አዲሱ የሰራተኞች የስራ መደብ ምዘና ደረጃዎች ምደባ ሰራተኛው የዜጎችን ፍላጎት በሚያሟላ ስነ ልቦና መንቀሳቀስ የሚስችል መሆኑ ተገለጸ

 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አዲሱ የሰራተኞች የስራ መደብ ምዘና ደረጃዎች ምደባ ሰራተኛው የዜጎችን ፍላጎት በሚያሟላ ስነ ልቦናመንቀሳቀስ የሚስችል መሆኑን የኢፌዴሪ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽንአስተወቀ፡፡

የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ በዛብህ ገብረየስ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባካሄደው የአስቸኳይ ስብሰባ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ባቀረባቸው የሰራተኞች የስራ መደብ ምዘና ደረጃዎች ምደባ እና ተያያዝ ጉዳዮች ዙሪያ ባሳለፈው ውሳኔ ዙሪያ ከፋና ብሮድካስቲን ኮርፖሬት ጋር የስልክ ቆይታ አድረገዋል፡፡

ኮሚሽነሩ በዚሁ ቆይታቸው ውሳኔው የመንግስ ሰራተኞች በልማዳዊ መንገድ ለረጅም ዘመናት በተደጋጋሚ ሲሰሯቸው የነበሩትን ስራዎች በአግባቡ በመመዘን በዘመናዊ አግባብ ስራ እና ሰራተኛን የሚያገናኝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ቀደም ሲል የመንግስት ቢሮክራሲ የሲቪል ሰርቪሽ ማሻሻያ በሚል በተቀረጹ በርካታ ማሻሻያና ማስተካከያዎች ስራዎች ሲመራ መቆየቱን ያስታወሱት ኮሚሽነሩ ውሳኔው በሀገሪቱ እየታየ ካለው ዙሪያ መለስ ለውጦች ጋር አስተሳስሮ ስራ እና ሰራተኛን በአግባቡ በማገናኘት ለእኩል ስራ እኩል ክፍያ የመስጠትን ሂደት ያሳልጣል ብለዋል፡፡

አፈፃፀሙ የደሞዝ ስኬል ሽግግርን አድርጎ የተጠናቀቀው ይህ ፕሮጀክት የደሞዝ ጭማሪ ለማድረግ ወይንም ማስተካካያ የመስራት አለማ እንደሌለውም ነው ያስገነዘቡት፡፡

ሰረተኛው የደሞዝ ልዩነትን ባልተመዘኑ ስራዎችን ለመፈለግ ከመስሪያ ቤት መስሪያ ቤት ወይንም ከዘርፍ ዘርፍ የሚያደረገውን ፍሰት የሚያስቀር መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

በዚህም ሰራተኛው የተመደበበት ቦታ እና የስራ ባህሉ በአደገበት ቦታ ላይ የበለጠ እየዘመነ የዜጎችን ፍላጎት በሚያሟላ ስነ ልቦና መንቀሳቀስ የሚያስችል መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባካሄደው የእቸኳይ ጊዜ ስብሰባ የሲቪል ሰርቪስ ባቀረባቸው የሰራተኞች የስራ መደብ ምዘና ደረጃዎች ምደባ እና ተያያዝ ጉዳዮች ላይ አንዳንድ ማሻሻያዎችን በማድረግ ከሃምሌ 1 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረጉ ውሳኔ ማስተላለፉ ይታወሳል፡፡

በእንቻለው ታደሰ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.