የአዲስ አበባና የድሬዳዋ ከተሞች ምክር ቤቶች ተወካዮች የአካባቢ ምርጫ ከቀጣዩ ሀገር አቀፍ ምርጫ ጋር እንዲካሄድ የቀረበው የውሳኔ ሐሳብ ጸደቀ

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተሞች ምክር ቤቶች ተወካዮች እንዲሁም የአካባቢ ምርጫ ከቀጣዩ ሀገር አቀፍ ምርጫ ጋር እንዲካሄድ የቀረበውን ረቂቅ የውሳኔ ሐሳብ በዛሬው 2ኛ አስቸኳይ ስብሰባው አጽድቋል፡፡

ምክር ቤቱ በ2011ዓ.ም ይካሄዳል ተብሎ የነበረውን የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተሞች ምክር ቤቶች አባለት ምርጫ እና የአካባቢ ምርጫ በተያዘው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ማካሄድ ባለመቻሉ ከቀጣዩ ሀገር አቀፍ ምርጫ ጋር እንዲካሄድ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ያቀረበውን ረቂቅ የውሳኔ ሐሳብ በመቀበል ነው ዛሬ ያጸደቀው።

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድም ሐምሌ 4 ቀን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጻፈው ድብዳቤ የሁለቱን ከተማ አስተዳደሮች ምክር ቤት ምርጫን በተቀመጠው ጊዜ ማለትም ዘንድሮም ‹‹ማካሄድ አይቻልም›› ብሏል።

በቀረው አጭር የዓመቱ ጊዜ ምርጫ አስፈፃሚዎችን ለመመልመል፣ ለማደራጀት እና ስልጠና ለመስጠት በቂ ጊዜ አለመኖሩን ቦርዱ በምክንያትነት አቅርቧል።

በዚህ የውሳኔ ሐሳብ መሠረትም አሁን በሥራ ላይ ያሉት የአዲስ አበባ እና ድራዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤቶች በሥራቸው ይቀጥላሉ።

የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተሞች ምክር ቤቶች ተወካዮች እንዲሁም የአካባቢ ምርጫ በ2010ዓ.ም መካሄድ የነበረባቸው ቢሆንም በወቅቱ በሀገሪቱ የነበረው ሁኔታ ለምርጫ ምቹ ባለመሆኑ 2011ዓ.ም ላይ እንዲካሄድ ይኸው ምክር ቤት ውሳኔ አሳልፎ እንደነበር ኤፍ ቢ ሲ በዘገባው አመላክቷል።

ምክር ቤቱ በአስቸኳይ ስብሰባው የገቢ፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የባንክ ሥራ አዋጅን ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሐሳብ መርምሮ ረቂቅ አዋጅን እየተመለከተ ነው።

በተመሳሳይ የገቢ፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የጉምሩክ አዋጅን ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሐሳብ በመርመር ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የከተማ ልማት፣ ኮንስትራክሽንና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እና የሕግ፣ ፍትሕና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበትን እና ካሳ የሚከፈልበትን ሁኔታ ለመወሰን የወጣ ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ ያቀረቡትን ሪፖርትና የውሳኔ ሐሳብ መርምሮ ረቂቅ አዋጁን እንደሚያጸድቅ ነው ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ የሚያመለክተው

አብመድ

ለኢቦላ ወረርሽኝ ቅድመ መከላከል ስራ ከ290 በላይ የህክምና ባለሙያዎች መሰማራታቸው ተገለፀ

የኢቦላ ወረርሽኝን ቀድሞ ለመከላከል የህክምና ባለሙያዎች በመላ ሃገሪቱ መሰማራታቸውን የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ። ለቅድመ መከላከል ስራውም ከ290 በላይ የህክምና ባለሙያዎች በመላ ሃገሪቱ መሰማራታቸውን ነው ኢንስቲቲዩቱ የገለፀው።

የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር በየነ ሞገስ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ፥ ወረርሽኙ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ የቅድመ መከላከል እና የቁጥጥር ስራዎች እየተከናወኑ ነው ብለዋል።

በዚህም በቦሌ፣ ድሬዳዋ፣ መቀሌ እና ባህር ዳር አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያዎች የተጓዦችን የሰውነት ሙቀት በመለካት የልየታ ስራ እየተከናወነ መሆኑን አስታውቀዋል።

በየብስ ትራንስፖርት ወደ አገር ወስጥ በሚገቡ መንገደኞች ላይ ደግሞ በ21 የፍተሻ መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች ክትትል በመደረግ ላይ መሆኑንም ገልፀዋል።

በተለይም ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የሚመጡ መንገደኞች ነጻ መሆናቸውን ለማረጋገጥ እስከ 21 ቀን ድረስ ክትትል እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል። እስካሁንም ከ17 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ልየታ የተደረገባቸው መንገደኞች የ21 ቀን ክትትል ተደርጎላቸው ነጻ መሆናቸው ታውቋል።

በአጠቃላይ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ኬላዎች የልየታ ማዕከል ተቋቁሞ እየተሰራ መሆኑንም የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል።

በዙፋን ካሳሁን

FBC

Ethiopia plants 350m trees in a day to help tackle climate crisis

 • National ‘green legacy’ initiative aims to reduce environmental degradation

theguardian – About 350m trees have been planted in a single day in Ethiopia, according to a government minister.

The planting is part of a national “green legacy” initiative to grow 4bn trees in the country this summer by encouraging every citizen to plant at least 40 seedlings. Public offices have reportedly been shut down in order for civil servants to take part.

The project aims to tackle the effects of deforestation and climate change in the drought-prone country. According to the UN, Ethiopia’s forest coverage was just 4% in the 2000s, down from 35% a century earlier.

Ethiopia’s minister of innovation and technology, Dr Getahun Mekuria, tweeted estimates of the number of trees planted throughout the day. By early evening on Monday, he put the number at 353m.

The previous world record for the most trees planted in one day stood at 50m, held by India since 2016.

Dr Dan Ridley-Ellis, the head of the centre for wood science and technology at Edinburgh Napier University, said: “Trees not only help mitigate climate change by absorbing the carbon dioxide in the air, but they also have huge benefits in combating desertification and land degradation, particularly in arid countries. They also provide food, shelter, fuel, fodder, medicine, materials and protection of the water supply.

“This truly impressive feat is not just the simple planting of trees, but part of a huge and complicated challenge to take account of the short- and long-term needs of both the trees and the people. The forester’s mantra ‘the right tree in the right place’ increasingly needs to consider the effects of climate change, as well as the ecological, social, cultural and economic dimension.”

አዲስ ብድርና ቁጠባ ተቋም በገፍ እየሰጠ ያለው ብድር እያወዛገበ ነው – ሁለት ወር ባልሞላ ጊዜ ከ200 ሚሊየን ብር በላይ አበድሯል

ዋዜማ ራዲዮ– በአብዛኛው በአዲስ አበባ አስተዳደር እንደሚተዳደር የሚነገርለት የአዲስ ብድርና ቁጠባ ከቅርብ ወራት ወዲህ እየሰጠ ያለው በዘመቻ መልክ እየተካሄደ ያለ ብድር በፋይናንስ ተቋሙና በከተማው አስተዳደር ውስጥ መደናገርና ጥርጣሬ አስከትሏል። ከዚህ ቀደም ይህ አክስዮን ማህበር ብድርን ሲሰጥ ተያዥን ጨምሮ የሚጠይቃቸው የተለያዩ ያሉ መስፈቶች ነበሩ። ሆኖም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ “ተያዥ አያስፈልግም” በሚያስብል ደረጃ ብድር እየሰጠ እንዳለ እየታየ ነው።ሁለት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥም ከ200 ሚሊየን ብር የበለጠ ብድር ሰጥቷል።

ቀለል ያለ ብድር ለስራ ፈጠራ መልካም መሆኑ ይነሳል።ነገር ግን ብድር ሲሰጥ ብድር የሚሰራበት ፕሮጀክት አዋጭ ነው ወይ? ፕሮጀክቱ ተሳክቶ ብድሩ ይመለሳል ወይ? የሚሉ ግምገማዎች ይደረጋሉ።

አሁን በአዲስ ብድርና ቁጠባ እየተሰጡ ያሉ ብድሮች እነዚህ መስፈርቶች ከቁብ ሳይገቡ ሶስት-ሶስት ሁነው የተደራጁ ወጣቶች አንዱ ለአንዱ ተያዥ እየሆኑ ከ300 ሺህ እስከ 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር እየሰጠ እንደሆነም ሰምተናል። ይህን ብድር በአዲስ አበባ ባሉ ወረዳዎችና በአዲስ አበባ ዙርያ ባሉ ከተሞች እየሰጠ መሆኑን ራሱ ተቋሙ በመገናኛ ብዙሀን በማስታወቂያ እያስነገረ ይገኛል። ለብድርም ሲባል የፕሮጀክት እቅድ ሽያጭ የተለመደ ስራ እየሆነ መጥቷል።

