” ዘፋኞች መንግስተ ሰማያት አይወርሱም የሚለው ጥቅስ ልክ እንዳልሆነ ገባኝ “

ዘፈን ኃጢያትነቱ ለአሌክስ አብርሃም የተገለጠለት የቴዲ አፍሮ አልበም ሲሆን ነው መሰለኝ።

ድሮ ድሮ ኃይማኖተኛ እያለሁ ዘፈን ለኔ guliy pleasure ነበር። በአንድ በኩል ሙዚቃ እወዳለው በሌላ በኩል ደግሞ የጳውሎስ መልክት ለገላትያ ሰዎች (በተለይ ገላትያ 5፤19፥21) ትዝ ሲለኝ ሁሌ እሳቀቅ ነበር። በኋላ ላይ ግን ዘፋኞች መንግስተ ሰማያት አይወርሱም የሚለው ጥቅስ ልክ እንዳልሆነ ገባኝ። በአጭሩ የአማርኛ መፅሃፍ ቅዱስ ትርጓሜ እዚህ ጥቅስ ላይ ስህተት አለበት። በየትኛውም የእንግሊዝኛ መፅሃፍ ቅዱስ version ላይ ዘፋኝነትን የሚያወግዝ የገላትያ መልእክት ፈልጋችሁ አታገኙም። ወላ King James, New international, or Standard Endlish version ላይ ዘፋኝነት የሚል ቃል የለም።

ዛሬ ኢንተርኔት ላይ ገብታችሁ ይህን ጥቅስ ብትፈልጉት የአንግሊዝኛ ትርጉሙን ብቻ ሳይሆን መፅሃፍ ቅዱስ ኦሪጂናሊ በተፃፈበት የግሪክ ቋንቋ ሳይቀር ጥቅሱን እስከ ትርጉሙ ማግኘት ትችላላችሁ። ጳውሎስ መልእክቱን የፃፈበት የግሪክ ቋንቋ ውስጥም ስለዘፋኝነት አላነሳም።

Disclaimer: ይሄን ሁሉ የዘበዘብኩት ለጥቅሱ ግድ ብሎኝ አይደለም። ዛሬ ላይ መንግስተ ሰማያት ይኑር አይኑር ራሱ እርግጠኛ አይደለሁም። የጳውሎስ መልእክቶችን ግን እንደጥሩ ሞራላዊ ምክር አያቻዋለው። ምክሮቹን ተግባራዊ ማድረግ መልካም ሰው እንድንሆን ማድረግ ብቻ ሳይሆን ስኬታማ እንድንሆንም አስተዋፅኦ አላቸው ብዬ አስባለሁ።

Tesfu Beshah face book

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.