ስራ ፍለጋ ወደ ፈረሰችው የመንና ሳዑዲ ሲጓዙ የነበሩ ከ40 በላይ ወገኖች ህይወት አለፈ! የትግራይ ክልል ለቤተሰብ መርዶ አረዳ

የኢትዮጵያ ፖለቲከኞችና አጫፋሪዎቻቸው ምን ዓይነት ልብ እንዳላቸው ለመረዳት ያስቸግራል። ሰው ወደ ፈረሰችውና ጠኔ ህዝቧን እየፈጀ፣ ጥይት እየቆላት ውዳለችው አገር ለመሰደድ የሚሞክረው ለምን እንደሆነ መረዳትና ቁመናቸውን ማስተካከል እንዴት ያቅታቸዋል? በኢትዮጵያ እውነታ ጎሳ በመለየት የምንባላበት ዘመን ነው? የትግራይ ክልል ወጣቶች የዛሬው መርዶ ምን ይነግረናል? ይህ የታወቀው ነው። ያልተሰማውና ያልታየውን ልጇ እንደወጣ የቀረባት እናት ጎጆ ይፈረድ። እንዲህ ያለ ህዝብና አገር እየመራን በገጀራ ለመጨፋጨፍ ሌት ተቀን መትጋት? በስልታን ጥማት ማበድ…. ለሁሉም ነብስ ይማር!!

የፋና ዘገባ – የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በቀይ ባህር ላይ በደረሰ የመርከብ መስጠም አደጋ ከ40 የሚበልጡ ወደ ሳዑዲ አረቢያና የመን ሲያመሩ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ህይወት በማለፉ የተሰማውን ሀዘን ገለፀ

የመስጠም አደጋው ከትግራይ ክልል አፅቢ ወንበርታና አካባቢው ተነስተው በቀይ ባህር ወደ የመንና ሳዑዲ ዓረቢያ ለማቅናት በጀልባ ሲጓዙ ነው የሰጠመው ተብሏል።

የአፅቢ ወንበርታ የህዝብና የመንግስት ግንኙነት ፅህፈት ቤት ሀላፊ ወይዘሮ የወይንእሸት ዘላለም ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ በመስጠም አደጋው ህይወታቸውን ላጡ 43 ዜጎች ቤተሰቦች ትናንት እና ዛሬ መርዶ ተነግሯል።

ቤተሰቦች እርማቸውን እንዲያወጡም በጋራ በቤተክርስቲያን የፍትሃት ስነስርዓት መከናወኑንም እና በነገው እለት ምሽት 12 ሰዓት ላይም የሻማ ማብራት ስነ ስርዓት እንደሚከናወን ላፊዋ የገለፁት።

በተጨማሪም በሳዕሲዕ ፃዕዳ እምባ ወረዳ በተመሳሳይ በአደጋው ህይወታቸውን ላጡ አራት ወጣቶች ቤተሰቦች መርዶ መነገሩን የወረዳው የህዝብና የመንግስት ግንኙነት ፅህፈት ቤት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልጿል።

መጋቢት 28 ለሊት ላይ አደጋው በየመንና ጅቡቲ መካከል ባለ የባህር ክልል ውስጥ ደርሶ የኢትዮጵያውያኑ ህይወት ማለፉን ከአደጋው ተርፈው ወደ ትውልድ

መንደራቸው የተመለሱ ሶስት ወጣቶች ለአከባቢው የመንግስት አካል አሳውቀዋል።

የክልሉ መንግስት በሀዘን መግለጫው በደረሰው አደጋ ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን በመግለፅ ለሟች ቤተሰቦችና ወዳጆች መፅናናትን ተመኝቷል።

በአካባቢው በህገወጥ ደላሎች ተታለው ወደ አረብ ሀገራት በሚጓዙ ወጣቶች ላይ መሰል በባህር ላይ የጀልባ መስጠም አደጋ የበርካታ ዜጎች ህይወት ማለፉን መረጃዎች ያሳያሉ።

 

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.