ሪፖርተር ጋዜጣ እንደዘገበው ደግሞ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ የአዲስ ብድርና ቁጠባ ሀላፊ አቶ አሸብር ብርሀኑን ማገዳቸውን ገልጿል። ሀላፊው የብድር አሰጣጡ ላይ ተቃውሞ እንደነበራቸውም የሰራ ባልደረቦቻቸው ለዋዜማ አረጋግጠዋል።

ከወትሮ በተለየ መልኩ የከተማ አስተዳደሩ በአዲስ ብድርና ቁጠባ በኩል እንዲህ ብድር ማሰራጨት ለምን ፈለገ ? በሚል ለአንድ የአክስዮን ማህበሩ የዘርፍ ሀላፊ ላነሳነው ጥያቄ ፣ ብድሩ እየተሰጠ ያለው የከተማ አስተዳደሩ በመደበው ገንዘብና ብድሩንም ቀለል ባለ ሁኔታ እንድንሰጥ ታዘን ነው የሚል ምላሽ አግኝተናል። በዚህም ሳብያ ባንኮች በተለይም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአዲስ አበባ ቅንጫፎች ከየወረዳው የአዲስ ብድርና ቁጠባ አክስዮን ማህበር ጽህፈት ቤቶች የባንክ ሂሳብ እንዲከፈትላቸው ደብዳቤ በተጻፈላቸው ወጣቶች የአገልግሎት ጥያቄ መጨናነቃቸውን ከባንኩ ምንጮቻችን ሰምተናል።

ይህ ክስተት የከተማው አስተዳደር ፖለቲካዊ ቅቡልነት ለማግኘት የዘየደው ስትራቴጂ መሆኑን ተደጋጋሚ አስተያየቶች ይሰማሉ።ታከለ ኡማ ምክትል ከንቲባ ሆነው ከተማውን ማስተዳደር ከጀመሩ ጊዜ ጀምሮ ወደ ስልጣን የመጡበት መንገድ ለሳቸው ሲባል ህግ ተስተካክሎ በመሆኑ ውግዘት የገጠማቸው ቢሆንም ቀላል የማይባል ነዋሪ ደግሞ ጊዜ ሰጥተን በስራቸው እንመዝናቸው በሚል ይሁንታን ቸሯቸዋል። የወሰዷቸው መልካም እርምጃዎች እንዳሉ ሁሉ በየተቋማቱ ባሉ የአመራር ቦታዎች ላይ ማንነት ተኮር የሆነ ምደባ ተደርጓል ተብሎ በመታመኑ ግን ከባድ ትችት ውስጥ ወድቀዋል።

አሁን እየታየ ያለው የብድር አስጣጥ በ1997 ምርጫ የደነገጠው የቀድሞው የኢህአዴግ አስተዳደር እስከ 2002 አ.ም ምርጫ ድረስ ከሶስት ሺህ ጀምሮ የተለያየ መጠን ያለው ብር እንደማይመለስ እየታወቀ በገፍ በከተማው ሲረጭ መቆየቱ ይታወሳል። በ100 ሺዎች የወሰዱት ብድር አልተመለሰም። በከተማውም በዚህ መልኩ በቂ ስራ መፍጠር አልተቻለም።አሁን እየታየ ያለው የብድር መስፈርት ልልነትም ከከዚህ ቀደሙ ጋር ተመሳሳይነት አለው። ለስራ ፈጠራ ብድር መቅረቡ የሚደገፍ ቢሆንም ገንዘቡ ስራ መፍጠሩ እና መመለሱ መረጋገጡ እጅጉን ተገቢ ነው።

የከተማ አስተዳደሩ በሁለት ቢሊየን ብር ተንቀሳቃሽ ገንዘብ በነዳጅ ማደያ እና በፈጣን ምግቦች ሽያጭ ዘርፍ ለአስር ሺዎች ስራ እፈጥራለሁ ብሎ በከተማው ምክትል ከንቲባ ታከለ በኩል በቅርብ ጊዜ ይፋ ያደረገውን እቅድ የት አድርሶት ነው? ዛሬ እንዲህ መጣደፍ ውስጥ የገባው የሚል ጥያቄን ማስነሳቱ ነው። በሁለት ቢሊየን ብር የወጣው እቅድም አተገባበሩ መልካም ከሆነ በመልካም ተወስዶ ነበር።

እንደ አዲስ ብድርና ቁጠባ አይነት ተቋማት ገንዘብ የሚያገኙት ከአለም አቀፍ ለጋሾችና ውጭ የኢትዮጵያ ንግድ በትንሽ ወለድ የሚሰጣቸውን ብድር ነው መልሰው የሚያበድሩት። አዲስ ብድርና ቁጠባ ለስሙ ከአስተኛ የፋይናንስ ተቋማት ውስጥ ተመደበ እንጂ ካፒታሉ ከአራት ቢሊየን በልጦ በአመትም ከስምንት ቢሊየን ብር በላይ አበድራለሁ ብሎ የሚያቅድ በኢትዮጵያ ለመጨረሻ ጊዜ ከተቋቋሙ የግል ባንኮች በሀብት የሚስተካከል ነው።[ዋዜማ ራዲዮ]

የወቅቱ የአገራችን ችግር፤ የሐሰት ዜና ወረርሽኝ!

ጎልጉል – በኢትዮጵያ ደረጃ የሚታየው መድረሻውን ያስቀመጠ የሀሰተኛ መረጃ ሻሞ ወይም እርባታ ሕዝብን እንደ ዋዛ እያሳከረ፣ አገርን ለአደጋ የሚዳርግ፣ ታስቦበት፣ በዕቅድ፣ በባለሙያ፣ በበጀት፣ በድርጅት፣ በመሪ፣ በሥልጠና የሚከናወን የዘመኑ የዲጂታል ጦርነት ነው።

ሰሞኑን የፓሪስ ከተማ ክፉኛ ተንጣ ነበር። የናጣት በማኅበራዊ ሚዲያ የተሰራጨ አንድ ሐሰተኛ መረጃ ሲሆን፣ መረጃው “የፓሪስ ውሃ ተመርዟልና አትጠጡ” የሚል የጅምላ ጥሪ ነበር። መረጃው የነፍስ ጉዳይ በመሆኑ የከተማዋን ነዋሪዎች ክፉኛ ናጣቸው። ይህንን አሸባሪ መረጃ ለመከላከል የፓሪስ አካባቢ ኃላፊዎች መግለጫ እንዲሰጡ አስገደዳቸው። በመሆኑም አርብ ሐምሌ 12፤ 2011 (ጁላይ 19) ተመረዘ የተባለው ውሃውእንደተባለው እንዳልተመረዘና ለመጠጥም ቢሆን ምንም የማያሰጋ መሆኑን አስረግጠው ተናገሩ።

ይህ የሐሰት መረጃ ፓሪስን ለዚህ ሊያደርሳት የቻለበት ዋናው ምክንያት አንድ ACRO የተባለ ዕንባጠባቂ ድርጅት በፓሪስ ቧንቧዎች በሚተላለፈው ውሃ ውስጥ ትሪትየም (tritium) የተባለ የኑክሊየር ንጥረነገር ከሌሎች አካባቢዎች ይልቅ በብዛት ይገኛል ብሎ መዘገቡን ተከትሎ ነበር።

ይህንን ቁንጽል መረጃ በመያዝ በርካታዎች በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የፓሪስ ውሃ ተመርዟል፤ አትጠጡ የሚል መረጃ በማሰራጨት ሕዝቡን ሲያውኩ ቆዩ። በመሆኑንም የመንግሥት ኃላፊዎች በዚሁ የማኅበራዊ ሚዲያ በመውጣት ውሃው ውስጥ ከሌሎቹ አካባቢዎች መጠኑ ከፍ ያለ የትሪቲየም ንጥረነገር ቢኖረውም “ተበክሏል” የሚያስብል ደረጃ ላይ አለመድረሱን አስረዱ። ዕንባጠባቂው ድርጅትም ቢሆን ንጥረነገሩ ከሌሎች አካባቢዎች በላቀ ሁኔታ በፓሪስ አካባቢ ይታያል ቢልም ከሚገባው መጠን አልፏል ግን አላለም ነበር።

በያዝነው ዓመት መጋቢት ወር ላይ የወጣ አንድ ሪፖርት እንደዘገበው የውሸት/ሃሰት መረጃ በተለይ በማኅበራዊ ሚዲያ እንደ ሰደድ እሣት እንደሚስፋፋ ተናግሯል። ከፍጥነቱ በተጨማሪ ለረጅም ጊዜ የመቆየትና በበርካታ ቦታዎች ለብዙ ሰዎች እንደሚዳረስ የጥናቱ ተማራማሪዎች ተናግረዋል። ሰዎች ከእውነተኛ መረጃ ወይም ዜና ይልቅ ሐሰተኛ መረጃ ለማሰራጨት በጣም ፈጣኖች እንደሆኑ መረጃው አመልክቷል።

