እዩ ጩፋ – ማን ነው ነብይ ያለህ?

ነብይ እዩ ጩፋ ነብይና ሃዋርያ ተብለው ከተነሱ ብዙዎች አንዱ ነው። ክራይስት አርሚ ኢንተርናሽናል የተሰኘ የፕሮቴስታንት ቤተክርስትያን መስርቶ በርካታ ተከታዮችን ማፍራት ችሏል። ክራይስት አርሚ በተሰኘው የቴሌቪዥን ጣቢያው በሚተላለፉ የፈውስ ትዕይንቶች ፣አጋንንትን በካራቴ በመጣልና በሌሎችም በርካታ ምክንያቶች አነጋጋሪና አወዛጋቢ ስለመሆኑ ጠይቀነው ምላሽ ሰጥቷል።

ደቡብ ውስጥ ነብያትና ሃዋርያት በዝተዋል ይባላል በዚህ ውስጥ ራስህን እንዴት ነው የምታየው?

ነብይ እዩ ጩፋ እውነት ነው ኢትዮጵያ ውስጥ የሚያገለግሉ የብዙ ነብያትና ሃዋርያት መነሻ ደቡብ ነው፤ እኔም ከዚያው ነኝ። ምናልባት እግዚአብሔር ቃል ኪዳን ሊኖረው ይችላል። ደቡቡም ሰሜኑም የእግዚአብሔር ነው። ነገር ግን እኔ የተወለድኩበት ወላይታ አካባቢ ብዙ ዋጋ የከፈሉ የወንጌል አባቶች የነበሩበት በመሆኑ ከዚያ ጋርም ሊያያዝ ይችላል ብዬ አምናለሁ።

ሰተኛ ነብያት በብዛት የሚነሱበት ጊዜ እንደሚመጣ በመፅሃፍ ቅዱስም ተፅፏል።እነዚህ ነብያትና ሃዋርያት ሁሉም እውነተኛ ናቸው?

እዩ ጩፋ በዚህ ጊዜ ሐሰተኛም እውነተኛም ነብያት አሉ። የሚታወቁት ደግሞ በሥራቸው፤ በፍሬያቸው ነው። እኔ ግን የእግዚአብሔብርን ወንጌል እያገለገልኩ የምገኝ የእግዚአብሔር ነብይ ነኝ ብዬ አምናለሁ።

ግን አንተም ገንዘብ ከፍሎ ምስክርነት ያሰጣል፤ ወደ ንግድነት ያደላ ይማኖታዊ አካሄድ ይከተላል ትባላለህ?

እዩ ጩፋ እውነት ነው ገንዘብ ከፍሎን ነው የሚል ነገር ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ተለቆ ነበር። ገንዘብ ከፍሎ የሚለው ነገር ፈጽሞ ውሸት እንደሆነ ግልፅ ማድረግ ስለነበረብኝ እኔም አንዴ መልስ ሰጥቼ ነበር። አጋንንት እስራት ውስጥ ያሉትን ነፃ ለማውጣት ነው የተቀባሁት። ከፍዬ አጋንንት ማስጮኸው ለምንድን ነው? ከፍዬ የማስጮህ ከሆነ የቀን ገቢዬ አስር ሚሊዮን እንኳ ቢሆን አያዋጣኝም። ሰው ደግሞ የማያዋጣውን አይሰራም። 

ማነው ነብይ ብሎ የሾመህ?

እዩ ጩፋ በዚህ ዓለም ሰው ሰውን የሚሾም ቢሆንም እውነተኛ ሿሚ እግዚአብሔር ነው። በቤተክርስትያን ከእኛ የቀደሙ ሰዎች በእኛ ላይ የተገለፀውን ፀጋ አይተው ወንጌላዊ፣ ዘማሪ ወይም ነብይ ብለው ይሾማሉ። እኔም በጣም በማከብራቸውና በምወዳቸው ቄስ በሊና ነው ሃዋርያ ተብዬ ሹመት የተሰጠኝ። ነገር ግን ከእሳቸው በፊት ቦዲቲ በሚባል ቦታ በማገለግልበት ወቅት ነብይ ሆኜ በቤተክርስትያን ሰዎች ተሹሜአለሁ። እንጂ እራሴን ነብይ ብዬ አልሾምኩም።

አንተ ቤተክርስትያን የሚያመልኩ ባለስልጣናት ወይም ታዋቂ ሰዎች አሉ?

እዩ ጩፋ ስማቸውን መጥራት ባያስፈልግም እስከ ሚኒስትር ደረጃ ያሉ አሉ። ግን ሰው ስለሚበዛ የስልጣን ደረጃቸው ከሕዝብ ጋር ተቀላቅለው እንዲገቡ የማይፈቅድላቸው አሉ። እነዚህን ሰዎች በተለይ እንደ ሰዉ አጠራር ቪአይፒ አግኝቼ የማገለግልበት ጊዜ አለ። 

የእግዚአብሔር ክብር ከእኔ ይበልጣል ብለው ቦታ ተይዞላቸው ከሰው ጋር ተጋፍተው የሚገለገሉም አሉ። ከአገር ውጪም ለትልልቅ ሰዎች ጸልዬ አውቃለሁ። ለምሳሌ ባለፈው ሱዳን ሄጄ ለፕሬዘዳንት ሳልቫኪር ቤተ መንግሥት ገብቼ ጸልያለሁ። ትልልቅ ሰዎችንም ወደ ቤተ ክርስትያን ጋብዤ አውቃለሁ።

ነቢይ እዩ ጩፋ

አጋንንት ማውጣትና ካራቴን ምን አገናኛቸው? ካራቴ ታበዛለህ

እዩ ጩፋ ካራቴ የተማርኩት አጋንንት ለማውጣት አይደለም። የለየለት ካራቲስትም አደለሁም። እኛ ጋ ከባህልና ከሁኔታዎች ጋር የተለመደ ነገር አለ። ከተለመደው ውጪ ሌላ አቅጣጫ ይዘሽ ስትነሺ ያስገርማል። አዲስ ነገር ነውና ካራቴው ያስገረመው፣ ያደናገረውና ያስደሰተውም አለ። ሁሌ ካራቴ ሁሌ አጋንንትን ጩኸና ውጣ አልልም። መንፈስ እንዳዘዘኝ ነው ማደርገው። 

በጌታ በእየሱስ ስም ጩኸና ውጣ ብዬ አዝዤ የወደቀውን መንፈስ አንስተው ሲያመጡ በካራቴ መታሁት፣ በቴስታ መታሁት ምን ጉዳት አለው? በእጅም በእግርም ጥዬ አውቃለሁ ይህን የማደርገው አጋንንት የተመታና የተዋረደ መሆኑን ለማሳየት ካለኝ ፍላጎት የተነሳ ነው። 

እግዚአብሔር መላ ሰውነቴን እንደሚጠቀም ማሳያም ነው። እኔ በካራቴ ከእኔ በኋላ ደግሞ በሌላ ስታይል አጋንንትን የሚመቱ ሊነሱ ይችላሉ፤ ይህ የራሴ ስታይል ነው። አንዳንዶች ካራቴውን የሚቃወሙት በቅናት፣ ሌሎች ደግሞ ከመፅሐፍ ቅዱስ ውጪ ነው በማለት ነው። ከካራቴም የተሻለ አሰራር ያላቸው ካሉ ግብዣዬ ነው። 

በቀይ ቦኔቶች ተከበህ ስትንቀሳቀስ ይታያል። እንዴት ነው እንዲህ ወታደሮች የምትጠበቀው?

