Category Archives: ህግ

ይህ ዓምድ ህግ ነክ ጉዳዮች ለግንዛቤና ለመረጃ ይረዳ ዘንድ የሚስተናገድበት ነው። ዓምዱ ቀደም ያሉ ብይኖችና የህግ አግባቦችን ያካትታል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ አራት ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ለመከላከያ ምስክርነት እንዲቀርቡ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ብይን ሰጠ፡፡

የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ በመሠረተባቸው የሽብር ተግባር ወንጀልና ከባድ የማነሳሳት ወንጀል እንዲከላከሉ ብይን የተሰጠባቸው አቶ ጉርሜሳ አያኖ፣ አቶ አዲሱ ቡላላ፣ አቶ ደጀኔ ጣፋና አቶ በቀለ ገርባ፣ በመከላከያ ምስክርነት የቆጠሯቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝና የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ ባለሥልጣናት ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀሩ፡፡

ተከሳሾቹ አባልና አመራር የሆኑበትን የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) የፖለቲካ ድርጅት በሽፋንነት በመጠቀም፣ በሰው ሕይወትና ንብረት ላይ ጉዳት በማድረስና በኃይል የፖለቲካ ሥልጣን ለመያዝ የሚንቀሳቀሰው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አባል በመሆን፣ ዓላማውን ለማሳካትና፣ በአገሪቱ ሁከትና ብጥብጥ እንዲነሳ ማድረጋቸውን ዓቃቤ ሕግ በክሱ ጠቅሶ ማስመስከሩ ተገልጿል፡፡ በመሆኑም ዓቃቤ ሕግ እንደ ክሱ ማስረዳቱን ፍርድ ቤቱ ገልጾ፣ በሰጠው ብይን ሦስቱ ተከሳሾች በሽብርተኝነት አዋጁ አንቀጽ 3(3፣4፣ እና 6) ሥር የተደነገገውን ማለፋቸውን ማስረዳት መቻሉን ጠቁሞ እንዲከላከሉ ፍርድ ቤቱ ብይን ሰጥቷል፡፡ የአቶ በቀለ ገርባን ግን ወደ ወንጀል ሕግ አንቀጽ 257 (ሀ) በመቀየር በከባድ ማነሳሳት እንዲከላከሉ ብይን መስጠቱ ይታወሳል፡፡

በመሆኑም ተከሳሾቹ የመከላከያ ምስክር እንዳላቸው ለፍርድ ቤቱ ገልጸው፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝን፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔን አቶ አባዱላ ገመዳን፣ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ለማ መገርሳን፣ ምክትላቸውን ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) እና ሌሎችንም በመከላከያነት ቆጥረው ነበር፡፡ ምስክሮቹ መጥሪያ እንዲደርሳቸውና የመከላከያ ምስክርነቱ ከማክሰኞ ጥቅምት 28 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ እንዲሰማም ትዕዛዝ ተሰጥቶ ነበር፡፡

ፍርድ ቤቱ በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ጥቅምት 28 ቀን 2010 ዓ.ም. ተከሳሾቹ የቀረቡ ቢሆንም፣ የመከላከያ ምስክሮች አልቀረቡም፡፡

የእነ አቶ በቀለ ገርባ ጠበቃ አቶ አመሐ መኰንን ቀጠሮው ቀደም ብሎ የተሰጠ መሆኑን አስታውሰው፣ ለምን እንዳልቀረቡም ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ መጥሪያው ወጪ እንዳልተደረገ ገልጾ፣ መመካከርና ማየት እንዳለበት በማስታወቅ ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠት አስፈላጊ መሆኑን ገልጿል፡፡

በዚህ መሀል አቶ በቀለ መናገር እንደሚፈልጉ አመልክተው ሲፈቀድላቸው፣ ‹‹በምስክሮች አቀራረብ ላይ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ የምስክር ትንሽና ትልቅ የለውም፡፡ እኛ በእስር ቤት ዕቃ አይደለንም፡፡ መጥሪያ አልደረሰም ከተባለ መጻፍ ነው፤›› በማለት ተናግረዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ አቶ በቀለ ለተናገሩት ምላሽ ሳይሰጥ ለኅዳር 6 ቀን 2010 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

Reporter Amharic ታምሩ ጽጌ

ሰው መርዳት ሽብርተኛ የሚያስብለበት አገር

ንግስት ይርጋ ፣ በአቃቢ ሕግ የቀረበበሽ የሽብርተኛ ክስ ተገቢ ነው በሚል ፍርድ ቤቱ እንድትከላከለ ዛሬ ወስኗል። አቃቤ ሕግ “ንግስት ይርጋ ሽብርተኛ” ናት ብልኦ ሲቀርብ ካቀረባቸው ክሶች መካከል

– በጎንደሩ ሰልፍ የቆሰሉትን ለማሳከም የለበሰችውን ልብስ አውልቃ ከ5ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ማሰባሰቧ
– የኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን ፎቶ ባነር ማሰራቷ
– የኮለኔል ደመቀ ፎቶ ያለበትን ቲሸርት በ120 ብር መግዛቷ
– ሰልፉ በሰላም በመጠናቀቁና በወጣቱ ተስፋ ስላለው እትዬ ጣይቱ ብሎ ስለተጠራች

እንግዲህ ምን ያህል በአገራችን የፍትህ ስርዓት እንዳለ በንግስት ላይ ከቀረበው አሳፋሪ. አስቂኝ ክስና ከፍርድ ቤቱ ዉሳኔ መረዳት እንችላለን።

ፍርድ ቤቱ ይሄን ዉሳኔ የወሰነው ከሕወሃት ደህንነት የፖለቲካ መመሪያ ስለተሰጠው መሆኑን የሚጠራጠር ይኖርል ብዬ አላስብም። ሕወሃቶች ደግሞ ለጎንደር ሕዝብ ትልቅ ንቀትና ጥላቻ ስላላቸው፣ ንግስት ይርጋን ፈቱ ማለት የጎንደርን ህዝብ አስደሰቱ ማለት ስለሆነባቸው ብቻ ነው፣ በበቀል ይችን እህት በወህኒ እንድትቆይና እንድትሰቃይ የሚያደርጉት።

