“ለምን ተገሉኛላችሁ? ለምን ትደፉኛላቹህ? … አታስፈራሩን ” ዮሃንስ ቧያለው

ዛጎል ዜና – የኪታባ ልጅ ወደ ጎጃም የሄደው ከስራ ባልደረባው በደረሰው የሰርግ ጥሪ ነበር። የስራ ባልደረባው ላለበት የቤተሰብ ሰርግ ወደ ጎጃም አንድ ጭልጥ ያለ ገጠር የሄደው የኪታባ ልጅ ተወልዶ ያደገው ጥቁር ኢንጪኒ አካባቢ ሲሆን የሚሰራው ወለጋ ዙሪያ ነው። በአቋሙ በመጠኑም ቢሆን አማራ ላይ የተዛባ አመለካከት ነበረው።

በዚሁ አቋሙ ትንኮሳ ሲበዛበት ወደ አውሮፓ ተሻገረ። አሁን ሲዊዲን አገር ህይወቱን እየመራ ነው። ለዛጎል አስተያየት ሲሰጥ ” አፍራለሁ” በማለት ነው። የአማራን ህዝብ ኑሮ በሄደበት ስፍራ ካየ በሁዋላ ነበሱ አሁን ድረስ ተጨንቃለች። የድህነቱን መጠን ለመግለጽ ይቸገራል። ይህ ምስኪን ህዝብ ያለ አግባብ ተፈርጆ ለመከራ መዳረጉ ያበሳጨዋል። ያመዋል። ይህንን ደሃ ህዝብ ለመርዳትና ኑሮውን ለመለወጥ ከመስራት ይልቅ አሁን ባለው መተራመስ እጅግ ያዝናል። የአማራ አርሶ አደር ከማንም በላይ የተገፋና የተበደለ እንደሆን ያምናል።

ዛሬ አማራ ክልል ምን እየሆነ እንደሆነ ለመረዳት አስቸጋሪ ነው። ክልሉ ውስጥ የተፈጠሩ ጋንጊስተሮች ክልሉን ቱሪስት እንዳይረግጠው፣ ባለሃብት ኢንቨስት እንዳያደርግ፣ ሌሎች ሰላም ተሰምቷቸው እንዳይመጡ ቅጥ ያጣ ተግባር ላይ ተሰማርተዋል። የህዝብ ንብረት ማውደም፣ ማቃጠል፣ መንገድ መዝጋት፣ ታጣቀው ማሸበር፣ ስርዓትን መናድ፣ በፈጠሩት ቡድን ውስጥ ሆነው ማሳደም፣ በፈጠራ ትርክትና በሚዲያ ሃሰት በማሰራጨት ማተራመስ ላይ ተሰማርተዋል።

በአማራ ክልል የታጠቀም ሆነ ያልታጠቀ ቡድን ህዝብን በሚያሸብር መልኩ እየተንቀሳቀሱ ነው። ይህ አስፈሪና አስደንጋጭ ሁኔታ ህዝቡን እያደር ስሜቱ እየጎዳና የጋንግ / የስፈርና የጎጥ መሪዎች እንዳያብቡ ስጋት ፈጥሯል። ወጣቶችን በየስፍራው እየነዱ ሲያሻቸው ሰክረው ጥይት እያንጫጩ ቪዲዮ የሚያሰራጩ ተበራክተዋል። አካሄዱን በሚገባ ካለማጤን በጅምላ የሚደግፉና የእነሱን ሃሳብ የሚያሰራጩ ወገኖችም ድርጊቱን እያባባሱ ነው።

አቶ ዮሓንስ ቧያለው በባህር ዳር ከህዝብ ጋር በተደረገ ምክክር በቀጥታም ባይሆን ከላይ የተባለውን የሚያጠናክር ሃሳብ ሰንዝረዋል። ልብ ላላቸው እሳቸው የሰጡት ማብራሪያ የመጨረሻው ደወል ይመስላል። ” ለምን እሞታለሁ፣ ለምንስ ትገሉኛልችሁ። ሌላውን ለማዳን እኔ ለምን እደፋለሁ…” ሲል የተናገሩት እንዲሁ በወፍ በረር አልነበረም።

