ምናላቸው ስማቸው አስራት ሚዲያ ተቀጠረ!!

አቶ ምናላቸው ስማቸው የአማራ ሳተላይት ሬዲዮና ቲሌቪዥን / አስራት ሰራተኛ ሆኖ መቀጠሩን ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የሚዲያው አባል ለዛጎል አስታወቁ። እሳቸው እንዳሉት ለጊዜው ክፍያው በወር ፫፭፻ ዶላር ነው። አቶ ሃብታሙ አያሌውም በቅርቡ ቅጥር ይፈጸምላቸዋል የሚል እምነት እንዳላቸው ተናገረዋል።

የኢሳት ቦርድ ያወጣውን መግለጫ ተከትሎ ለዛጎል የደረሰው ዜና እንደሚያስረዳው አስራት ሚዲያ ለአቶ ምናላቸው ቅጥር የፈጸመላቸው ከወር በፊት ነው። ደሞዛቸውም ቢሆን ለጊዜው እንጂ አራት ሺህ ዶላር ተደርጎ ይስተካከልላቸዋል። ቅጥሩ ለምን ይፋ እንዳልሆነ ተጠይቀው ” ይደርሳል” ሲሉ ለዛጎል የአሜሪካ ዘጋቢ ነግረውታል።

አቶ ምናላቸው የኢሳት ቦርድ ያሳለፈውን ውሳኔ እንደማይቀበሉ በፊርማቸው ካሳወቁት አስር አባላቱ መካከል አንዱ ናቸው። አስራት ሚዲያ መቀጠራቸውን የሰሙ የሚዲያው ወዳጆች ቅሬታ እያሰሙ መሆኑም ተጠቁሟል። ዜናውን የነገሩን እንዳሉት ቅሬታው “አቶ ምናላቸው ኢሳት ሲሰሩ ወቅሰውናል ለሌሎች አሳለፈው ሰጥተውናል ” የሚል ቢሆንም በሂደት እንደሚስተካከልና ቅሬታ አቅራቢዎቹ አቋማቸውን እንደሚቀየሩ ጠቁመዋል።

በተያያዘ አቶ ሃብታሙ አያሌውንም አስራት ሚዲያ እንደሚፈልጋቸውና ሊቀጥራቸው እየሰራ መሆኑንን የዜናው ባለቤት ነግረውናል። እንደዜናው ሰው ከሆነ እሳክሁን ስምምነት ባይደረሰም የአቶ ሃብታሙ አያሌው ዝውውር እውን እንደሚሆን ጥርጥር የለውም። አቶ ሃብታሙ በፊስ ቡክ አካውንታቸው አማካይነት ሃሳባቸውን እንዲገልጹ ጠይቀናቸው ለጊዜው ያሉት ነገር የለም። ይሁን እንጂ ሃሳባቸውን በሰጡበት ቅጽበት የምናካትት መሆኑን ከወዲሁ እንገልጻለን። አቶ ምናላቸውም ቢሆን በተመሳሳይ የሚሉት ነገር ካለ ለማካተት ዝግጅት ክፍሎ ፈቃደኛ ነው።

ኢሳት ተቃውሞ.jpg

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.