ህዝቡ ይሄን ማወቅ ያለበት መሰለኝ። ” ንግስት ይርጋ የአማራው ክልል ሕዝብን አመላካች ናት“ ብዬ ቀደም ሲል እንደጻፍኩት፣ በንግስት ላይ የተወሰነው ዉሳኔ ፣ በአማራው ክልል ሕዝብ ላይ የተወሰነ ዉሳኔ ነው። ንግስት ይርጋ በጎንደሩ አስደማሚ ሰልፍ ላይ የኮሎኔል ደመቀ ምስል ያለበትን ቲሸርት አድርጋ ነበር። በቲሸርቱ ላይ “ የአማራ ህዝብ አሸባሪ አይደለም” የሚልም ተጽፎ ነበር። ሆኖም ግን እነ ንግስት ይርጋ ፍጹም ሰላማዊ በነበረው በጎንደር ሰልፍ ላይ በመገኘታቸው ብቻ የሽብርተኛ ክስ ተቀባይነት ካገኘ፣ ሕወሃት “የአማራ ህዝብ አሸባሪ ነው” የሚል ዉሳኔ እንዳሳለፈ ነው መወሰድ ያለበት።

“አሸባሪ ነህ” የተባለ ህዝብ ፣ የተናቀ ህዝብ፣ አንገቱን እንዲደፋ የተደረገ ሕዝብ፣ ልጆቹን እያስበላ ያለ ህዝብ፣ በብአዴኖች ድለላና የቂቤ ንግግር እየተታለለ መቀመጥ ያለበት አይመስለኝም።

ሕወሃቶች የክልሉ ህዝብ ላይ በበቀል ነው የተነሱት። ይህ ህዝብ ካልተዳከመ ፣ ካልተመታ በስልጣናችን መቆየት አንችልም የሚል የፖለቲካ ስትራቴጂ ነው ያላቸው።

ግርማ ካሳ

በእነ ንግስት ይርጋ ብይን ላይ ከተነሱት መካከል አንዳንድ ነጥቦች

ትዝብት፡ በጌታቸው ሽፈራው 

1ኛ ተከሳሽ: ንግስት ይርጋ

  • የቆሰሉትን (በጎንደሩ ሰልፍ) ለማሳከም የለበሰችውን ልብስ አውልቃ  ከ5ሺህ ብር በላይ አሰባስባለች
  • የኮለኔል ደመቀ ዘውዱን ፎቶ ባነር አሰርታለች
  • የኮለኔል ደመቀ ፎቶ ያለበትን ቲሸርት  በ120 ብር ገዝታለች
  • ሰልፉ በሰላም በመጠናቀቁና በወጣቱ ተስፋ ስላለው እትዬ ጣይቱ ብሎ እንደጠራት……………

4ኛ ተከሳሽ አወቀ አባተ

የሽብር ቡድኑ አባል ፎርም  እንዲሞላ አድርጎት  ፎርሙን በመሙላት በግልፅ የሽብር ቡድኑ አባል በመሆን፡፡ (ግንቦት ሰባት ምርጫ ቦርድ እውቅና እንደሰጣቸው ፓርቲዎች አባሌ ሁን እያለ ፎርም ካስሞላ የዘመኑ ቀልድ ነው የሚሆነው)
5ኛ ተከሳሽ በላይነህ አለምነህ

“ቀይ ካርድ” ይዛችሁ  አደባባይ በመውጣት መንግስትን በኃይል ታገሉ እንዳለ… …(ቀይ ካርድ አፈሙዝ እለው እንዴ? ቀይ ካርድ ከኃይል ትግል ጋር ከተያያዘ በየ ሳምንቱ ጎንደር አደባባይ ላይ ብቻ ሳይሆን መስቀል አደባባይ አጠገብ፣ ስቴዲየም ቀይ ካርድ ሲመዙ የሚውሉ ዳኞችም እንደነ አወቀ አባተ የግንቦት 7ትን ፎርም ሞልተዋል ተብለው የአቃቤ ህግ ክስ እንዳይቀርብባቸው ያሰጋል!)

በሌላ በኩል፣ ዓቃቤ ሕግ ባቀረበው የሰነድ ማስረጃ እነ ንግስት ይርጋ  በ01/11/2009 ዓ.ም የተጻፈው የሰነድ ማስረጃ  ለፍርድ ቤቱ መቃወሚያ አስገብተው ነበር። ከአሁን ቀደም ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ ተመሳሳይ መቃወሚያ አስገብተው የአማራ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ብይን ሰጥቶላቸዋል። የአማራ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይህን   ያደረገው ኮ/ል ደመቀ ይከላከሉ አይከላከሉ የሚለውን ከመበየኑ በፊት ነው። 

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት እነ ንግስት  ያስገቡት የሰነድ ማስረጃ መቃወሚያ ላይ ብይን ሳይሰጥ ወደ ዋናው ብይን ገብቷል። የንግስት ጠበቃ ከብይኑ  በኋላ ፍርድ ቤቱ ያቀረቡትን የሰነድ መቃወሚያ ሊያይላቸው ይገባ እንደነበር ቅሬታቸውን አሰምተዋል። የሰነድ ማስረጃ መቃወሚያው ከዋናው ብይን ቀድሞ እንዲታይ የሚጠየቀው አግባብ አይደሉም የተባሉ የሰነድ ማድረጃዎችን መሰረት ተደርጎ ይከላከሉ ወይንስ አይከላከሉ የሚባል ብይን ሊሰጥ አይገባም በሚል ነው።

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት በእነ ነጋ የኔነው የክስ መቃወሚያ ብይን ላይ  የፌደራል ፍርድ ቤት ስልጣን የለውም ያለው የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ስልጣን ስር የሆነውን የኮ/ል ደመቀ ዘውዱ ጉዳይ ላይ የደህንነት መስርያ ቤቱ የፃፈው ሪፖርት በድምፅ ካልታገዘ በስተቀር በሰነድ ማስረጃነት ሊቀርብብኝ አይገባም ብለው ያቀረቡት የሰነድ መቀወሚያ ከብይኑ በፊት ተቀባይነት ማግኘቱ የሚታወስ ነው።  የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይሄ ስልጣን የለውም ያለው ችሎት ግን  የቀረበውን መቃወሚያ በዝምታ አልፎታል። 

የንግስት ጠበቃ እንደገለፁልኝ በህጉ አንቀፅ በ146 ላይ እንደተደነገገው መቃወሚያ የቀረበ እንደሆነ ፍ/ቤቱ በማስረጃው ላይ ለቀረበው ክርክር ወዲያውኑ ይወስናል።  ፍርድ ቤቱ የእነ ንግስትን የሰነድ ማስረጃ መቃወሚያ  በዝምታ ማለፉ የስነ ስርዓት እና መብት ጥሰት ነው ብለዋል ጠበቃው!