ጥናቱን ያደረጉ ተመራማሪዎች እንደ ግብዓት አድርገው የወሰዱት እኤአ ከ2006 – 2017 ድረስ በትዊተር የተሰራጩ ወሬዎች፤ የሐሰት መረጃዎችና ሹክሹክታዎችን መሠረት በማድረግ ነበር። በዚሁ ጥናት መሠረት 126,000 ሹክሹክታዎች በ3 ሚሊዮን ሰዎች አማካይነት፣ 4.5 ሚሊዮን ጊዜ ተሰራጭቷል፤ ተራብቷል።

የሐሰት መረጃዎች ባጭር ጊዜ ውስጥ ከ1,000 እስከ 100,000 ሰዎች ዘንድ ሲደርሱ፣ የእውነተኛ መረጃ ስርጭት ግን ከ1,000 ሰዎች በላይ አይዘልም። በሌላ አገላለጽ አንድ ሐሰተኛ መረጃ በቅጽበት ጊዜ ውስጥ 1,500 ሰዎች ዘንድ ሲደርስ፣ አንድ እውነተኛ መረጃ አንባቢያን ዘንድ የሚደርሰው በሚያስገርም ሁኔታ ስድስት እጥፍ ጊዜ ወስዶበት ነው። መረጃውን በማሰራጨት ቀዳሚውን ሥፍራ የሚወስደው ደግሞ ተራው ሕዝብ እንደሆነ የምርምር ዘባው አስረድቷል።

በአገራችን የለውጥ እንቅስቃሴ በመንግሥት ደረጃ ከተጀመረ ጊዜ ጀምሮ በዘመነ የትግራይ ነጻ አውጪ የ27 ዓመታት የግፍ አገዛዝ ዘመናት እምብዛም የማይታወቀው የሐሰት መረጃና ዜና በማኅበራዊ ሚዲያ በተለይም በፌስቡክና ዩትዩብ እየተሰራጨ እንደሚገኝ ብዙዎቻችን የምንመሰክረው ጉዳይ ነው። በእነዚህ የሐሰት መረጃዎች አማካኝነት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ክቡር የሰው ልጆች ህይወት እንደጠፋ፣ ንብረት እንደ ወደመ፣ ሰላም እንደ ደፈረሰ፣ አገራችን እንደታወከች፣ ወዘተ የሚክድ የለም።

የሃሰት መረጃ ለምን በረከተ? ከአፋኙ ዘመነ ህወሓት ይልቅ አሁን ለምን ሚዲያው በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ በሃሰት መረጃ ተሞላ? በዕቅድ የሚካሄድ የዲጂታል ጥቃት ውጤት ነው? ወይስ እንደው በዘፈቀደ የሆነ ተግባር ነው? በርካታ ገንዘብ የሚፈስበት ፕሮጀክት? ወይስ ጥቂት ግለሰቦች ከማኅበራዊ ሚዲያ ከሚገኘው ትርፍ ራሳቸውን ለማበልጸግ የሚያደርጉት የግል ፍላጎት ላይ የተተከለ የሳንቲም ለቀማ አባዜ? አገር ለማፍረስ የሚካሄድ የተቀነባበረ ተግባር? ወይስ የመንግሥትን ሸፍጥ ለማጋለጥ የሚደረግ የሚዲያ አርበኝነት? የለውጡን እንቅስቃሴ ማክሸፍ ዓላማቸው አድርገው በተነሱ የሚካሄድ ረቂቅ ሤራ? ወይስ “እውነትን እንዘግባለን” በሚል ፍካሬ ሳያውቁት የሌሎች ዓላማና ግብ ያላቸው ሴረኞች ቀጥተኛ መጠቀሚያና ሰለባ የመሆን ውሳኔ? ወዘተ። ጥያቄው ብዙ ነው። ጠያቂዎቹም በርካታ ናቸው።

ይህ ብቻ አይደለም ሌላም የጥያቄውና የአዙሪቱ መነሻ አለ። የትግራይ ነጻ አውጪ ባላሰበው ሁኔታ አገሪቱን እንዲነዳ ዕድል ካገኘበት ጊዜ ጀምሮ መሪዎቹ ባደባባይ ህዝብን ሲቀጥፉ፣ ዓይናቸውን ታጥበው ሃሰታቸውና ሸፍጣቸውን በሌላ ሸፍጥ ሲያስተባብሉ፣ አገርን በሚያክልና አገራዊ እሴት ባላቸው ታሪካዊ ንብረትና ማንነት ላይ ሲሻቀጡ በነበረበት የ27 ዓመታት የክሽፈት ዘመን ለምን የሃሰት ዜናን የማስተባበል ተቃራኒ ሤራ ልክ አሁን ባለው ደረጃ አልተስፋፋም? ዛሬ በንፅፅር ሚዲያው ክፍት በሆነበት ዘመን የጠራ መረጃ ለህዝብ ማድረስ እየተቻለ ዓላማ ያላቸው የሃሰተኛ ዜና ዘገባዎች ለምን ጎልተው ወጡ? ማንስ ነው የሚያመርታቸው? በምን ያህል የድርጅትና የስትራቴጂ ነዳፊዎች ዘገባዎቹ ተመርተው ይከፋፈላሉ? ማን ላይ ነው መሠረታዊ የማነጣጠሪያ መውጊያቸው የሚያርፈው? አንዳንድ ቁልፍ ጉዳዮች ሲነሱ እንዴት ተጠልፈው ወደ ሤራው ቋት እንዲገቡ ይደረጋሉ? የሚሉትን ዜጎች በጥሞና የመመርመር ፈቃደኛነቱ ካላቸው ቲያትሩ ዕርቃን የሚሆን የተገለጠ ምሥጢር ነው። “እረኛውን ግደል፣ መንጋው ይበተናል” እንዲሉ  ነውና!!

ባለፉት ጥቂት ቀናት የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር ሊቀመንበር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል “ኢህአዴግ ውስጥ እኔ ብቻ ልደመጥ የሚል የኦሮሞ ጽንፈኛ ኃይል ተነስቷል … ወደ ዋሻው ካልተመለሰ ኢትዮጵያ ትፈርሳለች” በሚል ሪፖርተር ላይ ተናገረ ተብሎ በየሚዲያው የተሰራጨው የሃሰት መረጃ እንደሆነ ታውቋል። መረጃው በፎቶሾፕ ተጠናክሮ በሪፖርተር ታፔላ ተቀናብሮ ሲቀርብ በርካታዎች እውነተኛ ነው በማለት አሰራጭተውታል። ከደብረጽዮን ባህርይና ህወሓት ከሚከተለው ፀረ ለውጥ አቋም አኳያ መረጃውን ትክክል ነው ብሎ ለመቀበል ብዙም የሚያዳግት አልነበረም። የመረጃው አሰራጪዎችም የተጠቀሙት ይህንኑ እሳቤ ጠንቀቀው ስለሚያውቁት ነው ማለት ይቻላል።  

አገር ለማዳን የሃሰት መረጃ ላይ ዘመቻ ከወጡ አገር ወዳዶች መካከል የሪፖርተሩ ዳዊት እንደሻው ይህንን ስለ ደብረጽዮን የተሰራጨውን መረጃ በተመለከተ ሲጽፍ ፎቶው “ከሳምንት በፊት ከታተመዉ ጋዜጣ የተወሰደ ነዉ፣ የወጣዉን ዕትም እና ተመሳሳይ የቅፅ ቁጥር በመጠቀም የተቀናበረ (photoshop) ነዉ” ይላል። ሲቀጥልም “ሪፖርተር ጋዜጣ የተመሠረተበት ዓመት ጳጉሜ 6 ቀን 1987 ዓ.ም ሲሆን በግራ በኩል በምታዩት የሀሰት ምስል 21987 ተመሰረተ ተብሎ ተለጥፏል” በማለት የመረጃውን ሃሰተኛነት አጋልጧል።