እዩ ጩፋ፡ አንድ ሚሊዮን ሁለት ሚሊዮን ሰዎች በሚገኙበት የሜዳ ላይ መንፈሳዊ ኮንፈረንስ ለህዝብ ደኅንነት ሲባል መንግሥት የጥበቃ ኃይል ያሰማራል። አንዱ ተጠባቂ እኔ ነኝ፤ ከጌታ በታች እኔን ይጠብቃሉ። ብዙ ሰው ግን እኔ ከፍዬ ያመጣኋቸው ይመስለዋል።

ብዙ የፖሊስና የወታደር ልብስ የለበሱን ከኋላህ አሰልፈህየእየሱስ ወታደር ነኝ ስታዘምር የሚታይበት ቪዲዮም አለ?

እዩ ጩፋ፡ እሱ እኔ በክልል ባዘጋጀሁት ኮንፈረንስ ከመንግሥት የተቀበሉትን ሃላፊነት ሦስት ቀን በሥራ ላይ በታማኝነት በማሳለፋቸው በመዝጊያው ቀን ኑ ፖሊሶች ብዬ ጠርቼ የፀለይኩበት ነው። ምክንያቱም ለመንግሥት ለአገርም መፀለይ ስላለብን። እነሱም የመንግሥት አንድ አካል ናቸው።

ወደ አገር ጉዳይ ከመጣን፤ በአሁኑ ወቅት በርካታ ፕሮቴስታንቶች በመንግሥት ከፍተኛ ስልጣን ላይ ናቸው ይባላል ይህ ላንተ የተለየ ትርጉም አለው? 

እዩ ጩፋ በአሁኑ ወቅት በጠላት አይን አገር እየፈረሰ ያለ ይመስላል በእኔ እይታ ግን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ከመጣ በኋላ አገር እየተገነባ ነው። ትልቅ ለውጥ መጥቷል። አንደኛው ለውጥ እግዚአብሔርን የሚያውቅና የሚፈራ መሪ ኢትዮጵያ ላይ መምጣቱ ነው። 

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን ከመምጣታቸው በፊት እግዚአብሄር በትንቢታዊ መንገድ የሰጠኝን መልእክት አስተላልፌ ነበር። ዩ ቲውብ ላይ ይገኛል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደሚመጡ ቀድሞ እግዚአብሄር ተናግሮኝ ተናግሬአለሁ።የፖለቲካ መናጋቱና መናወጡ በየትኛውም ዘመን አለ። ኢትዮጵያ ከመቼውም በላይ ወደ ተነገረላት ከፍታ እየሄደች ያለችበት ጊዜ ላይ ነን።

ስለ ኢትዮጵያ ብልፅግና ካነሳህ የልምላሜ ተስፋ የተጣለበት የህዳሴው ግድብ ተሰርቶ የሚያልቅ፤ እውን የሚሆን ይመስልሃል?

እዩ ጩፋ በእምነት የምትናገሪው ነገር አለ። እኔም የእምነት ቃል መስጠት እችላለሁ። በግሌ እንደ ቤተክርስትያን የጀመርናቸው ትልልቅ ፕሮጀክቶች አሉ። ሰው ሲያይ የማያልቅ የሚመስለው እኔ ግን እንደሚያልቅ አምናለሁ። ያልቃል የምለው ገንዘብ ስላለ ወይም በሌላ ምክንያት ሳይሆን አማኝ ሰው ስለሆንኩና እምነት የሁሉ ነገር ተስፋ ስለሆነ ነው። እንደዚሁ በእምነት አባይም ተገድቦ ያልቃል ብዬ አምናለሁ።

ፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ የሆኑ ባለስልጣናት ስለመብዛታቸው ጠይቄህ ነበር . . . ?

እዩ ጩፋ፡ ፕሮቴስታንት ስለሆኑ ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔርን የሚያውቁና የሚፈሩ በሚለው ብናገር ደስ ይለኛል። ከዚህ በፊት የነበሩት ባለስልጣናት እግዚአብሔርን ካለማወቃቸው የተነሳ ስልጣናቸውን ሰዎችን ለመጉዳት ተጠቅመውበታል። አሁን ግን ፕሮቴስታንት ባለስልጣናቱ ጌታን ስለሚፈሩ ጥሩ ሥራ ይሰራሉ ብዬ አምናለሁ እየሰሩም ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩን ወደ ቤተክርስትያንህ ጋብዘሃቸው ታውቃለህ?

እዩ ጩፋ አንድ ጊዜ ጋብዣቸው ነበር ግን በጊዜው ለሥራ ወደ ውጪ ሃገር ሄዱ። ከዚህ በኋላ ግን አንድ ፕሮግራም አለ እዚያ ላይ እንዲገኙ ደግሜ እጋብዛቸዋለሁ፤ እንደሚገኙም ተስፋ አደርጋለሁ።

ከጥቂት መታት በፊት አትታወቅም ነበር።ያጣህ የነጣህ ደሃ ሆነህ ታውቃለህ?

እዩ ጩፋ እዚህ ደረጃ ከመድረሴ በፊት ሰው በሚያልፍበት መንገድ አልፌአለሁ። ከመታወቄ በፊት ስለ እኔ ሰምተው የማያውቁ በሦስት በአራት ዓመት ወደ ስኬት እንደመጣሁ አድርገው ያስባሉ። ነገር ግን እጅግ አስቸጋሪና ዋጋ በሚያስከፍል መንገድ ነው የመጣሁት። 

ብዙ ተከታዮች አሉህ ብዙ ሰዎች የተማሩና በኢኮኖሚም ጥሩ ቢሆኑ ይህን ያህል ተከታይ የሚኖርህ ይመስልሃል?

እዩ ጩፋ እንደ አሜሪካ የሰለጠነና የበለፀገ አገር ላይም ቢሆን ተከታይ ይኖረኛል ብዬ ነው ማስበው። በጥረቴም በፍልስፍናም አይደለም ሰው የሚከተለኝ። ህዝቡ እንዲከተለኝ የሚያደርግ የእግዚአብሄር ሞገስ ስላለ እንጂ። ሰዎች ድሃ ስለሆኑና ስላልተማሩ ይከተሉኛል ብዬ አላስብም። ጥግ ድረስ የተማሩና ባለፀጎችም አብረውኝ አሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያዘጋጁትገበታ ለሸገርላይ ጋብዘውህ ነበር?

እዩ ጩፋአልሰማሁም አጋጣሚ አገር ውስጥም አልነበርኩም።

አረቦች ለፈውስ ወደ አንተ እንደመጡ የሚያሳዩ የተለያዩ ቪዲዮዎችን አይቻለሁ። የሶሪያ ስደተኞች ናቸው ወይስ አንተን ብለው የመጡ?