እስር ቤት ውስጥ ህይወቱ ያለፈው አርማዬ ዋቄ ማሞ “አይኔ እያየ ፊቴ ላይ ነው ልቡን ረግጥ የገደሉት”

(በጌታቸው ሺፈራው)

Image may contain: 1 person, closeupስም:_ አርማዬ ዋቄ ማሞ

ዕድሜ:_ 25

አድራሻ –  አዲስ አበባ፣ ኮልፌ ክ/ከ፣ ወረዳ 05፣ የቤት ቁጥር 1190

ስራ – ቧንቧ ጥገና

የታሰረበት ወቅት – ነሃሴ 2008ዓም

መጀመርያ የገባበት ክስ – እፅ ይዞ መገኘት

ሁለተኛ ክስ (የተደበደበበት) –  በ28/12/2008 በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ውስጥ ማረሚያ ቤቱ የሰጠውን ዩኒፎርም ና የሌሎቹን ዩኒፎርም ያቃጠለ በመሆኑ፣ የዞን አንድ መኝታ ቤት ሁለት መስታውት በመጥረጊያ እንጨት የሰበረና የዞን አንድ መኝታ ቤት ሶስቱን ግድግዳ ከሌሎች ግብረአበሮቹ ጋር በመሆን በብረት ያፈረሰ በመሆኑ

የክስ መዝገብ:_ በእነ ብስራት ብርሃኑ 15ኛ

የሞተበት ቀን:_ መስከረም 2/2010 ዓም ንጋት

የአርማዬ ዋቄ አባት፣ አቶ ዋቄ ማሞ ቃል:_

የአርማዬ ታናሽ ወንድሙ ቴዎድሮስ ዋቄ ተፈርዶበት ዝዋይ ታስሮ ነበር። በሌላ ክስ ቀጠሮ ስለነበረው ኮልፌ ቀራኒዮ የሚገኝ ፍርድ ቤት ይቀርባል። በወቅቱ አርማዬ የወንድሙን ችሎት ለመከታተል ፍርድ ቤቱ በር ላይ ተቀምጦ ነበር። በጊዜው የፅዳት ሰራተኞች ከሽንት ቤት ያገኙትን ነጠላ ጫማ የማን ነው እያሉ ይጠይቃሉ። ፖሊስ ግን ነጠላ ጫማውን ተቀብሎ ለአርማዬ ሰጠው። እሱ የእኔ አይደለም ብሎ ተከራከረ። ደብድበው፣ የአንተ ነው ብለው አስያዙት። እፅ ይዞ በመገኘት እሱንም ወንድሙንም ከሰሷቸው።

ከቂሊንጦ ቃጠሎ በኋላ ሸዋሮቢት ለምርመራ ተወስዶ ነበር። ሄጄ ጠይቄዋለሁ። ፊቱና እጁ አብጦ ነበር። እየደበደቡት እንደሆነ ነገረኝ። ቁጥጥር ስለነበር ብዙ ማውራት አልቻልንም። በቁምጣ፣ ራቁቱን ማለት ይቻላል የነበረው። እግሩ ላይም የድብደባ ምልክት ይታያል። ቂሊንጦ ሲመለስም ድብደባው የባሰ ነበር።ማታ ማታ እየደበደቡት መሆኑን ነግሮኛል። የጨብጥ በሽታ ነበረበት። ህክምና አላገኘም። ሸዋሮቢት ብልቱ ላይ ውሃ በሀይላንድ ሞልተው ስላንጠለጠሉበት ሱሪ መልበስም እንደሚቸገር ነግሮኛል። 2009 ክረምት ላይ ለ15 ቀን ከሌሎች ጓደኞቹ ጋር ተወስዶ ጨለማ ቤት ገብቶ፣ ራቁቱን ተደብድቧል። ቂሊንጦ ውስጥ ይደበደብ የነበረው ታሳምፃለህ ተብሎ ነው። እሱ አዲስ አበባ ቢወለድም የቤተሰብ የትውልድ ቦታ አምቦ መሆኑ እየተጠቀሰ ኦነግ ነህ እየተባለ ተሰቃይቷል። እንደሚገድሉት ዝተውበት ነበር። ይህን ነግሮኛል።

ቤተሰብ በሳምንት አንድ ቀን ነበር የምንጠይቀው። ነገር ግን በድብደባውና በዛቻው ምክንያት እንደሚገድሉት ስለሚያውቅ “በሳምንት ሶስት ጊዜ ጠይቁኝ። ከገደሉኝ አስከሬኔን ለመውሰድ እንኳ ቶሎ ቶሎ መጥታችሁ ጠይቁኝ” ብሎናል። መስከረም 1/2010 በዓሉን ውለን በነጋታው ነው የሄድነው። መስከረም 2 ጠዋት ሄደን ስንጠይቅ ሆዱን አሞት ሀኪም ቤት እንደሄደ፣ ከሰዓት 9 ሰዓት ላይ እንደሚመለስ ነገሩን። ነገር ግን ቤት ከተመለስብ በኋላ ወደ ማታ ለእህቱ ደውለው ጳውሎስ ሆስፒታል አስከሬኑን ውሰዱ አሏት። በምን እንደሞተ ለእኔ ግልፅ ነበር። አስከሬኑን አይቸዋለሁ። መሃል አናቱ ተጎድቷል።ፈርሷል። ሌላ አካሉ በሙሉ አብጧል።ሆዱ ተቀዶ እንደነገሩ ተሰፍቷል። ልቡና ኩላሊቱ እንደሌለ ነው መገመት የቻልኩት። እንደነገሩ ስለሰፉት እነዚህ አካላቱ መውጣታቸውን ያሳያል። እኛ በምን እንደሞተ ስለምንገምት በፋሻ ነው እንጅ በባዶ እጃችን አልነካነም። የሆስፒታሉን ምርመራ ውጤት መቀበል አላስፈለገኝም ነበር። የተቀበረው ቀራኒዮ ወረዳ ቅዱስ ፋኑኤል ነው። ካስፈለገ የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲታዘብልኝ ከተቀበረበት አውጥቼ እንዲመረመር ማድረግ እችላለሁ።

1ኛ ተከሳሽ ብስራት አበራ ጥቅምት 15/2010ጥቅምት ዓም ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ ምድብ ችሎት የሰጠው ቃል:_