ይህ እንግዲህ ስፍር ቁጥር ከሌላቸውና በአገራችን ሕዝብ ዘንድ ከተሰራጩ የሃሰት መረጃዎች አንዱ መሆኑ ነው። ከዚህ በፊት እጅግ በርካታ መረጃዎች ከሀሰተኛና በፎቶሾፕ ከተሰሩ ምስሎች ጋር ተቀነባብረው ወጥተዋል። ከጠ/ሚ/ር ጽ/ቤት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ፊርማ፣ ቀንና ቁጥር እንዲሁም ማኅተም ያለው ደብዳቤ ዶ/ር ብርሃኑ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ሆኖ ተሾመ በሚል ከወጣው ሃሰተኛ መረጃ ጀምሮ ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጩና ለደም መፋሰስ የሚጋብዙ ሥፍር ቁጥር የሌላቸው መረጃዎች በተለይ በፌስቡክ ሲሰራጩ ቆይተዋል። በዚህም ድርጊት በሚዲያው ዓለም ተዓማኒነት አለን ከሚሉት የዳያስፖራ የሚዲያ አውታሮች ጀምሮ እስከ ራሳቸውን “አክቲቪስት” ብለው የሚጠሩ ጭምር አውቀውም ይሁን ሳያውቁት ተሳታፊ ሆነው አንሾካሽከውታል፤ አሰራጭተውታል። የሚገርመው ማንሾካሾክ ታላቅ ተግባር ተደርጎ በኢትዮያዊያን ስም አደባባይ ሲያሸልምም ታይቷል። ይህንን ያስተዋሉ ባይበዙም ሃፍረታቸውን በመልዕክት ሳጥናችን ልከዋል።

ከላይ ለመግለጽ እንደተሞከረው እንዲህ ዓይነቶቹን አድራሻ አልባ ግጭት ጫሪ መረጃዎችን የሚያወጡት ኃይሎች የራሳቸው የሆነ ዓላማ እንዳላቸው ለመገመት ቢቻልም የፈጠራውን መረጃ የሚያራቡና የሚያከፋፍሉት ሌሎች  “እኔ የትኩስ መረጃ ባለቤት ነኝ”፤ “እውነትን ብቻ እንዘግባለን”፤ “የ … ገጻችንን ላይክ፣ ሰብስክራይብ፣ ታግ፣ ሼር አድርጉ” በማለት ከማኅበራዊ ሚዲያ ማስታወቂያ በሚገኝ “ገቢ” ራሳቸውን “ብልጥ ዲጂታል ጋዜጠኛ” ያደረጉና ኑሯቸውን በዚያ የመሠረቱ እንደሆኑ አይካድም፤ እነሱም አይስተባብሉም። አንዳንዶቹም በርካታ ድረገጾችንና የማኅበራዊ ድረገጽ አካውንቶችን በመክፈት “በሥፍራው የሚገኘው ዘጋቢያችን” እያሉ ከአንዱ ገጻቸው ወደሌላኛው መረጃ በማገለባበጥ የራሳቸውን ገጽ እንደ ምንጭ በመጠቀም አገር አፍራሾችና “ዲጂታል ኪስ አውላቂዎች” መሆናቸውን ያረጋግጡልናል።

ይህ ጉዳይ እጅግ ያሳሰበው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በመጋቢት ወር የማኅበራዊ ሚዲያን አጠቃቀም በተመለከተ ለሕዝቡ ማሳሰቢያ አዘል መግለጫ ሰጥቶ ነበር።  ያም ሆኖ ጉዳዩ ይበልጡኑ እየተባባሰ እንጂ እየበረደ አልመጣም። የባለሥልጣናትን ንግግር ሳይለፉ ከመንግሥት ሚዲያ በማውረድ (ዳውንሎድ በማድርግ) እና በመቆራረጥ፣ ለበጎ የተሰነዘሩ ሃሳቦችን ስም እየጠሩ እገሌ እገሌን “ነገረው፣ አጠጣው፣ አፈረጠው፣ አዋረደው፣ አስገባለት፣ ዘነጠለው፣…” የሚል የ“ጮኸ” ርዕስ በመስጠት የሪፖርቱን ወይም የንግግሩን ዓላማ በማሳት ወይም ከጉዳዩ ጋር የማይገናኝ ርዕስ በመስጠት ምንጭ ያለውን መረጃ ወደ አልተፈለገ አቅጣጫ የመምራት ልምድ ሃይ የሚለው ማጣቱም ሌላው ችግር ነው።

ሰሞኑን ወደተሰራጨ አንድ መረጃ እናምራ፤ “ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገዳዮች መሪ ነው” የሚለውን ጨምሮ በርካታ የነቀፌታና ጥላቻ አዘል ትችት በዶ/ር ዐቢይ ላይ የሰጡት ዶ/ር ደረጀ ዘለቀ የግድያ ሙከራ ተደረገባቸው በማለት ዘ-ሃበሻ በፊትለፊት ገጹ መዘገቡና ይህንኑ ተከትሎ የማኅበራዊ ገጾች ዜናውን ማራባታቸው ቀውስ ፈጥሮ ነበር። ዘ-ሐበሻ “ዜናውን” ያሰራጨው ከሳተናው ድረገጽ ላይ በመጥቀስ ነው። ሁለቱም ድረገጾች “እህትማማች” እንደሆኑ እዚህ ላይ ልብ ይሏል።

ባልተጣራ ምንጭ ዶ/ር ደረጀ በሰነዘሩት ትችት ሳቢያ የግድያ ሙከራ ተደረገባቸው የሚለው ዜና “ዶ/ር ደረጀ ዘለቀ በዐቢይ አህመድ ከተቀነባበረባቸው የሞት ድግስ መትረፋቸው እየተሰማ ነው። ትናንት እሁድ ጭንብል የለበሱ ገዳዮች በመኪና ደፍጥጠው እንዲገሏቸው የተጠነሰሰው ሴራ የሁለት ጎዳና ተዳዳሪዎችን ህይወት እና የመኪና ግጭቶችን በማስተናገድ ተጠናቋል” በሚል ሳምሶን ያይሉ በሚባሉና በሌሎች የማኅበራዊ ገጽ “አርበኞች” ተሰራጭቶ ነበር።

ዘ-ሐበሻ “ምንጮቼ” ያላቸው ክፍሎች እነዚህ ይሁኑ ሌላ በግልጽ ባይታወቅም፣ ዜናው መሰራጨቱን ተከትሎ በዶ/ሩ ቤተሰቦች፣ ወዳጆችና ባልደረቦች ዘንድ ቀላል የማይባል ችግር እንደፈጠረ ለማወቅ ተችሏል።

ይህንን የፈጠራ ዜና ለማሰራጨት የተፈለገበት ልዩ ምክንያት ይፋ ባይሆንም፣ ዜናው አገሪቱ ውስጥ መረጋጋት እንዳይፈጠር ሆን ብለው በጀት መድበው የሚሠሩ አካላት ያደረጉት ለመሆኑ ግን አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል፤ ጥቂት የማይባሉም ቁጣቸውን ገልጸዋል።

ሃሰተኛ ዜናዎችን እያሳደዱ ከሚያመክኑ ዜጎች መካከል አንዱ የሆነው ኤሊያስ መሠረት የፈጠራው ዜና መሰራጨቱን ተከትሎ ዜናውን እያራገቡ ላሉ፣ በዜናው ለተደናገጡ ወገኖች ምላሽ ይሆን ዘንድ ተጎዱ የተባሉትን ዶ/ር ደረጀ በማነጋገር ትክክለኛውን መረጃ አሰራጭቷል። ይህንን ነበር ያለው፤ “ዶ/ር ደረጄን ቅድም ስለዚህ ዜና ጉዳይ ሳወራቸው (እንዲህ ብለውኛል) “የሚገርምህ ምናለ ቲቪ ላይ ቀርቤ ባላወራሁ ነው ያሰኘኝ። ቤተሰብ እና ጓደኞቼ በጣም ነው የደነገጡት። ይህ ጭካኔ ነው። ሕዝቡ ግን የሃሰት ዜና እነማን እያሰራጩ እንደሆነ በዚሁ ይገንዘብ” ብለውኛል።

ዶ/ር ደረጀ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ባሳለፉት ትዕዛዝ መሠረት ማስክ ባጠለቁ ቅጥር ነፍሰ ገዳዮች በመኪና ግድያ ሊፈጸምባቸው እንደነበር ምንጮች ጠቅሶ የዘገበው ድረገጽ ሳተናው ሲሆን እህት “የሙያ አጋሩ” ዘ-ሐበሻ ደግሞ ዜናውን እንዳለ አውርዶታል። ሆኖም ዜናው የውሸት እንደሆነ ይፋ ከተደረገ በኋላ ዘ-ሐበሻ ይህንን ብሎ ነበር፤ “በሳተናውና በዘ-ሐበሻ ድረገጽ ላይ በዶ/ር ደረጀ ዘለቀ ላይ የግድያ ሙከራ ተደረገ የሚለው ዜና በስህተት የተለጠፈ ስለሆነ አንባቢዎቻችንን ስለተደረገው ስህተት ይቅርታ እንጠይቃለን” ብሏል። ይሁን እንጂ ዶ/ር ደረጀ ምንም የደረሰባቸው አደጋም ሆነ የአደጋ ሙከራ አለመኖሩን በይቅርታው ሃረግ ውስጥ አላካተተም።