እዩ ጩፋ እስከማውቀ እኔ ጋር እግረ መንገዱን የመጣ የውጭ አገር ሰው የለም። ፕሮግራም አስይዘው ትኬት ቆርጠው ነው የሚመጡት። ከኢራን፣ ኢራቅ፣ ዱባይና ኦማን ፕሮግራም አስተርጉመው የሚሆነውን ተአምራት እያዩና እየሰሙ ይመጣሉ።

ምን ያህል ሃብት አለህ?

እዩ ጩፋ ሃብቴ የማይመረመር የማይቆጠር ሰማያዊ በረከት ነው። በዓለማዊው የባለጠጋ መለኪያ ራሴን እንዴን እንደምገልጽ ግን እንጃ። አገልጋይ ነን ቤተክርስትያንን የምናንቀሳቅስበት ብር ይመጣል። መባ፣ አስራትና ስጦታ እያገኘን ያንን ደግሞ መልሰን ለአገልግሎት እናውላለን። እንደሚታወቀው በአንድ ጊዜ አስራ አራት ሺህ ሰው የሚያስተናግድ 97 ሚሊዮን ብር የሚያስወጣ የአዳራሽ ግንባታ እያካሄድን ነው። በአንድ ዓመት ውስጥ ያልቃል።

በግል ያለህ ምድራዊ ሃብትስ?

እዩ ጩፋ እስካሁን ያለኝ የማሽከረክረው መኪና ነው።

ወንጌልን ከመስበክ ይልቅ ፈውስና ተዓም ላይ ያተኩራል እየተባልክ ትተቻለህ?

እዩ ጩፋ ቅድሚያ የምሰጠው ለወንጌል ነው። ተዓምራት ወንጌል ከሌለ የለም።

ቃል ለወጣበት ዘይት(የተፀለየበት ዘይት) እስከ ሁለት ሺህ ብር ታስከፍላለህም ይባላል?

እዩ ጩፋ የተፀለየበት ዘይት(አኖይንቲንግ ኦይል) ሰዎች እኔ መድረስ የማልችልባቸው ቦታዎች እየወሰዱ እንዲፈወሱበት ነው ያዘጋጀነው። አሜሪካ፣ አውሮፓና አረብ አገር እየገባ ነው። አገር ውስጥም በየሰው ቤት እየገባ ነው። እኛ ቤተ ክርስትያን የገባ ሁሉ ይውሰድ የሚል መመሪያ ግን የለም። በነፃ ግን አይሰጥም ምክንያቱም ቤተክርስትያናችን የዘይት ፋብሪካ የላትም። ዘይቱ የሚመጣው ከውጭ ተገዝቶ ነው። ዘይቱ የሚታሸግበት ጠርሙስም የሚመጣው ከውጭ ነው። የጠርሙስ ክዳን፣ ጠርሙስ ላይ የሚለጠፍ ስቲከርም ማምረቻ ፋብሪካ የለንም። ይህን ሁሉ በገንዘብ ስለምናገኝ ነው በገንዘብ የምንቀይረው።

የምትጠይቁት ብር የተጋነነ አይደለም ወይ?

እዩ ጩፋ፡ አልተጋነነም እንዲያውም እኛ እንደ ቢዝነስ ሰው ብናስብ፤ ዶላር ስለጨመረ ዘይት ጨምሯል ብለን ዋጋ መጨመር እንችላለን። ለቲቪ በወር እስከ 640 ሺህ ብር እንከፍላለን። የቤተክርስትያን ኪራይ፣ የወንበር ኪራይ፣ የአገልጋዮች ክፍያና የሳውንድ ሲስተም የመሰሉ ወጪዎችም አሉ።

ወንጌላይየተሰኘው መዝሙር ክሊፕህ፤ ይህንኑ መዝሙር መድረክ ላይ ስትዘምረውም እንቅስቃሴው የወላይተኛ ጭፈራ ነው። እንዴት ነው እንዲህ ፈጣሪ የሚመሰገነው? የሚሉ ሰዎች አሉ።

እዩ ጩፋ ጨፋሪዎች ናቸው ከእኛ የኮረጁት። የወላይታ ባህል ጭፈራ ምን እንደሆነ ሳላቅ ለእግዚአብሔር ጨፍሬአለሁ። በቤተክርስትያን ሰው የለመደው ሽብሸባ[ተነስቶ እያሸበሸበ] ስለሆነ ነው። ይሄኛው እንቅስቃሴ ለዘፈን፤ ያ ለእግዚአብሄር ተብሎ የተፃፈ ነገር የለም፤ ሁሉም የእግዚአብሔር ነው። ስለዚህ እኛ ወደፊት የዘፋኞችን እንቅስቃሴ ሁሉ ለእግዚአብሔር ገቢ እናደርጋለን።

አለባበስህ ለየት ያለ ነው የልብስ ዲዛይነር አለህ?

እዩ ጩፋ፡ አዎ ዲዛይነሮቼ ግብፃዊያን ናቸው ልብሴ እዚያ ነው የሚሰራው።

BBC Amharic

It Has Africa’s Most Thriving Economy But Could Ethnic Tensions Shatter Ethiopia?

An Ethiopian army brigadier general accused of leading a failed coup against a regional government has been killed in a shootout with the security forces. Sputnik looks at the ethnic puzzle which is Ethiopia and muses about whether it is about to fall apart.

Brigadier General Asamnew Tsige was killed on the outskirts of the city of Bahir Dar, on Monday, 24 June, two days after he led an abortive coup to take over his native Amhara region.

Ethiopian forces had been hunting down Asamnew since soldiers loyal to him killed the regional governor Dr Ambachew Mekonnen and his adviser Ezez Wasie.

A few hours later the Chief of Staff of the Ethiopian Army General Seare Mekonnen was assassinated by a bodyguard.

 

Oromo Press@oromopress 
Before Asamnew Tsige, ADP security chief and secret member of ABN/NAMA, was activated to strike high-ranking Amhara officials and the chief of staff, the man was openly recruiting and training militias in plain sight. Both regional & fed gov did nothing then

Flags are flying at half mast in the capital, Addis Ababa, and the internet remains shutdown across Ethiopia as Prime Minister Abiy Ahmed attempts to make sure the ethnic tensions behind the weekend’s incidents do not erupt again.

Ethiopia's Prime Minister Abiy Ahmed, wearing an army uniform, addresses the public on 23 June 2019 after a failed coup
© AFP 2019 / HO
Abiy Ahmed

Mr Ahmed, 42, a former army intelligence officer, donned a combat uniform again on Sunday, 23 June, as he made an appeal for calm on Ethiopian television.

Ethiopia, a nation of 110 million people, has seen phenomenal rates of economic growth in recent years but the boom has not stopped growing ethnic tensions between different tribes, which have led to violence which has displaced 2.4 million people.

​Ethiopia – once known as Abyssinia – is a patchwork of different tribes which have always been held together by strong rulers.

A dynasty of emperors ruled the country for centuries – apart from a brief period of Italian colonial rule under Mussolini’s fascist regime – until Haile Selassie was deposed in 1974 and killed the following year.

He was replaced by a hardline communist regime known as The Derg, which was led by Colonel Mengistu Haile Mariam.

They ruled with an iron hand and stamped down on any attempts to whip up ethnic tensions between the various groups.

