስት በመገናናዎቹ እንዳሳየው የተጎዱ፣ ታመው ያገገሙ አይመስሉም።

ከቀናት በፊት Isaias: “Rumour of my health is in the mind of my enemy” ” ሟርቱ በጠላቶቼ አዕምሮ ውስጥ ነው” ያሉት አቶ ኢሳያስ የተወራባቸው የሞት ወሬ ” ለምን መጡ” በሚለው ትንተና ተቀይሯል።

“ኢሳያስ አለፉ” የሚለውን ዜና “በእንኳን ደስ አለህ” ሰበር ዜና ሲቀባበሉና ፍስሃቸውን ሲገልጹ የነበሩት ክፍሎች እስካሁን ማስተባበያ አልሰጡም። እንደ ዜናው ኢሳያስ በማለፋቸው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይና አቶ ወርቅነህ ገበየሁ ወደ ኤርትራ አቅንተዋል ተብሎም ነበር።

ሁሉም አልፎ ኢሳያስ ዛሬ አዲስ አበባ ቤተ መንግስት ናቸው። ለተለያየ የስራ ጉዳይና በኮሮና ወረርሽኝ አማካይነት የተፈጠረውን ስጋት አስመልክቶ እንደሚወያዩ ከመነገሩ ውጪ ሌላ የተባለ ነገር የለም።

——————————————————————————————————–

ሰሞኑን ፕሬዚዳንት ኢሳያስን አስመልክቶ  የሚናፈሰው ወሬ ከታማኝ የዜና ምንጮች ማስተባበያ ባይሰጥበትም በህይወት የመቆየታቸውና የመኖራቸውን  ጉዳይ የመጨረሻው ቁርጥ ቀን መቃረቡን  የሚያመላክቱ  መረጃዎች ማግነቱን ኢሬና  ታማኝ ምንጮች ነገሩኝ ሲል አየሩን አውኮት ነበር። ኤርትራ እንዴት ትቀጥል በሚለው ጉዳይ ጀነራሎች ስብሰባ ተቀምጠው ውሳኔ ማስተላለፋቸውን ተናግሮ ነበር።

ራዲዮ ኢሬና / ERENA / በመባል የሚታወቀው የኤርትራ መንግስት ተቃዋሚ  ሚዲያ  በተጠቀሰው እለት በየሰዓቱ በሚያስተላልፈው ተደጋጋሚ ዜና ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ኮማ ውስጥ እንዳሉ እየገለፀ ያውጅ ነበር። 

ኢሬና በተደጋጋሚ እንደዘገበው  የኤርትራ ጀነራሎች በትናንትናው በወቅቱ አስቸኳይ ስብሰባ ተቀምጠው ታሪካዊ የተባለ ውሳኔና ሹመት  አካሂደዋል። በዚሁ  ስብሰባ ፕሬዚዳንቱ በጊዚያዊነት አገር እንዲያስተዳድሩ የሰየሙዋቸው ጀነራል ተክሌ ማንጁስ ውክልናቸውን ተነስቷል፣ በዚሁ ውሳኔ መሰረት  ጀነራል ስብሃት ኤፍሬም ጦሩን እንዲመሩ፣ የማነ ቻርሊ የፕሬዚዳንቱን ጽ/ቤት እንዲያስተዳድሩ፣ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ የማነ ገብረ አብ የፖለቲካ ጉዳዮችን በበላይነት እንዲቆጣጠሩ ሃላፊነት መውሰዳቸው ተበስሮ ነበር።

ጀነራሎቹ ቀጣዩን የኤርትራ ጉዳይ “ አገራዊ መግባባት “ በሚሰፍንበት መልኩ ለማስቀጠል ይቻል ዘንድ በፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፉወርቂ ላይ ኩዴታ ለማካሄድ ሲያሴሩ ተደርሶባቸዋል በሚል በእስር ላይ ያሉት ከፍተኛ ባለስልጣናት እንዲፈቱ እንደወሰኑ፣ የሞቱም ካሉ ለቤተሰቦቻቸው መርዶ እንዲነገር ከስምምነት ላይ መድረሳቸውንም ነበር ኢሬና ሲተነትን የነበረው።

በኢትዮጵያ የስደት መንግስት ያቋቋሙትን የኤርትራ መንግስት ተቃዋሚዎች ስብስብ “ የኤርትራን ነፃ አገርነት አሳልፈው የሸጡ ከዳተኞች “ በማለት የሚጠራው ይህ ራዲዮ በቅርቡ በአየር ሃይል ውስጥ ከፍተኛ ሃላፊነት ስለተሰጣቸው        የፕሬዚዳንት  ኢሳያስ ልጅ በግልፅ የሰጠው አስተያየት አልነበረም።