ዜናው የፈጠራ ወይም የሃሰት ሆኖ ሳለ ዘ-ሐበሻ “በስህተት የተለጠፈ” ሲል ስህተቱን በማሳነስና በሌላ ሶስተኛ ወገን እንደተደረገ አድርጎ ማቅረቡ ይቅርታውን ሰባራ እንደሚያደርገው ለሙያው ቅርበት ያላቸው ይናገራሉ። የተሰራጨውን የሃሰት ዜና ተከትሎ እውነተኛ ቀውስ ቢደርስ፤ ግለሰቡ ጥቃት ደረሰባቸው በሚል የተነሳሳ ኃይል አፀፋ ቢመልስ፤ ወዘተ ተጠያቂ ሊሆን የሚገባው ሚዲያ ማስተባበያውን ሃሰተኛውን ዜና ባሰራጨበት መጠንና ድምጸት ልክ ሊሠራው በተገባ ነበር።

ከግራ ወደ ቀኝ ከበእውቀቱና አምባሳደር ፍጹም መካከል የሚገኘው ሔኖክ ዓለማየሁ ነው

የኢትዮጵያዊያን ስፖርት ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ በቅርቡ አትላንታ በተካሄደበት ወቅት የዘ-ሐበሻ አዘጋጅ “ሌት ተቀን እንቅልፉን በመሰዋት መረጃ በመስጠት ተመስግኗል”። አቶ አበበ ባልቻ ሽልማት ያበረከተለት የዘ-ሐበሻ ባለቤት ከተወደሰበት ሥራው አንዱና ትልቅ ተደርጎ የተወሰደው ከሐሰተኛ ዜና ረድፍ የሚመደበው “ሹክሹክታ” የሚለው ዝግጅቱ ነው። ይህ በየማኅበራዊ ገጾች ላይ የሚሰራጨው መረጃ አልባ ሃሜቶችን መሠረት ያደረገ ዝግጅት ለሽልማት የሚያበቃ መሆኑ የአዘጋጅ ኮሚቴ (ፌዴሬሽኑም ካለበት) የሽልማት መፈርት፣ ሽልማቱ ምንን ለማበረታት እንደሆነና ዓላማው ምን እንደሆነ ሽልማቱን ተከትሎ ሊቀርቡ የሚችሉ ጥያቄዎች ናቸው። ወይስ በያዝከው የሃሰተኛ መረጃ ስርጭት ቀጥልበት ማለት ይሆን? (በርግጥ የዶ/ር ደረጀ ሃሰተኛ ዜና ከመውጣቱ በፊት ሽልማቱ መሰጠቱ ግልጽ ነው፤ ሆኖም ይህ የዘ-ሐበሻ ሹክሹክታ ዓምድ በቅርቡ ጋብቻውን የፈጸመ የመብት ተሟጋችን መረጃ ያለባለቤቱ ፈቃድ ከሠርጉ አዘጋጅ በወዳጅነት ስም በመውሰድ ካሰራጨ በኋላ በባለጉዳዩ ተቃውሞ ከዩትዩብ ስለመውረዱን ጎልጉል መረጃ አለው)።

ሆኖም ግን “ሹክሹክታ” በራሱ የሚያሸልም ሆኖ ከሌሎች መቅረቡ፣ በተለይም በሙያው ከገዘፉና ዘመን ተሻጋሪ በሆነው ሥራቸው ትውልድ ሲያስታውሳቸው የሚኖሩ ሥመጥሮች የዚህ ሽልማት ተሳታፊ ሆነው መቅረባቸው፤ የመንግሥት ተወካይ (አምባሳደር) የሆኑትና ከወራት በፊት የጠ/ሚ/ሩ ፕሬስ ኃላፊ የነበሩት ፍጹም አረጋ መገኘታቸው ጉዳዩን ውስብስብ አርድጎታል። ይህ መሥፈርቱ ምን እንደሆነ ያልታወቀ የወዳጅነት ሙገሳና ሽልማት በተመለከተ ፌዴሬሽኑም ሆነ ሌሎች የሚልኩልን ካለ ለማስተናገድ ዝግጁ ነን። ዘ ሃበሻም የሚለው ካለ እናስተናግዳለን። እዚህ ላይ ይህንን ያነሳነው ለማሳያ እንዲሆን እንጂ ሌሎች በርካታ ችግሮች በማወቅም ይሁን ከላይ እንደተባለው ሆን ተብሎ በተለያዩ ሚዲያ እንደሚሰራጭ እሙን ነው።

ሃሰተኛ ዜናን ለመከላከልና ሕዝብን ከዚህ ሱስ ነጻ ለማውጣት የሚተጉ ባለሙያዎች በየጊዜው እንደ ሰደድ እሣት እየተሰራጨ የመጣውን ይህንን ወረርሽኝ ለመከላከል የሚከተሉትን ሀሳቦች ይለግሳሉ። እነዚህ ነጥቦች በቅርቡ (ጁላይ 18፤2019) በሳይኮሎጂ ቱዴይ ላይ የወጣ ነው

·        ሁሉንም መጠራጠር፤ የትኛውንም መረጃ ቢሆን 100 እርግጠኛ ነው ብሎ አለመቀበል፤ መጠን ያላለፈ ጥርጥር ይጠቅማል እንጂ አይጎዳም

·        ምንጩን ማጣራት፤ የመረጃው ባለቤት ማን እንደሆነ መጠየቅ፣ እንደዚህ ዓይነት መረጃ ለማውጣት የተፈለገበትን ምክንያት ለማወቅ መሞከር፣ ለምሳሌ ስለ ህወሓት የሚያጠና አይጋ ፎረም ላይ ስለ ህወሓት ቅድስና የተጻፈውን እንደ ማስረጃ አድርጎ መውሰድ ከንቱነት ነው

·        ጉግል አምላክ አይደለም፤ ጉግል ላይ ተፈላጊ መረጃ ማግኘት ይቻላል፤ ሆኖም በጉግል የሚጎለጎል ሁሉ ሙሉ ተዓማኒ መረጃ አድርጎ መውሰድ የዋኅነት ነው

·        ሰከን ማለት፤ የዜና በተለይ የሃሰተኛና ሐሜታዊ ዜና ዋና ባህርዩ ፍጥነት ነው፤ ሳያመዛዝኑ መስማት ወይም ማንበብና ለሌላው ማስተላለፍ፤ ስለዚህ የትኛውንም መረጃ ወደሌላ ከማስተላለፍ በፊት በሰከነ መንፈስ ማንበብና ማሰላሰል

·        ሌሎችስ ምን ይላሉ ብሎ መጠየቅ፤ አንድ መረጃ በአንድ ሚዲያ ከወጣ በኋላ ሌሎች የሚዲያ አውታሮች ስለ መረጃው ወይም በተመሳሳይ ጉዳይ ላይ ምን እንዳሉ ማጣራት

·        በአስተያየትና በዜና፣ በሐሜት አዘል መረጃና በእውነተኛ፣ በግምታዊ አስተሳሰብና መሬት በረገጠ አሠራር መካከል ያለውን ልዩነት በቅድሚያ መረዳት፤ አስተያየት፣ ወሬ፣ ሹክሹክታ፣ ሐሜት፣ መላምት፣ ወዘተ ዜና አይደለም

·        ርዕስ በማንበብ ብቻ አለመወሰን፤ በርካታ ሰዎች ዝርዝር መረጃውን እስከመጨረሻው ድረስ ሳይሆን የሚያነቡት ርዕሱን ብቻ በማየት የራሳቸው ድምዳሜ ላይ ነው የሚደርሱት፤ ይህንን የሚውቁ ጮሌዎች ርዕሱን በማጦዝ ቀልብ በመሳብ የሃሰት መረጃቸውን እንደሚያሰራጩ መረዳት

·        የወሬ (የዜና) ሱሰኛ አለመሆን፤ በርካታዎች “ዛሬ ደግሞ ምን አዲስ ነገር አለ” በማለት ወሬ ፍለጋ በማኅበራዊ ገጾች ላይ ጊዜያቸውን ስለሚያጠፉ ይህንን የሚውቁ ብልጦች የመረጃ ዶፍ በማዝነብ አሰሱንም ገሰሱንም ስለሚያወርዱባቸው ሰለባ ለመሆን የተጋለጡ ናቸው፤ በ2017ዓም Nature Human Behaviour ያወጣው ጥናት እንደሚጠቁመው ወሬ አነፍናፊዎችና “ዛሬ ምን አዲስ ነገር አለ” ባዮች እንደ ሰደድ እሣት ለሚሰራጩ የሃሰት መረጃዎች ተጋላጭና የቅድሚያ ተጠቂዎች ናቸው፤ እነዚህን ጠቃሚ ምክሮች ብቻ መከተል ከበርካታ ችግር ራስንና አገርን ለመታደግ ያበቃል።  ከሁሉም በላይ ምንም ይሁን ምን ቢያንስ ቢያንስ ጊዜ ወስዶ ሙሉውን ማንበብ ራስንና ሌሎች ከአደጋ ይጠብቃልና ልብ እንበል።     