But after the collapse of the Soviet Union, The Derg was defeated militarily by Eritrean separatists and by the EPRDF, a rebel alliance made up of the Tigray People’s Liberation Front (TPLF), the Amhara Democratic Party, the Oromo Democratic Party and the Southern Ethiopian People’s Democratic Movement.

https://twitter.com/GermanyDiplo/status/1143167361513639939/photo/1

​The TPLF – which hailed from the Tigray region of northern Ethiopia – was the most dominant clique and its leader, Meles Zenawi, was Prime Minister of Ethiopia from 1995 until his death in 2012.

Eritrea was granted independence in 1993 and while it remained impoverished and insular, Ethiopia sucked in foreign investment from China and elsewhere and recorded rising living standards in the first decade of the 21st century.

​Zenawi died suddenly in 2012 and was replaced by Hailemariam Desalegn, who hailed from the Wolayta tribe in southern Ethiopia.

Desalegn maintained similar policies to Zenawi and the Ethiopian economy continued to boom but he freed political prisoners – including Brig. Gen. Tsige – and loosened the EPRDF’s grip on power.

​As the country’s population has grown, competition for resources including water, land and housing, has triggered increasing numbers of flashpoints between different ethnic groups.

Oromo nationalists, who claimed they had been oppressed under Zenawi, have become increasingly truculent in recent years and now the Amhara are flexing their muscles. Brig. Gen. Tsige had been stoking up Amhara resentments with the Gumuz tribe, which had led to several deaths earlier this year.

​He was said to be recruiting an Amhara militia and many of those involved in the weekend’s events were said to be militiamen.

According to the World Population Review, the largest ethnic group in Ethiopia is the Oromos, who make up 34 percent of the population.

​The Amhara make up 27 percent while the remainder are Somali (6.2 percent), Tigrayan (6.1 percent) and various smaller tribes, many of them in southern Ethiopia.

Abiy Ahmed is an Oromo but he remains chairman of the EPRDF and is conscious of the dangers of letting the simmering Ethiopian pot of ethnicities boil over.

The next few days and months will show whether he is capable of keeping the lid on those ethnic tensions.

sputniknews

Ethiopia says plotter of failed coup is killed by military

Photo  – Ethiopians follow the news on television at a cafe in Addis Ababa, Ethiopia Sunday, June 23, 2019. Ethiopia’s government foiled a coup attempt in a region north of the capital and the country’s military chief was shot dead, the prime minister Abiy Ahmed said Sunday in a TV announcement. (AP Photo/Mulugeta Ayene)

Abc news – The Ethiopian army brigadier accused of leading a failed coup against a regional government has been killed in a firefight with the security forces, a spokesman for the Ethiopian prime minister’s office said Monday.

Brig. Gen. Asamnew Tsige was killed on the outskirts of Bahir Dar, capital of the restive northern Amhara region, Nigussu Tilahun told The Associated Press.

Ethiopian forces had been hunting down Asamnew since soldiers loyal to him on Saturday attacked a meeting of the Amhara government, killing the regional governor and his adviser. The regional attorney-general, wounded in that attack, died of his wounds on Monday, according to local media reports.

The attack in Bahir Dar was followed hours later by the assassination in the national capital, Addis Ababa, of the chief of Ethiopia’s military and a retired army general by a bodyguard.

The killings are widely seen as an attack on Ethiopia’s reformist Prime Minister Abiy Ahmed, who was elected last year.

An internet shutdown remains in force across Ethiopia following the Saturday killings.

Asamnew, the renegade brigadier blamed for the violence, had been pardoned by Abiy after being jailed by the previous government for allegedly plotting a coup. He had recently been inciting a rebellion by the people of Amhara in posts on social media, according to reports in Ethiopian media.

Addis Ababa was peaceful Monday as soldiers stood guard in Meskel Square and manned roadblocks throughout the capital.

The 42-year-old Abiy has captured the imagination of many with sweeping political and economic reforms, including the surprise acceptance of a peace agreement with Eritrea, the opening of major state-owned sectors to private investment and the release of thousands of prisoners, including opposition figures once sentenced to death.

Although Abiy’s reforms are widely popular, some members of the previous regime are unhappy with the changes and the prime minister has survived a couple of threats.

Last June, a grenade meant for Abiy killed two people and wounded many others at a big rally. Nine police officials were arrested, state media reported. In October, rebellious soldiers protested over pay and invaded Abiy’s office, but the prime minister was able to defuse the situation.

Ethiopia is a key regional ally of the U.S. in the restive Horn of Africa region.

Tibor Nagy, U.S. assistant secretary of state for Africa, said the latest violence was a “shock, but it could have turned out so much worse,” adding: “Thankfully Prime Minister Abiy escaped this attempt, because there are many, many more people in Ethiopia who support his reforms than those who are opposed to them.”

Speaking in South Africa on Sunday, Nagy said that “there are vestiges of the old regime” who are opposed to Abiy.

“I wish I could say that this is will be the last of these attempts, but no one can be certain,” Nagy said.

Flags are flying at half-mast Monday, which has been declared a day of national mourning following Saturday’s violence.

———

AP journalist Andrew Meldrum contributed to this report from Pretoria, South Africa.

Ethiopia’s army chief, three others killed in failed regional coup

U.S. Assistant Secretary of State for African Affairs, Tibor Nagy, said the attacks were probably prompted by disaffection over Abiy’s rise to power and his sweeping reforms.

“There are vestiges of the old regime in power. Some of the elites are very unhappy with some of the reforms that… Abiy is taking for a variety of reasons including, I’m sure, some ill-gotten gains,” Nagy told reporters in Pretoria, South Africa.

“It’s certainly not clear sailing for him (Abiy) from now on. He has an incredible number of issues he has to deal with,” said Nagy, a former U.S. ambassador to Ethiopia.

ADDIS ABABA (Reuters) – Ethiopia’s army chief of staff and the head of the northern state of Amhara were killed in two separate but related attacks when a general tried to seize control of Amhara in an attempted coup, the prime minister’s office said on Sunday.

Amhara state president Ambachew Mekonnen and his adviser were shot dead and the state’s attorney general was wounded in the regional capital of Bahir Dar on Saturday evening, Prime Minister Abiy Ahmed’s office said in a statement.

In a separate attack the same night, Ethiopia’s army Chief of Staff Seare Mekonnen and a retired general were both shot dead in Seare’s home in Addis Ababa by his bodyguard. The two attacks were linked, the statement said, without giving details.

Abiy’s office named Amhara state security head General Asamnew Tsige as responsible for the foiled coup, without giving details of his whereabouts. Asamnew was released from prison last year after receiving an amnesty for a similar coup attempt, according to media reports.

Abiy took office just over a year ago and embarked on unprecedented reforms in Ethiopia, Africa’s second-most populous country and one of its fastest-growing economies.

But the premier’s shake-up of the military and intelligence services has earned him powerful enemies, while his government is struggling to rein in powerful figures in Ethiopia’s myriad ethnic groups fighting the federal government and each other for greater influence and resources.

U.S. Assistant Secretary of State for African Affairs, Tibor Nagy, said the attacks were probably prompted by disaffection over Abiy’s rise to power and his sweeping reforms.

