ቆሻሻዎች ነን !! – አበባዬ – ዋይ ዋይ…

ይበትኑናል፣ እንዳሻቸው ይበታትኑናል። የነዱናል፣ በቃ እንዳሻቸው እንደ መንጋ እንነዳለን፤ ሲያሻቸው ይሰበስቡናል። በታትነው ሳንገጣጠም እንደተገጣጠምን ይነግሩናል።

አትመጣም ወይ ደህና አይደለህም ወይ?
አይናማዬ – ዋይ ዋይ…
አበባዬ – ዋይ ዋይ…
የኢትዮጵያ ልጅ ዋይ ዋይ… ደረት እየተደቃ እናቶች አብደው ያነባሉ። የምባ ደም። ይህ ሙዚቃ ለሚሆንላችሁ ዋ!! ቀን ያዘነብልና!! ዋ !! ቦሰና አነባች
ጀግና የሚታረደው፣ በክላሽ ሚደፋው፤
ላገሩ ነብረ፣ ለድንበር ነበረ
የኢትይዮጵያ ልጅ በስደት ነደደ ደሙ ተገበረ…. ዋይ … ዋይ… ደረት ይደቃል….. ይህ የወላድ ሲቃ የማያስዝናችሁ ዋ! ዋ! ቀን የተደፋ እለት!!
ኧረ እምዬ ማርያም ፊትሽን መልሺ ፤
ኧረ እምዬ ማርያም ሃይል የእግዚአብሄር ነው፣ ፊትሽን መልሺው ፤
ቅጠሉን ዳቦውን ሸጣ ነው ያሳደገችው…… ዋይ ዋይ!! ……. ይህ ሙዚቃ ነው? ይህ ሲቃ አይሰማም። እኒህ የሚለቀስላቸው የእንግዴ ልጆች ናቸው? ጎዶሎ ፍጡር ናቸው? ይህንን ሁሉ ፈጣሪ አያየውም? ይህ ሁሉ ሃዘን ከሆድና ከከርስ በላይ አይደለም? ይህ ኩራት ነው? ያበደው ጠየቀ!!
አልቅሱለት ምንድነው ዝም ዝሙ….
ያልሞተበት የለም እህትና ወንድሙ…..
አልቃሽ አብዳለች፣ መሬት ቁና ሆኖባት ከወዲያ ወዲህ ትባክናለች፣ ትንቆራጠጣለች፣ ይህ ዋይታ ሙዚቃ ነው? ይህ ዋይታ ያረካል? ይህ ዋይታ በድል አድራጊነት ያስጨፍራል? ይህ ዋይታ እስከመቼ ይቀጥላል? እድሜ ልክ? ዋይ ዋይ …. ይሰማል!!
ያበደው ሰላምታ አያበዛም። ነብስ ይማርም አይልም። ድንገት ለሚደፉ ግን ያዝናል። የለቅሶ ነዶ ተወዘወዘ። ወልደያ እናቶች ግጥም ደረደሩ …. አንጀታቸው ተቃጠለ። ተንተከተከ። ያበደው አለቀሰ። ቦሰናም አስከተለች። ደጎል ቤቱን ጥሎ ወጣ። ደጎል የሚያላዝኑ ውሾችን አይወድም። የሚያላዝን ውሻ ሲያጋጥመው አያሸተውም። ኩሩ ነው!! አዎ የፌስ ቡክ አላዛኞች!! የፌስ ቡክ ጀግኖች። የፌስ ቡክ ነጻ አውጪዎች። የፌስቡክ ታጋዬች። ይህንን ሁሉ መከራ እያያችሁ እርስ በእርስ የምትባሉ ህሊና ቢሶች…. ውሸታሞች… የሚዲያ ጥገኞች…. ያበደው የሚያደርገውን አጣ ….
ጥምቀት ላይ ጎረምሶች ተሳደቡ፣ አወገዙ …. እናም ተቀነደቡ!! ያበደው ዝም አለ!! ዜናውን እየሰማ የሚለው ጠፋው። ይህኔ ቦሰና ” እነዚህ ሰዎች ያማቸዋል?” ስትል ተነሳች። ራሳቸው ብስብስ፣ ግሞች፣ የነቀዝን፣ የሸተትን…. እያሉ መሳደባቸውን አወሳች። ታዲያ እነሱን ማን ከዚህ በላይ ሰድቧቸዋል? ጠየቀች፤
እውነት እኮ ነው። እስክንድር ነጋ ከዚህ በላይ ተሳድቦ ነው የታሰረው። አንዷለም አራጌ ” ብስብሶች” ብሎ ተሳድቧል? ኢሬቻ ላይ ” የገማችሁ” ብሎ የተናገረ አለ? ጨለንቆ ” የነቀዛችሁ” ያለ አለ? ታዲያ መሳሪያ ያስወደረው ስድብ ምንድን ነው? ከዚህ የከፋ ….. ያበደው ዞረበት። አገርና ምድሩ ተምታታበት። አጥወለወለው።
1983 የኢትዮጵያ ወታደር ሲነዳ ታየው። ሰላም ሁኑ። መጽናናት ላዘናችሁ !! ለቅሶና ዋይታ ልባችሁን ላደነደነ በርቱ!! አሁንም በህዝብ ስቃይ እየተቧደናችሁ መዝለቅ ለምትፈልጉ የራሳችሁ ጉዳይ……..

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.