የኮቪድ 19 ወረርሺኝ እያሻቀበ ነው፤ 29 አዲስ ተጠቂዎች ተመዘገቡ፤ ” ዛሬም መንግስት ይፍረስ?”

የወረርሺኙ መጠን የተቀዛቀዘ ነው በሚል በርካቶች ቢዘናጉም አደጋው አዝግሞ ወደ ከፋ ደረጃ ሊወድ እንደሚችል ምልክት እያሳየ ነወ። በኢትዮጵያ መንግስት ባስጠናው መሰረት ሰፊ ዝግጅት በሚያደርግበትና ሕዝብ በማስተባበር አደጋውን ለመቀነሰ በሚንቀሳቀስበት ወቅት ስልጣን ያስቀደሙ ዛሬ ምን እንደሚሉ በጉጉት እየተጠበቀ ነው።

ካለው የከፋ የሞትና የክስረት ደመና ስር ለስልጣን የሚራኮቱ ሰዎች መንግስት ለማፍረስ በሚተጉበት በዚህ ወቅት በሁለት ተከታታይ ቀናት 42 ሰዎች በበሽታው መጠቃታቸው ይፋ ሆኗል።

ፋና እንዳለው ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 1 ሺህ 847 የላብራቶሪ ምርመራ 25 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል። ይህም ቁጥር ቫይረሱ በኢትዮጵያ ከተከሰተ ወዲህ ከፍተኛው ሆኖ ተመዝግቧል።

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች ውስጥ 19 ሰዎች ምንም አይነት የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ እና ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች ጋር ንክኪ የሌላቸው መሆናቸውን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታውቀዋል።

3 ሰዎች ደግሞ ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች ጋር ንክኪ ያላቸው ሲሆን፥ ቀሪዎቹ ሶስቱ ደግሞ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው መሆናቸውንም ገልፀዋል። ቫይረሱ የተገኘባቸው ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ፥ እነዚህም እድሜያቸው ከ17 እስከ 65 ዓመት የሆኑ 24 ወንዶች እና 1 ሴት ናቸው።

ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች መኖሪያም 21 በአዲስ አበባ፣ 2 ደበቡብ ክልል ሃድያ ከንባታ ዞን፣ 2 በኦሮሚያ ክልል (በቦረና ለይቶ ማቆያ እና በፊንፊዜ ዙሪያ ልዩ ዞን) መሆኑንም ሚኒስትሯ ገልፀዋል። በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 187 ደርሷል።

በአሁኑ ወቅትም በአጠቃላይ ቫይረሱ ከተገኘባቸው ውስጥ 88 ሰዎች በለይቶ ህክንማ ውስጥ ያሉ ሲሆን፥ ከእነዚህም 1 ሰው በጽኑ ህክምና ላይ ይገኛል። እስካሁን 93 ሰዎች ከቫይረሱ ሲያገግሙ፤ 4 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ህይወታቸው ማለፉ እና 2 ሰዎች ደግሞ ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ይታወሳል።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.