“There are vestiges of the old regime in power. Some of the elites are very unhappy with some of the reforms that… Abiy is taking for a variety of reasons including, I’m sure, some ill-gotten gains,” Nagy told reporters in Pretoria, South Africa.

“It’s certainly not clear sailing for him (Abiy) from now on. He has an incredible number of issues he has to deal with,” said Nagy, a former U.S. ambassador to Ethiopia.

The shooting in Bahir Dar occurred when the state president – an ally of Abiy – was holding a meeting to decide how to put a stop to the open recruitment of ethnic Amhara militias by Asamnew, one Addis-based official told Reuters.

Asamnew had advised the Amhara people to arm themselves in preparation for fighting against other groups, in a video spread on Facebook a week earlier and seen by a Reuters reporter.

Abiy donned military fatigues to announce the attempted coup on state television on Saturday evening. Residents of Bahir Dar, about 500 kilometers (300 miles) northwest of Addis, said there was at least four hours of gunfire on Saturday evening and some roads had been closed off.

“The situation in the Amhara region is currently under full control by the Federal Government in collaboration with the regional government,” Abiy said in Sunday’s statement.

The U.S. Embassy tweeted it had heard reports of gunfire in Addis Ababa on Saturday night, and some residents told Reuters they heard six shots in a suburb near the country’s Bole International Airport around 9:30 p.m. local time.

The capital was quieter than usual on Sunday, with fewer cars or pedestrians on the streets.

Brigadier General Tefera Mamo, the head of special forces in Amhara, told state television that “most of the people who attempted the coup have been arrested, although there are a few still at large.”

He did not give details about Asamnew.

STRUGGLE FOR REFORMS

Since taking power, Abiy has released political prisoners, removed bans on political parties and prosecuted officials accused of gross human rights abuses, but his government is battling ethnic bloodshed once held in check by the state’s iron grip.

Now some of Ethiopia’s ethnic groups are disputing the boundaries of the country’s nine federal states, or arguing that they too should have regional governments, claims that threaten the dominance of other groups.

Amhara is home to Ethiopia’s second largest ethnic group of the same name and their native tongue, Amharic, is also the country’s official language.

Anti-government protests that lasted three years and eventually forced former prime minister Hailemariam Desalegn to resign in 2018 had begun in the neighboring state of Oromia but quickly spread to Amhara.

Demonstrators were angered by grievances over land rights, political and economic marginalization – issues that Abiy is now racing to address.

“He (Abiy) seems to be dismantling the EPRDF (ruling coalition) and is entertaining thoughts of altering the architecture of federalism, but he hasn’t given any clear direction he’s heading in,” said Matt Bryden, the head of regional thinktank Sahan Research.

“That uncertainty is creating a lot of competition and … driving a lot of the friction and violence.”

Abiy also changed many senior security officials when he came to power, Bryden said, creating more uncertainty that allowed armed groups that would once have been quashed to flourish.

Abiy’s changes have not gone unchallenged. A year ago, he survived a grenade attack that killed two people at a rally. In October, hundreds of soldiers marched on his palace demanding more pay. He defused the situation by doing push-ups with them but later accused them of trying to derail reforms.

The internet was down across Ethiopia on Sunday, although the government made no statement about this. Authorities have cut off the internet several times previously for security and other reasons.

Ethiopia is due to hold parliamentary elections next year, although the electoral board warned earlier this month that they were behind schedule and that instability could cause a problem for polling. Several opposition groups have called for the elections to be held on time anyway.

አሳምነው ጽጌ ተገደሉ !! አስቀድመው አብረዋቸው የሚሰሩ የጸጥታ አካላትን በየቢሯቸው አስረው እንደነበር ፖሊስ አረጋገጠ

የአማራ ክልል የጸጥታና የሰላም ሃላፊ ብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ጽጌ ባህር ዳር ዘንዘልማ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ የጸጥታ ሃይል በወሰደባቸው እርምጃ መገደላቸውን የክልሉ ፖሊስ አስታወቀ። ጀነራሉ የተከሰሱበትን የመንግስት ግልበጣ ሙከራ ከማድረጋቸው በፊት የጸጥታ አካላትን በየቢሯቸው አስረው እንደነበርም ታውቋል። መንግስት በምህረት ወደ አገር ቤት ያስገባቸው፣ በበረሃ ሲንከራተቱ የነበሩ፣ ከእስር የተፈቱ ሴል መስርተው ውስጥ ውስጡን ለውጡን ሲቦረቡሩ መቆየታቸው ተጠቁሟል።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር አንዳሻው ጣሰው በሰጡት መግለጫ የሴራው ዋና አቀነባባሪ የተባሉት ጄነራል አሳምነው በሰዓታት እንደሚያዙ በገለጹ በደቂቃዎች ውስጥ የክልሉ ፖሊስ እንዳለው ጄነራሉ ባህር ዳር አካባቢ ዘንዘልማ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በጸጥታ ሃይሎች መመታታቸውን ይፋ አድርጓል።

ኮሚሽነሩ እንዳሉት መንግስት በይቅርታ፣ በምህረት፣ በመደመር ስሌት ያቀፋቸው ከእስር የተፈቱ፣ በበረሃ በትግል ስም ሲንከራተቱ የነበሩ፣ ጠላት የነበሩ የተመቻቸላቸውን መልካም አጋጣሚ ለክፉ አላማ ተጠቅመውበታል። በከፍተኛ የጸጥታና የድህንነት ሃላፊነት ተመድበው ሲሰሩ  በህቡዕ የሚሰሩ ሴሎችን ፈልፍለው ለውጡን ሲቦጠብጡ ነበር። ለውጡን ለማሰናቀል ሲሰሩ ነበር።

ኮኒሽነሩ ቃል በቃል ባይናገሩም በረሃ ለበረሃ ሲነከራተቱ የነበሩና በምህረት ወደ አገር ቤት እንዲገቡ የተደረጉ ያሉዋቸው በተለይም በአማራ ክልል ስርዓት አልበኝነትን በማንገስ፣ አንዳንዴም በመሳሪያ የተደገፈ እንቅስቃሴ በማድርገና ከተማዋን በማወክ ህዝቡን ስጋት ላይ የታሉትን ወገኖች እንደሆነ አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል።

በጠቅላይ ኤታምዦር ሹም ሰዓረ መኮንን በመኖሪያ ቤታቸው በባህር ዳር የተሞከረው ቀውስ በቁጥጥር ስር እንዲውል አመራር እየሰጡ ባለበት ሁኔታ ከምሽቱ ሶስት ሰዓት አካባቢ አጥፍቶ እንዲጠፋ በተመደበ የግል ጠባቂያቸው መገደላቸውን ያወሱት ኮሚሽነሩ ” አጥፍቶ ጠፊ መቅጠር እቅዱ ሰፊ እንደሆነ የሚያሳይ ነው” ብለዋል። በርካታ መረጃዎች መገኘታቸውንም አመላክተዋል።

በአዲስ አበባና በባህርዳር ከፍተኛ አመራሮች ያሉበት የምርመራ ግብረ ሃይል ተቋቁሞ የምርመራ ስራ እየተሰራ መሆኑንን ኮሚሽነሩ አመልክተዋል። እጅግ ጥቂት የሚባሉ ሲቀሩ በርካታ የሴራው ተሳታፊዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ታውቋል። 