አገራችን በተለያየ ጽንፍ እየተናጠች ነው። አገር በማፍረስ ጉዳይ ላይ የተጠመዱ ወገኖች ጥቂት የማይባለውን የመረጃ ተጠቃሚ በሃሰት መረጃ እያወዛገቡት ይገኛል። ይህንኑ መረጃ ተቀብለው በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ወይም ለግል የኢንተርኔት ገቢ ሲባል በሰበር ዜና ስም እያሰራጩ ያሉት ዝም ማለት አገር ለማፍረስ ቀንተሌት ከሚተጉት ተለይተው ሊታዩ አይችሉም። ስለዚህ የአገር ጉዳይ የሚያሳስባቸው ሕዝብን የመምከርና የማነጽ ኃላፊነት አለባቸው። ሚዲያውም “ወሬ” ከማጦዝ ሰከን ብሎ ይህ ሁሉ መሆን የሚችለው አገር ስትኖር እንደሆነ መገንዘብ ይገባዋል። አገር ከፈረሰች በኋላ “ሰበርም” ሆነ “ትኩስ” ዜና ወይም “እጃችን የገባ ምሥጢርም” ሆነ “ሹክሹክታ” ዋጋ አይኖራቸውም፤ ለፈረሰ አገር ዜናም ሆነ የሃሜት ዜና ወይም ሹክሹክታ (ጎሲፕ) ማንም ጆሮ አይሰጥም። እናም ከ“ሻሞ” እንጠበቅ።

ለተቆርቋሪ ዜጎች – አገራችን በዚህ መልኩ ሤረኞች መጥነውና ደቁሰው ከማኅበራዊው፣ ከኢኮኖሚው፣ ከፖለቲካው፣ ከመዝናኛው ጎዳይ የሃሰት መርዝ እያመረቱ አገር አልባ ሊያደርጉን ሲባቱ አገር ወዳዶች ስለምን ዝም ትላላቹህ? የእናነት ዝምታ ለሴረኞች የሐሰተኛ መረጃ ወረርሺኝ ዳርጎናልና ድምጻችሁን እንድታሰሙ። በሚበጀውና በሚያመቻቹህ መንገድ ሤራውን ለማክሸፍ ያለ ቀስቃሽ እንድትተጉ በመጪው ትውልድና በአገራችን ስም እንማጸናለን።

ዝግጅት ክፍሉ – ይህ ጽሁፍ ሙሉ በሙሉ ከጎልጉል የተወሰደ ነው። ይህንን ጽሁፍ ተንተረሶ አስተያየት መጻፍ ለምትፈልጉ ክፍት ነው


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ንብረት ናቸው። ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን።

Ethiopia PM launches 4 billion tree planting project, starting in Oromia

Ethiopian Prime Minister Abiy Ahmed over the weekend kicked off what is meant to be a mission to plant four billion trees across the country – Africa’s second most populous nation.

The initiative which is under the banner of the National Green Development program is set to started during the rainy season.

“Over the past years Ethiopia’s forest coverage has decreased (in recent years) and the initiative is set mobilize national reforestation at 40 trees per head,” the PM’s office said in a social media post.

Abiy held discussions with the National Agri Transformation leaders in Adama city, in his home region of Oromia. He tasked participants – which included most high-profile government officials – on their role and responsibilities in modernizing the sector.

Ethiopia has in recent years have suffered from the negative impact of climate change especially in relation to droughts in parts of the country. Reports indicate that in 2017, over 2 million animals died in Ethiopia due to drought because of the scarcity of rainfall.

Office of the Prime Minister – Ethiopia

@PMEthiopia

PM Abiy Ahmed held discussions with national agri transformation leaders in Adama city on their role & responsibilities in modernizing the sector. He called upon them to champion the National Green Dev’t Program which aims to plant 4billion trees during the rainy season. 1/2

African news

Ethiopia coffee, oilseeds export revenues hit 1.2 bln USD amid growing interest from China

ADDIS ABABA, July 27 (Xinhua) — The Ethiopian government on Saturday said the country made more than 1.2 billion U.S. dollars in revenue from the exports of coffee and oilseeds during the just-concluded Ethiopian fiscal year that ended on July 7.

The revenue was generated from the export of coffee, mung beans, white kidney beans, sesame seeds and soya beans, state-affiliated Fana Broadcasting Corporate (FBC) reported on Saturday.

Large amount of the export revenue was generated from the export of coffee. Ethiopia is one of Africa’s largest producers of Arabica coffee, in which coffee production is dubbed as the backbone of the country’s agriculture-led economy.

Ethiopia also recently revealed a new initiative to uplift the current close to 600,000 tons of annual coffee production to 1.8 million tons within the coming five years period.

According to the Ethiopian Coffee and Tea Authority (ECTA), the Chinese market is expected to be a major destination for the nation’s coffee exports.

In April this year, China and Ethiopia signed a Memorandum of Understanding on coffee exports to China and to deepen bilateral trade cooperation.

Amid increasing demand for coffee among younger Chinese, penetrating the emerging coffee market is also increasingly seen as a major priority among Ethiopian coffee producers and exporters.

Ethiopia’s sesame production, which is also considered as one of Ethiopia’s top export commodities next to coffee, has in recent years witnessed growing interest from the Chinese market.

Haile Berhe, President of the Ethiopian Pulses, Oilseeds and Spices Processors-Exporters Association, told Xinhua recently that the export of sesame seed to China currently constitutes close to 70 percent of the East African country’s total export of the product to the global market.

China is already the east African country’s major export destination. Ethiopia, during the previous Ethiopian 2017-2018 fiscal year, had exported 245 million U.S. dollars of goods to China, according to the Ethiopian Ministry of Trade.

Genale Dawa hydro, Aisha wind power plants to start generation in Ethiopia

The Ministry of Water, Irrigation and Energy announced that the Genale Dawa III Hydro Power Plant and the Aisha Wind Power Plant will soon join the national power grid.

The Ministry, which declared the lifting of rolling blackouts on Monday, disclosed that the new power plants would play a role in curbing the power shortage the country is facing. The Minister of Water, Irrigation and Energy Sileshi Bekele (PhD) said that the Genale Dawa III hydro power plant, which has an installed generation capacity of 254 MW, will start generation in August 2019. Sileshi said work on the Genale hydro power project has been completed adding that it is under testing and commission work.

The Minister stated that the Genale Dawa area has two rainy seasons which will help the hydro power plant have a better energy out put. “We can use the turbines efficiently. The hydro power plant can operate with 72 percent efficiency,” he said. Genale Dawa will generate additional 1620 GWH.

The Genale Dawa III hydro power project is located in southeastern Ethiopia and is currently being built by China Gezhouba Group at a cost of around USD 450 percent. It set to generate more than 250MW upon completion. It is also projected to raise the country’s electricity installed generating capacity to 4,541 MW.

Sileshi said that the Aisha wind power plant which has an installed generation capacity of 125 MW will be joining the national grid in January 2020.

The Chinese electric company, Dongfang Electric Corporation Limited (DECL), is developing the wind farm project in Aisha area of Somali State, Ethiopia. The wind farm located 20 km distance from Ethio-Djibouti border was projected to cost USD 257 million.

The wind farm will have 80 turbines each having the capacity to generate 1.5 megawatt.

“These two projects would ease the current power shortage,” the minister said.

The minister disclosed that work is underway to develop solar, wind and geothermal power projects by independent power producers. According to him, six solar power projects with an aggregate generation capacity of 800 MW is in the bidding process.

Sileshi mentioned that the Grand Ethiopian Renascence Dam (GERD) will start generation in 2021. Ethiopian Electric Power, the state power company, which currently has a total installed generation capacity of 4,324 MW of electricity is building power plants with a total generation capacity of 8,774MW.

Sileshi told The Reporter that negotiations are underway to sign implementation agreements for the Corbetti and Tulu Moye geothermal projects. Independent power producers, Corbetti Geothermal and Tulu Moye Geothermal, have signed power purchasing agreements with EEP to develop 1000MW of geothermal power plants in the Oromia Regional State West Arsi Zone with an estimated capital of four billion dollars. “There are some outstanding issues that we need to address. We are still negotiating to sign the implementation agreements,” the Minister told The Reporter.

A power industry analyst told The Reporter that the geothermal projects are behind schedule as the government is dragging its feet to sign the implementation agreements. “Geothermal project is a reliable power source that can operate through out the year. The construction does not take long time like hydro power dams. So it will be wise for the government to expedite work on the geothermal power projects at this critical time when the country is facing a power crisis,” he said.