እንዲህ ያለውን የወከባ አካሄድ የፈሪ ፖለቲካ መሆኑን ያወሱት አቶ ዮሃንስ፣ በወከባ ምንም የሚሰራና የሚሆን ነገር እንደሌለ ገልጸዋል። በማስፈራራት ሰዎች የራሳቸውን ኔት ዎርክ ፈጥረው እስኪሞቱ ራሳቸውን ለመከላከል እንዲሟሟቱ ከማድረግ ውጪ የሚመጣ ነገር የለም። ጥርጣሬን በማስወገድ አብሮ መስራትና በሚዛን መተቻቸት አግባብ እንደሆነም አምለክተዋል። ከዚህ ውጪ ያለው የዛቻና የወዮልህ አካሄድ ዋጋ ቢስ መሆኑንን ገልጸዋል።

አንድ የሃሰት ዜና ሲሰራጭ ማጣራት የሚባል ነገር የለም። በጅምላ ማስፈራርትና ዛቻ ይጎርፋል።” ይህንን ታደርግና እንገልሃለን” የሚል ዛቻ የሰነዘራል። እንደ አቶ ዮሃንስ ገለጻ አሁን አሁን ሰዎች የሚጠጡትንና የሚበሉት እስከመምረጥ ተደርሷል። ይህ የሰዎችን ክብር የሚነካና ፍጹም ስርዓት የጎደለው ነው።

በቀበሌ አምስት የደረሰው ቃጠሎ ከህዝብ እና ከአስተዳደሩ አንጀት ሳይወጣ ሌላ ቃጠሎ፣ ለኤላ ንብረት ማውደም፣ ሌላ ጥፋት መፈጸም አግባብ መሆኑንን ለተሰብሳቢዎች የገለጹት አቶ ዮሃንስ፣ ስራ አጥ በበዛበት አገር ቱሪስት እንዳይመጣ፣ ስራ ላይ የተሰማሩ ጥቂቶች ቢኖሩም እነሱን ከስራ እንዲወጡ የሚሰሩበትን ማውደም …. ወጣቶች ሃይል አላቸው ነገር ግን ይህንን ሃይላቸውን ንብረት ለማውደም ሲጠቀሙበት ማየት ያሳዝናል ነው ያሉት።

በማህበራዊ ሚዲያ በሚሰራጭ ዘመቻና በቡድን ግርግር የክልሉ መስተዳድር ንቅንቅ እንደማይል አቶ ዮሃንስ የተናገሩት በምክንያት ነው። እሳቸው እንዳሉት ማንም ለአማራ ህዝብ አስባለሁ የሚል ድርጅት አብሮ እንዲሰራ አመቺ ሁኔታ በተፈጠረበት በአሁኑ ወቅት፣ ረዥም መንገድ በመሄድ ይህንኑ ቀናነት ማሳየት በተጀመረበት ወቅት፣ ለማናቸውን የፖለቲካ ድርጅቶችም ይሁን ግለሰቦች ፓርቲያቸው በሩን በበረገደበትና እርዳታ በሚሻበት ወቅት …. በግርገርና በሚዲያ እጅ ለመጠምዘዝ የሚደረገው ሩጫ ተቀባይነት እንደሌለው ለማሳየት ነው።