” ካሁን በሁዋላ ምህረት የለም” አቶ ሽመልስ፤ “ግድያው ሊቀጥል ይችላል” አቶ ድብረጽዮን

የትዕግስት ልክ እንዳለው ነው በንግግራቸው መጨረሻ ያስታወሱት። ለውጡን ለማስፋትና የዴሞክራሲ ምህዳሩን ለማስፋት የተሰራው ዓለምን ያስደነቀ ተግባር እንዲፋፋ ከልክ ያለፈ ትዕግስት ተደርጓል። አሁን ግን በዚህ የመቀጠል ሞራሉም፣ አቋምና ስነ ልቡና እንደማይኖር ነው ያስታወቁት። አያይዘውም ካሁን  በሁዋላ ምህረት እንደሌለ ነው አስረግጠው የተናገሩት።

ይህንን ያሉት የኦሮሚያ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ናቸው። በባህር ዳር ተሞክሮ የከሸፈውን የመፈንቅለ መንግስትና በጀነራል ሰዓረና ገዚአ አበራ ላይ ቅጥረኞች የፈጸሙትን ግድያ አስመልክቶ የክልላቸውን አቋም ያስታወቁት አቶ ሽመልስ ካሁን በሁዋላ በዚህ መልክ እናስባለን ለሚሉ ሁሉ መልዕት አስተላልፈዋል። በጓዶቻቸው መሰዋት እልህ እየተናነቃቸው መግለጫ ሲሰጡ የታዩት የኦሮሚያ መሪ፣ ለውጡን ለመቀልበስ በዚህ መልኩ የሚደረጉ ሙከራዎች ያለ አንዳች ምህረት እርምጃ ይወሰድባቸዋል። ለእንዲህ አይነቱ ተጋባር የተለመደው ከልክ ያለፈ ትዕግስት ብሎ ነገር የለም ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

ለዴሞክራሲ ሲባል ከፍተኛ ደረጃ ትዕግስት መመረጡን ያወሱት አቶ ሽመልስ ከዚህ በሁዋላ አረመኔዎችን፣ ናዚዎችን፣ የሚታገስ ትዕግስት እንደማይኖር፣ ሊኖርም እንደማይችል ሲያሳስቡ ከአማራ ክልል ጎን ጓዶቻቸው ጎን እንደሚቆሙ፣ ከአማራ ክልል ህዝብ ጎን እንደሚሰለፉ በማረጋገጥ ነው።

“አንልፈሰፈስም” ሲሉ አጠንክረው የተናገሩት የኦሮሚያ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር፣ “ኢትዮጵያዊነታችን ይበልጥ ይጠናከራል” ብለዋል። ለተጎጂዎች ቤተሰቦችም መጽናናትን ተመኝተዋል።

በአማራ ክልል የተሞከረውን የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ተቃውመው ግድያው ሊቀጥል እንደሚችል ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል። በአዲስ አበባ የተደረገው ግድያ ከባህር ዳሩ መፈንቅለ መንግስት ጋር ግንኙነት እንዳለው አመልክተዋል።

ድርጊቱ ህገመንግስቱንና የፌደራል ስርዓቱን ለመናድ የተደረገ መሆኑንን ያመለከቱት ዶክተር ደብረ ጽዮን፣ ግድያው እንደሚቀጥል Image result for shimeles abdi and debretsion gሲያስጠነቅቁ መነሻቸው ምን እንደሆነ አላብራሩም። በትግሉ ወቅት ግንባር ቀደም ተሳታፊ የነበሩትና የትግራይ ተወላጅ የሆኑት ጀነራል ሰዓረ ” ተደምረው” የአገር መከላከያ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ሆነው መሾማቸውን ተከትሎ እሳቸው ከሚመሩት ክልል የሆኑ ከፍተኛ ስድብና ” ከሃጂ” የሚል ዘለፋ በማህበራዊ ገጾች ሲሰነዘርባቸው እንደነበር ይታወሳል።

በዚሁ መነሻና ለውጡን ሙሉ በሙሉ አለመቀበሉን በይፋ የሚናገረው የህወሃት ሊቀመንበር መፈንቀለ መንግስቱን ለማውገዝ ግንባር መሆናቸው አብዛኞችን አነጋግሯል። በሌላ በኩል ደግሞ አጋጣሚው የተከፋፈለውን ኢህአዴግ ወደ አንድ ሊያመጣ ይችላል የሚሉ የህወሃት ሊቀመንበርን መግለጫ በመልካም ሲያነሱት ትስተውሏል።

የሶማሌ፣ የቤኒሻንጉል፣ የድሬደዋ፣ የአዲስ አበባ፣ የአፋር … ክልሎች መፈንቅለ መንግስቱንና የጀነራሎችን ግድያ እንደሚቃወሙ አመልክተዋል። በጥብቅ ኮንነዋል። ኮሎኔል አለበል በርካታ የድርጊቱ ፈጻሞዎች በቁትር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል። አዲስ አበባም ከጀነራሎቹ ግድያ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር የዋሉ መኖራቸውን መንግስት ይፋ አድርጓል።

የዛጎል የአዲስ አበባ ምንጭ እንዳለው ተጠርጣሪዎች እንዳያመልጡ ሲባል በረራ በጊዜያዊነት መታገዱን አመልክተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ልክ የሶማሊያን ኦፕሬሽን ጅግጅጋ ተገኝተው እንደመሩት ሁሉ የባህር ዳሩን ቀውስ እዛው ሆነው አመራር በመስጠት  ከከፍተኛ የሰራዊት አዛዦች ጋር እንዲከሽፍ እንዳደረጉ አመልክቷል።

Assassinations in Ethiopia amidst regional ‘coup’ attempt, condemned by UN chief

In a statement released on Sunday, António Guterres said he was “deeply concerned by the weekend’s deadly incidents”. The Governor of the restive Amhara National Region was killed along with an adviser, while in the capital Addis Ababa, another key ally of Prime Minister Abiy Ahmed, Chief of Staff General Seare Mekonnen was shot, along with another senior officer.  

Mr. Guterres called on “all Ethiopian stakeholders to demonstrate restraint, prevent violence and avoid any action that could undermine the peace and stability of Ethiopia”.  

UN Spokesperson

@UN_Spokesperson

.@antonioguterres is deeply concerned by this weekend’s events in Ethiopia. The United Nations remains committed to supporting the Government of Ethiopia in its efforts to address ongoing challenges. https://bit.ly/2x9L21g 

According to news reports, the Government has said the situation is now under control, which the Prime Minister addressed the nation on television urging Ethiopians to unite in the face of the “evil” coup attempt in Amhara. The region has been a hotspot of inter-ethnic violence, and the Government reportedly believes that the assassinations are linked. Many of those involved in the alleged coup attempt have been arrested, said Mr. Abiy’s office.  

The Prime Minister has made sweeping changes to the politics of the fast-growing African nation since taking office in April last year, transforming relations with neighbouring Eritrea, and making a series of bold internal reforms. 