ጀነራሎቹ ያሳለፉትን ውሳኔ  ከኩዴታ ጋር ያያዘው ኢሬና ራዲዮ የፕሬዚዳንት ኢሳያስን ጤንነት አስመልክቶ ከኳታር ወደ ዱባይ መዛወራቸውን ምንጮቹን በመጥቀስ አስታውቋል። በዘገባው በተደጋጋሚ ፕሬዚዳንቱ ራሳቸውን እንደማያውቁ አመልክቷል።በማያያዝም ወደ ዱባይ የተዛወሩት ለጉበት ለውጥ መሆኑንም ተናግሯል።

ክትትል እያደረገ በየሰዓቱ መረጃ የሚያቀብለው ሬዲዮ የኢትዮጵያ መንግስት በኤርትራ ጉዳይ ጣልቃ መግባት እንደሌለበት እየወተወተ ነበር። ከኢትዮጵያ በኩል ምንም ዓይነት መረጃ ባይሰጥም በኢትዮጵያ መንግስት ሙሉ በሙሉ የሚደገፈው  የተቃዋሚዎች ህብረት አንድ ቀን ቀደም ብሎ ባወጣው መግለጫ በኤርትራ አስተማማኝ ሰላምና ዴሞክራሲ የሚሰፍንበት ቀን መቃረቡን የገለፀው ህዝቡን በመማፀን ነበር። ይህ ሁሉ የተባለው በApril 27, 2012 የዛሬ ስምንት ዓመት ነበር። ኢሳያስ ኖረው ለዳግም የሞት ዜና ሲበቁ ኢሬና የተሰኘውና ፈረንሳይ የሚገኘው ሬዲዮ ጉዳይ ግን ብዙም አይሰማም።

እሳቸው የሚከተለውን መለሱ

ኢሳያስ ” በሽታ የለብኝም… የለመድኩት ወሬ ነው “

 “ እኛ ተመስገን ብለን አስራ ሁለት ሰዓት ስንተኛ፣ ውሸታሞቹ ሃያ ሶስት ሰዓት ከሃምሳ ዘጠኝ ደቂቃ እንቅልፍ የላቸውም ”

እንደተለመደው በቀላል አለባበስ አደባባይ ወጥተው “ እድለኛ ነኝ፣ በሽታ የለብኝም፣ በሽታው ወሬው ነው ” በማለት ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፉወርቂ ሲወራባቸው ለነበረው ሁሉ ምላሽ ሰተዋል። ፕሬዚዳንቱ ለERI – TV ለሰላሳ ደቂቃ በሰጡት  መግለጫ ሞተዋል፣ በጠና ታመዋል፣ አይተርፉም በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ “ የለመድኩት ወሬ ነው፤ ፊትም አልሰጠሁትም ” በማለት ሲወራባቸው የነበረውን ሁሉ በዜሮ አባዝተውታል።

ኤፕሪል 28/ 2012 በአስመራ አቆጣጠር 8 pm ላይ መግለጫ የሰጡት አቶ ኢሳያስ ይህ ሁሉ ሲወራባቸው ለምን ምላሽ እንዳልሰጡ ለተጠየቁት ሲመልሱ የሰጡት ምላሽ ግልፅ ባይሆንም ባለፈው ሳምንት አገር ቤት እንዳልነበሩ አላስተባበሉም። ስሙን ካልጠቀሱት የሄዱበት አገር ሲመለሱ ጋሽ ባርካን ጨምሮ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍል የፕሮጀክቶች ጉብኝት ላይ ነበሩ። አስራ አራት ሰዓት ያለማቋረጥ ጉዞ እንዳደረጉ ያመለከቱት አቶ ኢሳያስ፣ ረጅም ሰዓታት በድካም መተኛታቸውን አስረድተዋል።

ከዚያም እንቅልፉ ሳይለቃቸው የፕሬስ ፀሃፊያቸው ከሰጠቻቸው ወረቀቶች ላይ ስለሳቸው ሲወራ የነበረውን መመልከት እንደቻሉ ተናግረዋል። “ሞባይል የለኝም፤ ኢንተርኔትም አልጠቀምም ” የሚሉት አቶ ኢሳያስ የተወራውን ሁሉ እንደንፋስ እንደሚቆጥሩት አስምረውበታል። ውሸት በተወራ ቁጥር ቴሌቪዥን ላይ በመውጣት ማስተባበያ መስጠት እንደማይቻል በመጠቆም የተወራባቸውን ክፉ ወሬ ያመከኑት ፕሬዚዳንቱ “ እኛ ተመስገን ብለን አስራ ሁለት ሰዓት ስንተኛ፣ ውሸታሞቹ ሃያ ሶስት ሰዓት ከሃምሳ ዘጠኝ ደቂቃ እንቅልፍ የላቸውም ” ብለዋል።

