ቅዱስ ሲኖዶስ የኦሮሚያ ቤተክህነት አደራጅ ኮሚቴ የጠራውን መግለጫ መንግሥት እንዲያስቆም ጠየቀ

የኦሮሚያ ቤተክህነት አደራጅ ኮሚቴ የጠራውን መግለጫ መንግሥት እንዲያስቆም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ሲኖዶስ ጠየቀ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ቤተ ክህነት በኦሮሚያ ቤተክህነት አደራጅ ኮሚቴ የተጠራውን መግለጫ እንደማያውቀውና እውቅናም እንዳልሰጠው የጠቅላይ ቤተክህነት ምክትል ስራ አስኪያጅ ርዕሰ ደብር መሀሪ ኃይሉ በዛሬው የቅዱስ መግለጫ ላይ ተናግረዋል።

በተጨማሪም የኦሮሚያ ቤተክህነት አደራጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት ቀሲስ በላይ መኮንን ምንም እንኳ በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ትልቅ ሃላፊነት የነበራቸው ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ግን የኦሮሚያ ክልል እንባ ጠባቂ ቢሮ ሃላፊ መሆናቸውን የቤተክህነት የስብከተ ወንጌል እና ሃዋሪያዊ ተልእኮ መምሪያ ሃላፊ የሆኑት አቶ ሶሎሞን ቶልቻ ገልፀዋል።

ቅዱስ ሲኖዶስ የኦሮሚያ ቤተክህነትን የማቋቋም ጥያቄ መምጣት ያለበት ምእመናኑ ተወያይቶበት እንጂ በተወሰኑ ሰዎች ፍላጎት መሆን የለበትም ብሏል።

ከቀናት በፊት ቢቢሲ ያናገራቸው የአደራጅ ኮሚቴው ሰብሳቢ ቀሲስ በላይ የኦሮሚያ ቤተክህነትን የማቋቋም ጥያቄ ከማንነት እና ከቋንቋ ጋር የሚገናኝ እንደሆነ ገልፀው ነበር። ኮሚቴው ጥያቄውን ለቅዱስ ሲኖዶስ አቅርቦ ምላሽ እየጠበቀ እንደነበርም ገልፀው ነበር።

የ ዜሮ ክፍል ትምህርት ይሰጣል

በቀጣይ የትምህርት ዘመን በ30 ሺ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የ 0 ክፍል ትምህርት ይሰጣል። ለትምህርት ጥራት ልዩ ትኩረት በመስጠት በቀጣይ የትምህርት ዘመን በ30 ሺ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የ 0 ክፍል ትምህርት እንደሚሰጥ ተገለጸ።

29ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባኤ በጅግጅጋ ከተማ “ስር ነቀል የትምህርት ሥርዓት ለውጥ ለሁለንተናዊ ሀገራዊ ዕድገት” በሚል መሪ ሀሳብ ከዛሬ ጀምሮ ለሶስት ቀናት በመካሄድ ላይ ነው፡፡

የትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ጥላዬ ጌቴ በመክፈቻው ላይ እንዳሉት የሚፈለገውን የትምህርት ጥራት ለማምጣት የትምህርትና ስልጠና ስርዓቱ በየጊዜው መገምገም ይኖርበታል፡፡

ትምህርት ከድህነት ማምለጫና የዴሞክራሲ ስርዓት መገንቢያ በመሆኑ የነበሩ ክፍተቶችን ለማስተካከል የትምህርት ስርዓቱ በየጊዜው ይፈተሻል ብለዋል፡፡

በዚህም መዳረሻውን 2022 ዓ.ም ያደረገና በ2012 የሚጀምረው አዲሱ የትምህርትና ስልጠና ፍኖተ ካርታ ዝግጅት ተጠናቋል ብለዋል፡፡ በዚህም ለትምህርት ጥራት ልዩ ትኩረት መስጠት ከቀጣዩ የትምህርት ዘመን አንስቶ ዋናው ስራችን ነው ብለዋል። በዚህም በ30 ሺ የመደበኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የቅድመ መደበኛ ክፍል ወይም የ 0 ክፍል ትምህርት ይሠጣል ብለዋል፡፡

ለሶስት ተከታታይ ቀናት በሚቆየው በዚሁ የትምህርት ጉባዔ የ2011 የትምህርት ዘመን ዕቅድ አፈፃፀም ይገመገማል፤ የ2012 የአጠቃላይ ትምህርትና የከፍተኛ ትምህርት እቅድ ላይም ውይይት ይደረጋል፡፡ ኢዜአ

የትግራይ ነጻ አውጪ ጫጫታ – እጅ አዙር መግለጫ

  • ሕገ መንግስትንና ህብረ ብሔራዊ የፌደራሊዝም ስርዓት የማዳን አገር አቀፍ መድረክ ተሳታፊዎች የኣቋም መግለጫ

ሀገራችን ኢትዮጵያ የብዝሃንነት ሃገር እንደመሆንዋ ለልዩነታችንን እውቅና ሰጥቶ ሊያስተናግድ ካልቻለ ኣገዛዝና ጭቆና ህዝቦቿ ለመታደግ በየዘመኑ በተደረገው በማያቋርጥ ህዝባዊ ትግል በዓላማውና እና ይዘቱ ቡዙሀነትን ልያስተናግድ እና ዲሞክራሲያዊው ስርዓት ለመግንባት

Continue reading የትግራይ ነጻ አውጪ ጫጫታ – እጅ አዙር መግለጫ