The Secretary General said in his statement that he “welcomed the commitment of the Prime Minister and Government of Ethiopia to ensure that the perpetrators of these actions are brought to justice. The United Nations remains committed to supporting the Government of Ethiopia in its efforts to address ongoing challenges.” 

Around three million people have been displaced within Ethiopia, due to long-standing ethnic disputes, usually involving land ownership and rights. 

UN

Goodluck Jonathan Condemns Coup Attempt In Ethiopia, Says Nobody’s Blood Is Worth Political Ambition

Goodluck Jonathan, Nigeria’s former president has condemned the attempted coup to oust Ethiopian Prime Minister, Abiy Ahmed describing it as undemocratic.

His remarks is coming hours after the Ethiopian Prime Minister confirmed the death of the nation’s chief of army by his own bodyguard in an attempt to foil the coup.

He made the condemnation on Sunday while tweeting @GEJonathan.

His tweet reads: “Nobody’s Political Ambition Is Worth The Blood of Citizens in Ethiopia or Any Other Nation.

“I have long said, believed and practised the principle that nobody’s political ambition is worth the blood of any citizen.

“As such, it bleeds my heart when there is unnecessary and avoidable bloodshed, as has just happened in Ethiopia.

Goodluck E. Jonathan

@GEJonathan

Nobody’s Political Ambition Is Worth The Blood of Citizens in Ethiopia or Any Other Nation.

I have long said, believed and practised the principle that nobody’s political ambition is worth the blood of any citizen.

“I condemn the attempted coup against the democratically elected government of Prime Minister Abiy Ahmed.

“I go further to call on men and women of goodwill around the world to also condemn such anti-democratic actions and show solidarity to the democratically elected constitutional order in Ethiopia.

“Democracy has come to rest in Africa. Constitutionality and the rule of law are what we in Africa need, especially in the cradle of civilisation and the melting pot of the African Union.

“Africa hopes for a speedy return to normalcy and I stand ready to lend my voice and actions to make that possible. May God bless Africa and may He be with the government and people of Ethiopia at such a trying time.

saharareporters

ሰዓረ በተገዛ ጠባቂያቸው ተገደሉ፣ የአማራ ክልል ሁለት ከፍተኛ ባለስልጣናት አልፈዋል፤ “አሳምነው ጽጌ እርምጃ ተወስዶባቸዋል” ቢባልም መንግስት መሸሻቸውን አስታውቋል

“የኢትዮጵያ የሃገር መከላከያ ሚኒስቴር ጠቅላይ ኤታማጆር ሹም ጄነራል ሰዓረ መኮንን  በኢትዮጵያ የመጣው ለውጥ የሁሉንም ሕዝብ ተሳትፎ የጠየቀ በመሆኑ ሰራዊቱም የዚህ ለውጥ ተጠቃሚ እና ደጋፊ ነው ” ማለታቸውን ተከትሎ ለውጡ እሳት የሆነባቸው ክፍሎች “ከሃጂ” በሚል ከሹመታቸው ማግስት ጀምሮ ሲያወግዟቸው ነበር። ጀነራሉ ግን ሁሉን ወደ ጎን በመተው አገራዊ ሃላፊነታቸውን በታማኝነት ሲወጡ ቆይተው ቅጥረኞች ገድለዋቸዋል። በጡረታ ላይ የሚገኙት ሜጀር ጀነራል ገዛኢ አበራም በተመሳሳይ ተገድለዋል።

መንግስት ይፋ እንዳደረገው ውዱና ኢትዮጵያዊው ታማኙ ጀነራል በተገዛ ታጣቂያቸው በተተኮሰ ጥይት አልፈዋል። ይህ ባህር ዳር የተሞከረውን መፈንቅለ መንግስት ተስታኮ የተካሄደው የተቀነባበረ ግድያ አገሪቱን ለማተራመስ አጀንዳ ሰንቀው ብር የሚረጩት የሴራ ፖለቲካ አባቶች ተግባር እንደሆነ ጥርጥር የለውም።

ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ እንደተባለው ከለውጡ ማግስት ጀምሮ አገሪቱን ለማተራመስ በየአቅጣጫው የተከፈተውና የተሞከረው ዘመቻ አልሳካ ሲል አማራ ክልልን በማፍረስ፣ የአማራን ሕዝብ እርስ በርስ በማጫረስ፣ አገሪቱን ለማሽመድመድ፣ የመከላከያ ሰራዊትም ሙከራውን መቀልበስ እንዳይችል ለማስቻል ኤታማጆር ሹሙን በቅጥረኞች ለማስገደል እቅድ መያዙ ከማንም የተሰወረ አይደልም።

2019-06-23-2.png

በታሪክና በትውልድ ዘንድ ሲዘከሩ የሚኖሩት ሰአረ መኮንን ሲገደሉ በመከላከያ ውስጥ በሚፈጠር መራበሽ አዲስ አበባንም ለማንደድና ለማተራመስ የሚያስችል እቅድ እንደነበር መረጃዎች በሚወጡበት በአሁኑ ሰዓት፣ከፍተና በጀት ያላቸው የዲጂታል አርበኞች በማህበራዊ ገጽ የሃሰት ቅስቀሳቸውን በአማራ ስም እያሰራጩ ነው። ሙከራው ህዝብን ማተራመስ በመሆኑ ህዝብ ተጨማሪ ቀውስ እንዳይፈጠር ድርጊቱን ነቅቶ እንዲጠብቅ ከየአቅጣቻው ጥሪ እየቀረበ ነው።

መንግስት ነጻ ያወጣቸው አሳምነው ጽጌ መሩት የተባለው መፈንቅለመንግስት ቢከሽፍም የክልሉ መሪ ዶክተር አምባቸው መኮንንና ፣ የህዝብ አደረጃጀት አማካሪያቸው አቶ አዘዘ ዋሴ ህይወታቸው ማለፉን መንግስት ዛሬ ማለዳ ይፋ አድርጓል። የክልሉ አቃቤ ህግ አቶ ምግባሩ በጸና መቁሰላቸውም ተመልክቷል።

አንዳንድ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት አሳምነው ጽጌ የመንግስት የጸጥታ ሃይል እጃቸውን እንዲሰጡ ሲጠይቃቸው ፈቃደኛ ባለመሆናቸውና ተኩስ በመምረጣቸው ህይወታቸው ተገድለዋል የሚሉ መረጃዎች ቢወጡም መንግስት መሸሻቸውን ነው ይፋ ያደረገው። የአማራ ህዝብና ለአማራ እንቆረቆራለን የሚሉ ወገኖች ይህንን አስፈሪ ጊዜ  በማስተዋል ማሳለፍ ካልቻሉ በተደገሰላቸው የዓመታት የክፉዎች ወጥመድ ውስጥ በፈቃደኛነት የመቀርቀር አደጋ ውስጥ እንደሚገቡ ከወዲሁ አገር ወዳዶች እየመከሩ ነው።

“ለአማራ ትግል” መሪ መሆኑንን የሚናገረው ሄኖክ የሺ ጥላ ” እኛ” ሲል በእነ ዶክተር አምባቸው ላይ የተፈጸመውን ግድያ የድል ውጤት አድርጎና አሞካሽቶ አቅርቦታል። እንደሚቀጥልም በመጥቀስ ለፋኖ ጥሪውን አቅርቧል።