አይኔ እያየ ፊቴ ላይ ነው ልቡን ረግጥ የገደሉት። ሁላችንም ተደብድበናል። የእስር ቤቱ ኃላፊ ሱፐር ኢንተንደንት አሰፋ ኪዳነ እያለ ነው የተደበደብነው። 2009 ዓም ነሃሴ ላይ በነበረው ፍርድ ቤት” ከዚህ ማረሚያ ቤት አስወጡኝ። ይገድሉኛል ” ብሎ ተናግሮ ነበር። እንዲህ ሲል መሃል ዳኛው ሰምተዋል(ወደ ዳኛው እየጠቆመ)። ሁላችንም አደጋ ላይ ነን። የት እንሂድ? ገዳዮች እጅ ነው ያለነው። እኔ ተመልሼ ወደ ቂሊንጦ አልሄድም። ይገድሉኛል። እዚሁ በጥይት ይግደሉኝ ። የአርማዬ ጉዳይ ይመርመር። አንድ ቤት ውስጥ ያሉ በርካታ እስረኞች የተፈፀመበትን ድብደባ አይተዋል። አንድ ቤት ሰው በሙሉ ለዚህ ምስክር ነው።

በአማራ ክልል ሃሰተኛ የገንዘብ ኖቶችና ማስረጃዎች ያዘጋጃሉ የተባሉ ተያዙ

 በአማራ ክልል ሀሰተኛ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር የገንዘብ ኖቶችንና ሌሎች የትምህርት ማስረጃዎችን ያዘጋጃሉ የተባሉ ሁለት ግለሰቦች ተይዘው ለህግ ቀረቡ።

የክልሉ ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከህዝብ በደረሰው ጥቆማ መሠረት ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በህግ እንዲታይ እየተደረገ መሆኑን ገልጿል።

ግለሰቦቹ ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ፣ የብቃት ምዘና፣ የስራ ልምድ፣ መንጃ ፈቃድና ሌሎች ሀሰተኛ ሰነዶችን በማተም የወንጀል ስራ ሲያከናውኑ እንደነበርም ተገልጿል።

ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ሲውሉ ተዘጋጅተው ያልተሰራጩ 620 ሃሰተኛ ባለመቶና አራት ባለ ሃምሳ የብር ኖት፣ 162 ሀሰተኛ ባለመቶ የአሜሪካ ዶላርና መሰል የገንዘብ ኖቶች መያዛቸውን የኮሚሽኑ የምርመራና አቃቢ ህግ ዳይሬክተር አቶ ተመስገን መላክ አስረድተዋል።

የሳዑዲ ሪያልና የህንድ ሩፒ የገንዘብ ኖቶች እንዲሁም በሀገር አቀፍ ፈተናዎች ድርጅት ያልተሰጡ የ10ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናና የመሰናዶ ትምህርት ማጠናቀቂያ ውጤቶችን በመቀያየር የተሰሩ ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎችም ተይዘዋል።

በተለያዩ የግልና የመንግስት ኮሌጆች ስም የተዘጋጁ ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎች፣ መንጃ ፈቃዶችና የጤና ሙያ ፈቃዶች መያዛቸውንም ጠቁመዋል።

ግለሰቦቹ ለወንጀል መስሪያነት ሲገለገሉባቸው የነበሩ ላፕቶፕ፣ ዴስክቶፕ፣ ሁለት ባለከለር ፕሪንተሮች፣ አንድ ከለር አልባ ፕሪንተር፣ ፍላሾች እንዲሁም የተለያዩ የማህተም አርማዎችና ሌሎች ቁሳቁሶችም ተይዘዋል ነው ያሉት። 

ከዚህ ጋር ተያይዞም ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ፣ መንጃ ፈቃድና መታወቂያ ለመስራት ተጠርጣሪዎቹ የተቀበሏቸው የ48 ሰዎች ጉርድ ፎቶግራፎችም ተገኝተዋል።

ኮሚሽኑም በተጠርጣሪዎች ላይ ሲያደርግ የቆየውን ምርመራ አጠናቆ የሰነድ ማስረጃዎችን ወደ አቃቢ ህግ መርቶ ክሱን ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ማቅረቡን የኢዜአ ዘገባ ያስረዳል።

(ኤፍ ቢ ሲ)

ከአይኤስ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ 26 ተጠርጣሪዎች ተከሰሱ፤ “የጅሐድ ጦርነት ለማወጅ ነበር”

Via Reporter Amharic በኢትዮጵያ የጅሐድ ጦርነት ለማወጅ ዝግጅት እያደረጉ ነበር ተብሏል

አይኤስ ከሚባለው የሽብር ቡድን ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉና በአዲስ አበባ፣ በሐረርና በአላባ ከተሞች ውስጥ ቡድን በማደራጀትና በማስተባበር ላይ እያሉ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው የተገለጸ 26 ተጠርጣሪዎች ክስ ተመሠረተባቸው፡፡

ተከሳሾቹ አክራሪና ፅንፈኛ ሃይማኖታዊ ርዕዮተ ዓለም በመያዝና ዓላማቸውን ለማሳካት፣ ራሱን አይኤስ ብሎ ከሚጠራው የሽብር ቡድን ጋር ትስስር በመፍጠር፣ በሶማሊያ ቦሳሶ ከሚገኘው ከኤይኤስ ክንፍ ጋር ተገናኝተው ወታደራዊ ሥልጠና መውሰዳቸውን፣ የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የመሠረተባቸው ክስ ያስረዳል፡፡ ተከሳሾቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ሥልጠናውን ወስደው ወደ ኢትዮጵያ በመመለስ የጅሐድ ጦርነት ለማወጅ በእንቅስቃሴ ላይ እያሉ መሆኑንም፣ ዓቃቤ ሕግ በክሱ ጠቁሟል፡፡

አብዛኞቹ ተጠርጣሪዎች በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ሲሆኑ ኦሮሚያ፣ ሐረሪ፣ ደቡብና አማራ ክልሎች የሚኖሩ መሆናቸውን በክስ ቻርጁ ላይ የተጠቀሰው አድራሻቸው ይጠቁማል፡፡

ተከሳሾቹ በሕገ መንግሥቱ የተከበረውን የሃይማኖትና እምነት ነፃነት የሚቃረን፣ እንዲሁም ከእነሱ እምነት፣ አስተሳሰብና አስተምህሮ ውጪ በኢትዮጵያ ሊኖር እንደማይገባ የሚገልጽ አክራሪና ፅንፈኛ እስላማዊ መንግሥት ለመመሥረት እየተዘዋወሩ ወጣቶችን ይመለምሉና ያስተባብሩ እንደነበር ክሱ ይገልጻል፡፡