“ አሁን ” አሉ አቶ ኢሳያስ “ አሁን ውሸቱ ሁሉ አርጅቷል። አልቋል ” የኤርትራ ህዝብም ሆነ በውጪ አገር ያሉት ተረጋግተውና  በየሚሰሙትን ሁሉ እንደማስታወቂያ ባለመቀበል ህይወታቸውን እንዲመሩ ጥሪ አቅርበዋል። እስካሁን ለምን ዘገዩ በሚል ለተጠየቁት ውሸታሞች የሚሉዋቸው  ራሳቸውን እንዲያስተካክሉ እድል ለመስጠት በማሰብ እንደሆነ ጠቁመዋል።

ስለ እሳቸው መጥፎ ሲወራ አስር ዓመት በላይ መቆየቱን ያወሱት ፕሬዚዳንቱ፣ መንግስት ቢቀየር ፖለቲካው አንድ አይነት መሆኑን፣ የሚቀየር ነገር ቢኖር የፖለቲካው ገጽ እንደሆነ አመላክተዋል። “ ሁልጊዜ አንድ እብድ ወይም ውሸታም በተናገረ ቁጥር የቴሌቪዥን መስኮት ላይ እየቀረቡ መናገር ቁብ እንደሌለው ደጋግመው ተናግረዋል።

አሜሪካ ውሽጥ ያለ አንድ የሽያጭ ሰራተኛ ለገበያ ለማቅረብ  ያሰበውን እቃ እንዴት እንደሚያስተዋውቅና የተጠቃሚዎችን አዕምሮ በማሳመን  እንዴት እንደሚሸጥላቸው እንደሚያስብ ሁሉ፤ ዝም ብሎ እንደሚነፍስ ንፋስ የተሰየሙት ውሸታሞች የመገናኛ ቴክኖሎጂን በተሳሳተ መንገድ በመጠቀም የስነልቦና ጦርነት ማካሄዳቸውን ፕሬዚዳንቱ ገልፀዋል። በዚሁ መነሻ አሉ የሚባሉት ታላላቅ አገሮች ቴክኖሎጊን ህዝብ ለማስጨነቅ፣ ለመረበሽና ለማደናገር  እንደሚጠቀሙበት አመልክተዋል።

የጠጣርና የፈሳሽ ቸኮሌት ማስታወቂያ በመመልከት የቱ ይጠቅመናል ብለው ሳያስቡ መጎምጀት እንደማይጠቅም አቶ ኢሳያስ የተናገሩት ወደፊት ብዙ ይወራልና የምትሰሙትን ሁሉ አትመኑ የሚል መልዕክት ለማስተላለፍ ነበር። ስምንትና ዘጠኝ ታላላቅ አገራት ውስጥ  “ ዴሞክራሲ ተብዬ ”  እንጂ እውነተኛ የሰው ልጆች መብት አንደማይከበርባቸው ያወሱት ፕሬዚዳንቱ፣ አገራቱ ከወታደራዊ በጀታቸው በላይ የስለላ በጀታቸው እጅግ የናረ መሆኑን ጠቁመዋል።

እንደሚፈለገው እድገት ባይመዘገብም አሁን ያለው ጅምር አበረታች መሆኑን መላልሰው የጠቀሱት አቶ ኢሳያስ እንዲህ ያለው ወሬ ለምን እንደተወራባቸው፣ ምንጩ ከየት እንደሆነ፣  የሚያወሩት ሰዎች፣ ….የማወቅ ፍላገት እንዳላቸው አቶ ኢሳያስ አልሸሸጉም። አያይዘውም  የወሬው መነሻ ምክንያት ግልፅ እንዳልሆነላቸው ገልፀዋል።

በመግለጫቸው ማንንም በስምም ሆነ በድርጅት ደረጃ ጠርተው ለጉዳዩ ተጠያቂ ሳያደርጉ መግለጫ የሰጡት አቶ ኢሳያስ ህክምና ስለማድረጋቸውም ሆነ፣ አለባቸው ስለተባለው ህመም አንድም የተናገሩት ነገር የለም። የሳቸው መግለጫ እንዳበቃ በኢትዬጵያ መንግስት የሚደገፈውና ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጋር ሰዓት ተጋርቶ ዝግጅት የሚያቀርበው ዳሃይ ኤርትራ በፕሮግራም ለኤርትራ ህዝብ ጥሪ አቅርቧል።

