በምዕራብ ጎንደር ተጠርጣሪዎችን ይዘው ለማሳለፍ የሞከሩ የመከላከያ ሠራዊት አባላት በቁጥጥር ሥር ዋሉ፤ ምርመራም ተጀምሮባቸዋ

በምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ ቁጥር አንድ በሚባለው አካባቢ የብሔር ግጭት በመፍጠር ወንጀል፣ ተጠርጥረው የሚፈለጉ አምሥት ግለሰቦችን በመኪናቸው ሸራ አልብሰው ወደ መተማ ወረዳ ለማሻገር የሞከሩ አራት የመከላከያ ሠራዊት አባላት በአካባቢው ኅብረተሰብ በቁጥጥር ሥር ውለው ለፖሊስ ተላልፈው ተሰጥተዋል፡፡

የምዕራብ ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ ተወካይ ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ዓባይ አሻግሬ ለአብመድ እንዳስታወቁት በቁጥጥር ሥር የዋሉት የመከላከያ ሠራዊት አባላት በቋራ ወረዳ ቁጥር 4 ነፍስ ገበያ አካባቢ ሠላም በማስከበር ተግባር ላይ ለሚገኙ የኢፌዴሪ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ደመወዝ ለመክፈል ሄደው ከፍለው ሲመለሱ ነው፡፡

ተጠርጣሪዎቹ የመከላከያ ሠራዊት አባላትም ኮሎኔል አንገሶም አርአያ የ33ኛ ክፍለ ጦር 2ኛ ብርጌድ 1ኛ ሻለቃ አዛዥ፣ መጋቤ ሃምሳ አለቃ አባድር አብራሽ ሾፌር፣ አስር አለቃ ደጀን ቡልቶ የሒሳብ ባለሙያ እና ወታደር ሳምራዊት ገብረእግዚአብሔር የሒሳብ ባለሙያ መሆናቸውን ዋና ኢንስፔክተር ዓባይ ገልጸዋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ሌሎች አምሥት በብሔር ግጭት ወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦችን ሁለት ክላሽ፣ 322 ጥይት፣ 157 ሺህ 900 ብር፣ ዘጠኝ የክላሽ ካዝና፣ ሁለት የወገብ ትጥቅ እንደያዙ ለሥራ በሚገለገሉበት ተሽከርካሪ ደብቀው ወደ መተማ ወረዳ ጉባይ ቀበሌ ሲያጓጉዙ ነው ሚያዝያ 25 ቀን 2011ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 አካባቢ ሁሉም በኅብረተሰቡ በቁጥጥር ሥር የዋሉት፡፡

ኅብረተሰቡ በተደራጀና ሥነ-ምግባር በተሞላበት አግባብ በሕግ ማስከበር ተግባር የተሠማሩ ሰዎች ሕግን ሲተላለፉ ሕግን ለማስከበር ያደረገው ተግባር የሚመሠገን መሆኑን የገለጹት ተወካይ ኃላፊው ‹‹በእርግጥ የአካባቢው ኅብረተሰብ ለሕግ መከበር ቁርጠኛ የሆነና የሰለጠነ ነው፤ ከዚህ በፊትም አምሥት ብሬን በቁጥጥር ሥር አውሎ ለፖሊስ አስረክቧል፡፡ የደቦ ፍርድ የማይፈጽም ሕጋዊና ሕግ አስከባሪ ኅብረተሰብ ስላለንም ደስተኞች ነን›› ብለዋል፡፡

ድርጊቱ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊትን የማወክል እንደሆነ ያስረዱት ዋና ኢንስፔክተር ዓብይ ‹‹የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድርጊቱ የግለሰቦች መሆኑን በመግለጽ በፖሊስ ምርመራ እንዲካሄድባቸው ፈቅዷል፤ ምርመራውም ተጀምሯል›› ነው ያሉት፡፡
ከተጠርጣሪዎቹ መካከል ኮሎኔል አንገሶም አርአያ ከዚህ ቀደም በአካባቢው ሠላም ለማስከበር በሚደረገው ጥረት በተደጋጋሚ በመፈጸም ውስንነት በዞን ጥምር ኮሚቴ ሲገመገሙ እንደነበርም ተወካይ ኃላፊው አስታውቀዋል፡፡

አብመድ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.