However, Sileshi rebuffs the critic. “We can not rush to sign the implementation agreements as there are some issues that we should agree on. The implementation agreement could be so expensive that we can not afford,” he said.

Ethiopian Electric Utility which started power rationing last March revealed that it has stopped the rationing as of Monday July 8 as the water levels in the hydro power dams have improved.

Source: The Reporter

አገራችንን ከጥፋት፤ ሕዝባችንን ከመከራ ለመሰወር፤ በጌታ ፍቃድ

ከዶ/ር በቀለ ገሠሠ

መንደርደሪያ፤

ሁላችንም የወጣነዉ ከየእናቶቻችን ማህፀን ዉስጥ ነዉ፤ ለ9 ወራት በማህፀን ተሸከሙን፤ ወለዱን፤ አጠቡን፤ አበሉን፤ ሳሙን፤ አቅፈዉ አሳደጉን። በዚህም ምክንያት እናቶቻችንን ከማንም አስበልጠን እንወዳቸዋለን። እንደዚሁም አገር እናት ናት። ዕትብታችን የተቀበረዉ በርስዋ ዉስጥ ነዉ። ከመሬትዋ እህሎች በቀሉልን፤ በልተን አደግን። ከከርሰ ምድርዋ የሚወጣዉን ዉሃ ጠጥተን አደግን። ወተትና ምግብ የሚሰጡን ከብቶቻችን የሚግጡትና የሚጠጡት ዉሃ የሚገኘዉ ከዚያችዉ ምድር ነዉ። የምንተነፍሰዉ ጥሩ አየር የሚነፍሰዉ በርስዋ ላይ ነዉ። ስንሞት የምንቀበረዉ በርስዋ ዉስጥ ነዉ። ስለዚህ ዉድ አገራችንን የእናቶቻችን ያህል እንወዳታለን። አገር ደግሞ የጋራ ናት። ቸሩ አምላካችን ሲፈጥረን የዚያችን ፍሬ እኩል እንድንካፈል ነዉ። እንደፈለግን በነፃ ተዘዋዉረን ሠርተን እንድንኖርባት ነዉ። ይሄ ሁሉ በጣም ግልፅ ይመስለኛል። ከፋም ለማ፤ የብዙ ሺህ ዓመታት የጋራ ታሪክ ያለን ሕዝብ ነን። ዛሬ ግን በተግባር የምናየዉ ሌላ እየሆነ አስቸገረን፤ ብዙ የአፍሪቃ አገሮች ዲሞክራሲያዊ ሥርዓቶች እየገነቡ በሰላም ሲኖሩ እኛ ለምን ወደኋላ እንደምንቀር ስመለከት እጅጉን አዝናለሁ፤ መንፈሣዊ ቅናት ያድርብኛል። ሃሳብና ጭንቀት ዉስጥ ይከተናል። ተያይዘን ከምንጠፋ ተያይዘን ብንነሳ ይቀላል። ስለዚህ ዉድ አገራችንን ከጥፋትና ሕዝባችንን ከመከራ ለመሰወር እያንዳንዳችን የምንችለዉን ያህል አስተዋጽኦ እንድናደርግ በፈጣሪያችንና በልጆቻችን ስም አደራ እላለሁ፤ እግዜር ይታረቀን፤ የጌታችን በረከት አይለየን፤ አሜን።

፩ኛ/       ኢትዮጵያ የማን ናት?

መጠየቁስ? እንዳትሉኝ። ኢትዮጵያ የሁሉም ዜጎችዋ እኩል አገር ናት። እንኳን ለዜጎችዋና በፖሊቲካም ሆነ በሃይማኖት ምክንያት ከየአገሮቻቸዉ ተሰድደዉ የመጡትን በሙሉ እጇን ዘርግታ በመቀበልና በማስተናገድ የታወቀች ቅድስት አገር ናት። በመጽሐፍ ቅዱስ፤ በቅዱስ ቁራንና በታሪክ መዘክሮች በግልጽ የተቀመጠ ሃቅ ነዉ። ዛሬ ግን ፌደራላዊዉ ሥርዓት የተዘረጋዉ ጎሣንና ቋንቋን ብቻ መሠረት በማድረጉ ምክንያት ብዙ ግጭቶች እየተፈጠሩ ይገኛሉ። ከ80 በላይ ጎሣዎች በሚኖሩባት አገር ለሁሉም ዜጋ ተስማሚ የሆነ ሥርዓት መዘርጋት የግድ ይላል። ይሄን አስፈላጊና አንገብጋቢ ጉዳይ በተመለከተ እንደብዙዎቹ ግልፅ ስምምነት ላይ መድረስ እጅግ ያስፈልጋል ብዬ አምናለሁ።

፪ኛ/        ምን ዓይነት ኢትዮጵያን እንፈልጋለን?

 • ሰላም የሰፈነባትና ዜጎችዋ በነፃ እየተዘዋወሩ የሚኖሩባት፤ የሚነግዱባት፤ ወዘተ አገር
 • ፍትሕ ያልተዛባባት
 • ድህነትና በሺታ የማይፈራረቁባት
 • የሁሉንም ዜጋ እኩልነት የምታረጋግጥ ዲሞክራሲያዊት አገር።

፫ኛ/       ከመሪዎች ምን እንጠብቃለን?

በመጀመሪያ ከዬት ተነስተን ዬት እንዳለን አለመርሳት ያስፈልጋል። አምባገነናዊ አገዛዞችን አስወግዶ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመገንባት ዜጎች ከፍተኛ መስዋዕትነት የከፈሉባት አገር ናት። አሁንም በዚያዉ ጉዞ ላይ ነን። አሁን ያለዉ መንግሥት ነፃ የሆነ አገራዊ ምርጫ እስከሚካሄድ ድረስ በተለይ በሚከተሉት ሀሳቦች ዙሪያ ከፍተኛ ትኩረት ቢያደረግ የሚጠቅም ይመስለኛል፤

 • የዜጎች ደህንነትና እኩል መብት መጠበቁን ማረጋገጥ፤
 • የሺማግሌዎችን፤ የኃይማኖት አባቶችንና የምሁራንን ምክር መስማት፤
 • አገርና ሕዝብ ማረጋጋት፤
 • አስፈላጊ ተቋማትን ማቋቋምና ማጠናከር፤
 • በአገሩ ያለዉን ከባድ የፖሊቲካ ቀዉስ በትኩረት ዉስጥ በማስገባት ሁሉን ያካተተ ጊዜያዊ ህዝባዊ መንግሥት ማቋቋም፤
 • ከዚያ በኋላ ርትዐዊና ፍትሐዊ የሆነ ነፃ አገራዊ ምርጫ ማመቻቸት ይቻላል።

፬ኛ/       ከሺማግሌዎችና ከመንፈስ አባቶች ምን እንጠብቃለን?

አገሪቷ ለስንት ሺህ ዓመታት በሰላምና በነፃነት የኖረችዉ በአረጋዉያንና በኃይማኖት አባቶች ምክርና ፀሎት ነዉ። ፅዉቀት፤ ፀጋና የሕይወት ልምድ ያለዉ በነርሱ ዘንድ ነዉና። አሁንም ዉድ ሺማግሌዎችንና የኃይማኖት አባቶችን አጥብቄ የምለምነዉ፤

 • የአገሪቷ ታሪክ እንዳይዛባ ሃቁን እንዲመሰክሩ፤
 • ‘ድር ቢያብር አንበሳ ያስር’ የሚለዉን መርህ እንዲያስታዉሱ፤
 • በጭቁን ሕዝባችን መሃል ምንም ዓይነት ጥል እንዳልነበረ እንዲመሰክሩ፤
 • በከንቱ ፖሊቲከኞች ቅስቀሳ በተጋጩ ወገኖች መሃል እርቀሰላም እንዲያወርዱ፤
 • ለአገራችን አንድነትና ለሕዝባችን ደህንነት ፀሎታቸዉ እንዳይለየን።

፭ኛ/       ከምሁራንና ባለሙያዎች ምን እንጠብቃለን?

ዕድሜ ለተፈራረቁት አምባገነን መንግሥታት፤ ኢትዮጵያ ያሳድጉኛል በማለት በሌላት ዐቅም ለፍታ ያስተማረቻቸዉ  ብርቅ ልጆችዋ በጥይቶች ረገፉ፤ ከተረፉት መሃል ደግሞ ብዙዎቹ እንደባህር አሸዋ በዓለም ተበትነዉ በስደት ላይ ይገኛሉ። አሁንም ተስፋ መቁረጥ አይኖርብንም። ከያለንበት ሆነን ለአገራችን ሰላምና ዕድገት የምንችለዉን ሁሉ አስተዋጽኦ ከማድረግ መቆጠብ አይኖርብንም።  ‘የአገሩን ሰርዶ በአገሩ በሬ’ ተብሎ የሌ?