” አጃቢ ሲበዛና ሲሟሟቅ እኔ ነኝ ጀግና የሚል የቡድን መሪ እየተፈጠረ ነው። ይህንን ድሮ የማውቀው ቄራ አካባቢ ነበር” ሲሉ ተግባሩን ከዱርዬነት ጋር ያዛመዱት አቶ ዮሃንስ ” … ዝነኛ መሆን አንፈልግም። ብታንኳስሱንም አንሽመደመድም” ሲሉ በግልጽ አማራኛ በሰፊ ማብራሪያ አመልክተዋል። አያይዘውም ” በአጃቢና በቲፎዞ ከህግ በላይ መሆን አይቻልም” ብለዋል። ” አታስፈራሩን” ሲሉም ተማጽነዋል። ህዝቡ መንግስትን ብቻ ሳይሆን እንዲህ ያሉትን እንዲያወግዝም ጠይቀዋል።

 

መረር ብለው ” ተላላኪ አትድርጉን የናንተ ተላላኪ እንድንሆን አታስቡት ” ሲሉ በቡድን ለሚመሩትና ቡድን ለሚያደራጁት ማሳሰቢያ የሰጡት፣ ለህዝብም እንቅጩን የተናገሩት አቶ ዮሃንስ ቧያለው፣ ሃሳብን እንደሚቀበሉና ፓርቲያቸው በህዝብና ለክልሉ ህዝብ ከሚያስቡ ጋር ሁሉ እጅ ለእጅ ተያይዞ ይህንን ወቅት ለማለፍ የመስራት እቅድና እምነት እንዳለው አመልክተዋል። ጥሪም አስተላልፈዋል።

እሳቸውን ጨምሮ የአማራ ክልል መሪና ባለስልጣናት በተገኙበት መድረክ ላይ የመቶ ዓመት የቤት ስራ ለአማራ ክልል ተሰጥቶ እንደነበር ያወሱት አቶ ዮሀንስ፣ ይህ ውጥን ዛሬ መክሸፉን አውስተዋል። ካሁን በሁዋላ ወደ ቀድሞው መንገድ መመለስ አይታሰብም ሲሉም አስረግጠው ተናግረዋል። “ከትልቅነት ወደ ትንሽነት አንወርድም። በሌሎች አጀንዳና ጃኬት ውስጥ ገብተን ባለፈው እንደሆነው አንገት የሚደፋበት ሁኔታ ዳግም አይኖርም” ብለዋል።

ይህንን ካሉ በሁዋላ ወጣቶችን ” ስከኑ፣ አሁን የመስከን ጊዜ ነው ” ሲሉ የመከሩት የ ቧያለው ልጅ፣ ጀግነነትንም አስመልክተው ወቅታዊ አስተያየት ሰንዝረዋል። በክልሉ የሚታየውን መሳሪያ ወደላይ እያስጮሁ መፎከርና ማቅራራት፣ እንዲሁም በረባ ባልረባው ጥይት እየተኮሱ ለሚሸልሉት ይሁን ለሌላ በግልጽ ባይናገሩም ” ጀግና ማለት” ሲሉ ሃሳባቸውን ወርውረዋል።

” ጀግና ማለት” አሉ አቶ ዮሃንስ ” እኔ ጀግናው እያለ ክላሽ ሲተኩስ የሚውል አይደለም፤ ዝም ብሎ የመጨረሻ ጀግና ወታደርና ፖለቲከኛ ሳይተኩስ የሚማርክ፣ በሃሳብ የሚያሸንፍ፣ የማይቀር ከሆነ ደግም ሲተኩስ ጥያት የማይጨርስ ፣በቀላል ኪሳራ ዓላማውን ማስፈጸም የሚችል ማለት ነው፣ በአንድ ጥይት አልሞ አንድ የሚመታ … ” 