ከ2005 ዓ.ም. ጀምሮ የሽብር ቡድኑ ድምፅ ነው በሚባለው ‹‹ቢላል ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ›› የሬዲዮ ድምፅ አማካይነት፣ ዕርዳታ ያሰባስቡ እንደነበረም ጠቁሟል፡፡ በእስልምና ሃይማኖት ሽፋን አመፅ ለመደገፍ ገንዘብ እያሰባሰቡ እንደነበርም በክሱ ተገልጿል፡፡

‹‹እስላማዊ ታጋዮች›› በሚል ድረ ገጽና በ‹‹ዋትስአፕ›› አማካይነት በተለያዩ አገሮች ከሚገኙ የሽብር ቡድኑ አመራሮችም ጋር ይገናኙ እንደነበር ዓቃቤ ሕግ በክሱ አስረድቷል፡፡

በተለይ አሜሪካ ከሚገኘው አብድልሀብ ከሚባል የሽብር ቡድኑ አመራርና በሱዳን ከሚገኙ አመራሮች ጋር በስልክና በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች በመገናኘት፣ የተለያዩ ተልዕኮዎችን ለመፈጸም ትዕዛዝ ይቀበሉ እንደነበር በክሱ ተጠቁሟል፡፡

በቅፅል ስሙ አቡ አብደላ የሚባለው በክሪ አወል የተባለው አንደኛ ተከሳሽ፣ በጅዳና በየመን የአይኤስን የሽብር ቡድን በገንዘብ የማገዝ ሥራ ሲያከናውን ቆይቶ፣ በሐምሌ ወር 2008 ዓ.ም. ወደ አዲስ አበባ ከተመለሰ በኋላ፣ አሜሪካ ከሚገኘው የሽብር ቡድኑ አመራር ጋር ሲገናኝ እንደነበር ክሱ ያስረዳል፡፡ ተከሳሹ ‹‹አል ሸሪያ›› በሚባል ቡድን አማካይነት ኢትዮጵያ ውስጥ የጅሐድ ጦርነት ለማወጅ፣ በቅፅል ስሙ አቡዜር ከሚባለው ሁለተኛ ተከሳሽ መሐመድ ሐሰን ጋር በመገናኘት፣ የጅሐድ ጦርነት ስለሚጀመርበት ቀን ሲወያዩ መክረማቸውን ዓቃቤ ሕግ በክሱ አብራርቷል፡፡

የሽብር ቡድኑን ለማጠናከር አባላትን ሲመለምሉ፣ የጦር መሣሪያ የሚታጠቁበትን ሁኔታ ሲያመቻቹና ለሙስሊሙ ጥሩ አስተሳሰብ አለው ብለው ከሚያምኑት አይኤስ የሽብር ቡድን ጋር፣ ወታደራዊ ሥልጠና ለመውሰድ መስማማታቸውን ዓቃቤ ሕግ በክሱ ጠቅሷል፡፡ ስምምነታቸውን በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው ዓለም ባንክ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኘው አብዱ ሙስጠፋ በሚባለው ተከሳሽ ቤት ተሰባስበው፣ ለሥልጠና ወደ ሶማሊያ ለመሄድ ውሳኔ ማሳለፋቸውን ዓቃቤ ሕግ በክሱ አክሏል፡፡ ሥልጠና ወስደው ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሱ በኋላ የጅሐድ ጦርነት በመጀመር እስላማዊ መንግሥት ለመመሥረት ስምምነት ካደረጉ በኋላ፣ ወደ ሥልጠና ቦታ ለመሄድ ጉዞ ሲጀምሩ ሚያዝያ 26 ቀን 2009 ዓ.ም. በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ዓቃቤ ሕግ በክሱ ገልጿል፡፡

አብዛኛዎቹ ተከሳሾች ሐረርና አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውንም አክሏል፡፡ በአጠቃላይ ተከሳሾቹ በአዲስ አበባ፣ ሐረርና አላባ ውስጥ የሚገኙትን የሽብር ቡድን በመምራት፣ በማደራጀት፣ በአመራርነት በመሳተፋቸውና የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32(1ሀ) እና የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀጽ 7(1) ሥር የተደነገገውን በመተላለፍ፣ በሽብርተኛ ድርጅት ውስጥ በማንኛውም መንገድ መሳተፍ ወንጀል ክስ ተመሥርቶባቸዋል፡፡

ተከሳሾቹ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት ጥቅምት 30 ቀን 2010 ዓ.ም. ቀርበው ክሱ ተነቦላቸዋል፡፡ የክስ መቃወሚያ ካላቸው ለመጠባበቅ ለታኅሳስ 3 ቀን 2010 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡

ሃይለማሪያም – በአል አሙዲ ጉዳይ ” ሳዑዲ አንድ ሉዓላዊ አገር ናት፤ የምናደርገው ነገር የለም አሉ

በሳዑዲ አረቢያ እስር ላይ የሚገኙትን ሼክ መሐመድ አል አሙዲን አስመለክቶ አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ መግለጫ ሰጡ። በመግለጫቸውም ሳኡዲ አረቢያ ሉዓላዊ አገር በመሆኗ ሌላ የሚሰራ ነገር አለመኖሩን ተናግረዋል። በዲፕሎማሲያዊ መንገድ መርጃውን እየተከታተሉ መሆናቸውን አመልክተዋል።

የአንድን ተጠርጣሪ ጉዳይ “በዲፕሎማሲ መንገድ መረጃውን እንከታተላለን” ማለታቸውን የዘገበው ፋና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ የተባለውን አግባብ አላብራራም። አቶ ሃይለማሪም አይይዘው “ሳዑዲ አረቢያ ሉዓላዊ ሀገር እንደመሆኗ ከኢትዮጵያ መንግስት በኩል ሌላ ሊሰራ የሚችል ነገር የለም” ብለዋል።

ተቀማጭነታቸው በሎንደን የሆነው ቃል አቀባያቸው ” ከሳዑዲ አረቢያ ውጪ ባሉ ኢንቨስትመንቶችና የንግድ ተቋማት ላይ ችግር እንደማይፈጠር ከቀናት በፊት ለብሉምርግ መናገራቸው ይታወሳል። አቶ ሃይለማሪያምም ይህንን በመድገም “በኢትዮጵያ ባለው የእሳቸው ኢንቨስትመንት ላይ እክል ይፈጠራል ብሎ መንግስት አይምንም” ማለታቸውን ዘገባው ያስረዳል።

 