በእህል ማምረቻ፤ በአካባቢዉ አየር ብክለት መከላከያና መቋቋሚያ አስፈላጊ ቴክኖሎጂዎች ማሳደግ፤ በወንዞቻችንና ሃይቆቻችን ጥበቃ፤ በሰዎችና እንስሳት ጤናዎች አጠባበቅ፤ ወዘተ ላይ በቶሎ ካልተባበርን አገራችን ምድረበዳና ሕዝባችን ጉዳተኞች ሆነዉ እንዳይቀሩ እጅግ በጣም ያሳስበኛል። የተማረ ሰዉ ቃልኪዳኑን መጠበቅ ይኖርበታል፤ አለመዋሸት፤ ሃቁን መመስከርና ሣይንሱን ማስተማር ይጠበቅበታል። በሙያዉ ሠርቶ ማደር ስለሚችል ሕዝባችንን መታደግ እንጂ በክፉ ነገር ላይ መጣል ከቶ አይጠበቅበትም። አገሪቷ ለፍታ ያስተማረቻቸዉ ልጆችዋን እንዲከፋፍሉና እንዲያናክሱ ሳይሆን በእዉነተኛዉ መንገድ እንዲሄዱና እንዲታደጓቸዉ ነዉ።

፮ኛ/        ከወጣቶችስ ምን እንጠብቃለን?

ከሁሉም በላይ የሚያሳስበኝ የአሁኑ ወጣቶችና የመጪዉ ትዉልድ ዕጣ ፈንታ ነዉ። ግጭቶች እየተበራከቱ ናቸዉ። በሰላም ወጥቶ መግባት አጠራጣሪ እየሆነ ነዉ። አየሩ እየተበከለ ነዉ። መሬቶቻችን ጠፍና ምድረበዳ እየሆኑ ናቸዉ። ስለዚህ ለወጣቱ ትዉልድ የሚከተሉትን ቅን ምክሮች ስለግስ ትህትና በተሞላበት መንፈስ ነዉ፤

 • ተስፋ አትቁረጡ፤
 • ራሳችሁን ጠብቁ፤
 • በባልንጀሮቻችሁ ላይ አትጨክኑ፤
 • ራስ ወዳድነት እንዳያሸንፋችሁ፤
 • የአገራችሁን ትክክለኛ ታሪክ ጠንቅቃችሁ ለማወቅ ሞክሩ። አገር መገንባት፤ አንድነት ማጠናከርና ድንበራችንን ከዉጪ ጠላቶች መከላከል ቀላል ትግል አልነበረም፤ አባቶቻችን፤ አያቶቻችንና ቅድመ አያቶቻችን አጥንታቸዉን ከስክሰዉና ደማቸዉን አፍስሰዉ ነዉ ነፃ አገር ያስረከቡን።
 • ለእኩልነት መታገል እጅግ ያስፈልጋል፤ ለዚህም ነበር እልፍ አእላፍ ወጣቶች ለመሬት ላራሹና ለመደብ እኩልነት ከፍተኛ የሕይወት መስዋእትነት የከፈሉት።
 • ዘርና ጎሣ አትለዩ። አምላካችን በአምሳሉ የፈጠረን አንድ ሕዝብ ነን። እኛ ልጆች በነበርንበት ወቅት ሆነ በትግሉ ውስጥ እያለን ዘርና ጎሣን ለይተን አናዉቅም ነበር። እያንዳንዱ ግለሰብ መታት ያለበት በማንነቱ ብቻ ነዉ።
 • ትግላችሁ ለሁሉም ዜጋ ዲሞክራሲና እኩልነት እንጂ ለጭቆናና ለመጠፋፊያ እንዳይሆን ብርቱ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባችኋል።
 • በኢትዮጵያና ተመሳሳይ አገሮች ያለዉ ዋናዉ ችግር የመልካምና የዲሞክራሲያዊ አስተዳደር እጦት ነዉ። የሚታየዉም መፈናቀል፤ ረሀብና ችጋር ዋናዉ ምክንያት የዲሞክራሲና ሰላም እጦት ስለሆነ በዚህ ላይ መረባረብ ይኖርብናል።
 • የምትኖሩባትን ምድርና አየሯን ተንከባከቡ፤ ይህን ካደረግን ምድራችን እንኳን ለኛና ለሌሎችም ትተርፋለች።
 • ቸሩ አምላካችን ከመከራ ይሰዉራችሁ።

፰ኛ/       ከሁሉም በላይ ግን ሕዝባችንና አምላካችን አለ

ሕዝቤ ሆይ፤ ሁላችሁንም እጅግ አድርጌ እወዳችኋለሁ፤ አከብራችኋለሁ። በሁሉም የአገሪቷ ክፍሎች ዞሬ ዐይቻለሁ፤ በሙያዬ ትንሽም አስተዋጽኦ አድርጌያለሁ። ደግ ሕዝብ፤ እንግዳ ተቀባይ፤ ፈሪሃ እግዚአብሔር (በየአምልኮቱ) ያደረበት ነዉ። በየቦታዉ (ከሰሜን እስከደቡብ፤ ከምሥራቅ እስከምዕራብ) ያለዉም የሕዝባችን ችግር ተመሳሳይ ነዉ። ዋናዉ የዲሞክራሲ አስተዳደርና ሰላም መጥፋት ነዉ። ምድራችን በጠፍነት እየተጠቃ ከመሆኑ በስተቀር ሰፊ ነዉ፤ ለሁሉም የሚሆን፤ ከዚያም የሚተርፍ ነዉ። ሰላም ካለ የአየሩን ብክለትና የመሬቱንም ጠፍነት ልንከላከል እንችላለን።

ደጉ ሕዝቤ ሆይ፤ ለብዙ ሺህ ዓመታት የምትታወቀዉ በደግነትህና በአንድነትህ ነዉ። አሁንም በማንም በማንም እንዳትታለል፤ በዘር፤ በጎሣና በሃይማኖት እየተከፋፈልክ እርስ በርስ አትባላ። ባንድ ላይ ሆነህ ኑሮህን አሸንፍ። በህብረት ቆመህ ድንበርህን ከዉጪ ጠላት ተከላከል። ከክፍፍላችንና ከጥፋታችን የሚያተርፈዉ ሴይጣንና የዉጪ ወራሪ ጠላት ብቻ ነዉ። እስካሁን ድረስ በአንድነትህና በእግዚአብሔር ኃይል ነፃነትህን ጠብቀህ ቆይተሃል። አሁንም በዚያዉ ቀና መንፈሣዊ መንገድ ቀጥል። ለልጆችህና ለልጅ ልጆችህ ሰላም የሰፈነባት አገር አዉርስ።

የቸሩ ፈጣሪያችን በረከት ሳይለየን የዉድ አገራችንን አንድነትና የሕዝባችንን ደህንነት ይጠብቅለን።

ሩሲያ ነፃ ምርጫ እንዲካሄድ ለመጠየቅ ሰላማዊ ሰልፍ የወጡ 1 ሺህ ተቃዋሚዎችን አሰረች

በሩሲያ በዋና ከተማዋ ሞስኮ  ነፃ ምርጫ እንዲካሄድ ለመጠየቅ ሰላማዊ ሰልፍ የወጡ 1 ሺህ ተቃዋሚዎች መታሰራቸው ተገለፀ፡፡ በሰላማዊ ሰልፉ ምክንያት ለእስር ከተዳረጉት መካከል የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች እና ለሞስኮ ምክር ቤት ምርጫ በእጩነት የቀረቡ ግለሰቦች እንደሚገኙበት ነው የተነገረው፡፡

በመቶዎች የሚቆጠሩ አድማ በታኞች እና የብሄራዊ ዘብ አባላት  የሞስኮን መሀል መቆጣጠራቸው እና ተቃውሞ በሚደረግበት አካባቢ የሚገኝን መንገድ መዝጋታቸው ነው የተነገረው፡፡

ታዋቂ ፓለቲከኞች ሰልፉ ከመጀመሩ በፊት ለእስር እንደተዳረጉ የተነገረ ሲሆን 3 ሺህ 500 ሰዎች  በሰልፉ ላይ እንደነበሩና  ለእስር የተዳረጉት ሰዎች ቁጥርም ከፍ እያለ መምጣቱ ተጠቁሟል፡፡

የተቃውሞ ሰልፉ በሳምንት ውስጥ ሁለተኛው ጊዜ ሲሆን ባለፈው ቅዳሜ በተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ 20 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች ነፃ ምርጫ እንዲካሄድ ጠይቀዋል፡፡

ይህም በ2011- 12 ፕዚዳንት ቭላድሜር ፑቲን በድጋሜ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት መሆናቸውን ተከትሎ ከተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ በኋላ ትልቁ ነው ተብሏል፡፡

ምንጭ፡- አልጀዚራ – (ኤፍ ቢ ሲ)