Image may contain: text

መንግስት ማለዳ ላይ የሚከተለውን መግለጫ አሰራጭቷል። ትክክለኛ መረጃ በማከታተል ሰለሚሰጥ ህዝብ በሃሰተኛ መረጃ አከፋፋዮች እንዳይወናበድም አሳስቧል።

2019-06-23-1.png

አሳምነው ጽጌ – ነጻ ያወጣቸውን መንግስት ከዱ!! ዶክተር አምባቸው ሕይወታቸው ማለፉ እየተነገረ ነው

በአማራ ክልል የታሰበበት የመፈንቅለ መንግስት መሞከሩን ተከትሎ ለአራት ሰዓታት ስርጭቱን አቋርጦ የነብረው የአማራ ክልል ሚዲያ ብርጋዴር ጀነራል አሳምነው ጽጌ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራውን እንደመሩ አዲፓን ጠቅሶ ይፋ አድርጓል። ዶክተር አምባቸው ህይወታቸው ማለፉም እየተነገረ ነው።

ተደረገ የተባለው የመፈንቅለ መንግስት የአዴፓ ሊቀመንበር አቶ ደመቀ መኮንን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው አገር ውስጥ በሌሉበት ሁኔታ አጋጣሚ ጠብቆ መከናወኑ ጉዳዩን አነጋጋሪ አድርጎታል። መንግስት ታቅዶና በተደራጁ ሃይሎች የተፈጸመ ነው ሲል ለተናገረው ማጠናከሪያ ሆኖ ተገኝቷል።

ከሁሉም በላይ በየክልሉ ያሉ የጸጥታ ሃይሎች የህግ መተላለፍን፣ ህዝብ እየወተወተ ያለውን የጸጥታ ማስከበር ስራ እንዲሰሩ በኢህአዴግ ደረጃ የተወሰነውን ተግባራዊ ለማድረግ በተወሰነ ውሳኔ አጠቃላይ አለመግባባት እንዳለ ይሰማ ነበር። ጀነራል አሳምነው ጽጌ በተደጋጋሚ የሚሰጡት መግለጫና የክልሉን ሰላም የማስከበር አቅማቸው አነስተኛ በመሆኑ ከሃላፊነታቸው እንዲነሱ አስቀድሞ በተያዘው እቅድ መሰረት ተገምግመው ከሃላፊነታቸው እንዲነሱ አቋም መያዙን የዛጎል ምንጮች ይናገራሉ።

ወሳኔው ምን ሊሆን እንደሚችል መረጃ ያላቸው ጀነራል አሳምነው ጽጌ አስቀድመው ልዩ ሃይል አዘጋጅተው ወደ ስብሰባ እንደገቡና በግምገማው አለመግባባት ላይ ሲደረስ እሳቸው የሚያዙት ሰራዊት ገብቶ እርምጃ እንዲወስድ ሲያዙ በተነሳ አለመግባባት ሽጉጥ መታኮስ ተጀመረ። ዶክተር አምባቸው ክፉኛ ተጎድተው ወደ ሃኪም ተወስደዋል። ” ባህር ዳር ቀበሌ ፲፫ አሳምነውን ለመውሰድ ውጊያ ተጀምሯል። ይህንን ሰው መክቶ መታደግ የ አማራው እጣ ፈንታ ነው።ይጥፉ ወይስ እንጥፋ የሚለው ጥያቄ ዛሬም ህያው ነው” ሲል በፊስ ቡክ ገጹ ያሰፈረው ሄኖክ የሺ ጥላ መረጃ እንዳለው ጠቅሶ ዶክተር አምባቸው መሞታቸውን ይፋ አድርጓል።

የአማራ ክልል በአስመሳይ ተቆርቁሪዎች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ ማስጠንቀቂያ አስቀምጦ ወደ ተግባር ለመሸጋገር በተለያዩ መድረኮች የህዝብ ይሁንታ ያገኘው የዶክተር አምባቸው መንግስት፣ በቀናት ውስጥ ክልሉን የሚያተራምሱ ወገኖች ላይ እርማጃ ለመውሰድ ዝግጅቱን ባጠናቀቀበት ወቅት መፈንቅለ መንግስት መካሄዱ ጉዳዩ ከድርጅትም በላይ እንደሆነ በርካቶች አስተያየት እየሰጡ ነው።

በርካታ ሰራዊት እያሰለጠኑ የክልሉን ጸጥታ ማስከበር የተሳናቸው የክልሉ ጸጥታ ሃላፊ ከእስር ለቆ የሾማቸውን ሃይል በጠመንጃ ለመገልበጥ መሞከራቸው ዜናውን ለሰሙ ሁሉ መርዶ ሆኗል።

የፌደራል የጸጥታ ሃይላት በህብረት በሰዓት ጊዜ ውስጥ የተቆጣጠረው ኩዴታ መጨረሻው ወዴት እንደሚያመራ ባይታወቅም፣ በርካታ የድርጊቱ ተባባሪዎች መያዛቸው ታውቋል። የተገፈፈው ማዕረጋቸው የተመለሰላቸው አሳምነው ጽጌን በቁጥጥር ስር የማዋል ስራ እየተሰራ መሆኑ ታውቋል።

የእነ በረከት ስምዖንን ጉዳይ የያዙት አቃቤ ህግ ምግባሩ ከበደና አቶ አዘዘ ዋሴ በጸና መቁሰላቸውን የቅርብ ምንጭ በመጥቀስ የተለያዩ ምንጮች ይገልጻሉ። 

ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የተሰጠ መግለጫ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ላይ የተደረገው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ የሀገሪቱን ሕገ መንግሥት የሚፃረር፣ የክልሉ ሕዝብና መንግሥት ለረጅም ጊዜ የታገሉለትን ሰላምና መረጋጋት ለመንጠቅ የተደራጀ በመሆኑ የፌደራል መንግሥት ሙሉ በሙሉ ያወግዘዋል።

የፌደራል መንግሥት የጸጥታ መዋቅር የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራውን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ሥር አውሎ በፈጸሙት አካላት ላይ ተገቢውን ርምጃ እንዲወስድ ትእዛዝ ተቀብሎ ተፈጻሚ በማድረግ ላይ ይገኛል። ይህ ጥቃት በመንግሥት መዋቅር ላይ ብቻ ሳይሆን በአማራ ሕዝብ ላይ የተቃጣ መሆኑን በመገንዘብ የክልሉ ሕዝብ አካባቢውን በንቃት እንዲጠብቅና ተረጋግቶ ሁኔታዎችን እንዲመለከት ጥሪ ቀርቧል።

ይህን ሕገ ወጥ ሙከራ ክልሉ ብቻ ሳይሆን ማንኛውም ክልልና መላው ኢትዮጵያዊ ሊያወግዘው የሚገባ ሲሆን የፌደራል መንግሥት የታጠቁ ቡድኖችን ሕገ ወጥ እንቅስቃሴ የመቀልበስ፣ የመግታትና በቁጥጥር ሥር የማዋል ሙሉ ዐቅም ያለው መሆኑን ያረጋግጣል።