የሼኩን መታሰር ተከትሎ በሚድሮክ አካባቢ መደናገጥ መፈጠሩ ተሰምቷል። አንዳንዶቹም ጉዳዩ እንደማንኛውም ዜጋ ድንገተኛ እንደሆነባቸው ነው ያስታወቁት። ሃምሳ ሺህ የሚሆን የሰራተኛ ቁጥር ያቀፉት ኢንቨስትመንቶች መካከል አንዳንዶቹ ቀድሞውንም በችግር የተተበተቡ፣ የጸዳ አስተዳደርና የብቃት ችግር ያለባቸው ዘርፎች መኖራቸው ሲገለጽ መቆየቱን የሚያስታውሱ ከወዲሁ ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ ያሳስባሉ። እሳቸው በዚህ መልኩ የሚቆዩ ከሆነ ችግሩን መቋቋም ስለማይቻል ቆፍጠን ማለትና ዙሪያውን የመከታተል ስራ መሰራት እንደሚገባ አብዛኞች አስተያየት እየሰጡ ነው።

የኛ ሰው በሄግ ችሎት (ክንፉ አሰፋ – ዘ ሄግ)

Eshetu Alemu

ለ25 ዓመታት በኔዘርላንድ ውስጥ ሲኖር ሰብዓዊነት ማለት ምን እንደሆነ በደንብ የተረዳ ይመስላል። ምዕራባውያን ለሰብዓዊ ፍጡር የሚሰጡትን ዋጋ ሳይገነዘብ አልቀረም። አምላክ በአምሳሉ የፈጠረው የሰው ልጅ ህይወት ቀርቶ ለእንሰሶች ህይወት የሚሰጠውን ክብር ሌት ተቀን እያየ የአመለካከት ለውጥ አያደርግም ብሎ ለመናገር ይከብዳል።  እዚህ ሰብአዊ ፍጡርን በፖለቲካ አመለካከቱ መግደል ከቶውንም አይታሰብም።  መግደል አይደለም የሰው ልጅ ላይ እጁን የሚያነሳ፣ ጸያፍ ስድብ ከአንደበቱ የሚያወጣ እንኳ ባለስልጣን ቢኖር ዋጋ ይከፍላል።

መቶ አለቃ እሸቱ  በዚህ ሕብረተሰብ ውስጥ ለ25 ዓመታት ዘልቋል። ከ25 ዓመት በፊት የነበረውን ትውስታ ሁሉ አጭንቅላቱ ሰርዞ አዲስ የስነልቦና ተክለሰውነት ይዞ እየኖረ ነው። በሌላ አገላለጽ ከ30 ዓማታት በፊት የተከሰተውን ሁሉ እንዳያስታውስ ሜሞሪው ሙሉ በሙሉ ታጥቧል። ‘ወጣቱ የደርግ አባል’ ተብሎ ይጠራ የነበረው መቶ አለቃ እሸቱ አለሙ ዜግነቱ ወደ ሆላንዳዊነት ሲቀየር በሱ አመለካከት ሁለ ነገሩ ተቀይሯል።  ከዚያን ግዜ በኋላ  እያቆራረጠ መተንፈስን አቆሞ የነጻነት አየር ያገኘ መስሎት ነበር።  እንደማንኛውም የደች ዜጋ ይኖራል፣ ይዝናናል፣  የዜግነት መብቱን ያስከብራል።

“የተሳሳተ ሰው ነው የያዛችሁት” ነበር ያለው መቶ አለቃ እሸቱ ዓለሙ በዘ-ሄግ ከተማ የዓለም አቀፍ ወንጀል ችሎት ላይ ቀርቦ ቃሉን ሲሰጥ። እርግጥ ነው። አሁን “ነጻ ሰው ነኝ” ብሎ ራስን ላሳመነ ሰው ከዳይኖሰር የገዘፈ ወንጀል ከላይ ሲጫንበት ማስደንገጡ አያስገርምም። “አቃብያነ-ሕግ በምን እንደከሰሱኝ ስሰማ እጅግ ተደናግጫለሁ”  በማለት ለፍርድ ቤቱ የተናገረው ቃል ይህንኑ ያረጋግጥልናል።

ወንጀሉ ከበድ ይላል። በሆላንድ ሃገር (ዓለማቀፉን ችሎት ሳይጨምር)  እንዲህ አይነት የወንጀል ጉዳይ ሲቀርብ የመጀመርያው መሆኑን ነው መገናኛ ብዙሃን የሚነግሩን።   75 ወጣት እስረኞችን መግደል፣  9 እሰረኞችን ማሰቃየት፣  240 እስረኞች ላይ ከባድ ግፍ መፈጸም፣ … ከተዘረዘሩት ክሶች ዋነኞቹ ናቸው።  በሆላንድ የሰብአዊነት አስተሳሰብና ስነልቦና ውስጥ ለሚገኝ ሰው ይህንን ዱብ እዳ በአንድ ግዜ መቀበል ቢከብድም ምላሹ ግን ያስደነግጣል።  “ጎጃም ውስጥ እስር ቤቶች አይቼ አላውቅም!” ብሏል እሸቱ።  የሚደብር አካካድ። መካድ ካልቀረ በደንብ አድርጎ መሸምጠት ነበረበት።   “እኔ መቶ አለቃ እሸቱ አለሙ አይደለሁም። ተሳስታችኋል!” ቢል ነበር ጥሩ ክህደት የሚሆነው።  ከጉዳዩ ባያመልጥም!  “ላታመልጪኝ አታሯሩጭኝ”  ይል የለ ያገሬ ሰው።

በስልጣን ስካር ውስጥ በነበረበት ግዜ ያደረገው የነበረው ነገር  ሁሉ ላይታወሰው ይችላል።  በወቅቱ አይኖቹ ሁሉ ተጋርደው  የሚታየው ከፍ ብሎ የወጣበት የስልጣን ማማ  እና በዜጋው ላይ ሊፈርድ የተቀመጠበት ወንበር ብቻ ነው።  ቀይ ሽብርን ደርሼ በአይኔ ባላየውም በታሪክ አንብቤያለሁ።  የወጣቱ ደም እንደ ጎርፍ መፍሰስ  በወታደሮቹ  እንደጀብድ የሚታይበት ግዜ ነበር።  በስልጣን ለመቆየት ሲሉ ብቻ አንድን ትውልድ እንደዋዛ አጠፉት።  የሚገርመው የአሁኖቹ ባለተራዎች ከዚህ ያለመማራቸው ነው። እነሱም ደም ማፍሰሱን አላቆሙትም።  ስልት ቀየሩ እንጂ  ትውልዱን  አሁንም እየፈጁት ይገኛሉ። የቤተ መንግስቱን ቁልፍ በእጃቸው ሲያስገቡ የሚታወሩበት አዚም ግራ ይገባል። ሌላው ቀርቶ የሚያንማርዋ መሪ ኡን ሳን ሱ ቺ – ተቃዋሚ ሳለች  የኖቤል የሰላም ተሸላሚ ጀግና ነበረች።  ቤተ መንግስት ስትገባ  በአለም አንደኛዋ የተባለው የዘር ማጥፋት ወንጀል ውስጥ ተዘፍቃ እየዋኘች ትገኛለች።