አንድ ቢንላደን የዓለም ሃያል ነኝ የምትለዋን አሜሪካንን ምን ያህል እንዳስቸገራትና በጀሌዎች አማካይነት ምን ያህል ኪሳራ እንዳደረሰ ማስረዳት እንደማያስፈልግ ያወሱት አቶ ዮሃንስ፣ ” አንድን አካባቢ በሰብአዊ ጋሻነት ተጠቅመው የተደበቁ ዘራፊዎችና ጨፍጫፊዎች ምን ያህል ሊያስቸገሩ እንደሚችሉ፣ እንዴትም ማሸንፍ እንደምንችል እናውቃለን” ብለዋል። ብዙም ዝርዝር ውስጥ ሳይገቡ ” የሚሰራውን ሴራ እንረዳለን እናውቃለን” ካሉ በሁዋላ ወጣቶች፣ ህዝብና ቡድን የሚያደራጁ በራቸውን ሊዘጉ እንደሚገባ አሳስበዋል። 

” ሰላማችን የሚናጋው እንዲህ ባለው ሩጫ ነው” ሲሉ የገለጹት ተናጋሪው ” ነጻነታችንን እያጣጣምን ሰላማችንን እናውርድ” ሲሉ ለተሰብሳቢው ጥሪ አቅርበዋል። ክልሉ ሳያውቀው ማንም ሰው ሊታሰር እንደማይችልና እንደማይሞከር የጠቆሙት አቶ ዮሃንስ ማንም ግን ከህግ በላይ ሊሆን እንደማይችል በተደጋጋሚ አመልክተዋል። ዘረኝነትን አውግዘዋል። ጥፋትን በጥፋት መመለስ እንደማያዋጣ፣ ጠቁመዋል። አማራ ትልቅ ህዝብና 

የባህር ዳር ህዝብ በሰፊው መሬቱን የገለጸበትና የሰላም ስጋቱን ይፋ ያደረገበት ይህ ስብሰባ ” ህግ ይከበር” በሚል መንግስት ላይ ጫና የፈጠረ ነበር። የአማራ መገናኛ ብዙሃን ያሰራጨው የዚዲዮ ማስረጃ እንደሚያስረዳው ክልሉ ወደ ህግ ማስከበሩ ስራ ለመግባት የህዝብ ድጋፍ እያሰባሰበ መሆኑንን አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል። ውይይቱ በዶክተር አምባቸው አስተያየት ነው የተቋጨው።

ግንቦት 20 – “አይ ኢትዮጵያ ለካ ሰው የለሽም!”

ግንቦት 20 – “አይ ኢትዮጵያ ለካ ሰው የለሽም!”

ሰዎች መለስ ዜናዊን ከኮለኔል መንግስቱ ኃ/ማርያምና አልፎ ተርፎም ከዓጼ ኃ/ስላሴ ጋር “ኢትዮጵያዊ ዲክታቶር” ብለው በአንድ ቅርጫት ውስጥ ይከቱታል። ይህ አባባል ሀቅነት አለውን? ይነበብ!

መለስ ዜናዊ 1) ሁለት መፃህፍት ጻፈ። ሁለቱንም ተጀምረው እስኪያልቁ በ”ኢትዮጵያ ቅኝ አገዛዝ ስር ለዘመናት ስለማቀቀቸው” ስለኤርትራ ነፃነት የሚያወጉ ናቸው።

2) አንድ ሰው ህወሃትን ሲቀላቀል የመጀመሪያ የሚቀርብለት ጥያቄ በኤርትራ ነፃነት ታምናለህ ወይ የሚል ነው።

3) ማንም የህወሃት አባል በኤርትራ ላይ – ለምሳሌ ኢትዮጵያን ደግፎ ስለ ወደብ አስፈላጊነት ካነሳ – ወድያው ይታሰራል፣ ቶርቸር ይደረጋል፣ በእምነቱ ፅኑ ሆኖ ከተገኘ ይገደላል።

4) 70ሺ የኢትዮጵያ ወጣት ተሰውቶ ያመጣውን ወታደራዊ ድል አዲስ አበባ ላይ ሆኖ፣ “ያይናቸው ቀለም ካላማረን እናባርራለን” እያለ እያጭበረበረ፣ በኢትዮጵያ ወታደር ተገርፎ ወደ ሱዳን ሲሸሽ የነበረውን የሻቢያ ወታደር አራት ኪሎ ላይ ሁኖ፣ ሬድዮ ላይ ወቶ “ጦርነቱ በ24 ሰዓት ይቆማል” ብሎ የጠላት ጦር እንዲመለስ አደረገ።

