“ምርጫዎችን የማስፈጸም ብቸኛ ስልጣን ያለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ነው”ብርቱካን ሚደቅሳ

የክልል መንግሥታትም ሆኑ የፌዴራል አስፈጻሚ አካላት ምርጫን በተመለከተ ውሳኔ ቢያስተላልፉ ሕገ-መንግሥታዊ አይደለም፡፡

በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 102 የተቋቋመው ምርጫ ቦርድ በፌዴራል፣ በክልል እና በቀበሌ ደረጃ የሚካሄዱ ምርጫዎችን የማስፈጸም ብቸኛ ስልጣን የተሰጠው መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ገለጸ፡፡
የቦርዱ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ የህወሓት ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ከሚያዝያ 23-25 ቀን 2012 ዓ.ም በክልሉ እና በአገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፉን ፓርቲው በፌስቡክ ገጹ ላይ ማስታወቁን ተከትሎ ሂደቱ ህገ መንግስታዊ አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡
የቦርዱ ሰብሳቢ፤ የትግራይ ህዝብ በሕገ-መንግሥቱ መሠረት ራስን በራስ የማስተዳደር መብት እንዳለው በማስታወስ፤ ህወሓት ለትግራይ ህዝብ እውቅና ከሚሰጡ የፖለቲካ ሃይሎች ጋር በመሆን ክልላዊ ምርጫን ለማካሄድ ዝግጅት እንዲደረግ ውሳኔ ቢያሳልፍም፤ ውሳኔው ተግባራዊ ቢሆን የክልሉ መንግሥትም ሆነ ክልሉን የሚያስተዳድረው ፓርቲ ሕጋዊ እንደማይሆን ገልጸዋል፡፡
“ክልላዊ ምርጫውን ለማካሄድ አስበው ከሆነ ትክክለኛ አካሄድ አይደለም፡፡ ሕገ-መንግሥታዊ አይሆንም” ያሉት የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢዋ፤ በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 102 የተቋቋመው በእርሳቸው ሰብሳቢነት የሚመራው ምርጫ ቦርድ በፌዴራል፣ በክልል እና በቀበሌ ደረጃ የሚካሄዱ ምርጫዎችን የማስፈጸም ብቸኛ ስልጣን የተሰጠው መሆኑን ጠቅሰዋል።
እንደእርሳቸው ማብራሪያ፤ የትግራይ ክልልን የሚያስተዳድረው ህወሓት በክልሉ ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችል የሕግ ድጋፍ የለውም፡፡ ህወሓት ለቀናት ሲያደርግ የነበረውን ስብሰባ ካጠናቀቀ በኋላ ባወጣው መግለጫ ተቀባይነት የለውም፤ ህወሓት ምርጫውን በክልል ደረጃ ለማካሄድ ስለመወሰኑም ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በይፋ አላሳወቀም፡፡ የክልል መንግሥታትም ሆኑ የፌዴራል አስፈጻሚ አካላት ምርጫን በተመለከተ ውሳኔ ቢያስተላልፉ ሕገ-መንግሥታዊ አይደለም፡፡
የቦርዱ ሰብሳቢ በአስገዳጅ ሁኔታ ከአጠቃላይ ምርጫ በተለየ ጊዜ የአንድ አካባቢ ምርጫ ሊካሄድ እንደሚችል ጠቁመው፤ በሶማሌ ክልል አብዛኛው ድምጽ ሰጪዎች በኑሮ ዘያቸው ምክንያት በድምጽ መስጫ አካባቢ የማይገኙበት ሁኔታ ተፈጥሮ እንደነበረ በማስታወስ ከአጠቃላይ ምርጫ በኋላ በክልሉ ምርጫ እንደተከናወነ እንደ አብነት አንስተዋል፡፡
መንግሥት ምርጫውን ለማካሄድ ያስችላሉ ካላቸው አራት አማራጮች መካከል የሕገ-መንግሥት ትርጓሜ መጠየቅ የሚለውን አማራጭ ትናንት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማጽደቁ ይታወሳል::
አዲስ ዘመን ሚያዝያ 28/2012
ዘላለም ግዛው

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.