ልብ ያለው ልብ ይበል። በህይወት ዘመናቸው ክቡሩን ህይወት የቀጠፉ ሁሉ ደም ይጠራቸዋል። ግዜው ሊቀርብም ሊርቅም ይሽላል።  በመጨረሻ ግን… ማንም ከፍትህ አያመልጥም።  የሰው ደም አይለቅቅም!

እነሆ የ63 አመቱ  እሸቱ አለሙን በሆላንዱ ፍርድ ቆሞ አየሁት። ይህንን ሰው ከዚህ ቀደም አንድ ግዜ ብቻ በአካል አግኝቼ እንዳነጋገርኩት ትዝ ይለኛል። ቀደም ሲል በሆላንድ ላይ “ኢትዮጵያ ወዴት?” በሚል ርዕስ ተዘጋጅቶ በነበር ትልቅ ስብሰባ ላይ ሃሳብ ሲሰጥ በቪድዮ አይቼዋለሁ። ስለ ፍትህ እና ዲሞክራሲ ግንባታ ሲናገር በጣም ያስደምማል።  በእሸቱ ንግግር የተመሰጡት ፕሮፌሰር ጌታቸው ሃይሌ “… አነጋገርርህን  ስሰማ ስልጣኑን ለደርግ መልሰህ ስጥ ስጥ አለኝ” ሲሉ በዚያው ስብሰባ ላይ የተናገሩት የምጸት ቃልም ታወሰኝ።  ከዚያን  ግዜ ወዲህ  እሸቱ በኢትዮጵኖች ስብስብ ላይ ታይቶ አይታወቅም።

ባለፈው ሃሙስ ተጠቂዎች  በ ዘሄግ ፍርድ ቤት ቀርበው ቃል ሲሰጡ በስፍራው የነበረው ስሜት የተለየ ነበር። ሰውን  ሁሉ ስሜታዊ ያደረገው  የተጎጂ ወገኖች ምስክርነት ከተሰማ በኋላ፣  መቶ አለቃ እሼቱ 30 ዓመት ወደኋላ በትውስታ ተጉዞ ወደ አእምሮው  የተመለሰ ይመስላል።     እንባ እየተናነቀውም፣    “በወቅቱ እጅግ አስከፊ ነገር ተፈጽሟል።  ይህ ስርዓት ለፈጸመው በደል ሁሉ በጉልበቴ ተንበርክኬ ይቅርታ እጠይቃለሁ። ”  ሲል ተናገረ። በዚህ ግን አላበቃም።  ወዲያው አንድ ነገር ትዝ አለውና እንዲህ አለ።

“የሚነገረውን ወንጀል ሁሉ ግን  እኔ አላውቀውም!”

ይቅርታው እና ክህደቱ ትንሽ ግራ ያጋባሉ። ድርጊቱን አልፈጸምኩም ካለ – ሰው ራሱ ላልሰራው ወንጀል እንዴት ይቅርታ ይጠይቃል? ወይንስ  በውክልና  ይቅርታ እንዲጠይቅ ደርግ ሃላፊነት ተሰጥቶታል?

እ.ኤ.አ. ጥቅምት 16 ቀን 2017  የሆላንድ ፖሊሶች  የፍርድ ቤት ማዘዣ  በመያዝ  አምስተልቪን በሚገኘው መኖርያው እሸቱ አለሙን እስካገቱት ድረስ ድምጹም ተሰምቶ አያውቅም።     በደርግ ዘመን  በጎጃም ክፍለ ሃገር ዜጎችን በመግደል፣ በማሰርና በማሰቃየት ተከስሶ በወያኔ የሞት ፍርድ የተበየነበት መቶ አለቃ እሸቱ አለሙ  በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከዋለ ሁለት አመት ሞላው።

እሸቱ አለሙን ለፍርድ የማቅረብ ሂደቱ የተጀመረው ከዛሬ 18 አመት ገደማ  ነበር።  በወቅቱ ከገዥው ፓርቲ ደህንነት ሃላፊ የነበሩት አቶ ክንፈ ገብረመድህን ሆላንድ ሃገር ባሉ ተወካዮቻቸው አማካይነት እንቅስቃሴ ተጀመረና  ግፊቱ ወደ ሆላንድ የኢትዮጵያውያን ማህበር ጽህፈት ቤት ደረሰ። በወቅቱ የነበሩት የኢትዮጵያ ማህበር አመራሮች ጉዳዩን ከግምት ውስጥ አላስገቡትም ነበር። ለዚህም በቂ ምክንያት ነበራቸው።   በስልጣን ላይ ያለው መንግስት ከደርግ የባሰ ወንጀል እየፈጸመ ነበርና።

ወያኔ በቀጥታ የሆላንድ መንግስትን መጠየቅ ሲችል ለምን በዚህ መንገድ መጣ የሚለው ጥያቄ በወቅቱ በእምሮዬ መጣ።  ሁለት ምክንያት አለው።   አንደኛው ሁለቱ ሃገራት ወንጀለኛን አሳልፎ የመስጠት ስምምነት ስለሌላቸው እና በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ የኢትዮጵያ ወንጀለኛ መቅጫ ህግ የሞት  ቅጣትን ስላካተተ ነው።

በወቅቱ የነበረው የማህበሩ አመራር፣  “ግለሰቡ መዳኘት ካለባቸው ዘ ሄግ ያለው አለም አቀፉ ፍርድ ቤት ነው” ሲል ጥያቄውን ውድቅ ማድረጉ ይታወሳል።