መጨረሻም ኢትዮጵያን እያዋረደ መኖር ነበር አላማውና፣ በራሱ አነሳሽነት ዘ ሔግ ፍ/ቤት እንዲቆም አስወስኖ፣ በየማነ ጃማይካ የሚመራው የኤርትራ ቡድን ከአዲስ አበባ ወደ ዘ ሔግ ተጓዘ። ሌላው ኤርትራዊው ቡድን ከአስመራ ተነስቶ ዘ ሔግ ገባ። ገለልተኛ ዳኞቹ የሁለት ኤርትራውያን ወግ መሆኑን ተገንዝበው፣ “አይ ኢትዮጵያ! ለካ ሰው የለሽም” ብለው ፋይሉን ኤርትራን በሚጠቅም መንገድ ዘጉ።

አሁን ከኢሳያስ አፈወርቂ ሺ ጊዜ ጽንፈኛ ኤርትራዊ ብሄርተኛ የነበረው፣ ማንም የህወሃት “ባለስልጣን” ትግሬ “ስልጣኑን” የመለስ ትእዛዝ ማክበር እንጂ ሌላ “ሓባ ስልጣን” እንዳልነበረው ዛሬ በሃፍረት ሻማ ተከናንቦ የሚያስታውሰውን፣ በብቸኝነት 100% ስልጣን ተቆጣጥሮ “ኦሮሚያ” የሚል እና ሌሎች ትንንሽ፣ ሲጋጩ እንዲኖሩ ተደርገው ተጠፍጥፈው የተሰሩ አገሮችን ፈጥሮ፣ የጥላቻ መርዙን ሲረጭበን የኖረው መለስ ዜናዊ የገዛበት ዘመን ምን ግራ የሚያጋባ ሆኖ ነው “የጠላት አገዛዝ ዘመን” ተብሎ በታሪክ የማይዳኘው?

ይህ ጉዳይ መለስን በጠላትነት ፈርጆ ቁጭ ለማለት ሳይሆን፣ ከተፈረጀ በኋላ መለስ ከኤርትራ እና ከሱዳን ጋር የተፈራረማቸውን ኢትዮጵያን ክፉኛ የሚጎዱ ውሎች ኢትዮጵያን ሊወክሉ እንደማይችሉ ለማስረገጥ (to make them null and void)፣ ሌሎች እንደ ዶ/ር አብይ አህመድ ከመሪ፣ እንደ ሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ እንደ ዜጋ የመለስን ኢትዮጵያን የሚያዋርዱ ውሎችን ለማጽደቅ የሚጣደፉትን አደብ እንዲገዙ፣ እንደ ዶ/ር ያዕቆብ ኃ/ማርያም (‘አሰብ የማን ናት’ ደራሲ) እና ከአፋር ወገን የተገኘው አንደበተ-ርቱእ ኢትዮጵያዊው ምሁር ዶ/ር ኮንቴ ሙሳ በፅኑ ኢትዮጵያዊነት መንፈስ ትግሉን እንዲመሩ ለማድረግ፣ እና እንደ ቀይ ባህር የአፋር አገርን በህጋዊ መንግድ ከነ አሰብ ወደቡ ወደ ታሪካዊት ባለቤቷ ወደ ኢትዮጵያ ለማስመለስ በሚደረገው ትግል ለቀጣዩ ትውልድ ፅኑ የህግና የታሪክ መሰረት ሆኖ ስለሚያገለግል ነው።

የኢትዮጵያ ክብር በልጆችዋ ፅኑ ተጋድሎ ይመለሳል!

Abrha Belay