ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ወደ ጃፓን አቀኑ – የኢትዮጵያ እና ደቡብ ኮሪያ የቢዝነስ ፎረም ተካሄደ።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ወደ ጃፓን አቅንተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በደቡብ ኮሪያ የነበራቸውን ቆይታ በማጠናቀቅ ነው ወደ ጃፓን ያቀኑት።

በጃፓን ቆይታቸውም በጃፓኗ ዮኮሃማ ከተማ በሚካሄደው 7ኛው የጃፓን-አፍሪካ የልማት ፎረም (የቲካድ ) የመሪዎች ስብሰባ ላይ እንደሚሳተፉም ይሆናል።

ከጉባዔው ጎብ ለጎንም ከጃፓን ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ጋር ተገናኝተው እንደሚወያዩም ይጠበቃል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በጃፓን-አፍሪካ የልማት ፎረም (የቲካድ ) ላይ እንዲሳተፉ እና ከጉባዔው ቀደም ብሎም በጃፓን ጉብኝት እንዲያደርጉ በጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ ጥቂ ቀርቦላቸው እንደበረ ይታወሳል።


የኢትዮጵያ እና ደቡብ ኮሪያ የቢዝነስ ፎረም ተካሄደ። በፎረሙ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የደቡብ ኮሪያ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ጠይቀዋል።

ኢትዮጵያ ምቹ የቢዝነስ ሁኔታ ለመፍጠር እና ቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንት ፍሰትን ለማሳደግ የፖሊሲ እንዲሁም የህግ ማሻሻያ ማድረጓንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

በርካታ የደቡብ ኮሪያ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ በተለያዩ መስኮች መሰማራታቸውን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን ቢያፈሱ ውጤታማ እንደሚሆኑ ገልጸውላቸዋል።

የኮሪያ አፍሪካ ፋውንዴሽን ፕሬዚዳንት ዮዋን ሆን ቾይ በበኩላቸው፥ በኢትዮጵያ ያለው የኢንቨስትመንት ዕድል ለኮሪያውን ባለሃብቶች ምቹ አጋጣሚ መሆኑን አንስተዋል። ደቡብ ኮሪያ በአፍሪካ ያላትን የገበያ ድርሻ ከፍ ለማድረግም ኢትዮጵያን እንደምትመርጥ አስታውቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ከፎረሙ በተጓዳኝ ከሃዩንዳይ ኩባንያ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሊ ዎን ሄ ጋር ኩባንያው በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋዩን ማፍሰስ በሚችልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል።

በተጨማሪም ፖስኮ ከተባለ ትልቅ የብረት አምራች ኩባንያ ጋር በኢትዮጵያ የብረት ፋብሪካ በመክፈት በሀገር ውስጥ ያለውን የብረት ፍላጎት ለማሟላትና የሥራ ዕድል መፍጠር በሚቻልበት አግባብ ዙሪያ ተወያይተዋል።

በተመሳሳይ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከኮርያ አለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (ኮይካ) ፕሬዝዳንት ጋር ድርጅቱ ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍ የበለጠ ማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ መክረዋል።

ኮይካ በኢትዮጵያ በተለይም በትምህርት፣ በውሃና ግብርና ዘርፎች ላይ የሚያደርገውን የልማት ድጋፍም አድንቀዋል። ኮይካ በተለያዩ የልማት ዘርፎች ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍ ለማጠናከር ፍላጎት ያለው መሆኑን የድርጅቱ ሃላፊዎች ገልፀዋል።

በአልዓዛር ታደለ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.