እ.ኤ.አ. በ1998 ዩዲት ኑሪንክ የምትባል ታዋቂ የሆላንድ ጋዜጠኛ  ቢሮዋ ጠርታ ስለዚህ ጉዳይ  አነጋገረችኝ። እሸቱ አለሙ የጎጃም ነዋሪ ወጣቶች እንዲገደሉ እና እንዲታስሩ የፈረመበት ክምር ዶሴ በእጅዋ ነበር።  እንደ ጋዜጠኛ ሃላፊዋነትዋን ብቻ መወጣት እንደሚገባት ተነጋግረን ተለያየን። ጋዜጠኛ  ዩዲት – የኢትዮጵያ ማህበር አመራሮችን  (ጸጋ ታክሉን እና ወንድም አስረስን) እያጣቀሰች መረጃውን በአንድ ተነባቢ መጽሄት ላይ ለቀቀችው። …  ከዚያም ጉዳዩ በሆላንድ የአለማቀፍ ወንጀሎች ምርመራ ቡድን አይን ውስጥ ሊገባ ቻለ።

የሆላንዱ ፍርድ ሂደት ለእሸቱ አለሙ ህልም ሊመስል ይችላል።  የሚወዱትን ለተነጠቁት ለሟች ቤተሰቦች ግን እውን ነው።  እሸቱ አለሙን በባእድ ሃገር ፍርድ ቤት ብቻውን ቆሙ ለሚያየው ሰው እጅግ ያሳዝናል።    ከጎኑ አንዳች ሰው የለም።

በአይኑ ሳይሆን በልቦናው አትኩሮ ለሚመለከተው ሁሉ የሚነግረን መልእክት ግን አለ። … “እኔን ያየህ ተቀጣ!”

ይቀጥላል….   የፍርድ ሂደቱ ማክሰኞ ይቀጥላል።  ካቻልኩ በምስል ለማቅረብ እሞክራለሁ!

Al Amoudi arrested in Saudi Arabia in connection with alleged corruption

News of his arrest in Saudi Arabia is not yet reported by local media in Ethiopia.

Saudi-Ethiopian born billionaire Al Amoudi detained in Saudi Arabia

Billionaire Mohamed Al Amoudi is reportedly arrested in Saudi Arabia. His arrest has something to do with Saudi Government campaign against corruption, according to a report by Moroccan Newspaper LesEco which in turn cited Sabq, Arabic news and Reuters.

Although not mentioning Al Amoudi, Reuters reported that royals, ministers, and investors including Alaweed bin Talal are arrested as part of an anti-corruption purge.

The arrests came after King Salman made a decree about the creation of an anti-corruption committee with the chairmanship of his 32-year-old son, Crown Prince Mohammed, added the report by Reuters.

The arrests are made public and the decree says that it is a response to “exploitation by some of the weak souls who have put their own interests above the public interest, in order to, illicitly, accrue money” as cited by Reuters.

As thing stand now, some of the detainees are not in prison. They are held at Ritz-Carlton Hotel in Riyadh according to sources close to the Saudi government.

The Casablanca based newspaper, LesEco, seem to relate Mohammed Al Amoudi with Samir Group in Saudi Arabia, a company that markets a range of technological products.

Information in Wikipedia hints that he won a contract to build Saudi Arabia’s Oil Storage complex, estimated to be $30 billion, in 1988. His company MIDROC (Mohammed International Development Research and Organization Companies) acquired Yanbu Steel in Saudi Arabia in 2000.

In Ethiopia, he has invested in the hotel (he owns Sheraton Addis the biggest five-star hotel in the heart of Addis Ababa), construction, agriculture, mining, and banking sectors, among others. He also has investment in Sweden.

In 2016, Forbes estimated his net worth to be $10.9 billion.

News of his arrest in Saudi Arabia is not yet reported by local media in Ethiopia.

****

Source: BorkenaNews

ለ’ተከበሩ’ ዳኛ- የእርስዎም ልጅ መብቱን ከጠየቀ ይታሰራል… እባክዎ ልጆችዎን በማሰብ ይፍረዱልን” ታሳሪዎች

ችሎት ፊት የሚቀርቡ አቤቱታዎች ከቀን ወደ ቀን ልብ የሚሰብሩ፣ የውስጥ ሚዛንን የሚፈታተኑ፣ ሰውነትን የሚያርዱ፣ ተስፋ የሚያስቆርጡ፣ ቂም የሚያስቋጥሩና እልህ ውስጥ የሚከቱ የመሆናቸው ጉዳይ አሳሳቢ ነው። እስርን ታሳሪውና የታሳሪው ቤተሰቦች ጠንቅቀው የሚረዱት መከራ ነው።

ጋዜጠኛ ተመስገን ” ምድራዊ ሲኦል” ሲል እንደ ገለጸው በቂሊንጦ እስር ቤት ከሚገኙት ተጠርጣሪዎች መካከል ኢፋ ገመቹ በትላንትናው እለት ችሎቱን ላስቻሉት ዳኛ ” የእርስዎም ልጅ ነገ መብቱን ከጠየቀ ይታሰራል፤ ስለ እርስዎ ልጅም ጭምር ነው የምናገረው” ሲል እሱ የተጫማውን የችግር ጫማ በልጃቸው እንዲያዩት ተማጽኗቸዋል። ሲቀጥል ” የምንጠጣው ቆሻሻ ነው፣ ትል ነው፣ እዚህ የምታዩዋቸው የኩላሊት በሽተኞች ናቸው…” አስረዳ። እዚህ ላይ ይህንን የልጇን መከራ የሚሰሙ እናት፣ እህት ፣ ወንድም፣ ቤተሰብ፣ ወዳጅ፣ ሃቀኛ ተቆርቋሪ እንዴት አይነት ስሜት ውስጥ እንደሚገቡ ማሰብ ግድ ነው። በዚህ ስሜት ውስጥ ላሉ ስለ ዴሞክራሲ፣ ስለ እኩልነትና ስለፍትህ ማውራትና ማስተማር እንዴትስ ይቻላል? እንዲህ ያሉት ወደ አውሬነት ቢቀየሩ ጥፋቲ የማን ነው?

” ሳይፈረድብን ” ይላሉ ተከሳሾሹ፣ ” ሳይፈረድብን እንሰቃያለን” ኦሮመኛ ድምፃዊት ሴና ሰለሞንን ጨምሮ ሰባት የኪነጥበብ ባለሞያዎች በማረሚያ ቤት ያለውን አያያዛቸው ሰብዓዊ መብትን የጣሰ መሆኑን በመግለጽ ያማረሩት በጎፈነነ ስሜት ነው። “ከዚህ ማረሚያ ቤት ተርፈን የምንወጣ አይመስለንም” ሲሉ የፍትህ ያለህ ድምጻቸውን አሰምተዋል።

ሙሉ ዘገባውን እዚህ ላይ ያድምጡ