የፕሬዚዳንት ኢሳያስን የጤና መጓደል በተመለከተ “ አጋጣሚውን በመጠቀም አዲሲቷን ኤርትራ ለመመስረት እንነሳ ” ሲል ለወታደሮችና ለህዝቡ ጥሪ አቅርቧል።

በትናንትናው እለት የኤርትራ ጀነራሎች አስቸኳይ ስብሰባ በማድረግ የስራ ክፍፍል ማድረጋቸውንና የፕሬዚዳንቱ ጤንነት የከፋ ደረጃ ላይ መድረሱን ያስታወቀው ከፈረንሳይ የሚተላለፈው ERENA ኢሬና ራዲዮ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አደባባይ ወጥተው መግለጫ ስለመስጠታቸው  ያቀረበው  አስተያየት የለም። ዜናውንም አላስተባበለም።

ኢሬና ራዲዮ ጁላይ 15/2009 ከኤርትራ በተሰደዱ ጋዜጠኞች የተቋቋመና በሪፖርተር ዊዝ አውት ቦርደርስ የሚታገዝ፣ በኤርትራ ያለውን የፕሬስ ነፃነት ለማመጣጠን የሚሰራ ሚዲያ ነው።

የጦር መሳሪያ ማስመዝገብና በየዓመቱ ግብር መክፈል ግዳጅ መሆኑ ተደነገገ

የጦር መሣሪያን የመያዝ፣ የመግዛትና የመሸጥ ሥርዓቱ በመንግሥት እውቅና ብቻ የሚያደርግ ዓዋጅ ሥራ ላይ መዋሉንና የመሳሪያ ፈቃድ በየዓመቱ ማደስና ግብር መክፈል ግድ መሆኑንን ፋና ወይዘሮ አዳነች አቤቤን ጠቅሶ ይፋ አደረገ።

የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ጋር ባደረጉት ቆይታ ዓዋጁ በጦር መሣሪያ ዝውውርና አስተዳደር ላይ የነበረውን የሕግ ክፍተት ይሞላል።

በቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት በመንግሥት ኃላፊነት የተሰጣቸው አካላት ዓዋጁን በማስተግበር የጦር መሣሪያ ያለው ግለሰብም ይሁን ተቋም ምዝገባውን የማድረግ ግዴታ እንዳለባቸው ገልጸዋል።

የጦር መሣሪያ የያዘና ያስመዘገበ ሁሉ እንዲይዝ እንደማይፈቀድና ፈቃድ የሚሰጠው ተቋም ወይም ግለሰብ በዓዋጁ መሰረት ህጋዊ የሚያደርጉትን መስፈርት አሟልቶ መገኘት እንደሚጠበቅበት ወይዘሮ አዳነች አብራርዋል።

ዓዋጁ የአገር ውስጥ ድርጅቶችንና ሌሎች አካላትንም የሚያይበት ሕጋዊ አካሄድ እንዳለውም ዐቃቤ ሕጓ ገልጸዋል።

በመሆኑም ማንኛውም በአገር ውስጥ የሚንቀሳቀስ ድርጅት የጦር መሣሪያ እንቅስቃሴውም ይሁን ይዞታው ህጋዊነቱ የተረጋገጠና በውል የሚታወቅበት አሰራር ይዘረጋለታል ብለዋል።

በኢትዮጵያ እስካሁን ድረስ የጦር መሣሪያዎችን የመሸጥና የማዘዋወር ህጋዊ እውቅና የተሰጠው አካል ባለመኖሩ ግዥና ዝውውሩ የሚካሄደው ህግን ባልተከተለ መንገድ ነበር።

ይሁን እንጂ የጦር መሣሪያውን የገዛው አካል የምዝገባ መስፈርቱን ካሟላና ወንጀል ያልተሰራበት መሆኑ ከተረጋገጠ አስመዝግቦ መያዝ ይፈቀድለት እንደነበርም ይታወቃል።

አሁን ተግባር ላይ የዋለው ዓዋጅ አሰራሩ ሙሉ በሙሉ እንደሚያስቀርና የጦር መሣሪያን ሽያጭና ዝውውር የሚከታተል በመንግሥት እውቅና የሚሰጠው አካል እንደሚኖርም ወይዘሮ አዳነች አስረድተዋል።

በዓዋጁ መሠረት ለጦር መሣሪያ የሚሰጠው ፈቃድ በየዓመቱ ይታደሳል፤ ባለ ፈቃዱም በየዓመቱ ክፍያ ይፈጽማል።